cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

ስለ ፍትህ ስለ እኩልነት እና ስለ ዲሞክራሲ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 837
Suscriptores
-324 horas
+97 días
+730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በ4 ቢሊዮን ብር የሚገነባው የቅዱስ ያሬድ ሙዚየም⁉ ቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ምዕራፍ፣ ዝማሬና መዋሥዕት የተሰኙትን 5 የዜማ መጻሕፍት የደረሱ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው፡፡ ብቸኛው የግእዝ ሥነ ጽሑፍ መስራች እንደሆኑም ይነገራል፡፡ ለእኚህ ኢትዮጵያዊ ሊቅ የሕይወት ታሪካቸውን የሚዘክር ሙዚየም በታላቁ ራስ ዳሽን ተራራ ላይ በ4 ቢሊዮን ብር ወጪ ሊገነባ ነው፡፡ የፕሮጅክቱ ሰብሳቢ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ቅዱስ ያሬድ የመጀመርያው የዜማ ሊቅ ብቻ ሳይሆን በድርሰትም የመጀመርያው መሆናቸውን ገልጾ በስማቸው የሚገነባው ሙዚየም የቅኔ ትምህርት፣ የዝማሬ ትምህርትና በርካታ ዘርፎችን የሚያካትት እንዲሁም ብዙ ሊቃውንትን የሚያፈራ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ጋዜጠኛው አክሎም የአካባቢው ገበሬ ፕሮጀክቱን ስለወደደው 6 ሄክታር መሬት መስጠቱን ገልጿል፡፡ በዚህ ሙዚየምም የአሁኑ ትውልድ የራሱን አሻራ የሚያሳርፍበት ታሪካዊ፣ ሀይማኖታዊ እና ሀገራዊ ፋይዳ እዳለውም ጨምሯል፡፡ እነቅዱስ ላሊበላ በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሰሩት አስከዛሬ ላለው ትውልድ እንደጠቀመ ሁሉ እኛም ይሄንን በመስራት ለቀጣይ ትውልድ ትልቅ መሰረት የምንጥልበት ነውም ብሏል፡፡ በታላቁ ራስ ዳሽን ተራራ በደብረ ሐዊ ገዳም አቅራቢያ በሚገነባው ሙዚየም ውስጥ አንዱ የሆነው ህንፃ ቤተክርስቲያን የኖህ መርከብን ቅርጽ የሚይዝ መሆኑንም የፕሮጀክቱ ዋና አርክቴክት መኮንን ወርቁ ተናግረዋል፡። የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ይዘትም አካባቢውን የዋጀ እና በዋሻ መልክ የሚገነባ ሲሆን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ታግዞ የሚከወንም መሆኑንም አርክቴክቱ አንስተዋል፡፡ ሙዚየሙ በስማቸው የሚገነባላቸው ሊቁ ባለቅኔ የዜማ አባት ቅዱስ ያሬድ መጻሕፍትን በጣዕመ ዜማ ደርሰዋል፡፡ መዝሙረ ዳዊትን ጨምሮ ሌሎችንም ቅዱሳት መጻሕፍትን በዜማው ያመሠጠሩ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰፊ የአገልግሎት ድርሻ ያላቸው ግእዝ፣ ዕዝልና አራራይ የዜማ ዓይነቶች የቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰቶች ናቸው፡፡ #ማቲ_ሸገር የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu
Mostrar todo...
👍 1
👇👇👇👇👇
Mostrar todo...
ዛሬ 7 ነው የቅድስት ስላሴ አመታዊ እለት‼ ቅድስት ስላሴ በበረከቱ ይጎብኛችሁ🙏 አሜን🙏
Mostrar todo...
7👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቅዱስ ሲኖዶሰ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ለመነኮሳት ምህላ አወጀ⁉ " ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡" #ማቲ_ሸገር የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu
Mostrar todo...
👍 5 2
02:06
Video unavailableShow in Telegram
በቅርቡ በቅዱስ አባታችን በረከታቸው ይደርብንና በአቡነ ጴጥሮስ የህይወት ታሪክ ላይ ያጠነጠነ ፊልም ተሰርቶ ለእይታ ሊበቃ መሆኑን ሰምተናል‼ እስኪ ሃሳባችሁን አካፍሉኝ #ማቲ_ሸገር T.me/matiosbirhanu
Mostrar todo...
6.94 MB
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
ጀፒ እውነት ውሸት ነበር የመሰለኝ ማመን ይከብዳል ነብስህ በሰላም ትረፍ ወንድሜ😭 RIP😭
Mostrar todo...
😢 4
አሁን በኤፍ ኤም አዲስ 96.3 በቀጥታ ስርጭት እከሰታለሁ‼
Mostrar todo...
👍 3👎 1
እጅግ ድንቅና ስኬታማ ነበረ🙏 በዛሬው የማህበራችንን 8ተኛ መደበኛ ጉባኤ ማጠቃለያ ኮንፈረንስ በደመቀ እና ባማረ ሁኔታ አካሂደናል‼ ማህበራችን በብዙ ውጣውረዶች ውስጥ በስኬት ጎዳና በመጓዝ ለከተማችን ወጣት ድምጽ በመሆን ያገለገለ ድንቅ ተቋም ነው በዛሬው እለትም በዚህ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ሚና ለነበራቸው የቀድሞ አመራሮች እውቅና ሰተናል። ይህንን ፕሮግራም ያማረና የደመቀ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ አካላት ሁሉ ምስጋናችን ትልቅ ነው🙏 ማቲ ሸገር የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu
Mostrar todo...
👍 4🏆 2 1
ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 17 ይጀምራል ።ሁሉም ክርስቲያን ሊጾመው የሚገባ ከ7ቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው‼
Mostrar todo...
👍 2
💒 በዓለ ጰራቅሊጦስ እና ለሐዋርያት የተገለጠላቸው ልሳን 💒 𝗣𝗮𝗿𝗮𝗰𝗹𝗲𝘁𝗲(𝗽𝗮𝗿𝗮𝗸𝗹𝗲𝘁𝗼𝘀) — 𝗦𝘂𝗻𝗱𝗮𝘆 𝗼𝗳 𝗣𝗲𝗻𝘁𝗲𝗰𝗼𝘀𝘁 " ሚ መጠን ግርምት ዛቲ ዕለት ወዕፅብት ዛቲ ሰዓት እንተ ባቲ ይወርድ መንፈስ ቅዱስ እመልዕልተ ሰማያት ይህች ቀን ምን ያህል የምታስፈራ ናት? ይህች ሰዓት ምን ያህል የምታስጨንቅ ናት? መንፈስ ቅዱስ ከሰማየ ሰማያት የሚወርድባት" (ሥርዓተ ቅዳሴ) ሁሉም ኀይል የሚሆናቸውን መንፈስ ተሞሉ፣ ይናገሩ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዳደላቸው መጠን እየራሳቸው በየሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመሩ፡፡ (ዮሐ. ሥራ 2÷1) ወሀለዉ በኢየሩሳሌም ሰብእ ኄራን አይሁድ ይነብሩ እምኲሉ አሕዛብ ዘመትሕተ ሰማይ፡፡ ወሰሚዖሙ ዘንተ ቃለ ተጋብኡ ኲሎሙ ድንጉፃኒሆሙ፣ እስመ ሰምዕዎሙ ይነብቡ ኲሎሙ በነገረ በሓውርቲሆሙ፡፡ ወደንገፁ ወአንከሩ ወይቤሉ አኮኑ ሰብአ ገሊላ እሉ ኲሎሙ፡፡ እፎኑ እንከ ንሰምዖሙ ይነብቡ በነገረ ኲሉ በሓውርቲነ፡፡ ከሰማይ በታች ካሉ አሕዛብ ሁሉ የሚኖሩ ደጋግ አይሁድ ሰዎች በኢየሩሳሌም ነበሩ፡፡ ይህን ቃል ሲናገሩ ሰምተው ሁሉም ደንግጠው ተሰበሰቡ፤ ሁሉም በያገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና፡፡ ደነገጡ አደነቁ፤ እንዲህም አሉ፤ እነዚህ ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን፡፡ እንግዲህ በየሀገራችን ቋንቋ ሲናገሩ እንዴት እንሰማቸዋለን፡፡ (የሐዋ. ሥራ 2÷5)፡፡ "በዛቲ ዕለት ሰንበተ ክርስቲያን ወረደ ጰራቅሊጦስ መጥበቤ አዳብን ላዕለ ሐዋርያት ቡሩካን እንዘ ሀለዉ ጉቡኣን በጽርሐ ጽዮን ፡ ሰትዮሙ ዘኢኮነ ስቴ ወይን ሰትዮሙ ስቴ መንፈስ ዘበአማን ወተናገሩ በሐዲስ ልሳን።" ( ዝማሬ ዘቅዱስ ያሬድ ) በዓለ ጰራቅሊጦስ በመንፈስ ቅዱስ ለምትመራው የሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የልደት ቀኗ ነው፡፡ የሐዋርያትን ፈለግ በምትከተል ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከሚከበሩ ዘጠኝ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡ ይህም በዓል በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 በተገለጸው መልኩ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለ120ው ቤተሰብ የወረደበትን ዕለት የምናስብበት ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ ማለት ምን ማለት ነው? ጰራቅሊጦስ ማለት የግሪክ ቃል ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የሚገልጥ ነው፣ ትርጉሙም መንጽኢ (የሚያጸና)፣ መንጽሒ (የሚያነጻ)፣ ናዛዚ (የሚያጽናና፣ የሚያረጋጋ) ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ጰራቅሊጦስ ማለት ከሣቲ (ምስጢር ገላጭ)፣ መስተሥርዪ (ይቅር ባይ) እና መስተፍሥሒ (ደስታን የሚሰጥ) ማለት ነው፡፡ ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበዙት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በኋላ አይሁድን ፈርተው ይሸሹ ነበር፡፡ ከአይሁድ ፍርሃት ሙሉ በሙሉ መላቀቅ ያልቻሉ ደቀመዛሙርቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነርሱ ተለይቶ እንደሚያርግ ሲነግራቸው አዘኑ፡፡ ለተልዕኮ የጠራቸው፣ ዓለምን በወንጌል ብርሃን እንዲያበሩ የመረጣቸው ጌታ ግን ለድካማቸው አሳልፎ አልሰጣቸውም፡፡ ከትንሣኤው በኋላ እስከ ዕርገቱ ድረስ ለ40 ቀናት እየተገለጠላቸው እምነታቸውን አጸናላቸው፣ ቅዱስ ቃሉን አስተማራቸው፣ ለሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንም መሰረት የሆነ መንፈሳዊ ሥርዓትን አሳያቸው፡፡ ሰብሳቢ፣ ጠባቂ እንደሌላቸው የሙት ልጆች የሚሆኑ መስሏቸው ነበርና “ኢየኀድገክሙ ዕጓለ ማውታ ትኩኑ” ወላጆች እንደሌላቸው የሙት ልጆች ትሆኑ ዘንድ አልተዋችሁም" አላቸው፡፡(ዮሐ. 14፡18) ስለ ስሙ መከራን ለመቀበል እንዲጸኑ መንጽኢ (የሚያጸና) መንፈስ ቅዱስ ያስፈልጋቸው ነበርና “እኔ የአባቴን ተስፋ ለእናንተ እልካለሁ፤ እናንተ ግን ከአርያም ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ተቀመጡ፡፡” (ሉቃስ. 24፡49) በማለት ተስፋ ሰጣቸው፡፡ ይህም ተስፋ አስቀድሞ በነቢያት የተነገረ ነው ። (ትንቢተ ኢዩ. 2፡15)፡፡ “ወይቤሎሙ ከማሁ ጽሑፍ ከመይትቀተል ክርስቶስ ወይትነሣእ እምነ ምዉታን በሣልስት ዕለት፡፡ ወይሰብኩ በስሙ ለንስሓ ወለኅድገተ ኀጢአት ለኵሉ አሕዛብ እኂዞሙ እምኢየሩሳሌም፡፡ ወአንትሙሰ ሰማዕቱ ለዝንቱ ነገር፡፡ ወናሁ አነ እፌኑ ተስፋሁ ለአቡየ ላዕሌክሙ፣ ወአንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከ ትለብሱ ኀይለ እምአርያም፡፡ ክርስቶስ እንዲሞት በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ እንዲነሣ እንዲሁ ተጽፎአል አላቸው፡፡ ንስሓ እንዲገቡና ኀጢአታቸው እንዲሰረይላቸው፣ ከኢየሩሳሌም ጀምረው ለሕዝቡ ሁሉ በስሙ ያስተምራሉ፡፡ እናንተም ለዚህ ነገር ምስክሮቹ ናችሁ፡፡ እነሆ እኔ የአባቴን ተስፋ ለእናንተ እልካለሁ፣ እናንተ ግን ከአርያም ኀይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ተቀመጡ፣” (ሉቃ. 24÷46)፡፡ ሲል እርሱ መከራ መስቀልን ሊቀበል፣ ምስጢረ መስቀልን ሊፈጽም በመጻሕፍት እንደ ተገለጠና ያም እንደ ተፈጸመ፣ አሁንም መነሻው ከኢየሩሳሌም ኾኖ በኦሪት፣ በጣዖት ተለያይተው፣ በኀጢአት ገመድ ታሥረው ለኖሩ ኹሉም ወደ ክርስቶስ እንዲመለሱ፣ የነበሩበትን ትተው፣ ተጠጥተው በጥምቀት እንዲታደሱ፣ የኀጢአታቸውን ሥርየት እንዲቀበሉ የወንጌል ትምህርት ለኹሉ እንደሚሰጥ፣ እርሱም ከአብ ዘንድ እልክላችኋለሁ ያላቸውን ተስፋ እንደሚያጸናላቸው፣ እነርሱም ባዩት፣ በሰሙት፣ በተማሩት ሊመሰክሩለት እንደ ተመረጡ ካስረዳቸው በኋላ ኀይልን ከአርያም እስኪለብሱ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፡፡ ቀኑ ሞላ፡፡ የማያደርገውን የማይናገር፣ የተናገረውን የማያስቀር አምላክ ጌታ በተነሳ በሃምሳኛው ቀን፣ “በወንዶችና በሴቶች ባሮቼ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤” ያለውን ቃል በጽርሐ ጽዮን ፈጸመ፤ መንፈስ ቅዱስን ለደቀ መዛሙርት ሰጠ፡፡ በስፍራው የነበሩ ኹሉ ያንን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፡፡ እስራኤል እንደ ጠጡት ከደንጊያ እንደ ፈለቀው ውኃ አልነበረም፤ እሳታዊ ነበልባላዊ መጠጥ ነው፡፡ ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ሆኑ፣ ሁሉም በአንድ ቃል የክርስቶስን አምላክነት መሰከሩ፡፡ በጊዜው የነበረው ሁኔታ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደ ተገለጠው ቀጥሎ ባለው ሁኔታ ተጽፎአል፡፡ “ወአመ ተፈጸመ መዋዕለ ጰንጠቆስጤ እንዘ ሀለዉ ኲሎሙ ኀቡረ አሐተኔ፡፡ መጽአ ግብተ እምሰማይ ድምፅ ከመ ድምፀ ነፋሰ አውሎ ወመልአ ኲሎ ቤተ ኀበ ሀለዉ ይነብሩ፡፡ ጰራቅሊጦስ ስለምን ኀምሳው ቀን በተፈጸመ ጊዜ ወረደ? የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በግልጥ ለሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የተገለጠው ቅዱሳን ሐዋርያት፣ አርድእትና ቅዱሳት አንስት ከእመቤታችን ጋር በአንድነትና በኅብረት ለጸሎት ለምስጋና ተሰብስበው እያለ ነው ፡፡ “ኀምሳው ቀን በተፈጸመ ጊዜ፣ ሁሉም በአንድነት በአንድ ቦታ ተሰብስበው ነበር” (ሐዋ 2፡1-47) እንዲል፡፡ በነቢያትና በሐዋርያት መሠረትነት የቆመች ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን (ኤፌ. 2፡20) በዓለ ጰራቅሊጦስን በሐዋርያት ዘመን እንደነበረው ከጌታችን ትንሣኤ በኋላ በኀምሳኛው ቀን ታከብራለች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በዓለ ጰራቅሊጦስን “የቤተክርስቲያን የልደት ቀን” ሲል ጠርቶታል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የምትመራው የሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተመልታ ለሰው ልጆች ሁሉ እውነተኛ የክርስቶስን ወንጌል መስበክ የጀመረችበት ቀን ነውና፡፡
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.