cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
200
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🇪🇹☕️ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ🇪🇹☕️ አቡበከር ናስር በሙያ አጋሮቹ የዓመቱ ኮከብ ተጨዋች ተብሎ ተመርጧል። ----------------- የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን በተሰጠው ዕድል መሰረት የምንግዜውም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ጎል አግቢነት ሪከርድን በእጁ ያስገባውን የኢትዮጵያ ቡናውን አቡበከር ናስር የ2013 የዓመቱ የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጨዋች አድርጎ መምረጡን አሳውቋል። (ሪከርዱ እስኪሰበር ድረስ "የምንግዜውም" ተብሎ እንደሚጠቀስ ልብ ይባልልኝ።) ሙሉ ደብዳቤውን እንደሚከተለው እናነበዋለን።
Mostrar todo...
👍 3
👎 1
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት ውጤቶች ፣ የደረጃ ሠንጠረዥ እና የጎል አስቆጣሪዎች ደረጃ አጠቃላይ ።
Mostrar todo...
የሁለተኛ ደረጃን ለመያዝ ከፍተኛ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ የሚጠበቀው የ25ኛ ሳምንት የመዝጊያ ጨዋታ እንደሚከተለው ቃኝተነዋል። ሁለቱ የሸገር ክለቦችን በተከታታይ ያስተናገዱት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ያገኙትን ድል በሌላኛው የመዲናችን ክለብ ለመድገም እና የሁለተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁበትን ዕድል በራሳቸው ለመወሰን ጠንክረው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይገመታል። ሦስት ነጥብ ካገኙ አምስት የጨዋታ ሳምንታት ያለፋቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች ደግሞ ከድል ጋር ለመታረቅ እና በእጃቸው ያለው የኮንፌዴሬሽን ካፕ ተሳትፎ ደረጃን አጥብቆ ለመቀጠል ለጨዋታው እንደሚቀርቡ ይታሰባል። ከሜዳ ውጪ በነበሩ ችግሮች ያልተረጋጋ ዓመት እያሳለፈ የነበረው ሀዲያ ሆሳዕና ዋና አሠልጣኙን እና ወሳኝ ተጫዋቾቹን (15) ካጣ በኋላ እያሳየ ያለው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ እጅግ ግሩም ነው። በተለይ ከ20 ዓመት በታች የሚገኙ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ከቀላቀለ በኋላ ከፍተኛ ፍላጎት እና መታተር ይታይበታል። በዋናነት ደግሞ ለመከላከል ቅድሚያ እየሰጠ ወደ ሜዳ የሚገባው ስብስቡ ለተጋጣሚ ቡድን ተጫዋቾችን እጅግ ምቾት የማይሰጥ ሆኗል። ከምንም በላይ በቁጥር በዝቶ በራሱ ሜዳ የሚከላከል፣ ወደ ጎንም ሆነ ወደ ፊት እጅግ ግጥግጥ ያለ እና አካላዊ ጉሽሚያዎችን የሚያዘወትር ቡድን እየሆነ መጥቷል። ከዚህም መነሻነት ነገም ቡድኑ በዚሁ የጨዋታ አስተሳሰብ ወደ ሜዳ ሊገባ ይችላል። ለኳስ ቁጥጥር እምብዛም ፍላጎት የሌለው ሀዲያ ነገም ከኳስ ጀርባ በመሆን የቡናን የማጥቃት እንቅስቃሴ ለማምከን እንደሚታትር እሙን ነው። ይህ ቢሆንም ግን ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ቡድኑ ከመከላከል ወደ ማጥቃት የሚያደርገው ሽግግር ስል ነበር። ይህንንም መነሻ በማድረግ ቡድኑ ነገም በዚህ ፈጣን እና ስል ሽግግር ተጋጣሚው (ቡና) ላይ አደጋ ሊፈጥር ይችላል። ከዚህ ውጩ ተጫዋቾቹ ላይ የሚታየው የተጋይነት እና ያልሸነፍ ባይነት ስሜት በጎ ነገሮችን ይዞለት ሊመጣ ይችላል። ከአራት የአቻ ውጤቶች በኋላ ነገ ወደ ሜዳ የሚገቡት የአሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ ተጫዋቾች በደረጃ ሰንጠረዡ ከስራቸው የሚገኙ ክለቦች ነጥብ ጣሉ እንጂ ለረጅም ጊዜ የተቀመጡበትን የ2ኛ ደረጃ ያጡ ነበር። ከሁለቱ ጨዋታዎች በፊትም የሊጉ ሦስተኛው ትንሽ ግብ ያስተናገደ ክለብ የነበረው ቡድኑ በሁለቱ ጨዋታዎች ብቻ አምስት ጎሎችን አስተናግዷል። ይህ እየላላ የመጣው የኋላ መስመሩም ስህተቶችን እንደ ቡድንም ሆነ በተናጥል እያመስመለከተ ይገኛል። ነገም እነዚህ ክፍተቶች ካልታረሙ ቡድኑ በቀጥተኛ ተፎካካሪው (2ኛ ደረጃን ለመያዝ) ሊቀጣ ይችላል። ከምንም በላይ ቡድኑ ከማጥቃት ወደ መከላከል ሲሸጋገር በተደራጀ መንገድ መሆን ይጠበቅበታል። ከዚህ ውጪ ከኋላ በሚኖር የኳስ መስረታ ወቅት ተጫዋቾች ከስህተት መራቅ ይጠበቅባቸዋል። የዘንድሮው የውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ (41) የሆነው ኢትዮጵያ ቡና ነገም ተጋጣሚውን ተጭኖ በመጫወቱ ረገድ ብልጫ ሊኖረው ይችላል። ለመከላከል ቅድሚያ ሰጥቶ ወደ ሜዳ እንደሚገባ የሚገመተውን ሀዲያ ሆሳዕናንም በኳስ ቁጥጥር እና ሙከራዎች ሊበልጠው እንደሚችል ይታሰባል። በተለይ ደግሞ በተጋጣሚ የመከላከል ወረዳ ላይ በቁጥር በዝቶ በመገኘት ከግብ ጋር ለመገናኘት እንደሚጥር ይገመታል። ከዚህ ውጪ ጠጣሩን የሀዲያ የኋላ መስመር ለመዘርዘር የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎች ሊበረክቱ ይችላሉ። ከሁሉም በላይ ደግሞ በዘንድሮ የውድድር ዘመን 27 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈው አቡበከር ናስር የቡድኑ የጎል ማስቆጠሪያ ምንጭ ሊሆን ይችላል። የእርስ በእርስ ግንኙነት – ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዲያ ሆሳዕና ከዚህ ቀደም ሦስት ጊዜ በሊጉ ተገናኝተው ሁለቱን ኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ 2-1 አሸንፏል። በአንዱ ግንኙነታቸው (ዘንድሮ) ደግሞ ያለ ጎል አቻ ተለያይተዋል። https://t.me/joinchat/RFsPtGx0RZdmNmE0
Mostrar todo...

ድል ለቡንዬ 👆👆 https://t.me/joinchat/RFsPtGx0RZdmNmE0
Mostrar todo...
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት ውጤቶች ፣ የደረጃ ሠንጠረዥ እና የጎል አስቆጣሪዎች ደረጃ አጠቃላይ ።
Mostrar todo...
🇪🇹ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ⏰ #አለቀ ኢትዮጲያ ቡና 3 –3 ሲዳማ ቡና ⚽️⚽️⚽️አቡኪ 🏟 ሀዋሳ
Mostrar todo...