cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹

This is FANA Media and Communication Corporate’s official Telegram channel. For more updates please visit https://t.me/fana_televisions #ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
11 843
Suscriptores
+424 horas
+367 días
+22030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የ'ገበታ ለሀገር' ፕሮጀክቶችን ለየክልሉ አስረከበ ******************** በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተከናወኑት የ'ገበታ ለሀገር' ፕሮጀክቶች ዛሬ አንድ ሌላ ምዕራፍ ተከናውኗል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዛሬ ባዘጋጀው መርሃ ግብር ፕሮጀክቶቹን ለአማራ፣ ለኦሮሚያ እና ለደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስረክቧል። በተጨማሪም በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ተግባርን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይ ላይት ሆቴል ተቋሙ በኩል እንዲወጣ የስምምነት ፊርማ ሥነሥርዓት ተካሂዷል። ከአራቱ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ሶስቱ (ሃላላ ኬላ ሎጅ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ) በቅርቡ መመረቃቸው የሚታወስ ሲሆን፤ የጎርጎራ ፕሮጀክት ስራም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል። በጠቅላይ ሚኒስሩ ከፍተኛ ትኩረት እና አመራር የተከናወነው የ’ገበታ ለሀገር’ ስራ የብሔራዊው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱ ማዕዘን የሆነውን ቱሪዝምን የማሳደግ ዓላማ ያለው ነው። እነዚህ ፕሮጀክቶች በመጀመሪያው ፋይናንስ የማሰባሰብ ምዕራፍ የኅብረተሰቡን ድጋፍ በሰፊው ያሰባሰቡ፣ በግንባታቸው ምዕራፍ ግዙፍ የስራ ዕድል የፈጠሩ ብሎም ታላላቅ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንዲከናወኑ በር የከፈቱ ናቸው። በፈጠራ የተሞላ የፕሮጀክት ስራ እና አስተዳደር እና ፈጣን አፈፃፀም ምን ሊመስል እንደሚችል ማሳያም ሆነዋል። ቀጣይ የስራ ማስኬድ እና ማስተዳደር ተግባሩ ለብሔራዊ ሰንደቅ ተሸካሚው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሃላፊነት መሰጠቱም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ከማስቻሉም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ትውውቅ ከፍ ያለ ዕድል እንደሚፈጥር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Mostrar todo...
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ255 ሺህ የመዲናዋ ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ *************** የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ255 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች እና በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የመዲናዋ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርቷል። የማዕድ ማጋራቱ የተከናወነው በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት በኩል ሲሆን፤ ዓላማውም ነዋሪዎቹ በዓሉን በፍሰሐ እንዲያሳልፉት መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። ሰርተው ካገኙት ለወገኖቻቸው ማካፈልን ባሕል ላደረጉ የከተማዋ ልበ ቀና ባለሀብቶች እና በጎ ፈቃደኞች ከንቲባ አዳነች በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
Mostrar todo...
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፈተና መቼ ይሰጣል ? እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል። ፈተናው ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ ነው። ከ70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ይሰጣል ተብሏል። ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች #ብቻ ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራበት ነው። ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ለኢፕድ ከሰጠው መረጃ ተመልክተናል። በሌላ በኩል ፤ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ የሬሜዲያ ተማሪዎች ከታህሳስ ወር ጀምሮ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ቢሆንም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም። ተማሪዎቹ የትምህርት ጊዜያቸው እያለፈ እንደሆነና አስቸጋሪ ጊዜ እያሳለፉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ቅሬታ አቅርበዋል። 70% ፈተናው በሰኔ ወር ይሰጣ መባሉ ደግሞ እንዳስጨነቃቸው ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ - የነዚህ ልጆች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ? - ከዚህ በኃላ መቼ ተጠርተው ተምረው ለፈተና ይቀርባሉ ? - ለምን ምቹ ሁኔታ ከሌለ ቀደም ብሎ ሌላ ግቢ አይመደቡም ነበር ? -  አሁን መፍትሄ ምንድነው ? የሚሉ ጥያቄዎችን ይዞ የዩኒቨርሲቲውን አመራሮች በተደጋጋሚ በድምጽ እና በፅሁፍ ለማናገር ጥረት ቢያደርግም #ቁርጥ ያለ ምላሽ ማግኘት አልቻለም። በቀጣይም ጥረቱን ይቀጥላል። ዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ ካገኘ ያቀርባል። Via @tikvahUniversity @tikvahethiopia
Mostrar todo...
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ926 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ እሸቱ ጎዴቶ እንደገለጹት÷ የክልሉ የይቅርታ ቦርድ በይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ታራሚዎችን ከመንግስት፣ ከህዝብና ከታራሚ ጥቅም አኳያ ሲመረምር ቆይቷል። በተደረገው ምርመራም በአጠቃላይ የይቅርታ ጥያቄ ካቀረቡ 978 ታራሚዎች መካከል መስፈርቱን ያሟሉ 926 ታራሚዎች ጥያቄያቸው ለክልሉ መንግስት ቀርቦ የይቅርታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረዋል። የይቅርታው ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል 920 ታራሚዎች ከእስር የሚለቀቁ ሲሆን÷ስድስቱ ደግሞ የእስራት ጊዜያቸው የተቀነሰላቸው ናቸው። ታራሚዎቹ በማረሚያ ቤት በነበራቸው ቆይታ በአግባቡ ስለመታረማቸው፣ ስለመታነጻቸውና ስለመልካም ባህሪያቸው ምስክርነት የተሰጠባቸው መሆኑንም አመልክተዋል። #ዳጉ_ጆርናል
Mostrar todo...
👍 3 3
አስተራዜኒካ ኩባንያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት የደም መርጋት በሽታ እንደሚያስከትል አመነ‼️ ኮቪሽልድ የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት በ150 ሀገራት ላሉ ዜጎች በክትባት መልክ ተሰጥቷል። ክትባቱን የወሰዱ 50 ሰዎች የ100 ሚሊዮን ፓውንድ የጉዳት ካሳ እንዲከፈላቸው ክስ መስርተዋል። አስተራዜኒካ ኩባንያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት የደም መርጋት በሽታ እንደሚያስከትል አመነ፡፡ እስከ ታህሳስ 2023 ድረስ 61 ሚሊዮን የዓለማችን ዜጎች በኮሮና ቫይረስ ምክንት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ የሚሞቱ ዜጎችን ለማዳን በ150 የዓለማችን ሀገራት በክትባት መልክ ከተሰጡ ክትባቶች መካከል መቀመጫውን ለንደን ባደረገው የአስተራዜኒካ ኩባንያ ምርት የሆነው ኮቪሽልድ የተሰኘው ክትባት ዋነኛው ነው፡፡ የዚህ ኩባንያ ምርት የሆነውን ኮቪድሽልድ የተሰኘውን ክትባት ወስደን ለደም መርጋት እና በሰውነት ውስጥ ለሚከሰት የደም መፍሰስ ችግር ተዳርገናል ያሉ ዜጎች ክስ መስርተዋል፡፡ 50 ይናሉ የተባሉት እነዚህ ተጎጂዎች አስተራዜኒካ የተሰኘው ኩባንያ 100 ሚሊዮን ፓውንድ የጉዳት ካሳ ሊከፍለን ይገባል ሲሉ ክስ መመስረታቸውን ዘ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡ ክስ የተመሰረተበት አስተራዜኒካ ኩባያም ኮቪሽድ የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት የደም መርጋትን ጨምሮ ሌሎች የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዲከሰት ምክንያት እንደሚሆን አውቃለሁ ብሏል፡፡ ተጎጂዎች ባቀረቡት ክስ ላይ ክትባቱን በመውሰዳቸው ምክንያት ከስራ መቅረትን ጨምሮ በየዕለቱ የተለመዱ ስራዎችን መከወን እንደተሳናቸው ተናግረዋልም ተብሏል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ አስተራ ዜኒካ ኩባንያ ያመረታቸው የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች ካደረሱት ጉዳት ይልቅ ያተረፉት የሰው ህይወት ይበልጣል ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ድርጅቱ አክሎም ኮቪድሽልድ ክትባት በእንግሊዝ እና በህንድ በብዛት እንዲመረቱ ተደርጎ ወደ 150 የዓለማችን ሀገራት መሰራጨታቸው የብዙዎችን ህይወት መታደግ አስችሏልም ብሏል፡፡ ይሁንና ክትባቱን በወሰዱ የተወሰኑ ሰዎች ላይ የደም መርጋት እና መሰል የጤና እክሎችን አድርሷል ሲልም የዓለም ጤና ድርጅት ተናግሯል፡፡ አልአይን 👉"ፈጣን እና እውነተኛ ሀገራዊ መረጃ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችንን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ያድርጉ"👇👇👇 http://t.me/ayuzehabeshaofficial http://t.me/ayuzehabeshaofficial የውስጥ መስመር👉 t.me/ayulaw
Mostrar todo...
👍 4
ተያዘ‼️ መነሻውን መቀሌ በማድረግ ከሲሚንቶ ጋር ተጭኖ ወደ ከሚሴ ከተማ ሊገባ የነበረ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያ በቁጥጥር ሥር ውሏል። በሰሌዳ ቁጥር አማ 17744 ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ መነሻውን መቀሌ በማድረግ ከሲሚንቶ ጋር በድብቅ ተጭኖ መዳረሻውን ከሚሴ ያደረገው ህገ ወጥ የቡድን እና የነፍሰ ወከፍ የጦር መሳሪያ ከነ አሽከርካሪውና ረዳቱ በህብረተሠቡ ጥቆማ ደጋን ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ 2 ዲሽቃ ፣1 ስናይፐር ፣01 አርባ ጎራሽ ፣04 ኤስኬስ በአጠቃላይ 08 የነፍስ ወከፍ እና የቡድን መሳሪያ መነሻውን መቀሌ ካደረገው ተሽከርካሪ ከስሚንቶ ጋር ተጭኖ ለአሸባሪው ሸኔ ለማድረስ የታቀደ ነበር ተብሏል። 👉"ፈጣን እና እውነተኛ ሀገራዊ መረጃ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችንን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ያድርጉ"👇👇👇 http://t.me/ayuzehabeshaofficial http://t.me/ayuzehabeshaofficial የውስጥ መስመር👉 t.me/ayulaw
Mostrar todo...
ከራያ አላማጣ እና ኮረም የደረሰኝ መረጃ‼️ 🎯አላማጣ የህወሓት ሠራዊት ከከተማው በዓዲ ዔቦ (4 ኪ.ሜ )፣ በዲ ቦሬ (5ኪሜ በግምት) ርቀት ላይ ነው ያሉት። ከተማው የመከላከያ ሀይል ቁጥጥር ስር በመሆኑ ዛሬ ሌሊት በሀይል ወደ ከተማው ለመግባት አቅደው እንደነበር ከቦታው የደረሰኝ መረጃ ያሳያል። የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች እንዲሁም የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀይሉ ዛሬ በአላማጣ ስብሰባ ላይ እንደነበሩ ገልፀውልኛል። የከተማው ማሕበረሠብ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ነው ያለው። መንግስት ይህን ጭንቀታችን ተረድቶ አፋጣኝ መፍትሔ ይሰጠን ዘንድ እንማፀናለን ሲሉ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። 🎯ኮረም👇 ዛሬ አዲስ የህወሃት ቡድን ከማይጨው በኩል በጣም ብዙ ሀይል ወደ ወፍላ-ኮረም እያስገባ ነው። አንደገቡም ሁለት የአሸንጌ ሚሊሻዎች ላይ ከባባድ ድብደባ አድርሰዋል(በስም ጭምር ደርሶኛል)። የወፍላ~ኮረም ህዝብ ለከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት ተዳርገናል ብለዋል[አዩዘሀበሻ]። 👉"ፈጣን እና እውነተኛ ሀገራዊ መረጃ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችንን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ያድርጉ"👇👇👇 http://t.me/ayuzehabeshaofficial http://t.me/ayuzehabeshaofficial
Mostrar todo...
1
እንደዚህ ያሉ ሰዎችን ያብዛልን❗ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የበሱፍቃድ ሪልስቴት ባለቤት አቶ በሱፍቃድ ቦሌ መድሂኒዓለም አካባቢ ጫማ እያስጠረገ በነበረበት ሰዓት ultara 23 ስልክ ባጋጣሚ በተቀመጠበት ወንበር ላይ ረስቶ በመሄዱ ሊስትሮ ጠራጊው የስልኩን ባለቤት አፈላልጎ ቢሮው ድረስ ሄዶ አስረክቧል። እንደዚህ ያሉ ታማኝ እና ቅን ሰዎችን ያብዛልን። ልጁን የምታውቁት በውስጥ መስመር ላኩልኝ። አዩዘሀበሻ 👉"ፈጣን እና እውነተኛ ሀገራዊ መረጃ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችንን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ያድርጉ"👇👇👇 http://t.me/ayuzehabeshaofficial http://t.me/ayuzehabeshaofficial የውስጥ መስመር👉 t.me/ayulaw
Mostrar todo...
አስደንጋጩ እሳተጎሞራና ፍንዳታ‼️ በኢንዶኔዢያ የሚገኘው ራንድ ተራራ ላይ ዛሬ ማለዳ ከባድ የሆነ የእሳተገሞራ ፍንዳታ አጋጥሟል። በእሳተ ገሞራው ፍንዳታ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የመብረቅ ብልጭታዎች መከሰታቸውን ተከትሎ በስፍራው አስፈሪ ድባብን ፈጥሮ ነበር። በዚህ የተነሳ በተራራው አቅራቢያ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ለመሰደድ ተገደዋል ተብሏል። 👉"ፈጣን እና እውነተኛ ሀገራዊ መረጃ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችንን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ያድርጉ"👇👇👇 http://t.me/ayuzehabeshaofficial http://t.me/ayuzehabeshaofficial የውስጥ መስመር👉 t.me/ayulaw
Mostrar todo...