cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

The Blue Vet

The Blue Vet is an Inspiration and Wisdom for Livestock sector run under @BeyondStudent4Change Initiative. You want to share something use @YimeT, @Salah_8, and @BetyydrS,@Eleazi @DrBam @AronAlexVet Our YouTube channel 👇 https://youtu.be/ga4H3xO2ZmE

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 678
Suscriptores
+324 horas
+317 días
+3530 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Repost from Ethio Poultry PLC
የ15% ነገር ሲሆን ሲሆን ድጋፍ እና ማበረታቻ የሚያስፈልገው ነበር። የእንስሳት እርባታው ዘርፍ ከምን ጊዜውም በላይ መነቃቃት እያሳየ ያለበት ወቅት ነው። በተለይ ለወጣቱ የስራ እድል በማድረግ  እና የወር ደሞዝ የለት ጉርስን ለመሸፈን የሚያጥረውን እጅ ለመደገፍ ብዙዎች ወደ እንስሳት እርባታ ፊታችውን አዙረዋል። ያላቸው ላይ ተበድረው ሳይቀር ወደ ስራው ተሰማርተዋል። በተለይ የዶሮ እርባታ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። የእንስሳት እርባታ ትልቁ ወጪ ያው እንደምትገምቱት መኖ ነው። እስከ 70% የወጪ ክፍልን ሊይዝ ይችላል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ታድያ እንዲሁም በተወደደ የመኖ ግዢ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጨመር ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን ይመስለኛል። ገና በመቀጣጠል ላይ ያለ የእሳት ብርሃን እፍ አይባልም። ሲሆን ሲሆን ከነፋስ ይጠብቁታል እንጂ። እንደ አንድ ዘርፉ እያሳየ ያለውን መነቃቃት ፣ ለወጣት እየፈጠረ ያለውን የስራ እድል እና እየደገፈ ያለውን የገቢ ምንጭ እንደሚደግፍ ሰው። በእንስሳት መኖ ላይ የተደረገው የተጨማሪ እሴት ታክስ ጭማሪ ጉዳቱ አልተስተዋለም እላለሁ። ያሬድ ኤርሚያስ ከተማሪነት በላይ ለለውጥ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Mostrar todo...
👍 1
Repost from Ethio Poultry PLC
የተግባር ስልጠና እንዲህ ባማረ መልኩ ጨርሰናል። 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 ለተከታታይ አምስት ቀናት ስንሰጥ የነበረው ስልጠና በዚህ መልኩ ጨርሰናል። 90% የሚሆኑ ሰልጣኞቻችን ልምድ ያላቸው አርቢዎች ሲሆኑ በስልጠናው ሳይንሱ ተከትለው ውጤታማ የሚሆኑበትን መንገድ አሳይተናል። በተግባር ስልጠናው በቀላሉ ሰው ወደ ስራው እንዴት እንደሚገባና ከገባ በኋላ የዋጋ ዝቅ እና ከፍ በምንስአት እንደሚያጋጥም ጭምር አሳይተናል። ይህ ስልጠና ግብርና በሳይንስ እና በእውቀት ቢሰራ የተሻለ መስራት የሚቻልበትን በስጋ ዶሮ ከትንሽ መነሳት እንደሚቻል ያሳየንበት ነው። አብረን ሰርተን አብረን እንደግ🙏 በሁሉም እንለያለን! 0913375491/0913286608 0908915767/0986739324 አድራሻ: መገናኛ 24 ቀበሌ ታክሲ ተራ አዋሽ ባንክ ካለበተ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 ኢትዮ የዶሮ እርባታና ማማከር ሀላ/የተ/የግ ማህበር
Mostrar todo...
👍 2
2
በኢትዮጵያ ታሪክ አንጋፋው የጤና ተቋም - ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢኒስቲትዩት 60ኛውን አመት ዛሬ በደማቅ ሁኔታ አክብሯል! እኛም ተገኝተን በጋራ አከበርን! እንኳን ደስ ያለን! ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢኒስቲትዩት የሀገር ኩራት!
Mostrar todo...
Repost from Ethio Poultry PLC
የመኖ ጭማሪ በቀላሉ መታየት የሌለበት ውሳኝ📢 የወተት የእንቁላል እና የስጋ ዋጋን ለመቀነስ እየተሰራ በነበርንበት ሁኔታ በእንስሳት መኖ ላይ 15% VAT መጨመሩ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኗል። ይህ አዋጅ እውነት በእርባታው ኢንዱስትሪ ላይ ብቻ ሳይሆን በማህበረሰቡ የምግብ ፍጆታ ላይ ከባድ ተፅእኖ የሚፈጥር ሁነት ነው። ይህንን አካሄድ የእንስሳት ሀኪሞች ማህበር ፣ የእንስሳት መኖ አቀናባሪዎች ማህበር ፣ የዶሮ አርቢዎች ማህበር እና መላው የእንስሳት ባለሙያ አዋጁን ተቋውሞ አርቢው እና ሸማቹ ላይ በተለይ ደግሞ ኢንዱስትሪው ላይ የሚደርሰውን ተፅእኖ ሊቃወም የሚኒስትሮች ምክርቤት የገንዘብ ሚኒስቴር ሀላፊዎች ከእንደገና ያጤኑት ዘንድ እንጠይቃለን! ዶ/ር ሳላሀዲን አሊ Ethio Poultry General Manager #MINISTRY_FINANCE #ethiopoultry #EthioChicken #pmoofethiopia
Mostrar todo...
👍 1
01:15
Video unavailableShow in Telegram
የእንስሳት_ጤና_ጥበቃ_ኢኒስቲቲዩት_Final.mp4283.50 MB
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
#እንወያይ
#Open_A_Mic 🎤
የእንስሳት ጤና እና ደህንነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ37ተኛ ስብሰባው ወደ ህዝብ ተወካዎች ምክር ቤት ያስተላለፈው ረቂቅ አዋጅ ፋይዳ ምንድነው? ሰፊ የውይይት ጊዜ ይኖረናል እንዳያመልጣችሁ ነገ ፣ አርብ ፣ ሰኔ 21 2:16 ዓ.ም ⌛ ከምሽቱ 2:30LT 🔴 በቀጥታ ስርጭት በቴሌግራም: Campus Voice Channel Join us https://t.me/campus_voice_2016 https://t.me/campus_voice_2016 https://t.me/campus_voice_2016
Mostrar todo...
👍 1 1
አሁን ግን እንስሳቱም ባለሙያውም የሚከበር ይመስለኛል! ኢትዮጵያ በእንስሳት ሀብት ዘርፍ የእርሻና መስሪያ ሚኒስቴር ከተመሰረተ ከ1900 ዓ.ም ጀምሮ ከወጡ የዘርፉ አስቻይ አዋጆች፣ ደንቦች እና ህጎች እነሆ የተለቀውን አውጥታለች። ይህን እውነታ ለመመልከት ይረዳን ዘንድ እስካሁን ያወጣናቸው ብንመለከት አሁን ከወጣው ረቂቅ አዋጅ ትኩረታቸው ምን እንደሆነ መረዳት እንችላለን። ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ እንዲሉ መጀመሪያ ማውጣት የነበረብን አዋጅ እያለ ምን ላይ ስንንጠለጠል እንደነበረ በደንብ ለተገነዘበው ይህን እውነት ይረዳዋል። ከቀድሞው የላቀ ወይን እነሆ በመጨረሻው ሰዓት! ለዘርፋችን እድገት ቀና ማለት በር የከፈተ። በጥቂቱ እስካሁን ስለ ምን እያወጣን ነበር? - በኢትዮጵያ የእንስሳት ሀብት ዘርፍ የወጡ አዋጆችና ደንቦች 1. የቀንድ ከብቶችን የሚቃወም ተላላፊ በሽታ ስለመከላከል የወጣ አዋጅ - 1942 ዓ.ም 2. የሥጋ ምርመራ አዋጅ 3. የእንስሳት፣ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ገበያ ልማት ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ - 1990 ዓ.ም 4. ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢኒስትትዩት በልማት ድርጅትነት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ - 1991 ዓ.ም 5. የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ - 1994 ዓ.ም 6. የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂ ኢኒስትትዩት ማቋቋሚያ (ማሻሻያ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ - 1996 ዓ.ም 7. የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ - 2000 ዓ.ም 8. የኢትዮጵያ የሥጋና ወተት ቴክሎሎጂ ኢኒስቲትዩትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ - 2000 ዓ.ም 9. የንብ ሀብት ልማትና ጥበቃ አዋጅ - 2002 ዓ.ም 10. የኢትዮጵያ የሥጋና ወተት ቴክሎሎጂ ኢኒስቲትዩትን ማቋቋሚያ (ማሻሻያ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ - 2002 ዓ.ም 11. የቆዳ ኢንዲስትሪ ልማት ኢኒስትትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ - 2002 ዓ.ም 12. የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ - 2004 ዓ.ም 13. የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ - 2005 ዓ.ም 14. የቁም እንስሳት ግብይት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ - 2006 ዓ.ም 15. የሆርቲ ካልቸር፣ የቁም እንስሳት እንዲሁም የቆዳና ሌጦ ዘርፎችን ግብይት በሚመለከት የአስፈጻሚ አካል ሥልጣን እና ተግባር ለውጥ ማድረጊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ - 2012 ዓ.ም ወዘተ ብለን NVI, EAA, AHI እንዳሉም ሳንረሳ በቅድሚያ የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ ሳይኖረን ዙሪያ ጥምጥም ያወጣናቸው አዋጆች አንዱም እንስሳቱንም ባለሙያዎንም አላስከበሩም። አሁን ግን እንስሳቱን ባለሙያውም የሚከበር ይመስለኛል። ምክንያቱም አዋጁ ከስሙ እራሱ ደስ የሚል ስሜትን፣ ልክነትን ይፈጥራል። ሲቀጥዕል የእንስሳት ጤና እና ደህንነት ከዚህ ዙሪያ ጥምጥም ላወጣናቸው አዋጆችንም ሆነ ደንቦች መሰረት የሚሆን መጀመሪያ መሆን የነበረበት አዋጅ ነበር። አሁን ግን ያ ጊዜ አልፎ እንስሳትን እንደ ፈለግን ስንጠቀማቸው ስለሚሰጡት ጥቅም ብቻ ማሰብ የቀረ እንደሆ የሚያስረግጥ አዋጅ ነው። ወደኋላ ሄዶ እስካሁን ስለመጣንበት በደንብ የተገነዘበ ሰው የዚህ አዋጀ አስፈላጊነት በደንብ ይገነዘባል። የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ ማለት እንስሳት ወደሙ ማለት ነው፣ ከምርታቸው በፊት ጤናቸው ማለት ነው፣ ጤናቸው ከመታወኩ በፊት እንጠብቃቸዋለን ማለት ነው፣ የሰው ልጅ ምን በሽታ ከእንስሳት አይዘውም ማለት ነው። እናንተ ደሞ ጨምሩበት! እናንተስ ምን ተሰማችሁ?
Mostrar todo...
👍 3
አሁን ግን እንስሳቱም ባለሙያውም የሚከበር ይመስለኛል!
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.