cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

አሥራት ሚዲያ Asrat Media ®🇪🇹

ፈጣን ና ታማኝ መረጃ የሚያገኙበት የሚዲያ መረብ:: Broadcast & media production company መልክት ለመላክ @AsratNewsBot ተጠቀሙ ⌛️ አለም አቀፋዊነት 🌐 🌐 🌐 ⌛️ ወቅታዊነት ⌚️🕰🎙 ⌛️ ተደራሽነት 📲💻📡📺 ⌛️ ሚዛናዊነት ⚖ ⚖ ⚖ ከኛ ጋር ይሁኑ | ያጋሩ @Asrat_News

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
10 227
Suscriptores
-824 horas
-287 días
-13330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አዳዲስ ፋኖዎችን አሰልጥኖ አስመረቀ‼️ የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ዋና አዛዥ ሻለቃ ሀብቴ ወልዴና ሌሎችም የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ግንቦት 22/2016 ዓ.ም ለስድስት ወር ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሲሰለጥኑ ነበሩ ፋኖዎች ተመርቀዋል። የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ ሻለቃ ሀብቴ ወልዴ በምርቃን ስነስርዓቱ ላይ"የአማራ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ስልጠናውን በድል ተውጣችሁታል፤እናንተ የአማራ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ቀልባሽና የአማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁ በዚህ ልትኮሩ ይገባል ብሏል።
Mostrar todo...
👍 27
👍 9 2
Photo unavailableShow in Telegram
በረኸኞቹ ቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር አንዷ ሻለቃ ከግዳጅ መልስ።
Mostrar todo...
👍 6
ደብተራ እየተባሉ በኦነጋውያን ዘንድ የሚንቋሸሹት አባ ባሕሪ ግን ከኦነጋውያን የተሻለ የሞያና የሕሊና ታማኒነት ነበራቸው። የትኛውም የኦነግ ዶክተርና ፕሮፌሰር ሲራቀቅ ቢውል ከአባ ባሕርይ ስራ የተሻለ ጽሑፍ ስለ ኦሮሞ እስከዛሬ ሊያቀርብና ሊያገኝ አልቻለም። እንዴውም አንዳንዶቹ ለምሳሌ እንደ ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን ያሉ የኦሮሞ ብሔርተኞች የአባ ባሕርይን መጽሐፍ እየኮነኑ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ የተረጎሙትን የአባ ባሕርይን መጽሐፍ ግን የቻሉትን ያህል ዝቀው መጽሐፍ አሳትመዋል። ለነገሩ ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን ይህንን የሚያደርጉት አስተማሪዎቻቸው ፈረንጆቹ የኦሮሞን ታሪክ በሚመለከት ሲጽፉ የሚተነትኑት የተዋጣለቱን የአባ ባሕርይን መጽሐፍ ስለሆነ ነው። እንዴውም ኦነጋውያን ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች «ታሪካችን» የሚሉትን አጣመውና ፈጥረው ሲጽፉ ደብተራ እያሉ ከሚጠሏቸው ከአባ ባሕርይ የተሻለ የታሪክ ምንጭ ግን የላቸውም፤ አያቀርቡምም። እንደ እውነቱ ከሆነ አባ ባሕርይ እንኳን በሌጣዎች ኦነጋውያን አንደበት ግዕዝ ጠንቅቀው በሚያውቁ በኢትዮጵያ ልሒቃን ዘንድ እንኳ ለማጣጣል የማይመቹ ምሁር ናቸው። «ኦሮሚያ» የሚባለው ክልል መስተዳደር የኦሮሞ ታሪክና ባሕል ጉዳይ የሚያሳስበው ቢሆን ኖሮ የኦነግንና የተስፋየ ገብረአብን ፈጠራ የኦሮሞ ታሪክ አድርጎ በሌለ ታሪክ የጥላቻ ሐውልት ከሚያቆም በየቦታው የተቀበሩ የአብያተ ክርስቲያን ድርሳናትንና መዛግብቶችን ለማፈላለግና ለመፈተሽ ባጀት ቢመድብ ጥሩ ስራ በሰራ ነበር። በተስፋዬ ገብረ አብ ልብወለድ ላይ ተመስርቶ ኦሮምያ ክልል የሚባለው አካል ወጪውን ሸፍኖ በወያኔ ኮንትራክተሮች የተገነባበው የአኖሌ ሐውልት ላይ የባከነው ገንዘብ በየ አብያተ ክርስቲያናት ተቀብረው የሚገኙትን ድርሳናትና መዛግብቶች ለመፈተሽ ጥቅም ላይ ቢውል ኖሮ ስለ ኦሮሞ የተጻፈውን ታሪክ ይበልጥ የተሟላና የነጠረ እውቀት እንዲኖር ባገዘ ነበር። ኦነጋውያን የሚያወግዙት ስለ ገዳና ኦሮሞ ታሪክ የሰማይ ያህል ርቀት ከፍ ብለው እንዲናገሩ ያስቻሏቸውን አባ ባሕርይን ብቻ ሳይሆን አባ ባሕርይን ያፈራችውን የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጭምር ነው። ግብዝ ባይሆኑ ን ኖሮ ዶክተርና ፕሮፌሰር የሚሆኑበትን የአባ ባሕርይ ታሪክ ጥናት ዶሴ ጠብቃ ለብርሃን ያበቃችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መሆኗን ያውቁ ነበር። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አሁንም ልክ እንደ አባ ባሕርይ አይነት ገና ያልተመረመሩ ድርሳናትና መዛግብቶች አሏት። ከአባ ባሕርህይ ድርሰትና በኦሮሞ ታሪክ ዙሪያ ካበረከተቻቸው አስተዋጽኦዎች የምንማራቸው ቁምነገሮች መካከል አንዱ ቢኖር ከፍ ሲል ለመግለጽ የሞከርነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ማክበር ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ያፈራቻቸው አባ ባሕርይ የኦሮሞ ወታደራዊ ጭፍራ ጥንካሬ ተንትነው ሲያበቁ ባንጻሩ ደግሞ የኢትዮጵያን መንግሥት ድክመት ሲነቅፉ፣ እንደ እርሳቸው ካህን የሆኑ ሰዎችና ካህን ያልነበሩ ሰዎች ከውጊያ ለመሸሸ ሲሉ ካህንነትን መምረጣቸውን በመተቸት እውነታውን ሲያስቀምጡ፤ ኦሮሞን ጠላት ብለው አሳንሰው፣ የኢትዮጵያን መንግሥትና ወገኖቹን ወዳጅ ብለው አግዝፈው አልጻፉም። በእውነቱ እንደዚህ አይነቱ የኦሮሞ ታሪክ ፀሐፊ አባ ባሕርይ ሳይሆን አባ ኦሮሞ መባል በተገባቸው ነበር።
Mostrar todo...
👍 3👎 1 1😱 1
የሶማሌና የሲዳማ ልዩ ሀይል:: የሱማሌና የሲዳማ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በአማራ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ተሰልፈው በውጊያ እየተሳተፉ መሆኑ ተረጋገጠ! ከደሞዛቸው እጥፍ ተጨምሮላቸው የመከላከያ ሰራዊት መለዮ ልብስ በመልበስ በአማራ ክልሉ ውጊያ እየተሳተፉ የሚገኙት የሱማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላቱ ከግንቦት መጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ በጎጃም፣ ሸዋና በወሎ ግንባሮች መሰለፋቸውን የተማረኩ ምርኮኞች አረጋግጠዋል። የውጊያው ሁኔታ እጅግ ከባድ መሆኑን የገለፁት ምርኮኛ የሱማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላቱ፡ በርካታ ጓዶቻቸው እንደተሰውባቸው ተናግረዋል.... ሌላውን በዝርዝር የምናሰማችሁ ይሆናል። የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በምንጃር ሸንኮራ አከባቢ የመከላከያን መለዮ ልብስ በመልበስ ተኩስ የከፈቱት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይልና አድማ ብተና አባላት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስውቋል።
Mostrar todo...
👍 15🤔 1
አባ ባሕርይ ወይንስ አባ ኦሮሞ? የአባ ባሕሬይን መጽሐፍ አንብቦ ለጨረሰና የአጻጻፉን ጥራትና የስነ መዋቅሩን ልቀት ላስተዋለ ፊልም የማየት ያህል ቢሰማው አይፈረድበትም። መጽሐፉ በትዝታ አምስት መቶ ዓመትን ወደ ኋላ መልሶ ታሪኩ የተነገረበትን ዘመን የኖሩ ያህል ስሜት ይፈጥራል። ብዙዎቹ ኦነጋውያን ግን የአባ ባሕርይን መጽሐፍና መጽሐፉን ከግዕዝ ወደ አማርኛ በስተ እርጅና ዘመናቸው እረፍት ሳያምራቸው የተረጎሙልንን ፕሮፈሰር ጌታቸው ኃይሌን ሲያብጠለጥሏቸው ይውላሉ። ይህ የውለታ ቢሶቹ ኦነጋውያንና ተከታዮቻቸው አስጸያፊ ተግባር ግን የእውቀት ጾመኛነታቸውንና ድንቁርናቸውን እንዲሁም የበሉበትን ወጪት ሰባሪና የጎረሱበትን እጅ ነካሽ መሆናቸውን ከማሳየቱ በስተቀር ፋይዳ ያለውም። ኦነጋውያን ሕሊና አልባ ነውረኞች ስለሆኑ እንጂ የአስራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መነኩሴ አባ በሕርይ ፍጹም ሞያዊነትንና ስነ ምግባርን በተላበ መልኩ ባይናቸው ያዩትን የኦሮሞ እውነተኛ ታሪክ በመመዝገባቸው መታሰቢያ ሊቆሙላቸው በተግባና የሚገባቸውን የታላቅ ሰውነት ክብር ሊያጎናጽፏቸው በተገባ ነበር። ዛሬ ታሪክ እንጽፋለች የሚሉን ኦነጋውያን የታሪክ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ሁሉ የአባ ባሕርይን ሩብ ያህል ሞያዊና ሚዛናዊ የታሪክ አመዘጋገብ የላቸውም። የአባ ባሕርይን ጠንቃቃ ጸሐፊነትና ሞያዊ ስብዕና ለመገንዘብ ሩቅ ሳንሔድ ራሳቸው አባ ባሕርይ ያስቀመጡልንን ታሪክ ብቻ በማንበብ መጽሐፋቸውን ሲቋጩ ያሰፈሩትን መደምደሚያ ማየቱ ይበቃል። አባ ባሕርይ በመጽሐፋቸው በሙሉ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ከደቡብ ኢትዮጵያ ተነስተው ወደ ሰሜን በሚፈልሱበት ወቅት የተቀዳጇቸውን ድሎች እንደወረዱ ሲዘግቡ በተለምዶ በራስ ወገን ወይንም በሌላ አቅጣጫ የተፈጸመን ተግባር እንደ ጀብዱ ማንሳት ባልተለመደበት ዘመን ሆነው ያንን ታሪክ መጻፋቸው የርሳቸውን የተለየ የአጻጻፍ ዘዴና ሚዛናዊ አቀራረብ የሚያሳይ ነው። የአባ ባሕርይ በዘመናቸው ወደር የማይገኝላቸው ምሁርና የማያዳሉ ሀቀኛ ጸሐፊ መሆናቸውን በማያወላውል መልኩ ለመገንዘብ በድርሳናቸው ክፍል 18 ላይ በቀረበው ታሪክ ለሚዛናዊነታቸው በሰጡት ምክንያት ውስጥ የዘረዘሩትን አመክንዮ ማየት ይቻላል፤ “የቦረን ሙልአታ የዳሞትን ክርስቲያን አዳከማቸው፣ በታተናቸው፣ አገራቸውን አጠፋው። በሱ ዘመን ሸዋና ዳሞት ምድረ በዳ ሆኑ። አንድ ጊዜ የጋላን ድል፥ አንድ ጊዜ የክርስቲያን ድል ብጽፍ፥ ዛሬ ላንተ ፥ ነገ ለሌላህ የሚለው የመጽሓፍ ልማድ ነው። ድሉም አንድ ጊዜ ለዚህኛው ሌላ ጊዜ ለዚያኛው ነው። ሁል ጊዜ የሚያሸንፍ አንድ እግዚአብሔር (ብቻ)ነው። ሀገሪቱም በጋላ እጅ ገባች፤ የተረፈ የለም። ይህ መጽሐፍ በተጻፈበት ጊዜ የቢፎሌ ልጅ የሙልአታ ሹመት ሰባት ዓመት ሆኖታል። በዘመናቸው የሚሆነውን ውጊያና እልቂት በሕይወት ካለሁ እጽፈዋለሁ። ከሞትኩም ታሪኬንና የሚመጣውን ሉባ ታሪክ ሌሎች ይጽፉታል። ግን የሞተ ብፁዕ ነው፤ አርፏልና።" [ምንጭ፡ ጌታቸው ኃይሌ (1995)፥ የአባ ባሕርይ ድርሰቶች፤ ኦሮሞዎችን ከሚመለከቱ ሌሎች ሰነዶች ጋር፥ ገጽ 89]፤ ይህ አባ ባሕርይ አሳዝኝ በሆነ መልኩ የጻፉት ታሪክ በዘመኑ ሲሆን ያዩትን የዐይን ምስክርነት ነው። ይህ እንግድህ በወቅቱ ስለ ነገሥታት ገድል ቀባብተውና አሰማምረ ይጽፋሉ በሚል «ደብተራ» እየተባሉ ከሚሰደቡት መካከል የሆኑት የኢትዮጵያዊው የጋሞው መነኩሴ የአባ ባሕርይ የአጻጻፍ ዘይቤ ነው። ስለ እውነት ለመናገር ይህ የአባ ባሕርይ ሞያዊና ሚዛናዊ የአጻጻፍ ዘዴ ዛሬ ካሉትን ሁሉም ብሔርተኛ የታሪክ ደራቾችና ጸሐፍት ጋርም የሚወዳደር አይደደም። እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን አለም በሙሉ በጨለማ ይኖር በነበረበት በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንድ አባ ባሕርይ የሚባሉ የብርብር ማርያም መነኩሴ ቄስ ከፍ ሲል በተጠቀሰው የሕሊና ሚዛን እየመዘኑ በነበሩብት ወቅት ሲፈጸም ያዩትን ታሪክ ለብርሃን ለማብቃት ታሪካችንን አሳምረው ስለጻፉ የምስጋና ሐውልት ሊቆምላቸው ሲገባ ተማርን በሚሉት ኦነጋውያን ግን የኖሩበትን ዘመንና በዐይናቸውን ያዩትን ታሪክ ስለጻፉ ብቻ ሲያብጠለጥሏቸው ይውላሉ። የኦሮሞ ብሔርተኞች ውለታ ቢስ ሆነው ነው እንጂ እንደ ሰው ቢያስቡ ኖሮ አባ ባሕርይ በጻፋቸው የኦሮሞ መገልገያዎችና ልዩልዩ ስያሜዎችን በሙዚየምነት የያዘውና አዲስ አበባ የተገነባው «የኦሮሞ ባሕል ማዕከል» የኦሮሞን ባሕል፣ አደረጃጀትና አኗኗር በተሟላ መልኩ ስዕላዊ ይዘት ሰጥተው በጻፉት በአባ ባሕርይ ስም የባህል ማዕከሉን በሰየሙት ነበር። ይህንን ማድረግ ባይቻል እንኳ ልክ እንደ ኤሮፓዊው ኢራስመስ መንደስ ሁሉ በቀለሙ ሰው በአባ ባሕርይ ስም «አባ ባሕርይ ነጻ የትምህርት እድል» ወይንም Abba Bahrey Scholarship Program ተቋቁሞ ሕዳግ ሰጥተው የአማርኛውን ትርጉም ሙሉዕ በማድረግ ከፍ ወዳለ ደረጃ ላደረሱት ለፕሮፈሰር ጌታቸው ኃይሌ መጦሪያ እንዲሆናቸው «ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት» የሚባለው የገንዘብ ሽልማት፤ ከፕሮፌሰር ጌታቸው በፊት የአባ ባሕርይን ጽሑፍ ወደ አማርኛ በተሳካ መልኩ ለመለሱት ለብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ደግሞ የክብር ዶክትሬት ሊያበረክቱላቸው በተገባ ነበር። በነገራችን ላይ ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ የአባ ባሕርይን መጽሐፍ ወደ አማርኛ የተረጎሙት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ኤርትራዊው አስመሮም ለገሰ ስለ ገዳ ምርምር ማድረግ ሳያስብ ነው። ጥላቻ ካልሆነ በስተቀር የአባ ባሕርይን መጽሐፍ ተጠቅሞ የዶክትሬት ማሟያ የጻፈውን አስመሮምን የክብር ዶክትሬት ሸልሞ ፕሮፌሰር ጌታቸውንና ብላታ መርስዓ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ የሚገባቸው ክብር የማይሰጡበት አንዳች ምክንያት የለም። ኦነጋውያን አገር ለመመስረት ሲነሱ ስለ ኦሮሞ ባሕል ያስተጋቡትን እድሜን መሰረት ያደረገውን የገዳ አደረጃጀት ከስራ ስምሪት ጋር አዋደው ለታሪክ ያበረከቱት አባ ባሕሪ እንጂ አስመሮም ለገሰ አልነበረም። የገዳ ስርዓትን ለሁሉም ትውልድ እድሜን መሠረት አድርጎ ኦሮሞ በሚስፋፋበት ወቅት እያንዳንዱ የያንንዳንዱን ሰው ዕጣ ፈንታ የሚወስንና ዕድል የሚሰጥ መሆኑን የመዘገቡት አባ ባሕርይ እንጂ አስመሮም ለገሰ አልነበረም። ኦነጋውያን ባባሕርይ የተጻፈውንና በየ ስምንት አመቱ የሚካሄደውን የኦሮሞ ስልጣን ልውውጥ ታሪክ በማውሳት ፑልቶ ዲሞክራሲን ከኦሮሞ እንደወሰደ ለማያሳየት በማጣቀሻነት የሚያቀርቡት ብቸኛው ምንጭ የአባ ባሕርይን እንጂ የአስመሮምን የዲግሪ ማሟያ መጽሐፍ አይደለም። ሆኖም አስመሮም ለገሰን አክብረው አባገዳነትና የክብር ዶክትሬት ሲሰጡ አባ ባሕሬን ግን ደብተራ እያሉ ማውገዝ እንጂ ስማቸውን እንኳ በክብር ማውሳት አይሹም።
Mostrar todo...
👍 6
እነ ሽመልስ አብዲሳ የሚሰሩት ግፍ! ጅብሠም ለሞጆ ሳራግፍ ለኮቴ 1000 ብር አስከፈሉኝ ቀጣይ ወደ መቂ በመጓዝ አሸዋ ጫንኩ ከዛ እዛው መቂ መግቢያ 800 የሚሊሻ ክፈል አሉኝ ያው 400 የሻይ ስሰጠው አለፈኩ በድጋሚ መቂ መውጫው ላይ የኮቴ1000ክፈል አለኝ አሁንም በ500 የኪስ ከፍየ ተፋታን በመቀጠል አለምጤና የኮቴ 1000 ሲጠይቀኝ የሞጆውን ሳሳየው እሺ የሚልሻ ብሎ 700 ካርኒ ቆረጠልኝ ከዛ ደሞ ቆቃ ስደርስ አሁንም የኮቴ 1000 ስጠየቅ በ500ተፋታሁ ከዛ ሞጆ ስደርስ ሞጆ ሳራግፈ የቆረጥኩትን አሳየሁት ለቀቀኝ ተመስጌን ብዬ ጉዞዬን ቀጠልኩ ቢሸፍቶ ሳልደርስ ሃይወይ መግቢያው ላይ የኮቴ 1000 ስጠየቅ እዛም በ500ተፋታሁ ከዛ ደግሞ አለፈ እንዳልኩ እዛው ደብረዘይት አሁንም የኮቴ 500ደረሰኝ ቆረጠልኝ ማለት ነወ አሁን ከመቂ እስከ ደብረዘይት ድረስ የኮቴ እና የሚልሻ እየተባለ በድምሩ 4100 ከፈልኩ በጣም አዘንኩ ለዛውም 2000 ሺ ብር አስጥዬ ማለት ነው እና መፍትሄው ምን እንደሆነ ሳስብ በጣም ከበደኝ ይላል አንድ አሽከርካሪ። ሹፌሮች አንደበት ገፅ የተገኘ ጽሁፍ
Mostrar todo...
👍 12
00:32
Video unavailableShow in Telegram
ግቡ ግን መውጣት የለም📌 በቪዲዩ እንደምትመለከቱት በዛሬው ዕለት ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ላይ ከ200 በላይ ታታ ባስ የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ አዲስ ምልምል ሰራዊት ወደ አማራ ክልል በጎጃም በኩል እየገባ ነው። ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ፍቼ ከተማ ላይ የተቀረፀ ቪዲዮ!
Mostrar todo...
👍 37 2
በአስገራሚ የውጊያ ጥበብ የታየበት… በምስራቅ ጎጃም ዞን በቢቡኝ ወረዳ ዋብር ከተማ ዙሪያ በፋኖ መዝገቡ ዋለልኝ የተሰየመው ብርጌድ (መዝገቡ ዋለልኝ ብርጌድ ) እና የሰዴ፣ የቁይ፣ የስናን ፋኖዎቻችን በጥምረት በመሆን ጠላትን ቀለበት ውስጥ ከተው ውጠው አስቀርተውታል። ፋኖዎቻችን ይህንን ድንቅና ጥበብ የተሞላበት ውጊያ ያደረጉት ልዮ ስማቸው ሞላሌ፣ ጅብ ዋሻ፣ ፈረስ ሜዳ ተብለው በሚጠሩት አካባቢዎች ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን አራዊት ሰራዊትና ሌላውን የአገዛዙን ኃይል ከምድር በታች ማድረጋቸው ታውቋል። ከዚህ ማምለጥ የቻለው የግለሰብ ስልጣን ጠባቂ አራዊት ሰራዊት ንፁሃንን መጨፍጨፉ የታወቀ ሲሆን የዋብር ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጠባቂ መነኩሴ የሆኑትን ቄስ ገበዝ ይገኙበታል።
Mostrar todo...
👍 7
ከሃዋሳ (ብላቴ ማሰልጠኛ) የመጣው አራዊት ሰራዊት 11:30 አካባቢ አዲስ አበባ ደርሶ ወደ ጎሮ በሚባል አካባቢ እንዳለፈ ታውቋል። ምናልባትም ወደ ደብረብርሃን መስመር ሊያመራ እንደሚችል ተገምቷል። የሸዋም የጎጃምም መግቢያ መስመሮች በሙሉ ክትትል ቀጥሉ። Latest info (የቅርብ መረጃ) አሌልቱ ደርሰዋል።
Mostrar todo...
👍 11