cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

✍ጥበብ የእውቀት ሀይል ነው!!!

✔መከራና ችግር አንዳንድ ሰወችን ይሰብራቸዋል አንዳንዶቹን ደግሞ የአለም ሪከርድ እንዲሰብሩ ያደርጋቸዋል። ✔አሸናፊ ለመሆን አንድም ሰው እንኳን በማይተማመንብህ ወቅት በራስህ ማመን አለብህ። 🌟ተስፋ ሲለመልም ተአምራት ያብባሉ🍀🌼🌹 ✔ሙከራ ለተሳካ ውጤት በር ከፋች ነው! ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት @Honesty2022 ላይ ያድርሱን ❤ይቀላቀሉን❤ 👇👇👇 @habeshawit24

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
232
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ታሪክህን የሚቀይረው ከፈጣሪ ቀጥሎ ያንተ ቆራጥነት ነው! ከሰዎች ብዙ አጠብቅ! ሰዎችን አንዳስቀመጥክ አታገኛቸውም ጊዜና ሁኔታ ይቀይራቸዋል። ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ ማለት ስትጀምር በአመለካከት ከፍ ማለት ትጀምራለህ። https://t.me/positivevibee
Mostrar todo...
የአለማችን ከባዱ ስራ ማሰብ ነው፤ አጥብቆ የሚያስብ ሰው ህይወት ቀያሪ ውሳኔዎችን ስለሚወስን ስኬታማ ይሆናል። ለዛም ይመስላል ቶማስ ኤዲሰን እንዲህ ያለው "ከመቶ ሰዎች አምስቱ ያስባሉ፣ አስሩ የሚያስቡ ይመስላቸዋል፤ ሰማንያ አምስቱ ግን ከሚያስቡ ቢሞቱ ይመርጣሉ።"https://t.me/positivevibee
Mostrar todo...
Mostrar todo...
Merkato Online

Shop Easy, Save Time 😁Everything thing you need just a click away Contact 👉 @merkatoonline3

Mostrar todo...
Merkato Online

Shop Easy, Save Time 😁Everything thing you need just a click away Contact 👉 @merkatoonline3

"ያስጎነበሰክ ያላየኸውን እንድታይ ነው" የጎደሉህን ነገሮች ፣ ያስጎነበሱህን ነገሮች አጎንብሰክም ቢሆን ሳቅባቸወ፡፡ ሳቅባቸውና ራዕይህን ከማሳካት መቼም ቢሆን እንደማያሰናክሉህ ንገራቸው፡፡ ያንተ ራዕይ የተቀበረው ባጣኸው ፣ በተቆረጠው ፣ በሞተው ፣ በወደቀው ፣ ያረጀ ታሪክህ ውስጥ ሳይሆን በአሁኑ ማንነትህ ውስጥ ነው፡፡ አንተ የአሁን ነህ፤ አንተ ዛሬ ነህ፤ አንተ ትኩስ ነህ፡፡ የአንተ እውነተኛ ማንነት ፣ ባህርይና ስብዕና የሚለካው ትናንት በነበረህ የተመቻቸ ኑሮና በትናንቱ መልከመልካሙ ተክለ ሰውነትክ ፣ በጠንካራነትህና በባለጠጋነትህ ሳይሆን አሁን ባጎነበስክበት ፣ አሁን በወደቅክበት ፣ አሁን በተሰበርክበት ፣ አሁን በታመምክበት ፣ አሁን ባጣህበት ጊዜ ነው፡፡ አጎንብሰህ በዛው መንምነህ ፣ ወድቀህ ትቀራለህ ወይስ እንደ እባብ አፈር ልሰህ በድል አድራጊነት ትነሳለህ የሚለው ሀሳብ ያንተ ቁርጥ የሕይወት ምዕራፍ የሚለይበት ነው፡፡ ልክ ብቃት ያለው የመርከብ ካፒቴን ውቅያኖሱ ጸጥ ባለበትና ውኀው በተረጋጋበት ጊዜ ሳይሆን ማዕበሉ በተነሳና ውቅያኖሱ በተናወጠ ጊዜ ብቃቱ እንደሚታይ ሁሉ የአንተም ሕይወትህን የምትመራበት ብቃት አሁን ባጎነበስክበት ጊዜ ይፈተናል፡፡ አሁን በተጨነቅህ ጊዜ ይታያል፡፡ @habeshawit24 🙏🙏🙏ሰላም እደሩ🙏🙏🙏
Mostrar todo...
❌❌❌❌ ሰበር መግለጫ ❌❌❌❌ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ➥ ለጠቅላይ ሚነስትር ፅ/ቤት ➥ ለ ትምህርት ሚነስትር ➥ ለ የሀገረ አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ➥ ለ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ካውንስል ➥ ለ ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ➥ ለተለያዩ የሚዲያ አካላት ጉዳዩ :- የ 2012/2013 የ 12ኛ ክፍል ከፍተኛ ተቃውሞን ስለማሳወቅ እና መፍትሔን ስለመጠየቅ ይመለከታል ። እኛ ማለትም የ2012/2013 የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወሳጆች በተደረገው ኢ-ፍትሃዊ እና አድሎአዊ ተግባር ድምፃችንን ከፍ ብሎ እንዲሰማ እንፈልጋለን ። 15 ዓመት ሙሉ ሃሳባችንን በነጻነት ሠላማዊ በሆነ መልኩ መግለፅ እንደምንችል ለቅሬታችንም ተገቢውን እና አስፈላጊውን መልስ ማግኘት እንደምንችል ስነዜጋ እና ስነምግባር ባሉት ትምህርት ሲነገረን ኖረዋል። እኛም ይህን መሠረት አድርገን ግዴታችንን አሞልተን መብታችንን ማስከበር ይገባናል ብለን ተነስተናል ። ከዚህ ጋር በተያያዘም ተማሪዎች በከፍተኛ መልኩ ከ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ያወጣው የዩኒቨርስቲ መቁረጫ እና የግል መማሪያ ውጤት ከታች የተዘረዘሩትን ከፍተኛ ችግሮችን ያየና ያገናዘበ አይደለም ። ❌ ችግሮችና የተማሪ አቤቱታዎች እንደሚመለከተው ቀርበዎል:- 1ኛ በኮሮና ጉዳይ ....❓ 📚 በኮሮና ምክንያት ያለ አስተማሪ ፤ ከጓደኞቻችን የከበደንን ሳንጠያየቅ ለብቻችን ...በግል ጥረት ለማንበብ ጥረናል ። በቲቪ ተማሩ ተብለንም የፕሮግራሞች መዛባት , የወጥነት ችግር , የኮሮና ጭንቀት ወዘተ እንዳንከታተል እንዳረገን እየታወቀ ። ተፅህኖውም ምንም ከቁብ አለመቆጠር። በተለያዩ የማሕበራዊ ድሕረ ገጿች ተፅእኖ ። 2ኛ ማካካሻ ዙርያ ...❓ 📚 አንድም ሞዴል አለመፈተን ፤ 45 ቀን ማካካሻ በሚል ታች ባልወረደ ነገር አለባብሰው ለ7/8 ወር ከት/ት መራቅ ።በየገጠር ትምህረት ቤቶች ሙሉ በሙሉ አለመማር ። የትምህርት በ ቤቴ መርሐ ግብር ሁሉንም ያካተተ አለመሆኑ ። በስርጭቱ ያሉ ችግሮች እንዳሉ ሆነው ።ትምህርት ሚኒስቴር ምን አስቦ ነው ❓ 3ኛ የመራዘም ጉዳይ ... ❓ 📚 ለ4 ግዜያት ፈተና መራዘም ፤ ባልገባ ታብሌት ሊፈትኑን ቀን ቆርጠው ተዘጋጅተን መቀያየር ሀምሌ 15፤ መስከረም 30 ታህሳስ 24፤ ጥር መጨረሻ እየተባለ መራዘም። አራት ግዜ መራዘም ። በተማሪ የቀረቡ ሀሳቦችና ቅሬታዎች 1, ከነበረዉ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ቢያንስ የማለፊያ ነጥቡ በፊት ከነበሩት የማለፊያ ነጥቦች ያነሰ መሆን አለበት! ምክንያቱም 1.1 በሀገራችን በነበረዉ አለመረጋጋት 1.2በኮረና ቫይረስ ምክንያት እቤት በስጋት ለወራት መቀመጣችን 1.3የፈተና ግዜዉ ከ4 ግዜ በላይ መራዘም 1.4የትምህርት ቤት የዝግጅት እጥረት 1.5የተማሪዎች አዕምሮ ቀዉስ ዉስጥ መግባት ወ.ዘ.ተ ሲሆኑ ይህ ሁሉ ምክንያት ባለበት እንዴት ነጥብ ሊጨምር ይችላል? በ2011 ባች በሀገሪቱ አለመረጋጋት ምክንያት ተብሎ የማለፊያ ነጥብ ከግማሽ በላይ ወርዶ ነበረ የዘንድሮ አመት ከበቂ በላይ ምክንያት እያለ መቀነስ ሲገባዉ እንዴት ከግማሽ በላይ ሊጨምር ይችላል? 2, ለየግል ተቋማት ማለፊያ ነጥብ መቀነስ አለበት ምክንያቱም 3 አመት ቀልድ አይደለም ለዲኘሎማ ከታሰበማ ከ10 ጀምሮ ተምረን አሁን ስራ ይዘን ዲግሪ በግል እንማር ነበር እስከ 12 ድረስ መሄድ ባላስፈለገ ነበር ቤተሰብ ከልጆቹ ብዙ ይጠብቃል 3, ስለፈተናዉ አፈታተን ቁጥጥር በጥልቀት ይፈተሽልን 3.1 ፈተናዉ መሰረቁ 3.2 አስተማሪ ሰርቶ ለተማሪ መልስ መስጠቱ 3.3 ተማሪዉ ያለምንም ፍርሃት ኩረጃን እንደ ዲሞክራሲያዊ መብት በመመልከት አስተማሪዉ ተማሪዎች በነፃነት በህብረት እንዲሰሩ መፍቀድ 3.4 ተማሪ ስልክ ይዞ እስከ መግባት ቸልተኝነት የተሞላበት የፈተሻ አካላት ና በገንዘብ ስልክ የሚያስገቡ አካላት መኖር 4. internet አገልግሎት አለመቋረጥ 4.1 የተሰረቀዉ መልስ እንዲሰራጭ አድርጓል ትምህርት ሚንስተሩ ይህንን ሚዛናዊ ማድረግ ይኖርበታል ''የማትኖሩበትን ፍትሀዊነት አታስተምሩን!!'' ❌❌❌ ቅሬታዎች እና አቀራረባቸው❌❌❌ 1 :- ደብዳቤ በማስረጃ ማስገባት በፎቶግራፍ በቪድዮ ወዘተ 2 :- በቀጥታ ከፍተኛ አካላት እንዲያዩት ማድረግ ሚኒስትሩ እናም የበታች አካላት 3 :- በፍጥነት ለውሳኔ እንዲደርሱ ጥያቄ ማቅረብ አቀራረባቸው ➥ መገናኛ ስፍራ ካሳንቺስ ከ INTER CONTINUTAL HOTEL ከፍ ብሎ በሚገኝው የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ። ➥ ሰዓት 2:30 መደረግ ያለባቸው ነገሮች ➥ እኛነታችንን ሚገልፅ መታወቂያ ➥ አፍ መሸፈኛ ማስክ ➥ ሳኒታይዘር ➥ በተቀናጀና በማስረጃ የተደገፈ እና በሰላማዊ መንገድ ይሆናል ። ፍትሕ ለ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ። @Habeshawit24
Mostrar todo...
"ለጠላቶችክ ደስታ ብለክ ሳይሆን መሸነፍክ ለሚያስከፋቸው ሰዎች ብለክ ጠንካራ ሁን" ዛሬ ውስጥህ ሰላም አጥቶ መኖር አስጠልቶካል? ተስፋ እንዳትቆርጥ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ሰዎች ከሰው ክብር ዝቅ አርገውክ በሚጠሉክ ሰዎች ተከበሀል? የሚወዱክ ይመጣሉ፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ስንት የደከምክበት ቢዝነስ ብልሽትሽቱ ወጥቷል? ቀና በልና አማራጮችን ተመልከት፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ በትዕምርትህ የተዘጋጀከውንና የደከምክበትን ያህል ውጤት አላመጣህም? ትምርት በቃኝ እንዳትል፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። የተሸነፍከው የወደክ ፣ የተሰበርክ ቀን አይደለም። የተሸነፍከው በወደክበት ለመቅረት አምነክ የተቀመጥክና ዳግም መሞከር ያቆምክ ዕለት ነው። በል ተነስ የእኔ አንበሳ፤ ይቺ ምድር ለተሸናፊ ቦታ የላትምና "ለችግሮችህ በሙሉ ትልቅ ችግር ሁንባቸው።" 🙌መልካም አዳር፤ ቸር ያሰማን🙌 🙏🙏የነገ ሰው ይበለን🙏🙏 join&share 👇👇👇👇👇 @habeshawit24
Mostrar todo...
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏 • በተለያዩ ጊዜያት ሃላፊነት ይሰጠናል፡፡ በእዉነቱ ከሆነ 'የማደጎ ራእይ' በራሱ መጥፎ ባይሆንም ከሰዉ ተቀብሎ ለማሳደግ ግን በሳል መሆንን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ የሰዉ ልጅ ለሌላ ሰዉ በማደጎነት ይሰጣል...'ይህንን ልጅ አሳድገዉ' ተብሎ • ሃሳብና ራእይም እንዲሁ ነዉ፤ አባቶቻችን በትንሹም ቢሆን ሲመግቡት የነበረዉን 'የሃሳብ ማደጎ' ለኛ አስረክበዋል፡፡ ጥሩም መጥፎም ሊሆን ይችላል...ቁም ነገሩ የተቀበልነዉ ሃሳብ ጥሩ ከነበረ የበለጠ እንዴት እናፋፋዋለን? እናሳድገዋለን? መጥፎ ከነበረ ደግሞ እንዴት ወደትክክለኛዉ መንገድ ሊመጣ ይችላል ብለን ማሰቡ አይከፋም፡፡ • የሃሳብ ማደጎ ከትዉልድ ትዉልድ ይተላለፋል፡፡ ካለበት ቦታ ሆኜ የተሻለ አሻራ አኑሮ ማለፍ የሚፈልግን ሃሳብ የበለጠ መለወጥ፣ ማስፋት ያስፈልጋል፡፡ በኛ ሀገር የህይወት ሩጫ ዉስጥ ግን ለምን እንደሆነ ባላዉቅም ይህንን ነገር አናገኘዉም፡፡ የሆነ ሃሳብ ወይም ራእይ ከሰዎች በሚሰነዘርብን ሰአት ቶሎ ብለን መጥፎዉን ጎን ማጉላት ይቀለናል፡፡'ይሄማ ፈፅሞ የማይሆን ቅዠት ነዉ...የማይመስል ሃሳብ' ምናምን እያልን እናጣጥላለን፡፡ • ሁላችንም በጊዜና በቦታ ዉስንነት የተገደብን ነን፡፡ ዛሬ ወጣት 'የነብር ጣት' የተባልነዉ ነገ ጉልበታችን ዝሎ ለሚቀጥለዉ ትዉልድ ምንም ነገር ሳናስተላልፍ 'የሃሳብ ቃሪያ የተጠቀጠቀበትን ጉርሻ' አጉርሰን ከምንሄድ ዛሬን ማስተዋሉ መፍትሄ ነዉ፡፡ አለበለዚያ 'እንቆቅልሹን ያልፈታ የትናንሽ ራእዬች ባሪያ' የሆነን ትዉልድ ደጓሚ ሆነን እንቀራለን፡፡ Join&share @habeshawit24
Mostrar todo...
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏 • በተለያዩ ጊዜያት ሃላፊነት ይሰጠናል፡፡ በእዉነቱ ከሆነ 'የማደጎ ራእይ' በራሱ መጥፎ ባይሆንም ከሰዉ ተቀብሎ ለማሳደግ ግን በሳል መሆንን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ የሰዉ ልጅ ለሌላ ሰዉ በማደጎነት ይሰጣል...'ይህንን ልጅ አሳድገዉ' ተብሎ • ሃሳብና ራእይም እንዲሁ ነዉ፤ አባቶቻችን በትንሹም ቢሆን ሲመግቡት የነበረዉን 'የሃሳብ ማደጎ' ለኛ አስረክበዋል፡፡ ጥሩም መጥፎም ሊሆን ይችላል...ቁም ነገሩ የተቀበልነዉ ሃሳብ ጥሩ ከነበረ የበለጠ እንዴት እናፋፋዋለን? እናሳድገዋለን? መጥፎ ከነበረ ደግሞ እንዴት ወደትክክለኛዉ መንገድ ሊመጣ ይችላል ብለን ማሰቡ አይከፋም፡፡ • የሃሳብ ማደጎ ከትዉልድ ትዉልድ ይተላለፋል፡፡ ካለበት ቦታ ሆኜ የተሻለ አሻራ አኑሮ ማለፍ የሚፈልግን ሃሳብ የበለጠ መለወጥ፣ ማስፋት ያስፈልጋል፡፡ በኛ ሀገር የህይወት ሩጫ ዉስጥ ግን ለምን እንደሆነ ባላዉቅም ይህንን ነገር አናገኘዉም፡፡ የሆነ ሃሳብ ወይም ራእይ ከሰዎች በሚሰነዘርብን ሰአት ቶሎ ብለን መጥፎዉን ጎን ማጉላት ይቀለናል፡፡'ይሄማ ፈፅሞ የማይሆን ቅዠት ነዉ...የማይመስል ሃሳብ' ምናምን እያልን እናጣጥላለን፡፡ • ሁላችንም በጊዜና በቦታ ዉስንነት የተገደብን ነን፡፡ ዛሬ ወጣት 'የነብር ጣት' የተባልነዉ ነገ ጉልበታችን ዝሎ ለሚቀጥለዉ ትዉልድ ምንም ነገር ሳናስተላልፍ 'የሃሳብ ቃሪያ የተጠቀጠቀበትን ጉርሻ' አጉርሰን ከምንሄድ ዛሬን ማስተዋሉ መፍትሄ ነዉ፡፡ አለበለዚያ 'እንቆቅልሹን ያልፈታ የትናንሽ ራእዬች ባሪያ' የሆነን ትዉልድ ደጓሚ ሆነን እንቀራለን፡፡ 🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌 @habeshawit24
Mostrar todo...
መታመንስ እንደ ሀቺኮ! ፅናትስ እንደ ሀቺኮ!! ድንገት እግር ጥሏችሁ በጃፓኗ ቶኪዮ ሽቡያ ባቡር ጣቢያ ብትከሰቱ አንድ የውሻ ሀውልት ታያላችሁ! ታሪኩ እንዲህ ነው፣በጃፓን ቶኪዮ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ኢዛቡሮ ኡኖ የአኪታ ዝርያ የሆነ ውሻ እንዲኖራቸው የረጅም ጊዜ ፍላጎት ነበራቸው። ታዲያ ይህን ያወቀ አንድ ተማሪያቸው አንድ ሀቺኮ የሚባል ውሻ አምጥቶ ሰጣቸው። አዲሱ ባለቤቱና ሀቺኮ ብዙም ሳይቆዩ የቅርብ ጓደኛሞች ሆኑ ፡፡ ሀቺኮ እያደገ ሲሄድም ማለዳ ላይ ፕሮፌሰሩ ወደ ስራ ሲሄዱ የሽቡያ ባቡር ጣቢያ ድረስ አብሮ እየሄደ ሸኝቷቸው ይመለሳል፣ማታ 11 ሰዓት ላይም ባቡር ጣቢያ ሄዶ ይቀበላቸውና ቤት ድረስ አብሯቸው ይመጣል። ታዲያ ከእለታት በአንዷ ክፉ ቀን (እ.ኤ.አ. ግንቦት 21 ቀን 1925) ሀቺኮ ፕሮፌሰሩን ሸኝቶ ውሎውን ቤቱ አድርጎ ማታ እንደልማዱ ሊቀበላቸው ባቡር ጣቢያ ተገኝቶ ቢጠብቃቸው ቢጠብቃቸው የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩበት።ለካ ሰውየው በስራ ገበታቸው ላይ ሳሉ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ገጥሟቸው ሞተው ኖሯል። ሀቺኮ ግን ይመጣሉ እያለ ተስፋ ባለመቁረጥ በየቀኑ ባቡር ጣቢያው ድረስ እየሄደ ይጠብቃቸዋል። ይህን ያደረገው 1 ቀን ብቻ አይደለም ጥቂት ወራትም አይደለም ድፍን 10 አመት አንዲትም ቀን ሳያዛንፍ እንጂ! በመጨረሻም እሳቸውን በሚጠብቅባት ባቡር ጣቢያ ሞተ፡፡ ሀቺኮ ለ10 አመታት ፍቅርና ታማኝነት ተምሳሌት በመሆኑ ጃፓናውያን ይኮሩበታል ይወዱታልም።ያ እግር ጥሏችሁ ካያችሁት ያልኳችሁ ሀውልትም ለሀቺኮ መታሰቢያነት ያሰሩለት ነው፡፡ በነገራችን ላይ የዚህ ውሻ ታሪክ ፊልም ሆኖ ተሰርቷል፡፡ አስደናቂ ነው!! ታሪኩን ከወደዳችሁት Join &share 👇👇👇👇 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ❤️@habeshawit24❤️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ 🙏🙏ሰላም እደሩ🙏🙏
Mostrar todo...