cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ቤተ ቅዱስ

የተለያዩ 💠 መንፈሳዊ ጽሁፎች 💠 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራት 💠የቅዱሳን እናቶቻችን እና አባቶቻችን ገድላት 💠 መንፈሳዊ ምስሎችን የምታገኙበት channel 👇👇👇 ቤተ ቅዱስ በ አግዚአብሔር ስም ቻናሉን share በማድረግ ተባበሩን https://t.me/bet

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
196
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

እንደ "ቅራኔ መፍቻ" እኅቱን እየተቆጣ፣ እየሰደበና እየመታ ያደገ ወንድ፥ ሲያገባም "ቅራኔ መፍቻ" ዘዴው ሚስቱን መቆጣት፣ መስደብና መምታት ነው። ሌላ ቅራኔ መፍቻ ዘዴን አይቶ አያውቅማ፤ አልተለማመደማ! አንዳች ችግር ሲፈጠር ወላጆቿን ወይም ታላቅ ወንድሟን እየዋሸች ያደገች ሴትም፥ ስታገባ ተመሳሳይ ነገር ሲገጥማት እንደ መፍትሔ የምታመጣው ዘዴ ውሸትን ነው። ለምን ሌላ ዘዴ ታመጣለች? ላምጣስ ብትል እንዴት ታመጣዋለች? © ገብረእግዚአብሔር ኪደ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝ 💥ሰላም የቤተ ቅዱስ  አባላት እና የchannelu ቤተሰቦች ከታች በተቀመጠው የደቂቀ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የtiktok account search በማድረግ ✨ follow ✨like ✨Share እንድታደርጉ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!!! ሰናይ ምሽት @dekikebrihan1211111 @dekikebrihan1211111 @dekikebrihan1211111
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
✥✥✥ ቤተልሔም ሰማይን መሰለች ✥✥✥ ✥   በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሸ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ አንቺም በተድላ በደስታዬ ጊዜ ሽልማት ሆንሽኝ፡፡ በኃሤትም ጊዜ ክብ ዘውዴ ሐቲም ቀለበቴ ነሽ፡፡ ✥    በሐሳቤም ሁሉ አንቺን አደንቃለሁ፡፡ እንዲህም እላለሁ፡፡ እግዚኣብሔር ለሰው ልጅ ምን ያህልጸጋ ክብር ሰጠ፡፡ ✥   እግዚኣብሔር ከሰው ልጅ የማይተባበሩ ሥስት ልደታትን ተወለደ፡፡ እኔም ዓውቄ አደነቅሁ፡፡ ባራተኛው እንጂ የበጎ ዕረፍት አላገኘሁም፡፡ ✥  አዳም ከሕቱም ምድር የተወለደ በተፈጥሮ ነው፡፡ እኔን ግን የጠቀመኝ የለም፡፡ ሔዋንም ከአዳም ግራ ጐን ተወለደች እርሷም በተፈጥሮ ነው፡፡ ለኔ ግን የጠቀመችኝ የለም፡፡ ✥    ቃየልም እንደ ሰው ሁሉ በዘር በሩካቤ ተወለደ የጠቀመኝ የረባኝ የለም፡፡ ስንኳን እኔን እራሱንም አልጠቀመም፡፡ እሊህ ሦስቱ ልደታትም ለማንም ለማን አይረቡም አይጠቅሙም፡፡ ✥     ክርስቶስ ግን ያለዘር ያለሩካቤ ከድንግል ተወለደ ለሁሉ የሚረባ የሚጠቅም ሆነ፡፡ ✥  ለዚህ ልደት መስገድ መገዛት ይገባል፡፡ ክብር ምስጋና ለዚህ ልደት ይገባል ጌትነትና ገናንነት፣ ኀያልነት፣ አዚዝነት፣ እልልታ፣ ግርግታ ለዚህ ልደት ይገባል፡፡ ✥   ይህ ጥበብ ፍልስፍና ዕጹብ ድንቅ ነው፡፡ ለዚህ አንክሮ ይገባል ይህም የሥጋዊ ምሥጢር ምን ይረቅ ምን ይጠልቅ፡፡ ለዚህ አንክሮ ይገባል፡፡ ይህም ሰው መሆን ሥጋ መልበስ እጅግ ዕፁብ ድንቅ ነው፡፡ ✥      የሔዋን ደኅንነቷ እመቤታችን ሆይ የድንግልናሽ ኃይል እጅግ የሚያስደንቅ ዕጹብ ነው፡፡ ✥     የአዳምን መርግመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያጠፋሽለት እመቤታችን ሆይ የማይመረመር ረቂቅ ምሥጢር ባንቺ ተደረገ፡፡ ✥    እሳትና ውሀም ባንድነት ተስማምተው መኖራቸው እጅግ ድንቅ ነው የሚያስፈራውንም ያንበሳ ደቦል ፀዓዳ በግዕት በክንዷ መታቀፍዋ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ✥    ከድንግልም ብላቴና ጡቶች ወተት መፍሰስ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ በበረትም ለድኆች ልጅ የሰማይ ሠራዊት መስገድ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ✥    ዓለምን ሁሉ የመላ ኣምላክም ከበረት ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅሎ መገኘቱ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ በረት ከጽርሓ አርያም ቁመት ረዘመ ከሰማይም ዳርቻ ሰፋ፡፡ ✥    ሕዝቅኤል ካየው ሠረገላ ዳንኤልም ካየው ኪሩባዊ ዙፋን በረት በለጠ፡፡ ይኽውም አደፍ ጉድፍ ሳይኖርባት ንጽሕት የወለደችው ንጹሕ በግ ነው፡፡ በረት ለንጹሑ መሥዋዕት ሽታ መሰብሰቢያ ሆነ፡፡ ✥    ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በረት ቻለው ወሰነውም፡፡ በረት የተመሰገነ ነው፡፡ የኃያላን ጌታ በውስጡ ተገኝቷልና፡፡ ✥   በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች እመቤታችን የተመረፀች ድንግል የሰማዩን ሠራዊት አሰገደቻቸው፡፡ የዓለም ጌጽ ሽልማት የሁሉ አባት የሚሆን መላእክትን የፈጠረ ጌታ ከርሷ ተወልዷልና፡፡ ✥   በረት ተመሰገነ ምድርን በውሃ ላይ ያጸናት እርሱ ስለተጠጋባት ድንግልም የመላእክትን አለቆች ገዛቻቸው በኪሩቤል ላይ የሚቀመጥ እሱ በማኅፀኗ ስላደረ፡፡ ✥    በረት ኪሩቤል እንደሚሸከሙት ዙፋን ሆነ ስፍራውም እንደ ጽርሓ አርያም ድንግል እንደ አብ ሆነች አንድ ልጅም በጎል ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅሎ ተገኘ፡፡ ✥   ዮሴፍና ሰሎሜ በወዲህና በወዲያ ላምና አህያም በወዲህና በወዲያ በበረቱ ጐንና ጐን ባራቱ ማዕዘን በዙፋኑ ቀኝና ግራ በጐንና በጐኑ አራቱ እንስሶች እንዳሉ፡፡ ✥   የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ ተሠራ፡፡ ቤተ ልሔም ሰማይን መሰለች ስለ ፀሐይም በቅዱሳን ላይ የሚያበራ ለዘወትርም ጨለማ የማይቃወመው ኅልፈት ጥፋትም የሌለበት ዕውነተኛ ፀሓይ በውስጧ ተገኘ፡፡ ✥  የብርሃኑም ክበብ መምላትና መጉደልን ስለሚያፈራርቅ በጨረቃ ፈንታ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች የድንግልናዋም ምስጋና በሁሉ የመላ ነው፡፡ ለዘወትርም የማይጐድል እመቤታችን የተመረፀች ድንግል ማርያም ተገኘች ስለ ከዋክብትም መላእክተ ብርሃን ታዩ፡፡ ✥   ወደዚህ ማኀበር አንድነት እኖር ዘንድ ማን በከፈለኝ ከመላእክት ጋር እንዳመሰግን ከዋላጅቱም ጋር እንዳደንቅ ከእርኞችም ጋር እንዳገለግል፡፡ ✥    በረቱንም እጅ እነሣ ዘንድ ማን በከፈለኝ የሙታን ሕይወት የኃጥኣንም ንጽሕና የቅቡፃን ተስፋ የተጨነቁትንም የሚያድን ጌታ ወደተቀመጠበት፡፡ ✥   የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰበቱን ምድር እስም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡ ✥   ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡ የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡ ✥   አሁንም ያን ጊዜ በዕብራይስጥ ማሪሃም ከተባለች ከተመረጠች ድንግል ማርያም ጋራ ያን ጊዜ ካሉት አላንስም ሀሳቤን ከዚያ እንዳለሁ አድርጌ አለሁና፡፡ ✥   በሥጋ አልነበርሁም በመንፈስ ግን አለሁ፡፡ ባነዋወር አልነበርሁም በሃይማኖት ግን አለሁ በገጽ አልነበርሁም በማመን ግን አለሁ፡፡ ✥   ሳልኖር እራሴን እንዳለሁ ያረደረግሁ እኔ የተመሰገንሁ ነኝ ጌታችን በወንጌል እንደተናገረ እንዲህ ሲል ሳያዩኝ የሚያምኑብኝ ግን የተመሰገኑ ናቸው፡፡ ✥   እኔ ባሪያህ ስለሃይማኖቴ የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ ስለ ዕውነቴ አይደለም ስለ መረዳቴም የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ ስለ ንጽህናዬም አይደለም በእግዚአብሔር ስም ስለ ኣመንኩ የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ በናቱም ጸሎት ስለ አመንሁ ንዑድ ክቡር ነኝ፡፡ ( አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አርጋኖን ዘሰኑይ) ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ 
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
"እርሷን ያየ ሰላም አለው" ቅዱስ ዲዮናስዮስ ❤️
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
👆
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
Enkuan aderesachehu
Mostrar todo...
+ ደስ ይበላችሁ! ደስ ይበላችሁ! ደስ ይበላችሁ! + ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ 4፡4 ላይ ‘‘ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ’’ ካለ በኋላ መልሶ ‘ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ’ አለ፡፡ አንዴ ደስ ይበላችሁ ካለ ቢበቃም በዛው ዓረፍተ ነገር ድጋሚ ‘ደስ ይበላችሁ’ ማለት ለምን አስፈለገው? ለነገሩ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መልእክቱ ላይ ደስ ይበላችሁ ያለው እዚህ ዓረፍተ ነገር ላይ ብቻ አልነበረም፡፡ በጣም አጭር በሆነው ባለ አራት ምዕራፉ ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ ጳውሎስ 16 ጊዜ ደስ ይበላችሁ ፣ ደስ ብሎኛል ፣ ደስ ይበለን ፣ ደስታዬ ተፈጸመ ፣ ደስ አለኝ ፣ ደስታ ፣ ደስ ፣ ደስ ብሏል፡፡ በዚም ምክንያት የፊልጵስዩስ መልእክት የደስታ መልእክት ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህን የምታነቡ ሁሉ እኔም ከሐዋርያው ጋር ልላችሁ እወዳለሁ ፤ ደስ ይበላችሁ! ምናልባት በዚህ ሰዓት በከባድ የመንፈስ ጭንቀትና ችግር ውስጥ ወይም በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ያለ ሰው ይህንን የቅዱስ ጳውሎስ ‘ደስ ይበላችሁ’ ጥሪ ሲያነብ ‘አንተ ደልቶሃል ወዳጄ እኔ እንኳን ደስ ሊለኝ ሰማይ ምድሩ ተደፍቶብኛል’ ማለቱ አይቀርም፡፡ የሚገርመው ግን ጳውሎስ ይህንን ዐሥራ ስድስቴ ደስ ይበላችሁ የሚል ደብዳቤ የጻፈው እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ነበር፡፡ እግሩ በሚቀዘቅዝ ጉድጓድ ውስጥ በሚከረክር ብረት ታስሮ ፣ እጆቹ ከመሬት ጋር በሰንሰለት ተጣብቀው እያለ ፣ ከታሠረ ሦስት ዓመት ሊሞላው ሲል በፈገግታ ተሞልቶ ‘ደስ ይበላችሁ’ የሚል ደብዳቤ ጻፈ፡፡ እስር ቤት ውስጥ ያለ ሰው ደብዳቤ እንዲጽፍ ዕድል ቢሠጠው ምን ብሎ የሚጽፍ ይመስልሃል? ‘የእስር ቤቱ አበሳ’ ‘የወኅኒው ምሥጢሮች’ ‘ገራፊዎቼና ጭካኔያቸው’ ‘የግርፋቴ ጠባሳዎች’ የሚል ዓይነት የደረሰበትን ሥቃይ የሚገልጹ መጻሕፍት አይጽፍ ይሆን? ያም ባይሆን ለቤተሰቦቹ ሲጽፍ ‘ኸረ ቁንጫውን አልቻልሁትም! ምግቡ አልተስማማኝም ፣ እገሌ ምነው አልጠየቀችኝም ደህና አይደለችም? ፣ እነ እንቶኔ ግን የማይጠይቁኝ ለምን ይሆን? እኔ ለእነርሱ እንዲህ ነበርሁ? ነግ በኔ አይሉም ወይ? ‘ያስተዛዝበናል ይኼም ቀን ያልፍና’ የሚል ይዘት ያለው ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም ባይሆን እንኳን ከእስር ቤት ውስጥ ሆኖ 16 ጊዜ ‘ደስ ይበላችሁ’ የሚል ደብዳቤ ጽፎ ለቤተሰቡ የሚልክ ሰው አይኖርም፡፡ እንደዚያ ብሎ ቢጽፍ እንኳን ቤተሰቦቹ ‘አእምሮው እየተነካ ነው! እነዚህ ሰዎችማ የሆነ ነገር ሳይወጉት አይቀሩም! ራሱን ሊያጠፋ ይሆን?’ ብለው ይጨነቃሉ እንጂ የእስር ቤቱን እንኳን ደስ አላችሁ ከቁም ነገር ቆጥረው ‘እንኳን አብሮ ደስ አለን’ አይሉም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የጻፈውን ደብዳቤ ግን ቤተ ክርስቲያን ከማንበብ አልፋ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አካተተችው፡፡ ጳውሎስ ደስ ያለው በእስር ቤቱ ፣ በሥቃዩ አልነበረም፡፡ ደስ ይበላችሁ ያለው በጌታ ነው! ከሚደርስበት መከራ በላይ የደረሰለት ፈጣሪ በልጦበት ውስጡ በደስታ ተሞልቶ ስለፈሰሰ ከታሰሩት አልፎ ውጪ ላሉት ደስታ እስከመመኘት ደረሰ፡፡ ጭንቅ ጥብብ ብሎህ ይህንን የምታነብ ወንድሜ ሆይ ጳውሎስም እንዳንተ ጭንቅ ላይ ሆኖ ‘በጌታ ደስ ይበልህ’ እያለ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ስታስብ መከራህ ሁሉ ትንሽ ይሆናል፡፡ ጳውሎስን በቀዝቃዛው ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ ደስታ ያሰጠመው ፈጣሪውን አስቦ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበር ውጪ ላሉት ክርስቲያኖች ‘በደስታ እጸልያለሁ’ አለ ፣ እሱ በሌለበት በተለያየ ምክንያት ወንጌል የሚሰብኩ ሰባኪያን በመብዛታቸው ‘ክርስቶስ ይሰበካልና ደስ ብሎኛል’ አለ፡፡ እስር ቤት መጥተው ላልጠየቁት ሰዎችም ‘አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ስለ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.