cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ARLO*አርሎ - ከእራስ ጋር ጨዋታ

ያለን ✊ እርግጠኛም የሆንበት አሁን እና አሁናችን ብቻ ነው። ዓላማችን👉🏻👉👉🏾ለሰው ልጅ ልቡን እና አዕምሮውን በማጣመር ዓለምን መምራት መቆጣጠር ማስቻል! የመልካም ስብዕና ግንባታ ፕሮግራም 👉አነቃቂ ሀሳቦች 👉ጥቅሶች 👉ግጥሞች 👉ኢትዬጲያዊ እና ጠቅላላ እውቀት 👉የመጽሐፍ ጥቆማ 👉አጫጭር ታሪኮች @nansab ✍ 🤝🤝@yemamlak✍✍🤝💌

Mostrar más
Advertising posts
216Suscriptores
Sin datos24 hours
-17 days
-330 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Mostrar todo...
ወደፊት ተራመድ - በደራሲና ገጣሚ ከፈለኝ ዘለለው - ሐዋዝ ሀሳብ Hawaz Hasab

ደራሲና ገጣሚ ከፈለኝ ዘለለው የ "ጥበብ ከተማ" ተብላ በምትታወቀው "ቀጨኔ" ውስጥ በ 1969 ዓ.ም ተወለደ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በ "ቀጨኔ ደብረ ሰላም" ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ "እቴጌ መነን" ት/ቤት አጠናቋል። ከጥበብ ጋር የተገናኘ ትምህርቱን ብዙ ስመ - ጥር ጥበበኞችን ባፈለቀው "ሆሊ ላንድ አርት አካዳሚ" ውስጥ ተምሮ "በአፃፃፍ ፣ በትወና እና በመድረክ ዝግጅት" ተመርቋል። ደራሲና ገጣሚ ከፈለኝ ዘለለው የበርካቶችን አዕምሮ በገንቢ ሀሳቦች በማነፅ የሚታወቀው የ "ሐዋዝ በጎ ሀሳብ ማጋሪያ ማዕድ" ዋና አዘጋጅ መሆኑም ይታወቃል። በ 1995 ዓ.ም "የሻማ ብርሃን ፩" ፤ በ 2004 ዓ.ም "አገልፋኖ" ፤ በ 2007 ዓ.ም "አሞዛ" ፤ በ 2014 ዓ.ም መጀመሪያ "ሐዋዝ" እና በ 2014 ዓ.ም መጨረሻ "የሻማ ብርሃን ፪" የተሰኙ አምስት አትጊ መፅሐፍትን አሳትሞ ለአንባብያን አበርክቷል። መፅሐፍቶቹም አፍሮ ሪድ (AfroRead) በተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት በዓለም አቀፍ ገበያ በ E- book እና Audio Book ለሽያጭ በቅተውለታል፡፡ "ሐዋዝ" የግዕዝ ቃል ሲሆን ፤ ትርጓሜውም "የሚያምር" ፣ "ደስ የሚል" ፣ "መልካም" እና "ቆንጆ" የሚል ነው፡፡ ይህንን ውብ ኢትዮጵያዊ ቃል የ "ዩቲዩብ ቻናላችን" መጠሪያ ስም አድርገን የተጠቀምንበት ዋና ምክንያት ፤ በዩቲዩብ ቻናላችን ላይ የሚለቀቁ ሀሳቦች ሁሉ ፤ ከመዝናኛነት በዘለለ … ደስ የሚሉ ፣ የሚያምሩ ፣ እንዲሁም የሰው ልጆችን አዕምሮ ፤ በበጎ ሊያንፁ የሚችሉ ፤ ቅንና ጠቃሚ ጭብጦች የሚተላለፉበት ዩቲዩብ ቻናል እንደሚሆን ፍፁም በመተማመን ነው፡፡

🌟 የማያረጅ ክንፍ ለልብ እንጂ ለገላ የለውም 🌟 ቅንነት ቁስልን ይሽራል ፤ ይቅር ባይነት ጠባሳን ያጠፋል ፤ ጥበበኛነት ከትላንት ህመም የዛሬን ጤና ይሰራል.... ከስህተት ፍራቻ ነፃ የሚያወጣ ስህተትን የመጋፈጥ .. ሀላፊነትን የመቀበል .. እራስን የመኖር እውነት ህይወት ላኖረ የመገዛት ትህትና ብቻ ነው። 💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙
Mostrar todo...
👍 1 1
በህይወት .. ከሚገባን እውነት በላይ ቅን እምነታችን የህይወታችን ውድ ስጦታችን ነው። ከልክነታችን በላይ ቅንነታችን ለመኖራችን ትልቁ በጎ ገፅ ነው። በእርሱ ውስጥ ደግሞ ብዙ ስህተቶችን ልናስተናግድ እንችላለን ...ታዲያ የዛኔ መመዘኛችን ልክ አለመሆናችን ሳይሆን ቅን ሀሳባችን ነው። 🌟🌟🌟🌟🌟 ጴጥሮስ በግብሩ ቢወድቅም በቅን ሀሳቡ ዳግም በምህረት ቆሟል። 🌟🌟🌟🌟🌟 🏄🏽‍♀️🏄🏽‍♀️🏄🏽‍♀️🏄🏽‍♀️🏄🏽‍♀️🏄🏽‍♀️🏄🏽‍♀️ 💙 መኖር መልካም ነው! 💙 የህይወትን በጎ ገፅ ለመቃኘት ቤተሰባችን ይሁኑ     💙💙💙 ARLO 💙💙💙 https://t.me/+OJvsW66bzAlhMWJk https://t.me/+OJvsW66bzAlhMWJk 🌾💙🌾💙🌾💙🌾💙🌾
Mostrar todo...
♦️ሰንሰለታማ ሕይወት ♦️ ቆይታ ከመምህር ደራሲና ገጣሚ ከፈለኝ ዘለለው ጋር https://youtube.com/watch?v=ijXwEfGsLRs&si=l2BE-wgjdlEF0ZX6
Mostrar todo...
♦️ሰንሰለታማ ሕይወት ♦️ ቆይታ ከመምህር ደራሲና ገጣሚ ከፈለኝ ዘለለው ጋር

ባለክንፉ        በለአክናፉ ዓለም ሙሉ ሳለች ለርሱ ለህፃንነት ንፁህ ነፍሱ አደገና        አወቀና               ተማረና ጎድላ አገኛት በመማሩ    ተመለሰ ወደኋላ ካለማወቅ         ካለመማር             ካለማደግ በነበረው ጊዜ ቀና     ዳግም ህፃን        ዳግም አዲስ            ዳግም ባዶ    በሚመስል ትህታና     ከእድሜ ሳይሆን     ከንፁ እምነት   ደግሞ እንዳዲስ          በይቅርታ   ተወለደ ልብ* አለና!
Mostrar todo...
1
ኢትዮጵያ የሕይወቴን ሰላም የዓይኖቼን ብሌን አታሳየኝ አምላክ ሲከፋት ሀገሬን የሰው ልጅ ሲጨንቀው ሲያጣ መሸሸጊያ ሀገሩ ናት ዳሱ ለስጋው ማረፊያ ቢራብም ቢታረዝ ክፉኛ ደህይቶ ክብሩ ነው ለሰው ልጅ ሀገሩን ማቆየት ለሀገሩ ሞቶ! ገፃችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!👇 https://www.youtube.com/channel/UCgK1RJHl2dQDQdLlJFUExfQ https://youtu.be/IVkkB1mH8A4
Mostrar todo...
ኢትዮጵያ (ክብሬ እና መልኬ) - በደራሲ እና ገጣሚ ከፈለኝ ዘለለው - ሐዋዝ ሀሳብ Hawaz Hasab

ዛፍ … ከገዛ ራሱ ላይ እየተገነጠሉ … የመጥረቢያ እጀታ በመሆን እየቆረጡና እየፈለጡ ሕልውናውን አደጋ ላይ በጣሉበት የራሱ ቅርንጫፎች አምርሮ አዝኗል። ነገሩ ራስ አይወቀስ ራስ አይከሰስ እንዲሉት ዓይነት ነው! በዛፍ ውድቀተ ዘመን … አዛኝ ቅቤ አንጓቾች ተሰብስበው ዛፍ ሆዬ ተቆርጦ ከወደቀበት ሥፍራ ይከሰቱና ... "እንደው ምን በድለህ... ምንስ አስቀይመህ ይሆን ይህን ሁሉ ጉዳት ያደረሱብህ!... ድንቅ እኮ ነው! አንተ ጥላ ሰጪ እንጂ ጠላት አይደለህ... ምን አድርግ ብሎ ነው ..."ብረት" ተብዬ … ክፋትን ስንቅ አድርጎ በጭካኔው የዘመትብህ!? የትኛውንስ ነውር ነውረህ ነው የበደል ክንዱን ያሳረፈብህ!? ... አዬዬ እንዲህ የፍርድ አልባ ሀገር ነዋሪዎች ሆነን እንቅር! አይ ጊዜ! ይገርማል! ለማንኛውም … ሕመምህን ፈዋሽ በማጣት በደረሰብህን ሀዘን ከልብ አዝነናል፡፡ ተቆጭተናልም!! … አንተስ ግን እስከመቼ ነው የጠላቶችሁ ሎሌ ሆነህ የምትኖረው?! ማንስ ነው ችግርህን ችግሬ ብሎ ከተጨቋኝነት ነፃ የሚያወጣህ ነፃ አውጪ!? ተንቀሀል! እጅግ ተደፍረሀል እኮ! ምን እስክትሆን ነው ፍዘቱ! በል የወዳጅነት ምክራችንን ስማ! ከዛሬዋ ዕለት ጀምረህ… ጠላትህን እሹሩሩ ማለት አቁምና እንዴትም ብለህ አንድ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ጀምር!" ብለው የአጥፍተህ ጥፋ ወኔን በተረጋጋ መንፈሱ ውስጥ ዘሩበት። በዛፍ እሳትነት ላይ ነዳጃቸውን ረጩ፡፡ አጉል መካሪ ከእሳት ጨማሪ እንዲሉት አይደል። ዛፍ ... በመካሪዎቹ የአስተሳሰብ ድንዛት ተናደደ! ... በእይታ ጥበታቸው ተነካ!... በገረጀፈ ዕውቀታቸው አፈረ!..."ኑ ብሉ ሳልላችሁ ወጥ አውጣልን ማለታችሁ አሳፍሮኛል! እባካችሁ ካላስቀየምኳችሁ … ያለ ዕውቀት ... ጥልቀት በሌለው ሀቅ ማንንም አትምከሩ! ያለ ጥበብ ... በባዶ ሕሊና ማንም ላይ አትፍረዱ! ያለ እውነት ... በጃጀ ብልሀት አትስበኩ! አጥፊነት የድንቁርና ውጤት ነው። ከድንቁርና ሳትርቁ ለማስተላለቅ አትራቀቁ! የእኔ ... የ "ዛፍ" ጠላት "ብረት" አይደለም። የእኔ ጠላት ...የእኔው የገዛ የራሴ ጠማማነት ነው። የሩቅ ጠላት የለኝም። ደግሞስ የውስጥ ጠላት ከሌለ የውጭ ጠላት እንደማይጎዳ አታውቁምን!? አዎን የእኔ ቆራጭና ፈላጭ የራሴው አካል ነውና ለእኔ መውደቅ ሌላውን ያለሀጢያቱ አትኮንኑ" ሲል ቁጣን በተሸከመ ሀይለ ቃል መልስ ሰጣቸው። … እውነቱን እኮ ነው ዛፍ ... ወንፊት የራሷን በርካታ ቀዳዶች ሳትደፍን መርፌ ባለባት አንዲት ቀዳዳ ብትናደድ ምን ይሉታል!? ራስን ሳይገሩ ሌላን መምከሩስ ነገሩን ማምረር አይሆንምን!? ቀጠለ ዛፍ... "እናም የእኔን እከክ እኔው እንዳከው ተዉኝ! ሕመሜን ፈዋሽ እንጂ ቁስሌን አባባሽ አልፈልግም። ለራሴ ችግር የራሴን መፍትሔ እሻለታለሁ።" ብሎ በእፎይታ ተነፈሰ። ይኸው ነው እንግዲህ ... ልክ እንደዛፉ የራሱን ችግር ከመረዳት የተነሳ ሰው ቢቸገርም ለችግሩ መፍትሔ አያጣም። ችግራችን መቸገራችን ሳይሆን የችግራችንን ምንጭ በውል አለማወቃችን ነው። ብናውቅም አውቆ አላዋቂነታችን አጠፋፍቶናል! ሰዎች በጫሩን ቁጥር ተቃጥለን የምናቃጥል ከሆነ ታሪካችንን ሁሉ በዜሮ እያባዛን የዜሮነት ዘመን ላይ በዜሮነት መኖር የሁላችንም ዕጣ ፈንታ ይሆናል። ለዛፉ መቆረጥና መውደቅ የዛፉ ጠማማ ቅርንጫፎች የመጥረቢያው እጀታ በመሆን ግዙፍ ትብብር ለግሰዋል። የመጥረቢያ ብረት... ያለዛፉ እንጨት ... ቆርጦ የመጣል አቅም ኖሮት አያውቅም። ያስቸገረን የእኛው ጠማማ ነውና የመፍትሔ ውሳኔአችንን ጠማማችንን ከማቅናት ስንጀምር በሁካታ ሳይሆን በእፎይታ መኖር ከባድ አይሆንብንም። በእኛው የክብሪት እሳት እየነደደች ያለች ቤታችን የእኛኑ ማጥፊያ ውሃ ትሻለች። ክብሪቱን የጫረ እጅ … ውሃን መቅዳት እንደማይሰንፍ አምናለሁ። "ሐዋዝ" የግዕዝ ቃል ሲሆን ፤ ትርጓሜውም "የሚያምር" ፣ "ደስ የሚል" ፣ "መልካም" እና "ቆንጆ" የሚል ነው፡፡ ይህንን ውብ ኢትዮጵያዊ ቃል የ "ዩቲዩብ ቻናላችን" መጠሪያ ስም አድርገን የተጠቀምንበት ዋና ምክንያት ፤ በዩቲዩብ ቻናላችን ላይ የሚለቀቁ ሀሳቦች ሁሉ ፤ ከመዝናኛነት በዘለለ … ደስ የሚሉ ፣ የሚያምሩ ፣ እንዲሁም የሰው ልጆችን አዕምሮ ፤ በበጎ ሊያንፁ የሚችሉ ፤ ቅንና ጠቃሚ ጭብጦች የሚተላለፉበት ዩቲዩብ ቻናል እንደሚሆን ፍፁም በመተማመን ነው፡፡

every time you're about to judge someone harshly, remember this: they were once a child, pure and untainted, just like you. life, with its twists and turns, shapes us in myriad ways. their journey, filled with its own battles and scars, might have led them down paths you can't understand. but beneath the layers of what life has made them, that innocence still exists. recalling this doesn't just soften your heart, it transforms your perspective.
Mostrar todo...
👍 1
ሚስት በደላላ ያገባው አባወራ መጨረሻ // Geez Entertainment 2024 https://youtube.com/watch?v=CDQVHcZ8hqY&si=oakZWB_o7syd0PjN
Mostrar todo...

ያለቦታው የዋለ ያለዋጋው ከመተመኑ በላይ ፤ የሚተመንበትም መጠን በልኬቱ ካሎነ ቢያንስም ቢበዛም ስህተት ይሆናል። እንቁ ያለስፍራው በዝቅታ ቢገለጥ በዋጋው ልክ መክበርን አያገኝም .. ወርቅ ያለልኩ እጅግ ቢከብር ድምቀቱ በተሰጠው ክብር ልክ አያስጌጥም .. ሁሌም ሁሉም ነገር በልኩ እና በቦታው ሲገለጥ ያምራል.. ይህን መረዳት ሚያስችለን የመበላለጥ ሚዛን ሳይሆን ዋጋን የማወቅ ጥበብ ነው። ወርቅም ወርቅ እንቁም እንቁ ናቸው ፤ የተፈጥሮ ገፅታቸው እራሳቸውን ብቻ የሚወክሉበት መታያ የሰጣቸው።
Mostrar todo...