es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ETHIO CRYPTO ™

ETHIO CRYPTO ™

Ir al canal en Telegram

Join us✨ for insightful analysis, expert tips, and exclusive strategies to maximize your returns in the dynamic world of digital assets. we launch projects on how to make money online🌟

Mostrar más
3 571
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
-8230 días
Archivo de publicaciones
የ56 አመቱ የቻይና ሚሊየነር ለ27ኛ ጊዜ ፈተና ሊፈተን ነው። ሊያንግ ላለፉት አራት አስርት አመታት አስከፊውን የ"ጋኦካኦ" ፈተና በደርዘን ጊዜ ወስዷል። ገና በ16 ዓመቱ በ1983 ነበር ለመጀመሪያ
የ56 አመቱ የቻይና ሚሊየነር ለ27ኛ ጊዜ ፈተና ሊፈተን ነው። ሊያንግ ላለፉት አራት አስርት አመታት አስከፊውን የ"ጋኦካኦ" ፈተና በደርዘን ጊዜ ወስዷል። ገና በ16 ዓመቱ በ1983 ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ፈተናውን የወሰደው። T.me/student_Text

የሞባይል ስልክን ተጠቅመው ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተና እንዲዘጋጁ የሚያደርግ መተግበሪያ ተሰራ exam time የተባለው ይህ የስልክ መተግበሪያ በዋነኝነት  ለመደበኛ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲሁም በሬሜዲያል ፕሮግራም በድጋሚ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተናን የሚወስዱ ተማሪዎች ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት ለማገዝ ታስቦ የተሰራ  ነው። think hub innovations ያዘጋጀው ይህ መተግበሪያ መጀመሪያ የተሰራው ከ2 አመት በፊት ቢሆንም አሁን ላይ ለውጦች እና ማሻሻያዎች ተደርገውበት በድጋሚ ስራ ላይ ውሏል። አዲሱ exam time መተግበሪያ የድሮውንም አዲሱንም ስርዓተ ትምህርት ያካተተ ነው። በውስጡ የሚገኙት አጫጭር ማስታወሻዎች እና የቪዲዮ ማብራሪያዎችን ይህንን በተከተለ መልኩ የ12ኛ ክፍል ይዘቶችን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የ 9፣10 እና 11ኛ ክፍል ይዘቶችን ደግሞ በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት መሰረት አዘጋጅቶ አቅርቧል። ይህ መተግበሪያ ተማሪዎች ከጥናት ሳይዘናጉ ያላቸውን ቀሪ ጊዜ በአግባቡ እንዲጠቀሙ የሚረዳ ሲሆን ይህንን  የሞባይል አፕሊኬሽን ለመጠቀም ለጊዜው  ምንም አይነት ክፍያ አይጠይቅም። ተማሪዎች ከplaystore ላይ በማውረድ መጠቀም ይችላሉ

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ ማድረጋቸውን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ከበደ ዶ/ር በቅርቡ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ መጠናቀቁም ተገልጿል። የፈተናው ሕትመት በቀጣይ ቀናት እንደሚጀመር ለኢሳት የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥም አረጋግጠዋል፡፡ ለ3ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡ @student_TexT

#National_Exam " የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት እየተገባደደ ነው ፤ ... በቀጣይ የፈተናው ሕትመት ይጀመራል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የፀጥታ ችግር በሌላባቸው አካባቢዎች ብቻ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በዛሬው ዕለት አሳውቋል። የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው ሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተማሪዎች ምዝገባ ተካሂዶ መጠናቀቁን የገለጸው መ/ቤቱ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተናው ምዝገባ ማከናወናቸውን ጠቁሟል። የፀጥታ ችግር ባለባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በዚህ ሣምንት ይከናወናል ብሏል። የፈተና ዝግጅት ሥራው የሀገሪቱን ሥርዓተ ትምህርት የተከተለ እና ተማሪዎቹን በአግባቡ በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን አገልግሎቱ ገልጿል። የፈተናው ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን አመልክቶ በቀጣይ የፈተናው ሕትመት እንደሚጀመር አሳውቋል። የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የመስጫው የጊዜ ሰሌዳ ወደፊት ይፋ እንደሚሆንም የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ኢዜአ ዘግቧል። https://t.me/student_text

#ደብረማርቆሰ_ዩኒቨርሲቲ ደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም ነባር እና አዲስ አንደኛ ዓመት መደበኛ ቅድመ-ምረቃ እና የሬሜዲያል ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል፡፡ በዚህም መሠረት የምዝገባ ጊዜዉ እንደሚከተለዉ ተገልጿል፦ - የ1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ነባር ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያላችሁ ነባር ተማሪዎች ከመጋቢት 16-17/2016 ዓ.ም - በ2016 ዓ.ም የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ፍሬሽማን እና የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ከመጋቢት 16-17/2016 ዓ.ም ማሳሰቢያ: * ለነባር 1ኛ ዓመት ተማሪዎች እና የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያላችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደዉ #በየነበራችሁበት ካምፓስ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡ * በሀገር አቀፍ የማለፊያ ዉጤት ያመጣቹህ አዲስ የአንደኛ ዓመት(ፍሬሽማን) ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደዉ #በዋናዉ ግቢ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡ * የ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ የሪሜድያል ተማሪዎች በስማችሁ ቅደም ተከተል መሰረት ስማችሁ ከA-G የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እና ስማችሁ ከA-H የሚጀምር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ #የምትመዘገቡ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በዋናዉ ካምፓስ የምትመዘገቡ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡ * አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው እንዲሁም ስምንት 3x4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡ - በተለያየ ምክንያት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ 1ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ @Student_tExt

መቱ ዩኒቨርሲቲ ሰሞኑን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የመቱ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 96.38 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳ
መቱ ዩኒቨርሲቲ ሰሞኑን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የመቱ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 96.38 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ፈተናውን ከወሰዱ 138 የመቱ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 133 ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸው ተገልጿል። በስድስት የጤናና ህክምና ትምህርት ክፍሎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተናውን ወስደው፤ ከሚድዋይፈሪ ትምህርት ክፍል ሁለት እንዲሁም ከሔልዝ ኢንፎርማቲክስ ትምህርት ክፍል ሦስት ተማሪዎች ፈተናውን ሳያልፉ ቀርተዋል። https://t.me/Student_Text

የመውጫ ፈተና ዛሬ በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች  መሰጠት ጀምሯል። ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከዛሬ ካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት እንደተጀመረ ገልጿል። በዛሬው እለት በጤና ፕሮግራሞች በተጀመረው ፈተና ጠዋት 15,440 ተማሪዎች በ23 የጤና ፕሮግራሞች የተፈተኑ ሲሆን ከሰዓት 14,807 ተማሪዎች በ13 ፕሮግራሞች ተፈትነዋል። ፈተናው በሁሉም የፈተና ማዕከላት ከተማ እየተሰጠ ሲሆን የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የተመደቡ ታዛቢዎች በየተመደቡበት ተቋማት በመገኘት ስራ  መጀመራቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። የሁለተኛ ዙር ፈተናው 👉 በ47 የመንግስት ተቋማት 👉 በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145  ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች ይፈተናሉ። ፈተናው የካቲት 11/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል። @Student_Text

መጠይቅ ይሙሉ በየትኛውም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሒሳብ የእንግሊዘኛ እና የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዓይነቶችን የምታስተምሩ መምህራን መጠይቅ እንድትሞሉ ተጋብዛችኋል። መጠይቁ በትምህርት ሚኒ
መጠይቅ ይሙሉ በየትኛውም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሒሳብ የእንግሊዘኛ እና የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዓይነቶችን የምታስተምሩ መምህራን መጠይቅ እንድትሞሉ ተጋብዛችኋል። መጠይቁ በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ በ2016 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን አቅም ለማጎልበት የሚሰጣቸው ስልጠናዎች የመምህራንን የስልጠና ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ለማድረግ የተዘጋጀ ነው። ለመሙላት 👇👇👇👇👇👇👇 https://forms.office.com/r/B8GAUYUg4H @Student_Text

የመውጫ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። ከየካቲት 6 እስከ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚሰጠው ፈተና  ከ112 ሺህ በላይ ነባርና አዳዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ማድረጋቸውን በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰዒድ መሃመድ  ተናግረዋል። የፈተና ጥያቄዎች የኮምፒውተር ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት መስኮች ልየታን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ነው ኃላፊው የገለፁት። ባለፈው ዓመት በፈተና አሰጣጥ ሂደትያጋጠሙ ችግሮች ዘንድሮ እንዳይደገሙ በቂ ዝግጅት መደረጉን አቶ ሰኢድ ተናግረዋል፡፡ @Student_Text

የሲቪክስ ትምህርት ከ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና መውጣቱ የሚፈጥረው ተፅዕኖ የለውም ''ትምህርት ሚኒስቴር'' የሥነ ዜጋ እና ሥነ ምግባር ትምህርት ከማጠቃለያ ፈተና ላይ መውጣቱ በተማሪዎች ውጤትና ባ
የሲቪክስ ትምህርት ከ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና መውጣቱ የሚፈጥረው ተፅዕኖ የለውም ''ትምህርት ሚኒስቴር'' የሥነ ዜጋ እና ሥነ ምግባር ትምህርት ከማጠቃለያ ፈተና ላይ መውጣቱ በተማሪዎች ውጤትና ባሕሪ ላይ ተፅዕኖ እንደማይፈጥር ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የማኅበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዑመር ኢማም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት፤ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውስጥ የሥነ ዜጋ እና የሥነ ምግባር ትምህርት እንዳይካተት ተደርጓል። እንደ አቶ ዑመር ገለጻ፤ ሌሎች የትምህርት ዓይነቶች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚሰጡ ሲሆን ሥነ ዜጋ እና ሥነ ምግባር የሚባል ትምህርት ግን በአሁኑ ጊዜ ከ10ኛ ክፍል በላይ አይሰጥም። ተማሪዎች የሚመዘኑት በአራት ዓመት ቆይታቸው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ነው። በዚህ ምክንያት የሥነዜጋና ሥነምግባር የትምህርት ዓይነት ከማጠቃለያ ፈተናው ሊወጣ ችሏል። @Student_Text

National Exam በ2016 የ12ኛ ክፍል ፈተና የሥነዜጋ እና ሥነምግባር ትምህርት የማይሰጥ ሲሆን ባለፉት ዓመታት ሳይሰጥ የቆየው ኢኮኖሚክስ ዘንድሮ ይመለሳል። የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አ
National Exam በ2016 የ12ኛ ክፍል ፈተና የሥነዜጋ እና ሥነምግባር ትምህርት የማይሰጥ ሲሆን ባለፉት ዓመታት ሳይሰጥ የቆየው ኢኮኖሚክስ ዘንድሮ ይመለሳል። የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ ከቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ? " በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ምክንያት 12ተኛ ክፍል ፈተና ላይ የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ተማሪዎቹ እንዲይዙት የሚፈለገውን እውቀት፣ ክህሎት ባህሪያት መቅሰማቸው የሚፈተኑበት ይሆናል። የሥነ ዜጋ እና ሥነ ምግባር ትምህርት በ12ተኛ ክፍል ፈተና ላይ እንዳይሰጥ የተደረገው በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ምክንያት ትምህርቱ ከ10ኛ ክፍል በኋላ ስለማይሰጥ ነው። ኢኮኖሚክስ ከዚህ ቀደምም ይሰጥ ነበር። መሃል ላይ የሆኑ የጥናት ሃሳቦች ተነስተው ከፈተና እንደወጣ እናውቃለን፤ አሁን ግን ወደ ሥርዓተ ትምህርቱ ተመልሷል፤ መጽሐፍ ታትሞለታል። እንዲማሩ እየተደረገ ካለው ጥረት አንጻር ወደ ፈተና ቢገባ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል። የዘንድሮ ፈተና መቼ ይሰጣል ? ለሚለው ፤ ከክልሎች ጋር ምክክር እያደረግን ነው። በቅርቡ እናሳውቃለን። " @Student_Text

MOE ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡ የተፈጥሮ ሣይንስ ፦ ➡ እንግሊዝኛ፣ ➡ ሒሳብ፣ ➡ ፊዚክስ፣ ➡ ኬሚስትሪ፣ ➡ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት የማኅበራዊ ሣይንስ፦ ➡ እንግሊዝኛ፣ ➡ ሒሳብ፣ ➡ ታሪክ፣ ➡ ጂኦግራፊ፣ ➡ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል። በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል። ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል። የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። የ2016 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና መቼ ሊሰጥ ታቅዷል ? የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደም ሰጥተው በነበረ ማብራሪያ ፤ የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው። ሚኒስትሩ ፤ የዚህ ዓመት ፈተና ድብልቅ / ሃይብሪድ መሆኑንም በወቅቱ ገልጸው ነበር። ድብልቅ ፈተና ማለት ግማሹ ኦንላይን የኢንተርኔት ችግር የሌለባቸው አካባቢዎች የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ በነበረበት አካሄድ በወረቀት ለመስጠት ነው እቅዱ። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ሰጥተውት በነበረው ማብራሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንኳን የመግዛት አቅም ባይኖረውም ለፈተናው የሚሆኑ ታብሌቶችን ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር ለፈተናው ጊዜ በመውሰድ ፈተናውን በድብልቅ እንደሚሰጥ አሳውቀዋል። የ2016 ዓ/ም ፈተና ድብልቅ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ የሶፍትዌር ስራው መጠናቀቁንም ይፋ አድርገው ነበር። የዘንድሮው ምዝገባ በኦንላይን እንደሚሆን ተፈታኞች በአካል ተገኝተው ፎቶ እንዲነሱ እንደሚደረግ እና በዚህ ረገድ ቁጥጥሩ ጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል ። @StudeNT_TeXT

#ደብረማርቆስ_ዩኒቨርሲቲ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም ነባር እና አዲስ የቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ የ3ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርትና ከዚያ
#ደብረማርቆስ_ዩኒቨርሲቲ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም ነባር እና አዲስ የቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ የ3ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ የቅድመምረቃ ተማሪዎች ከጥር 16-17/ 2016 ዓ.ም፤ የ2ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ነባር መደበኛ የቅድሙምረቃ ተማሪዎች ከጥር 23-24/2016ዓ.ም፤ የ1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ነባር መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያላችሁ ነባር ተማሪዎች ከየካቲት 7-8/2016 ዓ.ም፤ በ2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ አዲስ ገቢ የ1ኛ ዓመት ተማሪዎችና በ2016 በሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች፣ ከየካቲት 7-8/2016 ዓ.ም፣ ለሁሉም ነባር የተከታታይ ፕሮግራም የቅድመምረቃ ተማሪዎች ከጥር 04-05/2016 ዓ.ም ለሁሉም የመደበኛ እና ተከታታይ ድህረ-ምረቃ ነባር ተማሪዎች ከጥር 04-05/2016 ዓ.ም ማሳሰቢያ: ለነባር ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደዉ በየነበራችሁበት ካምፓስ ይሆናል፡፡ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዉጤት የተመደባችሁ አዲስ የአንደኛ ዓመት ምዝገባ የሚካሄደዉ በዋናዉ ግቢ ብቻ ይሆናል፡፡ የ2016ዓ.ም አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ተማሪዎች በስማችሁ ቅደም ተከተል መሰረት ስማችሁ ከA-G የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችና እና ስማችሁ ከA-H የሚጀምር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ የምትመዘገቡ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በዋናዉ ካምፓስ የምትመዘገቡ ይሆናል https://t.me/StudenT_TeXT

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ከጥር 13 እስከ 15/2016 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አሳውቋል፡፡ ወደ ዩኒቨርሲቲው
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ከጥር 13 እስከ 15/2016 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አሳውቋል፡፡ ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ 👉 ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣ 👉 ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ 👉 ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ። @StUdENT_TExT

የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ  እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉን የደስታ እና የጤና ያድርግላችሁ :: መልካም የ ገና በዓል ተመኘን

photo content
+1

ከቀጣይ አመት ጀምሮ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል የፈተና ምዝገባ የሚደረገው በዲጅታል መሆኑ ተገለፀ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከቀጣይ አመት ጀምሮ የፈተና ምዝገባ የማደርገው በዲጅታል ነው ብ
ከቀጣይ  አመት ጀምሮ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል  የፈተና ምዝገባ የሚደረገው በዲጅታል መሆኑ ተገለፀ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት  ከቀጣይ አመት ጀምሮ የፈተና ምዝገባ የማደርገው  በዲጅታል ነው ብሏል።አገልግሎቱ በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር  በጋራ በሰጠው መግለጫ ነው ይሄን ያስታወቀው።በየአመቱ በሃገር አቀፍ እና  የክልል አቀፍ የፈተና ምዝገባዎች ሲደረጉ አገልግሎቱ በርካታ ሚሊየን ብር እንደሚያወጣ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ተናግረዋል። አሁን የፈተና አገልግሎቱ የፈተና ምዝግባዎችን በዲጅታል እንዲደረጉ የሚያደርግ በመሆኑ ይሄን ወጪ እንደሚያስቀር አንስተዋል።ይህንንም ማሳካት እንዲቻል በተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ  ገልጸዋል። ለዚህም ከ32 ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞች ተመልምለው ወደ  ተለያዩ  አከባቢዎች ተደልድለዋል ብለዋል።ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመን በ2015 ዓ.ም የሙከራ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ በሙሉ ኃይል ወደ አገልግሎት መግባቱን ገልጿል። @StUdENT_TExT

#ትግራይ በትግራይ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መሰጠት ተጀመረ። የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር በሚያስተዳድራቸው 76 ወረዳዎች በሚገኙ 1114 ትምህርት ቤቶች 60 ሺህ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክላሊው ፈተና ለመውሰድ መቅረባቸው የክልሉ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ አስታውቋል። ኤጀንሲው ፤ ከጦርነቱ በኋላ በ2012 ዓ.ም መፈተን ሲገባቸው ሰኔ 2015 ዓ.ም ላይ ከተፈተኑ ተማሪዎች 98 በመቶ ማለፋቸው አስታውሷል። የአሁኑም ፈተና ያለውን ችግር በመቋቋም በተደረገው ጥረትና ዝግጅት የተሻለ ውጤት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክቷል። የዚህ ዓመት የ8ኛ ክፍል ፈተና በቴክኖሎጂ ተደግፎና ታግዞ በቶሎ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። @StUdENT_TExT

#wollo university ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ማሥተማር ተግባር ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን አስታወቀ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ጥር ወር ለሚጀምረው የመማር ማሥተማር ተግባር ቅድመ ዝግጅቱን እያጠና
#wollo university ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ማሥተማር ተግባር ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን አስታወቀ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ጥር ወር ለሚጀምረው የመማር ማሥተማር ተግባር ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቋል። የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ታረቀኝ ትንታጉ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ ዩኒቨርሲቲው ጥር አንድና ሁለት ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅቷል። በተማሪዎች አገልግሎት በኩል የክሊኒክ፣ የመኝታ ክፍል፣ የመዝናኛ እና የቤተ መጽሐፍ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ግብዓት ማግኘት ፈታኝ ቢሆንም የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ለተማሪዎች የምግብ አገልግሎት በቂ ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት። ዩኒቨርሲቲው ባለፈው አመት በካምፓሱ ውጤታቸውን ያሻሻሉ 3 ሺህ 400 ተማሪዎች በዘንድሮው አመት የመግቢያ ውጤት ያመጡ 600 ተማሪዎች በጥቅሉ 4 ሺህ አዲስ ተማሪዎችን ይቀበላል ተብሏል፡፡ በዘንድሮው አመትም 3 ሺህ 600 የሪሜዲያል ተማሪዎች እንደሚማሩ ታረቀኝ ትንታጉ (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡ @student_Text