cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

📜📜የግጥም ምሽት📒📒

እውነት የሚያዳምጥ ሠው እውነት ከሚናገር ሠው አይተናነስም፡፡

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Publicaciones publicitarias
138
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

..ከጠዋቱ 12 ሰአት ሁኗል...በጊዜ ነዉ የነቃሁት...ፍቅር እንደያዘኝ አመንኩ...አዎ ፍቅር ይዞኛል..በአንቺ ፍቅር ምክንያት ፈገግ ብዬ እየተኛሁ ፈገግ እንዳልኩ እነሳለሁ...ከብርድ ልብሴ ዉስጥ ሳልወጣ አንቺን ብቻ አስባለሁ..ፈገግታሽን አየር ላይ እስለዋለሁ..ድምፅሽ በጆሮዬ ይስረቀረቃል..ስልኬን አነሳና ፎቶሽ ላይ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች አፈጥበታለሁ...የምታሳሳ ዉብ ሴት መልሳ ታፈጥብኛለች .. ልቤ ፍስስ ስትል ይሰማኛል..እሳሳልሻለሁ..ፎቶሽን ሳም አደርገዉና ስልኩን ደሬቴ ላይ አስቀምጠዋለሁ።...ከተሰማኝ የቆየዉን ስሜት በአካሌ ላይ ዘራሽዉ..ሲያንኳኩት አልከፈት ያለዉን ልቤን በምትሀትሽ ወገግ አደረግሽዉ...በንፁህነትሽ ሞላሽኝ...በፍቅርሽ አሞቅሽኝ..ልቤ ካንቺ ልብ ጋር የተሰፋች ያህል ተሰማኝ።...ምክንያት ሳልደረድር እጄን ሰጠሁሽ..ማፍቀርን ብፈራም ልቤ ጥሎኝ አንቺ ልብ ዉስጥ ከትሟል።...ወደ ምድር ሳንላክ ነፍሶቻችን ሰማይ ቤት የሚተዋወቁ..እዛዉ የተጣመሩ...የተሳሰሩ...እልፍ ህይወትን የኖሩ ያህል ይሰማኛል።..ከጠማማዉ አጥንቴ የሰራሽ ሄዋኔ ነሽ..እየፈራሁ በግዴ አፈቀርኩሽ...ልኬቱን በማላዉቀዉ ፍቅር አፈቀርኩሽ ...እስኪ ልጠይቅሽ መንገደኛ አይደለሽም አይደል..? አትጎጂኝም አይደል የኔ ገነት..? ያመነሽን ልቤን እርቃኑን አታስቀሪዉም አይደል..? ...ብዙ ህልሞቼን ካንቺ ጋር መኖር እፈልጋለሁ..ወደፊቴን ካንቺ ጋር እዉን ማድረግ እፈልጋለሁ...እቅፎችሽ ዉስጥ እንዳለሁ ማለፍን እመኛለሁ።...ከማፍቀር በላይ አፈቅሬሻለሁና።❤️ 🥰ከእለታት አንድ ቀን በጠራዉ ንጋት የተፃፈ።..መሉዉን መፃፍ አልቻልኩም አውራ ጣቴ ደክሞት እያለከለከ ነዉ።..ስለዚህ ቀንጨብ አደረኩላችሁ።.. ✍ ከ(🙈🥰😊) ለ(😍😭🙈) ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Mostrar todo...
አለው በትዝታሽ " እንዴት ነሽ አለሜ ሰማይቤት ተመቸሽ ቦታውስ እንዴት ነው ላንቺ የተሰጠሽ እነማንስ አሉ ካነቺ ጋር ሚኖሩ ልክ እንደኛ ናቸው ወይስ የተፈሩ ኑሮሽስ እንዴት ነው ምን ተወዷል እዛ ሽንኩርት ነው ዘይት የትኛው አስቤዛ ንገሪኝ ግድ የለም ስመጣ እንድዘጋጅ አይሆንህም ብለሽ ሳትመልሺኝ ከደጅ ንገሪኝ አለሜ እባክሽ በኔ ሞት ... አይይ .... ውዴ!! የኔንማ ተይው ምን ብዬ ልንገርሽ ባትሰሚው ይሻላል ግድ የለም ይቆይሽ ባለሽበት ሆነሽ ላንቼ ከተመቸሽ አኔ እንዳለው አለው ጥለሽኝ እንደሄድሽ ከቀዝቃዛው ጎጆ በዝቶብኝ ትዝታ እዛችው ሶፋ ላይ ሆኜ በዝምታ ቀሚስ አስቀምጬ ከትዝታሽ ጋራ ይመሻል ይነጋል ብቻዬን ሳወራ በሀሳብ እየናኘው ደግሞ ቆዝማለው እዛው ቁጭ ብዬ በሀሳብ እነጉዳለው ካለሽበት ድረስ ምናለ መጥቼ እንዳፍላው ፍቅራችን ባቅፍሽ በእጆቼ ፈገግ ብለሽ ባይሽ በዛ ውብ ጥርሶችሽ ሮማን ከመሰሉት ከስርጉዱ ጉንጭሽ ብዬም አስባለው ምናለ ብስምሽ ደግሞ ላላገኝሽ ከትዝታሽ ባህር ይቀሰቅሰኛል ተመለስ እያለ ከሄድኩበት ሀገር ከፊቴ እየመጣ የሚያምረው ፈገግታሽ ከሀሳብ ያነቃኛል ጥዑም ዜማው ሳቅሽ ከወዲያኛው አለም አንቺ ካለሽበት መልሶ ያመጣና ጭልጥ የደርገኛል ደግሞ ይመልስና አሁንማ አርጅቼ ፊቴም ተሸብሽቦ የእቃ ማጠቢያ መስያለው ሽቦ ያ ፅኑ ጉልበቴ አሁን ደክሞ ሀይሉ ዓይኖቼም በናፍቆት ሁሌ ያነባሉ ፀጎሬም ሸብቷል ፥ እርጅናውም ፀንቷል፥ ቢሆንም ግን አለው ኑሮ ቢከብደኝም ብቸኝነት ነግሶ ቢያጎሳቁለኝም በሳቅ በጨዋታ ጎጆዬ ባትሞቅም መቼም እኖራለው እንዳንቺ ባይሆንም። በዳኒዘር
Mostrar todo...
ግጥሙ ከተመቻችሁ ገብታችሁ ድምፅ ስጡ
Mostrar todo...
#ኮድ_02 #Mesfn_tesfamikael ወንድሜ አለችኝ 😭😭 ባል እና ሚስት ሁነን በእቃቃ ጨዋታ ልቤ💖 ውስጥ ገባች አይቻት ለአንድ አፍታ በሌባ እና ፖሊስ በአባሮሽ ጋጋታ🏃‍♀️🏃‍♂️ እሷን አባርሬ መያዝ ሳመነታ በአኩኩሉ ጊዜ እሷ ስትፈልግ ተደብቀን እኛ እንዳትደክም ብዬ ነበር የምታያት ከሁሉም አንደኛ ለአቅመ ትምህርት ደርሰን ፊደልን ስንማር ሀሁ........አቡጊዳ........አይን አይኗን እያየሁ ነበር የምቆጥር ጠዋት በማለዳ፣ከሰአት እስከ ማታ ከቤቷ🏠አልጠፋም እያልኩ ለጨዋታ አባቷ ሲገርፏት እኔ እያለቀስኩ😭😭 ቁርሴን🍲ከእሷ ጋራ እየተጎራረስኩ ለቡሄ አመትበዓል ሆያ ሆዬ እያልኩኝ ከቤቷ🏠 በር ላይ ቁሜ እያዜምኩኝ ሙልሙል🥖ልትሰጠን ከቤቷ ስትወጣ አይኗን ያየሁ ጊዜ የምለውን ሳጣ🤔🤔 በልጅነት ፍቅር❤በንፁህ ልቦና በልጅነት መውደድ💘በፅዱ ህሊና ቀን ቀን እየወለደ አመታት ሲተኩ ፍቅሬ እና እድሜዬ ተያይዘው ሲያድጉ ለአቅመ አዳም ደርሼ ድምፄ ሲጎረንን አካሌ ሲፋፋ ለአቅመ ሔዋን ደርሳ ሽንጥ እና ዳሌዋ እንደጉድ ሲሰፋ ፍቅሯ እየጨመረ የልቤን ይዞታ ቦታውን ሲያስፋፋ የልጅነት ፍቅሬ💞እያደር ሲጨምር የሚወዳት ልቤ❣️እሷኑ ሲዘክር መላ አካላቴ እሷን አምጣ ሲለኝ አንድ ቀን ቆርጬ ልነግራት ወሰንኩኝ ወስኜም አልቀረሁ ቦታው ላይ ቀጠርኳት እየተንተባተብኩ አንዳች ሳላስቀር ዘክዝኬ ነገርኳት በሰማችው ቅፅበት ፊቷ ደማመነ😔😔 ከሚያምሩት አይኖቿ እንባ ተቋጠረ😢😥 በለቅሶ ተውጣ😭ማውራት እያቃታት እንዲህ ተናገረች "አንተ ማለት ለእኔ ወንድሜ ነህ"ብላ ጥላኝ ኮበለለች።።😔😔😔😔 ✍️ Mesfn tesfamikael @fond_hut
Mostrar todo...
ግጥሙን ከወደዳችሁት vote አርጉኝ
Mostrar todo...
ዘር ሲቆጠር ልጅ አባት አያት ቅድመ አያት ቅም አያት ቅማንት ሽማት ምንዥላት እንጅላት ፍናጅ ቅናጅ እሰልጥ አመልጥ ማንትቤ ደርባቴ ተብሎ እንደሚቆጠር ያውቃሉ😳😂😳 @poeitct @poeitct @poeitct
Mostrar todo...
"ከረቡኒ ፊልም የምወዳቸው አባባሎች" ☞ከሀብት ሁሉ ትልቁ ሀብት ልብን መስጠት ነው። ☞ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታ ራስህን ነው። ☞ሀገር እንዳትጠፍ ትልቅ ነገርን አታጥፍ። ☞ሕይወት ሁለት ጎን አላት ማግኘት እና ማጣት ፣ ማጣትም በራሱ ሁለት ጎን አለው የምታገኘውን ነገር ማጣት እና የማታገኘውን ነገር ማጣት። ☞ ሀብታሞች የተፈጥሮን ሕግ ሰብራችኃል። በሚሰራበት ሰዓት ትሰራላችሁ በሚተኛበትም ሰዓት ትሰራላችሁ። ምነው ስትባሉ ድህነትን ለማጥፍት 24 ሰዓት እንሰራለን ትላላችሁ ። ድህነትንስ ታሸንፉታላችሁ ሳታውቁት ግን ለውሳችሁ ሰላምና እና ደስታ ትሸነፉላችሁ። ☞ጭቃው በሸክላ ሰሪው እጅ ላይ ነው... ሰው በአምላኩ እጅ ላይ ነው እንደወደደ አድርጎ የሚሰራው ፈጣሪ ነው። እኛ ማድረግ ያልቻልነውን ፈጣሪ ያደርግልናል ። ☞ሠማይና ምድር የቆመው በቃል ነው። .. ያ ቃል ለኛ ጥበብን ይሰጠናል ልክ ለነዚህ እጆች እንደተሰጡት... አብዬ ከዚህ በኅላ ጥበብ ከሰጠህ ጋር አትታገል እርሱ እራሱ አንድያ ልጁን ሰጥቶናልና። ☞ ትክክለኛ ማሸነፍ በሰው ዘንድ የእራስን አመለካከት ማጋባት ነው። ከተጣላህ ወይም ከሸሸህ አንተ ተሸንፈሀል ከራስህም ከሰውም ጋር ተጣልተኃል ። አንተ እራስህን ለፍቅር ብታዋርድ አንተ ከፍ ከፍ ትላለህ ስለዚህ ትንሽ አቀርቅር። ☞ ጥሩ በልክ አይመዘንም ፣ ልክ ነው በጥሩ የሚመዘነው። ☞ተፈጥሮን በተቃውምን ቁጥር፣ ስልጣኔ ባበዛን ቁጥር፣ ችግራችን ይበዛል ችግራችን ደግሞ የምንወዳቸውን ነገሮች ያሳጣናል። ☞አምላክህን ደስታህን በቅንነት ብትጠይቀው ይሰጥሀል። ብቻ በቤትህ በሀቀኝነት ኑር። ☞ ተስፍን የሰጠ የታመነ ነው። ለህይወትክ መንገድ መፈለግያ የሚሆን የምንግዜውም የኢትዮጽያ ምርጥ ፊልም #JOIN & share 👇👇👇 @poeitct @poeitct @poeitct
Mostrar todo...
ተናፍቀሻል በሏት . . እንኳን ሳቅ ጨዋታሽ ፍልቅልቅ ፈገግታሽ ኩልትፍትፍ የሚለው ጣፋጩ አንደበትሽ እንኳን ከናፍርሽ እንኳን ወገብ ዳሌሽ በተነካ ቁጥር ክራር የሚያከረው አመልካቹ ጡትሽ ይናፍቃል ኩርፊያሽ ከነ ጋንኤልሽ!!! ማይክል ሰለሞን (የቡዜ ልጅ) ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @poeitct @poeitct
Mostrar todo...
እኔ አንቺን ስወድሽ ፣ ሀገሩ ጰረንቆ ተራራና ጋራው ፣ ጫሉቆ መንጢቆ በየ ዩንቨርስቲው ፣ ተማሪ አመጋፂው ባንዳና ሀገር ወዳድ ፣ ዲቢፂው ዲቢፂው በየ ክልሉ ላይ ፣አራጅ አረዝገሮ ዘረኛው በሙሉ ፣ አጨዟ ሠተሮ ብቻ ምን አለፋሽ ... ህይወት እዚም እዛም ፣ እንደቢራቢሮ ስታንከራትተኝ .... ፍቅሬን ምገልፅበት ፣ አንዲት ቃል አቃተኝ ቅኔና ቀን ጠፋኝ ፣ ቅንጣት ጊዜ አጣሁ ቋንቋ አላግባባ ሲል ላንቺና ላገሬ ፣ ልሳን ይዤ መጣሁ፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ እናም.... ትርጉም አትጠብቂ ልሳኔን ፈትቼ ፣ ላላስረዳሽ ነገር ተርጓሚው በዝቶ ነው ፣ ትርጉም ያጣው ሀገር፡፡ @poeitct @poeitct @poeitct
Mostrar todo...
ትን ካሳለፍን በኋላ ተሰናበትናቸው፡፡ ወደ መኪናችን እየተመለስን ‹‹ቁርዓን የት ነው የሚማሩት?›› አልኳት፡፡ ‹‹አሁን እዚህ ትንሽዬ ቁርኣን ቤት አለች፡፡ የወር ክፍያ እኛ እንከፍልላቸዋለን፡፡›› ‹‹ድሮ እኮ ምንም አልነበረም! የእውነት ሁሉም ነገር ደስ ይላል፡፡ ዛሬ ያደረግነው ነገር የልጆቹ ህይወት ውስጥ ምን ያህል ቦታ እንዳለው እንደነሱ ተቸግሬ ስለማውቅ እረዳዋለሁ፡፡ በርቱበት ከጎናችሁ ነኝ!›› ‹‹አንድ የደፋር ጥያቄ ልጠይቅህ?›› ተሸኮረመመች፡፡ ‹‹እስካሁን አንድም የፈሪ ጥያቄ አልጠየቅሽኝም እኮ!›› ‹‹ማህሌትን የምትወዳት ስለውለታዋ ነው ወይስ?›› ገርማኝ ፈገግ አልኩ፡፡ ‹‹ታውቂያለሽ ….. ቆንጆ ናት፡፡ ግን ደግሞ ከሷ የበለጡ ቆነጃጅት ይኖራሉ፡፡ ገንዘብ አላት ….. ከሷ የበለጡ ሀብታም የሀብታም ልጆች ይኖራሉ፡፡ በህይወት ዘመኔ ግን የሷን አይነት ስነ-ምግባር ማንም ላይ አልተመለከትኩም፡፡ ፍቅር ምንድነው? ከነብሷ በላይ ምኗን ላፈቅር እችላለሁ? ምንም! እሷ እኮ የህይወቴ ተዓምር ናት፡፡ እሷ በእኔ ህይወት ውስጥ ስትመጣ የስንት ሰው ህይወት ውስጥ ነብስ እንደዘራች ታውቂያለሽ? እህቴን ከነበረችበት የሰቆቃ ህይወት ወደተከበረች እመቤትነት የቀየራት …… አብዱኬን ከወያላነት ወደ አባወራነት ያሻገረው ….. አቤላን ያለሀሳብ በሄደበት በምቾት የሚያስተምረው ….. እኔን የሚሊየን ብር መኪና የሚያስነዳኝ …… ምን ይመስልሻል? የእሷ በህይወቴ ውስጥ መምጣት ነው፡፡ ሀብታም ሆና እልም ያልኩ መናጢ የሙት ልጅ መሆኔ እኔን ከመወዳጀት አላገዳትም፡፡ ብዙ ሀብታሞች ነበሩ በእምነትም የሚመስሉኝ! ዞር ብሎ ያየኝ ግን አልነበረም፡፡ እሷ ግን እኔን ለመደገፍ የሐይማኖታችን መለያየት አላገዳትም፡፡ ብቻ ምን ልበልሽ? ስለራሴ ያለኝ አመለካከት እንኳን የተሻለ እንዲሆን ያደረገችው እሷ ናት፡፡ ሀፍሷ …. ሚቾ እኮ ተዓምር ናት፡፡ ከፈጣሪ እንኳን ተስፋ ስቆርጥ …… ጨለማው አይነጋም ብዬ ሳስብ የፈነጠቀችልኝ ብርሀኔ ናት፡፡ የማፈቅረው ከሷ የሚወጣውን እያንዳንዱን ትንፋሽ ሳይቀር ነው፡፡ ነገርኩሽ እኮ ገሀነም እንደምትገባ ባውቅ ከሷ ጋር ገሀነም ለመግባት ዝግጁ ነኝ፡፡ ማፍቀር ማለት በአይኗ ማማር ….. በዳሌዋ ስፋት መማረክ ከመሰለሽ ተሳስተሻል፡፡ ማፍቀር ነብስን ነው፡፡ ሁሉ ነገሯን አፍቅሬዋለሁ፡፡ የሷ ስለሆነ ብቻ ሳላውቀው እንኳን ያለአንዳች ማንገራገር ሐይማኖቷን ተቀብያለሁ፡፡›› ‹‹ግን ይኼን ሁሉ ነገር ያደረገችው ሐይማኖትህን ለማስቀየር ቢሆንስ?›› ብሶቴን ቀሰቀሰችው፡፡ ‹‹ፍቅረኝነትን እስክንጀምር አንድም ቀን ስለሀይማኖቴ አንስታብኝ አታውቅም፡፡ ተርቤ ስታበላኝ ሀይማኖቴን አልጠየቀችኝም፡፡ የሚያስጠላኝን የሙስሊሞችና የኦርቶዶክሶች ወሬ ልንገርሽ? በዘይት ተታለሉ ምናምን የምትሉት ጉድ ነው፡፡ ስንራብ አብሉን ስንል የላችሁም፡፡ ሰው አብልቶን በጨለማችን ጊዜ ሲደርስልንና በእምነቱ ተማርከንም ይሁን በስነ-ምግባሩ ተስበን ሐይማኖታችንን ስንቀይር በዘይት ተታለሉ ትላላችሁ፡፡ የት ነበራችሁ ስንራብ? የት ነበራችሁ ጨጓራችን ሲነድ? የት ነበራችሁ ስንታሰር? የት ነበራችሁ ስንታመም? የናንተ ጭቅጭቅ ሱሪ ማስረዘም ይቻላል አይቻልም ነው አይደል? ለናንተ እምነት ማለት ዘፈን ሰማች፣ ቀሚሷ ተጣበቀ …. ከወንድ ጋር እንዲህ ሆነች እያሉ ሐጥያት መፈላፈል ነው አይደል? ከፈረ ….. መናፍቅ ምናምን ለማለት የሚቀድማችሁ የለም፡፡ በጣም ደግ ከተባላችሁ ደግሞ ቤተ-እምነታችሁ በር ላይ ለተኮለኮሉ ነዳያን እየተመፃደቃችሁ አንድ አንድ ብር ታድላላችሁ፡፡ ምን ይጠቅማቸዋል? ደግሞ ግዴታ መንገድ ላይ ወድቀን መለመን አለብን ማለት ነው? በኛ ቦታ ቆማችሁ የኛን ህመም አይታችኋል? አላያችሁም፡፡ በወሬ ሳይሆን በተግባር ያሳየንን እንከተላለን፡፡ ይኼ ደግሞ መብታችን ነው፡፡›› ማልቀስ ጀመረች፡፡ ንዴቴ አልበረደም ቀጠልኩ፡፡ ‹‹ሌላው ደግሞ እስኪ አንድ ቀን እንኳን ከቤተ እምነታችሁ ውጪ ላለው ሰው ስለሀይማኖታችሁ ጥሪ አድርጋችኋል? አታደርጉም! የሐይማኖቱም ተከታይ ሐይማኖቱን ለማወቅ ገንዘብ ከሌለው አይችልም፡፡ አሊያም ደግሞ በየሰዓቱ ቤተ-እምነታችሁ እየተመላለሰ ካሪኩለም የሌለው የለብለብ ትምህርት ማዳመጥ ግድ ይለዋል፡፡ ገና የራሳችሁን ኮተት ሳትሞሉ ጴንጤው ወይም ሌላው መንገድ ላይ ወጥቶ የገነት መንገድ ተገልጦልኛል ኑ አብረን እንግባ እያለ የገባውን ሲያስረዳ ትቀጠቅጡታላችሁ፡፡ እናንተ ያላሳያችሁትን መንገድ በጠቆመ? እናንተ ያልሞላችሁትን ክፍተት በሞላ? ምን አይነት ሀይማኖተኝነት ነው ይኼ? እውነቱን ልንገርሽ አብዛኛው የሀገራችን ህዝብ የአባቴ እምነት እያለ ሐይማኖቱን የያዘ ነው፡፡ ስለሐይማኖቱ ገና ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ እናንተ እስክትነቁ ፕሮቴስታንቱም፣ ሐዋርያቱም፣ ጆቫውም ሁሉም ና አብረን ገነት እንግባ እያለ ይጠራዋል፡፡ ሲርበው ያበላዋል፡፡ ሲቸገር ይደርስለታል፡፡ አባቶቼ ልክ አልነበሩም እያለ ሐይማኖቱን ይቀይራል፡፡ እኔ በግልፅ ነግሬሻለሁ፡፡ ፈጣሪ ጉዳዬ አይደለም፡፡ ማህሌት ነገ ሌላ ሐይማኖት እንከተል ካለችኝ ደስ ያላትን እቀበላለሁ፡፡ ለምን መሰለሽ፡፡ እኔ እሷን ተቀብያለሁ! የኔ ሐይማኖት የሷ ደግነት ነው፡፡›› መራመድ አቅቷት መንገዱ ላይ ተቀምጣ መንሰቅሰቅ ጀመረች፡፡ ፊቷ ቲማቲም መስሏል፡፡ እሷ ላይ እንደዚህ መጮህ እንዳልነበረብኝ ተሰማኝ፡፡ ስትረጋጋ ይቅርታ ጠየቅኳት፡፡ ‹‹ይቅርታ ሀፊ …… እናተን እንደዚህ ማለት አልነበረብኝም …. የቻላችሁትን እየሰራችሁ ነው፡፡›› እንባዋን እያበሰች ከተቀመጠችበት ተነሳችና ‹‹ምንም አላጠፋህም፡፡ ያልከው ሁሉ ልክ ነው፡፡ እኛም የቻልነውን እናግዝ ብለን እየተንቀሳቀስን ነው፡፡ እኛን እንኳን ተረድቶ ከጎናችን የሚቆመው ሰው በጣም ትንሽ ነው፡፡ በጣም ይቀረናል፡፡ በጣም!›› ወደ መኪናችን ተመልሰን እንደተቀመጥን ድጋሚ መንሰቅሰቅ ጀመረች፡፡ ‹‹ሀፊ ….. Please በቃ ተረጋጊ!›› ‹‹ታውቃለህ ነገ ጌታዬ ተርቤ አላበላችሁኝም ….. ስጠማ አላጠጣችሁኝም ….. ስታረዝ አላለበሳችሁኝም የሚልበት ቀን አለ ….›› ‹‹ፈጣሪ ደሞ ይበላል? ይጠጣል? ይለብሳል?›› ‹‹ያኔ እኛ አሁን አንተ ያልከውን ጥያቄ እንጠይቀዋለን፡፡ መልሱ ምን መሰለህ? ….›› መንሰቅሰቋ በረታ፡፡ ‹‹ምንድነው መልሱ?›› ‹‹ባርያዎቼ ሲታረዙ አላለበሳችኋቸውም፡፡ እነሱን ብታለብሱ እኔን ታገኙ ነበር፡፡ ሲራቡ አላበላችኋቸውም፡፡ እነሱን ብታበሉ እኔን ታገኙ ነበር፡፡ ሲጠሙ አላጠጣችኋቸውም ብታጠጧቸው በነሱ ውስጥ እኔን ታገኙ ነበር ይላል፡፡ ላንተ ሐይማኖት መቀየር ተጠያቂው ስትቸገር ያልደረስንልህ እኛ ነን፡፡ ያኔ ጌታዬ በተራቡት ሰዎች ጉዳይ ሲጠይቀኝ ምን ብዬ እመልሳለሁ?›› ተንሰቀሰቀች፡፡ ‹‹ራስህ ቀጥታ ለምን አልሰጠሀቸውም ትይዋለሽ አትጨነቂ!›› ሁሉም አባላት መጡ፡፡ ፕሬዝዳንቱ የኔ መኪና ውስጥ ከኋላ ተቀመጠ፡፡ ትህትናውን እንደተላበሰ ‹‹ወደድከው?›› አለኝ፡፡ ‹‹እሷ አለቃቀሰች እንጂ በጣም ወድጄዋለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ቤተሰብ ነኝ እንደውም!›› ‹‹ደስ ይለናል! …. እና ድሮ የምታውቀውን ሰው አላገኘህም?›› ‹‹አይቻለሁ ማንንም ማናገር አልፈለግኩም፡፡ ትዝታዬን መቀስቀስ ይሆንብኛል ብዬ ፈራሁ፡፡ ባይሆን ወደፊት ከደፈርኩ እስኪ ….›› መኪናችንን አስነስተን መመለስ ጀመርን፡፡ እየተመለስን ሚቾዬ ደወለች፡፡ በመኪናው ስፒከር ማዋራት ጀመርኩ፡፡ ‹‹አብርሽዬ ማር …..›› ‹‹ሚቾዬ ቆንጆ …..›› ‹‹ውሎ እንዴት ነው?›› ‹‹ምርጥ ነበር በጣም! ያልደፈርኩትን ደፈርኩ፡፡›› ‹‹ስማ ደግሞ
Mostrar todo...