cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ethiopian Electric Utility

EEU Official Telegram Channel Web: www.eeu.gov.et

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
24 799
Suscriptores
+1524 horas
+617 días
+37930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን በሚገኘው የራይቱ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት የገኒር ከተማን ጨምሮ በምስራቅ ባሌ ዞን ውስጥ የሚገኙ ከተሞች የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል። የቴክኒክ ብልሽቱን ለማስተካከል የዘርፉ ባለሙያዎች ጥረት እያደረጉ መሆኑን እየገለጽን ክቡራን ደንበኞቻችን በትግዕስት እንዲጠብቁ መልዕክት እናስተላልፋለን። #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ውድ የመኖሪያ ቤት ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኛችን፤ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳቦትን በቀላሉ ለማስላት ያመችዎት ዘንድ ይህንን #የታሪፍ መረጃ ይጠቀሙ፡፡ ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብዎትንም በወቅቱ ይፈፅሙ! #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Mostrar todo...
👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ በተፈጸመ ዝርፊያ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደረሰ በ2016 በጀት አመት ብቻ ከሦስት መቶ በላይ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ዝርፊያ የተፈፀመ ሲሆን ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የተቋሙ ሃብት ላይ ኪሳራ ደረሷል፡፡ በበጀት ዓመቱ ከተፈጸሙ ከሶስት መቶ በላይ ወንጀሎች ውስጥ በ31 ግለሰቦች ላይ ብቻ ከአንድ ዓመት እስከ 18 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል። በተመሳሳይ "የተቋሙን ሰራተኞች በመምሰል ከስምንት ደንበኞች ከ30 እስከ 40ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ሲቀበሉ የነበሩ ህገ-ወጦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጦ የ18 ዓመት ጽኑ እስራትና የ20 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ተወሰኖባቸዋል። በህገ ወጥ መንገድ ቆጣሪ ለማስገባትና ያልተገባ ጥቅም በመጠየቅ ተሳትፈው የተገኙ ሶስት የተቋሙ ሰራተኞችም አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ከስራ እንዲሰናበቱ ተደርጓል። በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀመው ዝርፊያ በተቋሙ ላይ ከሚደርሰው ጉዳት በተጨማሪ በዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ወንጀልን በመከላከል ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል። #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Mostrar todo...
👍 9 1
Photo unavailableShow in Telegram
የመልሶ ግንባታ ስራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦቱ ይቋረጣል ነገ ማክሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ በሀረር ከተማ ስላሴ ቤተክርስቲያን አካባቢ፣ አሚር ኑር አዳራሽ እና ሸዋ በር አካባቢ፣ ቡዳ በር ፣ ደከር፣ ሞቢል፣ አጂብ፣ ምስራቅ እዝ ቀበሌ 05፣ 15 በከፊል ቀበሌ 14 ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ድሬ ጥያራ እና አካባቢው የመልሶ ግንባታ ስራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦቱ ይቋረጣል፡፡ ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ውድ ደንበኞቻች የኃይል አቅርቦቱ በስራ ምክንያት የሚቋረጥ መሆኑን አውቃችሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እድታደርጉ እናሳውቃለን። #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Mostrar todo...
👍 14
Photo unavailableShow in Telegram
የታሪፍ ክለሳው የኃይል ብክነቱን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተጠቆመ ለኃይል ብክነት ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ የሚጠቀሰው በማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የሚከሰት የኃይል ብክነት በመሆኑ ኔትወርኩን በአስተማማኝ ሁኔታ በመገንባት እየባከነ ያለውን ኃይል ጥቅም ላይ ለማዋል የታሪፍ ክለሳው ጉልህ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡ በሀገሪቷ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት የኃይል ማስተላለፊያ እና ማሰራጫ መስመሮች ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ እና በተለያየ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የተጎዱ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ የጥገና እና የመልሶ ግንባታ ስራ የሚያስፈልጋቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ተጭነው ያንብቡ!! http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/news/detail/819?lang=am
Mostrar todo...
👎 8👍 5
የቦንጋ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ኤሌክትሪክ በአንድ ቀን ዘመቻን በይፋ ተቀላቀለ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሪጅን የቦንጋ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ኤሌክትሪክ በአንድ ቀን ዘመቻን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡ ማዕከሉ ዘመቻውን በይፋ የተቀላቀለው በበጀት አመቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሳያከናውኑ የቆዩ ውዝፍ ስራዎችን ለማጠናቀቅና የህብረተሰቡን የኃይል ጥያቄ ለመመለስ ነው፡፡ በተጨማሪም በአገልጎት አሰጣጡ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታት፣ የደንበኞችን ጥያቄ በአጭር ጊዜ መመለስና የተቋሙን የአዲስ ደንበኞችን ቁጥር ለመጨመር ነው። እስካሁን በተሰራው ስራ የቦንጋ ከተማ ዲንቻ እኛ ባንዲራ አካባቢ ደንበኞችን የሃይል ጥያቄ መመለስ የተቻለ ሲሆን በቀጣይ በሌሎች አካባቢዎችም ተጠናክሮ ሚቀጥል ይሆናል፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Mostrar todo...
9👍 5
Mostrar todo...
ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቻችን በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣የጤናና ደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡

11👍 6👎 3
ባለፉት አስር ተከታታይ የቅዳሜና የህዝብ በዓላት ሲካሂድ የቆየው ነፃ የስራ ዘመቻ ተጠናቀቀ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከየካቲት 09 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አስር የቅዳሜ ቀናትና በተመረጡ የህዝብ በዓላት ሲያካሂደው የቆየው የነፃ የስራ ዘመቻ መረሃ ግብር ዛሬ ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቋል፡፡ ተቋሙ በጀት ዓመቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሳያከናውኑ የቆዩ ውዝፍ ስራዎችን በነፃ የስራ ዘመቻ ለማካካስ መርሃ ግብር አውጥቶ ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን በስራ ዘመቻው የኃይል አቅርቦቱ እንዲቆራረጥ ብሎም በአግባቡ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዳይሆን የሚያደረርጉ መንስኤዎችን በመለየትና ምላሽ በመስጠት ያልተቆራረጠና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም የሃይል ማሰራጫ መስመሮች የጥገና ስራ፣አዲስ ሃይል ማገናኘት፣ የካርድ መሙላት፣ ውል እድሳት፣ ያልተፈቱ የህብረተሰብ ቅሬታዎችን መፍታት እና በመደበኛ የስራ ቀናት ያልተጠናቀቁ ጅምር ስራዎች የማጠናቀቅ ስራ ተሰርቷል፡፡ የስራ ዘመቻው መካሄዱ ደንበኞች በስራ መደራረብ ምክንያት በመደበኛ የሥራ ቀን ያላገኙትን አገልግሎት ለመስጠት ከማሳችሉም በላይ ያላለቁና በእንጥልጥል ላይ ነበሩ የመስክና የቢሮ አገልግሎቶች ለማጠናቀቅ ምቹ ሁኔታም ፈጥሯል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅርቡ ባፀደቅው የሠራተኞች ህብረት ስምምነት መሰረት ጥራት ያለው አገልግሎት ለደንበኞቹ ለመስጠትና የእርካታ ደረጃቸውን ለማሳደግ ከመደበኛ የስራ ቀናት በተጨማሪ ቅዳሜ ለግማሽ ቀን በቋሚነት አገልግሎት እንደሚሰጥ መግለጻችን የሚታወስ ነው፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Mostrar todo...
👍 3 1👏 1
የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በግንባታ ላይ ያለውን የልህቀት ማዕከል ጎበኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ኮተቤ አካባቢ አየተገነባ ያለውን የተቋሙን የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ጎብኝተዋል፡፡ የልህቀት ማዕከል ግንባታው እየተከናወነ ያለው ኮተቤ በሚገኘው የተቋሙ ግቢ ውስጥ ሲሆን አጠቃላይ ግንባታውም በ16.7 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ የሚከናወን ሲሆን ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ 9 ነጥብ 3 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር በጀት ተመድቦለታል፡፡ በግንባታ ላይ የሚገኘው የልህቀት ማዕከል በዋናነት የኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ ሙያ ማዳበሪያ፤ ሁለገብ የሰው ኃይል ማሰልጠኛ፣ የምርምርና የልህቀት ማበልፀጊያ፣ ብሄራዊ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ስካዳ መቆጣጠሪያ ጣቢያ፣ የዲስትሪቡዩሽን ዕቃዎች ጥራት ፍተሻ እና ላብራቶሪ ፋሲሊቲዎችን የሚያሟላ ነው፡፡ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከሉ አጠቃላይ ሲቪል ግንባታ ስራዎች ዘጠኝ የተለያዩ ስፋትና ከፍታ ያላቸው ህንፃዎች እንዲሁም በፊፋ ስታንዳርድ የሚገነባ ዘመናዊ ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ስታዲየምን ያካተተ ነው፡፡ በመከናወን ላይ ያለው የልህቀት ማዕከል ግንባታ ከዋና ግቡ በተጨማሪ፤ደረጃውን የጠበቀ የስብሰባ አዳራሽ፣ የሰልጣኞችና እንግዶች ማረፊያ ቤቶች እና ክሊኒክን የያዘ ነው፡፡ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታው በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እየተከናወነ ያለ ሲሆን፤ አጠቃላይ የግንባታ ስራውን ለማጠናቀቅ ሁለት አመታት ተቀምጦለታል፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የምህንድስና ጥናት፣ ዲዛይን፣ሱፐርቪዥንና ኮንትራት አስተዳደር ስራው በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት የተከናወነ ሲሆን፤የፕሮጀክቱ የማማከር እና የክትትል ስራ ደግሞ መንግስታዊ ተቋም በሆነው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እንዲሁም በተቋሙ የግንባታ ስራዎች ቢሮ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Mostrar todo...
👍 9 1👏 1
1