cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ወንጌል ያሸንፋል️

"ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።" (የማቴዎስ ወንጌል 24: 14) ☞ ቻናላችንን በዩቲዩብ ለመከታተል👇 ይጫኑት። http://bit.ly/2KM5PzL ለሀሳብ አስተያየት👇 📨 @ApostleAbz ☞ አብረውን ለማገልገል #0930703775 ይደውሉ።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
917
Suscriptores
-124 horas
-87 días
-2530 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🌇✅ Hope Package 🕹 ኢትዮቴሌኮም ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር አገልግሎቱን በማዘመን የሚገኝ አንጋፋ ተቋም ነው። ድርጅታችን ካርድ መፋቅ፣ መሙላት፣ የአገልግሎት ጊዜ ማለቅ እና የመሳሰሉ ችግሮች ሳይገጥሞ ህይወትዎን በዕቅድ መምራት እንዲችሉ መፍትሄ ይዞ ቀርቦላችዋል። በመሆኑም ወራዊ እና ዓመታዊ የድምፅ እና ወይም የኢንተርኔት ጥቅሎች በ25% ቅናሽ እነሆ ስንል በታላቅ ደስታ ነው። 📞 ወራዊ ቋሚ የድምፅ ጥቅል 🌠 100 ብር 500 ደቂቃ 🌠 200 ብር 1000 ደቂቃ 🌠 300 ብር 1500 ደቂቃ 🌠 400 ብር 2000 ደቂቃ 🌠 500 ብር 2500 ደቂቃ 🌠 600 ብር 3000 ደቂቃ 🌠 700 ብር 3500 ደቂቃ 🌠 800 ብር 4000 ደቂቃ 🌠 900 ብር 4500 ደቂቃ 🌠 1000 ብር 5000 ደቂቃ 🎇 900 ብር ወራዊ ያልተገደበ ⏳ወራዊ ቋሚ የኢንተርኔት ጥቅል 🌠 100 ብር 2 GB 🌠 200 ብር 5 GB 🌠 250 ብር 7 GB 🌠 300 ብር 10 GB 🌠 350 ብር 15 GB 🌠 400 ብር 20 GB 🌠 450 ብር 25 GB 🌠 500 ብር 30 GB 🌠 700 ብር 40 GB 🌠 800 ብር 50 GB 🎇 900 ብር ወራዊ ያልተገደበ 💡ያልተገደበ ዓመታዊ የድምፅ ወይም የኢንተርኔት ጥቅል ከመልዕክት ጥቅል ጋር በየወሩ 700 ብር፤ አጠቃላይ ዓመታዊ 5500 ብር ብቻ! 💡ያልተገደበ ዓመታዊ የድምፅ፣ የኢንተርኔትና የመልዕክት ጥቅል በየወሩ 1200 ብር፤ ጠቅላላ ዓመታዊ 9,500 ብር ብቻ!!! ✦ ለደንበኝነት ዛሬውን ይደውሉልን። 🖲 አድራሻችን፦ አ.አ፣ አዳማ፣ ሀዋሳ፣ አርባምንጭ { A.A, Adama, Hawassa& Arba Minch} ✅ ስለመረጡን እናመሰግናለን! ✅ ☎️ +251977285469 📨 t.me/hopemanager በቴሌግራም👇 https://t.me/+fuJOHc8LPpdlZDZk
Mostrar todo...
Repost from Ethiopian SDA
❤️‍🩹 አማናኖ ድርታኮቴ 🎖 ዘማሪት ሠላምነሽ ደመቀ 🔰 አቃማ አድቬንቲስት ቤ/ክ ⏰ 12 መዝሙር 📀 58 ደቂቃ 💥 Don't sleep 💥 by Akama SDA Church 🔰 በኢትዮጵያና ከሀገር ውጭ በብዛት የመዝሙሩን አልበም +251977285469 ደውለው መግዛት ይችላሉ። ✅ አድምጡት፤ ብሩካን ናችሁ! ✅ Join us 👇👇👇 https://t.me/EthiopianSDA
Mostrar todo...
. ለካስ ቀን ይመጣል Singer Yitbarek Tamru Amazing Gospel cover Song ።።።።(Worth listening)።።።።    ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲   ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳ       ▷ @Song4Christ ◁       ▷ @Song4Christ ◁              △Join us△
Mostrar todo...
መንፈሳዊ ስጦታዎች 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ክፍል 39 ✍✍✍ የመፈወስ ስጦታ 🌾🌾🌾🌾🌾 የፈውስ ስጦታ በሰውነት ላይ ያለን ማንኛውንም ደዌ የምናራግፍበት ስጦታ ብቻ አይደለም።በብሉይ ኪዳን ያሉ መጵሐፍትን ስናነብ ሀገር እንደ ሀገር ከገባበት ውጥንቅጥ እንዲወጣ ምድሪቷ ህዝቦቿ እንዲሁም የሚያጨነግፍው ውሃዎች እንደተፈወሱ ተፅፎልናል። በኤርሚያስ የትንቢት መጵሐፍ ውስጥ እግዚአብሄርን ባለማወቅ እግዚአብሄርን በመበደልና በመካድ የረከሰችው እስራኤልና ይሁዳ ምድሪቱ በኃጢያት ምክንያት ፈፅማ የረከሰች ለጠላቶቿም ተላልፋ እንድትሰጥ የተፈረደባት እንደነበረች እና ኤርሚያስ ግን ፈውስን ይጠብቅ እንደነበር ተፅፎዓል። “ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ መልካም ነገር ግን አልመጣም፤ የፈውስ ጊዜን ተመኘን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነብን።” ኤርምያስ 8፥15 (አዲሱ መ.ት) “ምድሪቱ በዝናብ እጦት የምትጐዳው፣ የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው? ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ ደግሞም ሕዝቡ፣ “በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።”ኤርምያስ 12፥4 (አዲሱ መ.ት) በኤልሳ ዘመን የኢያሪኮ ከተማ ለኑሮ የተመቸች ከተማ ነበረች ዳሩ ግን ውሃው መጥፎ ከመሆኑ የተነሳ ምድሪቱ ፍሬ እንዳትሰጥ አድርጎት ነበር ወይም ምድሪቱን ጭንጋፍ አድርጓት ነበር።ኤልሳም በእግዚአብሄር መንፈስ ተመርቶ በአዲስ ማሰሮ ውስጥ ጨው በማድረግ ወደ ውሃው ምንጭ በመሄድ ጨው ጣለበትና እግዚአብሄር የተናገረውን ቃል ለህዝብ ተናገረ ።እግዚአብሄር ውሃውን ፈውሼዋለው አለ ውሃውም ተፈወሰ። 2ኛ ነገሥት 2 (አዲሱ መ.ት)¹⁹ የከተማዪቱም ሰዎች ኤልሳዕን፣ “እነሆ ጌታችን፤ እንደምታያት ይህች ከተማ ለኑሮ የተመቸች ናት፤ ይሁን እንጂ ውሃው መጥፎ ሲሆን ምድሪቱም ፍሬ የማትሰጥ ናት” አሉት።²⁰ እርሱም፣ “እስቲ በአዲስ ማሰሮ ጨው ጨምራችሁ አምጡልኝ” አለ፤ እንዳለውም አመጡለት።²¹ ከዚያም ወደ ውሃው ምንጭ ሄዶ ጨው ጣለበትና “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ይህን ውሃ ፈውሸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ለሞት ምክንያት አይሆንም፤ ምድሪቱንም ፍሬ እንዳትሰጥ አያደርጋትም’ አለ።”²² ኤልሳዕ እንደ ተናገረውም ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ የተፈወሰ ነው። የመፈወስ ስጦታ መንፈስ ቅዱስ ከሰጣችሁ ችግር ያለበትንን ማንኛውንም ነገር በእናንተ በሚሰራው በመንፈስ ቅዱስ በኩል ፈውስ ያገኛል። ከዚህ በመቀጠል መናፍስትን የመለየትን ስጦታ እናጠናለን!!! ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ!! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/acham1583/528 🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕
Mostrar todo...
👑Kingdom Of Heaven Ministry❤️

መንፈሳዊ ስጦታዎች ❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥 ክፍል 38 ✍✍✍ የመፈወስ ስጦታ 🍁🍁🍁🍁🍁 የመፈወስ ስጦታ የመፈወስ ስጦታ በሶስት አይነት ሰዎች ላይ እንደሚገለጥ መፅሀፍ ቅዱስ ይናገራል።የመጀመሪያው በሁሉም አማኞች ላይ ሲሆን ለእምነታቸው እንደ ምልክት በእጆቻቸው ላይ ይፈፀማል።ማርቆስ 16 (አዲሱ መ.ት)¹⁷ የሚያምኑትን እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ልሳንም ይናገራሉ፤¹⁸ እባቦችን በእጃቸው ይይዛሉ፤ የሚገድል መርዝ ቢጠጡ እንኳ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውንም በሕመምተኞች ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱም ይፈወሳሉ።” ሁለተኛው ደግሞ ለቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች የተሰጠ ሲሆን እነርሱም የታመመው ሰው ጋ በመሄድ በዘይት ሲፀልዮ የሚሆን የእምነት ፀሎት ሲሆን ይህም ለታመመው ፍፁም ፈውስን ያስገኝለታል። ያዕቆብ 5 (አዲሱ መ.ት)¹⁴ ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።¹⁵ በእምነት የቀረበ ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሰዋል፤ ጌታም ያስነሣዋል፤ ኀጢአትም ሠርቶ ከሆነ፣ ይቅር ይባላል። ሶስተኛው ደግሞ ለክርስቶስ አካል ብልቶች እንዲታነፁበት መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው የመፈወስ ስጦታ ነው። '' ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ”— 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥9 የመፈወስ ስጦታ እንደሌሎቹ ስጦታዎች ሁሉ አንዱ መንፈስ ቅዱስ እንደ ወደደ ለወደደው ሰው የሚሰጠው ስጦታ ነው። የመፈወስ ስጦታ ደግሞ በተለያዮ ምክንያቶች መስራት ያቆሙ የሰውነት ክፍሎችን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ነው።ብልቶቻችን ታመሙ ሲባል መስራት አቆሙ ወይም ከአእምሮችን ጋር ግንኙነቱ ተቋርጧል ወይም በከፊል መስራት አቁሟል እንዳይሰራም የተጋረጠ ነገር አለ እንደ ማለት ነው። የሚሰራን የሰውነት ክፍል መልሶ እንዲሰራ ማድረግ…

መንፈሳዊ ስጦታዎች 🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ክፍል 40 ✍✍✍ መናፍስትን የመለየት ስጦታ 🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣 መናፍስትን የመለየት ስጦታ በምድር የሚኖሩ ሰዎችን ከባህሪያቸውና ከድርጊቶቻቸው ተነስተን እንደምለየው የሰውን ውስጣዊ ማንነት በውስጣችን ባለው በሰው መንፈስ አማካኝነት እንደምናውቀው መንፈሳዊውም ዓለም በእግዚአብሄር መንፈስ የሚታወቅ የሚለይ ነው። መንፈሳዊው ዓለም በሁለት ይከፈላል።የእግዚአብሄር አለምና የዚህ ዓለም አምላክ የሆነው የክፋት ሰራዊቶች መንፈሳዊ አለም።የእግዚአብሄር መንፈስ የእግዚአብሄርን አለም ከክፋው ዓለም ለይተን የምናይበትን መንፈሳዊ ዓይን ሰጥቶናል። መናፍስትን መለየት ሲባል ዲያቢሎስ ያለበትን የዲያቢሎስ ስራ ብቻ ማየት ማለት አይደለም ልክ ነው የዲያቢሎስን ስራና አጋንት የተቆጣጠረውን ሰው መለየት አንዱ መናፍስትን መለየት ነው ዳሩ ግን ብቸኛ አገልግሎት አይደለም። መናፍስትን መለየት ማለት የእግዚአብሄርን መገኘት ስራውንና የእግዚአብሄር መንፈስ ያለበትን ከሌለበት መለየት የእግዚአብሄርን መላክና ራሱን የብርሃን መልአክ አድርጎ ከሚለውጠው ክፉ መለየት. መንፈስ ቅዱስ የሞላበትንና የክፉው የሞላበትን በንግግር በእይታ በልዮ ልዮ መንገድ መለየት ነው። መናፍስትን የመለየት ስጦታ ለቤተክርስቲያን እጅግ ጠቃሚ የሆነ ስጦታ ነው።መናፍስትን የሚለይ ሰው በቤተክርስቲያን ውስጥ ካለ በቤተክርስቲያን ውስጥ የኤልዛቤል መንፈስ መሰልጠን አይችልም።ነብይ ሳይሆኑ ነብይ ነን ሐዋሪያ ሳይሆኑ ሐዋሪያ ነን የሚሉ ሰዎች እንደ ልባቸው መፈንጨት አይችሉም። መናፍስትን የሚለዮ ሰዎች መርማሪዎች ወይም ፈታኞች ናቸው። በኤፌሶን ያለችው ቤተ ክርስቲያን የተመሰከረላት በዚህ ነው።“ሥራህን፣ ጥረትህንና ትዕግሥትህን ዐውቃለሁ። ክፉዎችንም ችላ ብለህ እንዳላለፍሃቸው፣ ሐዋርያት ሳይሆኑ ሐዋርያት ነን የሚሉትንም መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው ዐውቃለሁ።” ራእይ 2፥2 (አዲሱ መ.ት) ከኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን በተቃራኒው በጴርጋሞ የነበረችው ቤተክርስቲያን በጌታ ኢየሱስ የተወቀሰችው ትምህርቶችን መለየት ባለመቻሏ ነበር።ጌታ ምን አይነት ትምህርትን ለይታ ከውስጧ ማውጣት እንዳቃታት ሲናገር የበለዓምንናየኒቆላውያንን ትምህርት የሚከተሉ ሰዎች እንደሆነ ይናገራል። ራእይ 2 (አዲሱ መ.ት)¹⁴ ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤ የእስራኤል ልጆች ለጣዖት የተሠዋ ምግብ እንዲበሉና እንዲሴስኑ በፊታቸው መሰናከያ ያስቀምጥ ዘንድ ባላቅን ያስተማረውን የበለዓምን ትምህርት የሚከተሉ አንዳንድ ሰዎች በመካከልህ አሉ፤¹⁵ የኒቆላውያንን ትምህርት የሚከተሉ ሰዎችም በአንተ ዘንድ አሉ።¹⁶ ስለዚህ ንስሓ ግባ፤ አለዚያ ቶሎ እመጣብሃለሁ፤ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ። የበለዓም ምክርና ትምህርት እስራኤልን ከተነገረላቸውና እግዚአብሄር ከማለላቸው ተስፋ አጉድሎ ብዙዎችን በምድረ በዳ ያስቀረ ክፉ ትምህርት እንደነበር ሙሴ በዘገበልን ዘኁልቅ 22.23.24 እንዲሁም 25 ላይ ተመዝግቧል። ጌታ ኢየሱስ በጴርጋሞ ቤተክርስቲያን ሾልከው የገብት ሰዎች ባህሪያዊ አስተምህሮ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉት ቅዱሳን ከዘላለም ህይወት የሚያጎድል ክፉ ትምህርት በመሆኑ ማንነታቸውን በማወቅ እንድታወጣቸው ያዛል።ዛሬም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰውን እግዚአብሄር ከመፍራት ከመቀደስ ለእግዚአብሄር በመለየት የእግዚአብሄር ወራሽ ከመሆን ሰዎችን የሚያጎድሉ ክፉ ትምህርቶችን ሰይጣን አሾልኮ እያስገባ ይገኛል እነዚህን በመለየት ትምህርታቸውን በማውገብ የእግዚአብሄርን ህዝቦች ከክፉ ነገር የሚጠበቁት በቤተክርስቲያን መናፍስትን የመለየት ስጦታው ያላቸው ቅዱሳን ሲበዙ ነው።በኢየሱስም ይህ ስጦታ ይብዛልን!! ይቀጥላል ከታች ሊንክ በመጫን የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!!! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/acham1583/532 🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕
Mostrar todo...
👑Kingdom Of Heaven Ministry❤️

መንፈሳዊ ስጦታዎች 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ክፍል 39 ✍✍✍ የመፈወስ ስጦታ 🌾🌾🌾🌾🌾 የፈውስ ስጦታ በሰውነት ላይ ያለን ማንኛውንም ደዌ የምናራግፍበት ስጦታ ብቻ አይደለም።በብሉይ ኪዳን ያሉ መጵሐፍትን ስናነብ ሀገር እንደ ሀገር ከገባበት ውጥንቅጥ እንዲወጣ ምድሪቷ ህዝቦቿ እንዲሁም የሚያጨነግፍው ውሃዎች እንደተፈወሱ ተፅፎልናል። በኤርሚያስ የትንቢት መጵሐፍ ውስጥ እግዚአብሄርን ባለማወቅ እግዚአብሄርን በመበደልና በመካድ የረከሰችው እስራኤልና ይሁዳ ምድሪቱ በኃጢያት ምክንያት ፈፅማ የረከሰች ለጠላቶቿም ተላልፋ እንድትሰጥ የተፈረደባት እንደነበረች እና ኤርሚያስ ግን ፈውስን ይጠብቅ እንደነበር ተፅፎዓል። “ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ መልካም ነገር ግን አልመጣም፤ የፈውስ ጊዜን ተመኘን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነብን።” ኤርምያስ 8፥15 (አዲሱ መ.ት) “ምድሪቱ በዝናብ እጦት የምትጐዳው፣ የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው? ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ ደግሞም ሕዝቡ፣ “በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።”ኤርምያስ 12፥4 (አዲሱ መ.ት) በኤልሳ ዘመን የኢያሪኮ ከተማ ለኑሮ የተመቸች ከተማ ነበረች ዳሩ ግን ውሃው መጥፎ ከመሆኑ የተነሳ ምድሪቱ ፍሬ እንዳትሰጥ አድርጎት ነበር ወይም ምድሪቱን ጭንጋፍ አድርጓት ነበር።ኤልሳም በእግዚአብሄር መንፈስ ተመርቶ በአዲስ ማሰሮ ውስጥ ጨው በማድረግ ወደ ውሃው ምንጭ በመሄድ ጨው ጣለበትና እግዚአብሄር የተናገረውን ቃል ለህዝብ ተናገረ ።እግዚአብሄር ውሃውን ፈውሼዋለው አለ ውሃውም ተፈወሰ። 2ኛ ነገሥት 2 (አዲሱ መ.ት)¹⁹ የከተማዪቱም ሰዎች ኤልሳዕን፣ “እነሆ ጌታችን፤ እንደምታያት ይህች ከተማ ለኑሮ የተመቸች ናት፤ ይሁን እንጂ ውሃው መጥፎ ሲሆን ምድሪቱም ፍሬ የማትሰጥ ናት” አሉት።²⁰ እርሱም፣ “እስቲ በአዲስ ማሰሮ ጨው…

መንፈሳዊ ስጦታዎች 🍁🍁🍁🌾🍁🍁🍁 ክፍል 35 ✍✍✍ ተዓምራትን የማድረግ ስጦታዎች ✋🤚✋🤚✋🤚✋🤚✋🤚 ተዓምራት የሌለው የሚፈጠርበት ያለው አካላዊ ለውጥ የሚያደርግበት መለኮታዊ ችሎታ ነው።ለምሳሌ ውሃ የወይን ጠጅ ሲሆን አካላዊ ለውጥ አምጥቷል በደረቅ ግንባር አይን ሲፈጠር ደግሞ የሌለው ተፈጥሮአል። ኢየሱስ ሰባት ተዓምራዊ ምልክቶችን ማድረጉ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ተመዝግቦልና እነዚህን ሰባት ተዓምራዊ ምልክቶችን በማጥናት ተዓምራዊ ምልክት ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ይቻላል ስለዚህም እንድታጠኑት እጋብዛለው። ተዓምራዊ ምልክቶች የሚያደርገው እግዚአብሄር ሲሆን የሚደረጉበት ምክንያት እኛ የእግዚአብሄርን ቃል ስንሰብክ መልዕክቱ ከእኛ ሳይሆን ከራሱ መሆኑን ለማሳየት እግዚአብሄር ተዓምራዊ ምልክቶችን ያደርጋል። ተዓምራዊ ምልክቶች እግዚአብሄር የእኛ አገልግሎት እውነተኛ መሆኑን የሚመሰክርበት መንገድ ነው።እግዚአብሄር ለኢየሱስ እንዴት ባለ መልኩ እንደመሰከረለት ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ ነበር፡"““የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ ይህን ቃል ስሙ፤ እናንት ራሳችሁ እንደምታውቁት፣ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ታምራትን፣ ድንቅ ነገሮችንና ምልክቶችን በእርሱ በኩል በማድረግ ለናዝሬቱ ኢየሱስ መስክሮለታል።” — ሐዋርያት 2፥22 (አዲሱ መ.ት) በተጨማሩም በሐዋሪያቱ በበርናባስ በጳውሎስ የተሰበከውን ቃል ጌታ በብዙ ምልክቶችና ድንቅ ተዓምራት እንዳረጋገጠ ተፅፎዓል። “ጳውሎስና በርናባስም ስለ ጌታ በድፍረት እየተናገሩ ብዙ ጊዜ እዚያው ቈዩ፤ ጌታም የሚናገሩትን የጸጋውን ቃል በታምራዊ ምልክትና በድንቅ ሥራ እየደገፈ ያረጋግ ጥላቸው ነበር።” — ሐዋርያት 14፥3 (አዲሱ መ.ት) ስለዚህ በአጭር አማርኛ ታምራት ድንቆችና ምልክቶች እግዚአብሄር ለእኛ እየመሰከረልን ወይም በእኛ የሚሰበከው የምስራች እውነተኛ መሆኑን እያረጋገጠልን እንደሆነ ማስተዋል ይገባል። አገልጋይ ተዓምራዊ ምልክቶች በእጆቼ ካልተደረጉ ማለት አይችልም ተዓምራዊ ምልክቶችንም እንዲደረጉ በእጆቻችን መፀለይም አለበት ብዬ አላምነም የማምነው አንድ ነገር ቢኖር እኛ ከእግዚአብሄር ጋር አብሮ ሰራተኞች ነን። “እኛ ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነን።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥9 (አዲሱ መ.ት) ከእግዚአብሄር ጋር አብሮ ሰራተኞች ነን ማለት እኛ የምንሰራው አለ እግዚአብሄር በእኛ የሚሰራው አለ።እኛ የምንሰራው ቃሉን መስበክ ሲሆን በእኛ የተሰበከው ቃል የእግዚአብሄር ቃል መሆኑን ጌታ ደግሞ ምልክቶችን በማድረግ ያፀናዋል።በእኛ ተዓምራት ይሁኑ ብለን ካልን ከእግዚአብሄር ጋር ሳይሆን እኛ ብቻችን ካልሰራን እያልን ነው።የእኛን ስራ እግዚአብሄር ከሚሰራው ስራ ጋር አንቀላቅለው አንደባልቀው በስራው የሚታየው እግዚአብሄር መሆኑን በመናገር ሰሪውን እያስከበርን ለስራው ዋጋ እየሰጠን ከእርሱ ጋር አብረን መስራት ይጠበቅብናል። “ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ወጥተው፣ በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፤ ትምህርታቸውንም ተከትለው በሚፈጸሙ ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።” — ማርቆስ 16፥20 (አዲሱ መ.ት) በአገልግሎታችን ታምራት ድንቅ ምልክቶች እንዲሆኑ በጣም ምትፈልጉ ከሆነ ኢየሱስን ስበኩ የምትሰብኩት የምትናገሩትን ደግሞ እርሱ ያፀናዋል። ይቀጥላል ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ!!!! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/acham1583/521🤏 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️🙏🙏
Mostrar todo...
👑Kingdom Of Heaven Ministry❤️

መንፈሳዊ ስጦታዎች 🧚🧚🌾🌾🧚🌾🌾 ክፍል 34 ✍✍✍ ተዓምርናፈውስ ተዓምራትና ፈውስ እምነትን ተከትሎ የሚደረጉ ምልክቶች ናቸው።በእኛ ውስጥ ራሳችንን ክደን ኢየሱስ እንዲኖር ህይወቱም በእኛ እንዲሰራ በእምነት ከእግዚአብሄር ጋር ስንስማማ ኢየሱስ በእኛ ህይወት ውስጥ መኖር ሲጀምር መለኮታዊ ችሎታዎች የመለኮቱ ኃይልና የብርታቱ ጉልበት በእኛ ይታያል። ኢየሱስ የሰናፍንጭ ቅንጣት የምታህል እምነት ካለህ ተራራውን ተነቅለህ ሲድ ብትሉት ይሄዳል ሲል ተናግሮዓል ተራራን ነቅሎ ከነበረበት ስፍራ ወዳልነበረበት ወደሌላ ስፍራ ማድረግ ተዓምር ነው ይህ ተዓምህ ግን የሚሆነው በእምነት ነው። “እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “እምነታችሁ በማነሱ ምክንያት ነው፤ እላችኋለሁ፤ የሰናፍጭ ቅንጣት የምታህል እምነት ቢኖራችሁ፣ ይህንን ተራራ፣ ‘ከዚህ ተነሥተህ ወደዚያ ሂድ’ ብትሉት ይሄዳል፤ የሚሳናችሁም ነገር አይኖርም — ማቴዎስ 17፥20 (አዲሱ መ.ት) ማዕበል ፀጥ እንዲል ማዘዝ ልዕለ ተፈጥሮአዊ አቅምን ይጠይቃል እምነት ካለን ልዕለ ተፈጥሮአዊው አቅም በእኛ መገለጥ ይጀምራል በዚህም ተፈጥሮን እናዛለን ማህበሉን ፀጥ በል ስንለው በመታዘዝ ፀጥ ይላል።የኢየሱስ ማህበሉን ማዘዝና ማህበሉም ለኢየሱስ መታዘዙ ደቀ መዛሙርቱን ያስገረመ ጉዳይ ነበር።የተገረሙት እነርሱ ማድረግ ያልቻሉትን ስላደረገ ነው።እምነት ሰው ማድረግ የማይችለውን እግዚአብሄር ማድረግ የሚችለውን በእግዚአብሄር መንፈስ አማካኝነት በኢየሱስ ስም በእምነት ማድረግ መቻል ነው። “ኢየሱስም፣ “እናንተ እምነት የጐደላችሁ፤ ለምን ይህን ያህል ፈራችሁ?” አላቸው፤ ከዚያም ተነሥቶ ነፋሱንና ማዕበሉን ገሠጸ፤ ወዲያውም ጸጥታ ሰፈነ።”— ማቴዎስ 8፥26 (አዲሱ መ.ት) ተዓምር ሰው ማድረግ የማይችለውን ሰው ሊሰራው የማይችለውን ከሰው ችሎታና አቅም በላይ የሆነውን በእግዚአብሄር ጉልበትና…

መንፈሳዊስጦታዎች 🔥🔥🔥🌾🔥🔥🔥 ክፍል 44 ✍✍✍ መናፍስትን የመለየት ስጦታ 🍁🍁🍁🔥🔥🔥🍁🍁 የማጠቃለያ አሳቦች በ1 ቆሮ 12÷10 መለየት የሚለው ቃል ብዙ አሳቦችን ከያዘ የግሪክ ቃል የመጣ ነው።በዚህ ቃል ውስጥ ማየት መገንዘብ መመርመር መርዳት መስማት በትክክል መፍረድ የሚሉ አሳቦች ሁሉ ይጠቃላል።የዚህን ስጦታ ብቃት "መናፍስትን መለየት" በማለት ይጠራዋል። ከዚህ ክፍል በፊት ባየነው ክፍሎች ውስጥ ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ እንዳስጠነቀቀው በተለይ በዚህ በዘመኑ ፍፃሜ ብዙ ሐሰተኛ ነቢያትና አሳቶች እንደሚነሱ ይናገራል ግን ይህ የሚያስገርም አይደለም ምክንያቱም ሴይጣን ራሱን ወደ ብርሃን ራሱን ይለውጣል። 2ኛ ቆሮንቶስ 11 (አዲሱ መ.ት)¹⁴ ይህም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም፤ ምክንያቱም ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለዋው ጣል።¹⁵ እንግዲህ የእርሱ አገልጋዮች፣ የጽድቅ አገልጋዮች ለመምሰል ራሳቸውን ቢለውጡ የሚያስገርም አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል። ዛሬ ብዙ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ አይማኖቶችና መሪዎች የሐሳዊ መሲህ እንጂ የክርስቶስ አለመሆናቸው የተገለጠ ነው።እነርሱ የበግ ለምድ ለብሰው የሚዞሩ ተኩላዎች ናቸው፡ስንዴዎችም ሳይሆኑእንክርዳዶች ናቸው። ዋናው ጉዳይ ስንዴውን ከእንክርዳዱ በጉን የበግ ለምድ ከለበሰው ተኩላ የብርሃን መላክን ብርሃን አስመስሎ ራሱን ከለወጠው ከሰይጣን የፅድቅ አገልጋዮችን ከአስመሳዮች እንዴት እንለያለን የሚለው ጥያቄ ነው። ክርስቲያኖች የመለየት ወይም የመመርመር ስጦታ ቢያንስ ደግሞ ይኸው ስጦታ ያላቸውን ሰዎች እንድንቀበላቸው የሚያስፈልገን ለዚሁ ነው። “ወዳጆች ሆይ፤ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ምክንያቱም ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።”1ኛ ዮሐንስ 4፥1 (አዲሱ መ.ት) አማኞች ዛሬ የሚታዮትን የተለያዮ መናፍስትና የእምነት ትምህርቶች መመርመር ወይም መፈተን አለብን።ባመዛኙ የምንመረምራቸው የእግዚአብሄር ቃል በሆነው በመጵሐፍ ቅዱስ ነው።ይሁን እንጂ እግዚአብሄር አንዳንድ በክርስቶስ ውስጥ ያሉ አማኞችን እውነትን ይለዮ ዘንድ የማወቅ መለኮታዊ ስጦታን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ይሰጣል። “ለሌላው ደግሞ መናፍስትን የመለየት፣ ።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥10 (አዲሱ መ.ት) በአጠቃላይ የመመርመር ወይም የመለየት ስጦታ ያለው ሰው ባብዛኛው ከእግዚአብሄር ዘንድ በሆነውና ባልሆነው ነገር መካከል ያለውን ልዮነት ሊናገር እንደሚችል መገንዘብ አስፈላጊ ነው። በኢየሱስ ስም ይህ ስጦታ ያላቸው ሰዎች ይብዙልን!!አሜን። ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!!!! 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 https://t.me/acham1583/537 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Mostrar todo...
👑Kingdom Of Heaven Ministry❤️

መንፈሳዊ ስጦታዎች 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ክፍል 43 ✍✍✍ መናፍስትን የመለየት ስጦታ መናፍስትን የመለየት ስጦታ ለምን አስፈለገን ካላችሁ መንፈስ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄርም መንፈስ ባለመሆኑና መንፈስንም ሁሉ ማመን ስለማይገባን መናፍስት ከእግዚአብሄር መሆን አለመሆኑን በሚገባ እንድንመረምር መጵሐፍ ቅዱስ ይመክረናል። “ወዳጆች ሆይ፤ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ምክንያቱም ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።”1ኛ ዮሐንስ 4፥1 (አዲሱ መ.ት) ሐሰተኞች በመኖራቸው እውነተኞችን ከሐሰተኞች በመመርመር ልንለይ መንፈስንና የመንፈስን አሰራር ልንለይ ይገባናል።ዮሐንስ ይህንን ምክር ከእግዚአብሄር ለተወለዱ ለእግዚአብሄር ልጆች ያስተላለፈው ምክር በመሆኑ ሁላችንም መርማሪዎች ልሆን ይገባናል። ሰዎች መናፍስትን ባለመለየታቸው በተለይም አሁን በእኛ ዘመን ብዙዎችን በማታለል ከእውነተኛው እምነት የሚያስክዱ የአጋንትን ትምህርት የሚከተሉና የሚያስተምሩ ሰዎች ተነስተው እንደነበርና ዛሬም እንደሚነሱ መፅሐፍ ቅዱስ በግልጥ ይናገራል። “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች እምነትን ክደው አታላይ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት እንደሚከተሉ መንፈስ በግልጥ ይናገራል።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥1 (አዲሱ መ.ት) መዘንጋት የማይገባን ነገር ቢኖር መጋደላችን ከስጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከዚህ ከጨለማው ዓለም ገዥዎች ከስልጣናት ከኃይላት በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሰት መናፍስት ሰራዊቶች ጋር በመሆኑ አሰራሩን መለየት ይገባናል። “ምክንያቱም ተጋድሎአችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከሥልጣናትና ከኀይላት እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው።” — ኤፌሶን 6፥12 (አዲሱ መ.ት) ዛሬም መርሳት የማይገባን ነገር ቢሆን…

መንፈሳዊ ስጦታዎች 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ክፍል 37 ✍✍✍ ተዓምራት የማድረግ ስጦታ 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 ተዓምራዊ ምልክቶች እግዚአብሄር ህዝቦቹን በሙሉ ወደ እኛ የሚጠራበት የሚሰበስብበት መንገድ ነው።ሐዋሪያው ጴጥሮስና ዮሐንስ በኢየሩሳሌም ወደ ቤተመቅደስ ለዘጠኝ ሰዓቱ ፀሎት ሲሄዱ በዕብራይስጥ ውብ ወይም መልካም በሚሏት መመላለሻ ሰዎች እያመጡ የሚያስቀምጡት ከአርባ አመት የሚበልጠው መራመድ የማይችል ሽባ ሰው መዳን ህዝብን በሙሉ በሰለሞን አደባባይ ላይ ዕለት ዕለት ወደ ሚሰበሰብ ሐዋሪያት ስቦዓቸዋል። “እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ።” — ሐዋርያት 3፥11 እግዚአብሄር ተዓምራቶችን የሚያደርገው ህዝብን አንተን አንቺን ለማስደነቅ ሳይሆን ባየውና በሰማው ነገር ተደንቆ ለመጣው ህዝብ የሚደንቀውን የክርስቶስን የመስቀል ላይ ስራ እንድንመሰክር ነው።ጴጥሮስ ወደ እነርሱ በመገረምና በመደነቅ ለተሰበሰበው ህዝብ አይኖቻቸውን ከእነርሱ ላይ በማንሳት ወደ እግዚአብሄር ወደ ኢየሱስ ዞር ለማድረግ ኢየሱስን ሰበከ ።እኛም እኛ እንደሰራነው መደነቅ የለብንም ይልቁንም እግዚአብሄር ለምን ታምራት ድንቆችችና ምልክቶችን እንዳደረገ በመረዳት አጋጣሚውን ተጠቅመን ራሳችንን ሳይሆን ኢየሱስንና የኢየሱስን መስበክ አለብን። ሐዋርያት 3 (አዲሱ መ.ት)¹² ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ በዚህ ለምን ትደነቃላችሁ? ደግሞም በእኛ ኀይል ወይም በእኛ ጽድቅ ይህ ሰው ድኖ እንዲመላለስ እንዳደረግነው በመቊጠር፣ ለምን ወደ እኛ አትኵራችሁ ትመለከታላችሁ?¹³ የአባቶቻችን አምላክ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው፤ እናንተ ግን እንዲሞት አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ጲላጦስ ሊፈታው ቢፈልግም እናንተ በእርሱ ፊት ካዳችሁት፤¹⁴ ቅዱሱንና ጻድቁን ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ፤¹⁵ የሕይወት መገኛ የሆነውን ገደላችሁት፤ እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው፤ እኛም ለዚህ ምስክሮች ነን። ከዚህ በዋላ የመፈወስ ስጦታን እንጀምራለን!!ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ!! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/acham1583/525 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
Mostrar todo...
👑Kingdom Of Heaven Ministry❤️

መንፈሳዊ ስጦታዎች 🍁🍁🍁🌾🍁🍁🍁 ክፍል 36 ✍✍✍ ተዓምራት የማድረግ ስጦታ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ሐዋሪያት ተዓምራት ድንቆችና ምልክቶች ካልተደረጉ ብለው ፀልየው አያውቁም የሚፀልዮት አንድ ነገር ነው።የመጀመሪያው ቃሉን በግልጥ መናገር እንዲሰጣቸው ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ እግዚአብሄር የሚሰብኩትን ብላቴና እንዲያከብር እጆቹንም በመዘርጋት ድንቆችን ተዓምራቶችንና ምልክቶችን በማድረግ አብሮአቸው እንዲሰራ ነው። ሐዋርያት 4 (አዲሱ መ.ት)²⁹ አሁንም ጌታ ሆይ፤ ዛቻቸውን ተመልከት፤ ባሪያዎችህም ቃልህን በፍጹም ድፍረት መናገር እንዲችሉ አድርጋቸው።³⁰ ለመፈወስ እጅህን ዘርጋ፤ በቅዱሱ ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ድንቅና ታምራት አድርግ።” ሐዋሪያት ስጠን ብለው የሚለምኑት አለ ደግሞ እኛ እናድርግ ሳይሆን አድርግ ብለው እግዚአብሄርን የሚጠይቁት ጉዳይ አለ።ስለዚህም ቃሉን መስበክና የምትሰብኩት ቃል እንዲሰጣችሁ ቃሉንም በፍፁም ግልፅነት እንድትሰብኩ እንፀልይ ተዓምራት ድንቆችንና ምልክቶችን ግን እኛ እናድርግ ተብሎ አይፀለይም አንተ አድርግ ምክንያቱም እኛ ከእግዚአብሄር ጋር አብሮ ሰራተኞች ነን።ይህ ፀሎት መልስ ያገኘው ወዲያው ነበር።ወዲያው ያሉበት ስፍራ ተናወጠ መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ ተዓምራት ግን አላደረጉም ያደረጉት ቃሉን መስበክ ነው ቃሉ ሲሰበክ ቃሉን የሚያፀናው ጌታ ነው ቃሉም የሚፀናው በተዓምራዊ ምልክት ነው። “ከጸለዩም በኋላ የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በድፍረት ተናገሩ።” — ሐዋርያት 4፥31 (አዲሱ መ.ት) ቃሉን እንስበክ የቃሉ ባለቤት ቃሉን በምልክቶችና በተዓምራት ያፀናዋል። ኢየሱስ ወደ አባቱ ወደ አባታችን ሊያርግ ሲል ለሐዋሪያቱ የሰጠው አንድ ተልዕኮ ነው ይህውም ወንጌልን መስበክ ኢየሱስ ስበኩ አስተምሩ እያጠመቃችሁም ደቀ መዛሙርቴ አድርጉ ብሎ ብቻ…

መንፈሳዊ ስጦታዎች 🔥🔥🔥🌾🌾🔥🔥 ክፍል 42 ✍✍✍ መናፍስትን የመለየት ስጦታዎች 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 መንፈሳዊ ስጦታዎችን ስናጠና አብዛኛዎቹ ስጦታዎች የመናገር ስጦታዎች ናቸው።“ለአንዱ በመንፈስ የጥበብን ቃል መናገር ይሰጠዋል፤ ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ የዕውቀትን ቃል መናገር ይሰጠዋል፤”1ኛ ቆሮንቶስ 12፥8 (አዲሱ መ.ት)ከጥበብና ዕውቀት ውጪ ትንቢትን መናገር ልሳን መናገር እነዚህ ሁሉ በንግግር የሚገለጡ ስጦታዎች ናቸው። መናፍስትን የመለየት ስጦታ ሰዎች የሚናገሩበት መንፈስ የመለየት ስጦታ ነው።የእግዚአብሄር የሚመስል ቃል የሚናገር ሁሉ የእግዚአብሄር ሰው አይደለም።በመቄዶኒያ ዋና ከተማ በፊሊጲሲዮስ እነ ጳውሎስን የፈተናቸው ጉዳይ ይህ ነበር። ሐዋርያት 16 (አዲሱ መ.ት)¹⁶ አንድ ቀን ወደ ጸሎት ስፍራ ስንሄድ፣ በጥንቈላ መንፈስ ትንቢት የምትናገር አንዲት የቤት አገልጋይ አገኘችን፤ እርሷም በዚህ የጥንቈላ ሥራዋ ለአሳዳሪዎችዋ ብዙ ገንዘብ ታስገኝላቸው ነበር።¹⁷ ይህችው አገልጋይ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፣ “እነዚህ ሰዎች የመዳንን መንገድ የሚነግሯችሁ፣ የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው!” በማለት ትጮኽ ነበር፤¹⁸ ይህንም ብዙ ቀን ደጋገመችው፤ ጳውሎስ ግን በዚህ እጅግ በመታወኩ ዘወር ብሎ ያን መንፈስ፣ “ከእርሷ እንድትወጣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ” አለው፤ መንፈሱም በዚያው ቅጽበት ወጣላት። ሴትዮዋ የምትናገረውን ንግግር ብቻ ከወሰድነው የእግዚአብሄር አገልጋይ እንጂ ጠንቋይ አትመስልም እንደውም ለነ ጳውሎስ እውቅና የምትሰጥ ሴት ነው የምትመስለው የምትናገርበት መንፈስን ግን እነ ጳውሎስ ራሱ የለዮት ከብዙ ጊዜ በዋላ ነው። መናፍስትን ስለመለየት ሳጠና በጣም የገረመኝን አንድ ክፍል ልንገራችሁ ሰይጣን ሰዎችን እውነተኛ አገልጋይ መሆን አለመሆናቸውን ያውቃል የኢየሱስን ስም የጠራውን ሁሉ በኢየሱስ ማመን አለማመኑንና እውነተኛ ክርስቲያን መሆን አለመሆኑ ያውቃል። ምሳሌ የአስቄዋ ልጆች ሐዋርያት 19 (አዲሱ መ.ት)¹³ እየዞሩ አጋንንትን ያስወጡ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶቹ፣ “ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ ስም እንድትወጡ አዛችኋለሁ” እያሉ የጌታን የኢየሱስን ስም ርኵሳን መናፍስት በያዟቸው ሰዎች ላይ ለመጥራት ሞከሩ፤¹⁴ የአይሁዳዊው የካህናቱ አለቃ የአስቄዋ ሰባት ወንዶች ልጆችም ይህንኑ ያደርጉ ነበር።¹⁵ ርኩስ መንፈሱም፣ “ኢየሱስን ዐውቀዋለሁ፤ ጳውሎስንም ዐውቀዋለሁ፤ እናንተ ግን እነማን ናችሁ?” አላቸው። ሰይጣን ይሄን ያህል ሰዎችን ከለየ እኛ ደግሞ እርሱ ራሱ አሾልኮ ካስገባብን የሐሰት ሐዋሪያ ነቢያትና አስተማሪዎች ራሳችን ለመጠበቅ ሰዎች የሚናገሩበት መንፈስ መለየት የግድ ያስፈልገናል። አገልጋዮች ብቻ ሳይሆኑ በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አካል ሆነው የተጨመሩ አማኞች የሚኖሩበትን የህይወት ስርዓት በማወቅ ከእግዚአብሄር ቃል ጋር ያላቸውን አብርሆት በማወቅ ና በመፈተን እግዚአብሄር በዚህ ምድር እንድንኖረው ወደ ወሰነልን የህይወት ስርዓት በማስገባት በዓለም እንደ ብርሃን ልጆች እንድንታይ ብቁ የሚያደርጉት ሰው የሚመላለስበትን መንፈስ የሚለዮ ፈታኞች ወይም መናፍስትን የመለየት ስጦታ የተሰጣቸው ሰዎች ናቸው። ቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ሁሉ የክርስቶስ አካል አይደለም።ቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ሁሉ የእግዚአብሄር ልጆችም አይደሉም የእግዚአብሄር ልጆች በእግዚአብሄር መንፈስ የሚመሩ እንደ መንፈስም ፍቃድ የሚመላለሱ ናቸው። መናፍስትን የሚለዮ አገልጋዮች ሰው በስጋ ወይስ በመንፈስ እየተመላለሰ እንደሆነ ፈትነው ስለሚያውቁ ሰውን ከስጋ ሐሳብ አላቀው ወደ እውነተኛ መንፈሳዊነት ያደርሳሉ። ይቀጥላል ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን አብሮ ሰራተኛ ቤተሰብ ይሁኑ!!!!! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/acham1583/534 🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕
Mostrar todo...
👑Kingdom Of Heaven Ministry❤️

መንፈሳዊ ስጦታዎች 🔥🔥🧚🧚🔥🔥 ክፍል 41 ✍✍✍ መናፍስትን የመለየት ስጦታዎች 🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣 መናፍስትን የሚለዮ ሰዎች ፈታኞች ናቸው ““ብረት እንደሚፈተን፣ የሕዝቤን መንገድ፣ አካሄዳቸውንም እንድትፈትን፣ አንተን ፈታኝ አድርጌሃለሁ።” — ኤርምያስ 6፥27 (አዲሱ መ.ት) “መንገዳቸውን እንድታውቅና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል ፈታኝ አድርጌሃለሁ።”— ኤርምያስ 6፥27 አገልጋዮች በሶስት መንገድ ይናገራሉ።የመጀመሪያው የእግዚአብሄርን ቃል ከእግዚአብሄር በመስማት ሲሆን ሁለተኛው እግዚአብሄር ሳይናገር የራሳቸውን ሀሳብ የእግዚአብሄር ቃል አድርገው የሚናገሩ ሰዎች ናቸው።ሶስተኞቹ ደግሞ እግዚአብሄር ሳይናገረው ሰይጣን ወደ አእምሮአቸው የሚያስገባውን ሀሳብ እግዚአብሄር የገለጠላቸው አድርገው ወይም መስሎአቸው የሚናገሩ ናቸው።እነዚህ ሶስቱም የእግዚአብሄር አገልጋዮች ሆነው በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው ዳሩ ግን ከመጀመሪያዎቹ ውጪ ያሉት ሌሎቹ የእግዚአብሄር ዕቃ አይደሉም።እንግዲህ መናፍስትን የመለየት ስጦታን መንፈስ ቅዱስ የሰጣቸው ሰዎች አገልጋዮች የሚናገሩበትን መንፈስ በመፈተን ወይም በመለየት አማኞችን ከሰውና ከዲያቢሎስ ቃል የሚጠብቁ ጠባቂዎች ናቸው። “እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውም፤ አልተናገርኋቸውምም። የሐሰት ራእይ፣ ሟርት፣ ከንቱ ነገርንና የልባቸውን ሽንገላ ይተነብዩላችኋል።”ኤርምያስ 14፥14 (አዲሱ መ.ት) ሚኪያስና ሌሎች አራት መቶ ነቢያት ሚኪያስ የእግዚአብሄርን ቃል ሲናገር ሌሎች ግን የሐሰት መንፈስ እንደተጠቀመባቸው ተፆፎዓል። “ሚክያስ ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! ለእርሱ የምነግረው እግዚአብሔር የነገረኝን ብቻ ነው” አለ።”1ኛ ነገሥት 22፥14 (አዲሱ መ.ት) የሐሰት መንፈስ በነቢያቱ ላይ…

መንፈሳዊ ስጦታዎች 🔥🔥🧚🧚🔥🔥 ክፍል 41 ✍✍✍ መናፍስትን የመለየት ስጦታዎች 🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣 መናፍስትን የሚለዮ ሰዎች ፈታኞች ናቸው ““ብረት እንደሚፈተን፣ የሕዝቤን መንገድ፣ አካሄዳቸውንም እንድትፈትን፣ አንተን ፈታኝ አድርጌሃለሁ።” — ኤርምያስ 6፥27 (አዲሱ መ.ት) “መንገዳቸውን እንድታውቅና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል ፈታኝ አድርጌሃለሁ።”— ኤርምያስ 6፥27 አገልጋዮች በሶስት መንገድ ይናገራሉ።የመጀመሪያው የእግዚአብሄርን ቃል ከእግዚአብሄር በመስማት ሲሆን ሁለተኛው እግዚአብሄር ሳይናገር የራሳቸውን ሀሳብ የእግዚአብሄር ቃል አድርገው የሚናገሩ ሰዎች ናቸው።ሶስተኞቹ ደግሞ እግዚአብሄር ሳይናገረው ሰይጣን ወደ አእምሮአቸው የሚያስገባውን ሀሳብ እግዚአብሄር የገለጠላቸው አድርገው ወይም መስሎአቸው የሚናገሩ ናቸው።እነዚህ ሶስቱም የእግዚአብሄር አገልጋዮች ሆነው በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው ዳሩ ግን ከመጀመሪያዎቹ ውጪ ያሉት ሌሎቹ የእግዚአብሄር ዕቃ አይደሉም።እንግዲህ መናፍስትን የመለየት ስጦታን መንፈስ ቅዱስ የሰጣቸው ሰዎች አገልጋዮች የሚናገሩበትን መንፈስ በመፈተን ወይም በመለየት አማኞችን ከሰውና ከዲያቢሎስ ቃል የሚጠብቁ ጠባቂዎች ናቸው። “እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውም፤ አልተናገርኋቸውምም። የሐሰት ራእይ፣ ሟርት፣ ከንቱ ነገርንና የልባቸውን ሽንገላ ይተነብዩላችኋል።”ኤርምያስ 14፥14 (አዲሱ መ.ት) ሚኪያስና ሌሎች አራት መቶ ነቢያት ሚኪያስ የእግዚአብሄርን ቃል ሲናገር ሌሎች ግን የሐሰት መንፈስ እንደተጠቀመባቸው ተፆፎዓል። “ሚክያስ ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! ለእርሱ የምነግረው እግዚአብሔር የነገረኝን ብቻ ነው” አለ።”1ኛ ነገሥት 22፥14 (አዲሱ መ.ት) የሐሰት መንፈስ በነቢያቱ ላይ ገብቶ ሐሰትን ማናገሩ፡1ኛ ነገሥት 22 (አዲሱ መ.ት)¹⁹ ከዚያም ሚክያስ እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ የእግዚአብሔር ቃል የሚለውን ስማ፤ ‘እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፣ የሰማይ ሰራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ፤²⁰ እግዚአብሔርም፣ “በገለዓድ በምትገኘው ሬማት ላይ ዘምቶ እዚያው እንዲሞት፣ አክዓብን ማን ያስተው?” አለ።’ “ታዲያ አንዱ ይህን፣ ሌላውምያን አለ፤²¹ በመጨረሻም፣ ‘አንድ መንፈስ ወጣ፤ ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ፣ “እኔ አስተዋለሁ” አለ።’²² እግዚአብሔርም፣ ‘እንዴት አድርገህ?’ ሲል ጠየቀው። “እርሱም፣ ‘እኔ እወጣለሁ፤ በገዛ ነቢያቱም አፍ ሁሉ የሐሰት መንፈስ እሆናለሁ’ አለ። እግዚአብሔርም፣ “በል እንግዲያው ውጣና አስተው፤ ይሳካልሃል” አለው። በህዝቅኤል ዘመን ትልቅ ችግር የነበረው የራሳቸውን ቃል የራሳቸውን ሀሳብ የእግዚአብሄር ሀሳብና ቃል አድርገው የሚናገሩ ራሳቸውን ነቢይ ያደረጉ ሰዎች ነበሩ። ““የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት በሚናገሩት በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፤ ከገዛ ራሳቸው ትንቢት የሚናገሩትን እንዲህ በላቸው፤ ‘የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤”ሕዝቅኤል 13፥2 (አዲሱ መ.ት) እነዚህ ሰዎች ሞኞች ናቸው።ሰውን እና እግዚአብሄርን የሚያታልሉ የሚመስላቸው ከንቱዎች ናቸው። “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንዳች ነገር ሳያዩ የራሳቸውን መንፈስ ለሚከተሉ ሞኞች ነቢያት ወዮላቸው!” ሕዝቅኤል 13፥3 (አዲሱ መ.ት) እግዚአብሄር ከራሳቸው አመንጭተው ትንቢትን የሚናገሩትን የሐሰት ነቢያት በፍርስራሽ ውስጥ እንደሚኖሩ ቀበሮዎች መሆናቸውን ተናግሯል። “እስራኤል ሆይ፤ ነቢያትሽ በፍርስራሽ መካከል እንደሚኖሩ ቀበሮዎች ናቸው።”ሕዝቅኤል 13፥4 (አዲሱ መ.ት) ሐሰትን ሰዎች ለምን ይናገራሉ? እግዚአብሄር ለሆዳቸውና ለገንዘብ ብለው እንደሆነ ይናገራል። “ዕፍኝ ለማይሞላ ገብስና ለቍራሽ እንጀራ ስትሉ ሐሰትን የሚያደምጥ ሕዝቤን እየዋሻችሁ መሞት የማይገባውን በመግደል፣ መኖር የማይገባውንም በማትረፍ በሕዝቤ መካከል አርክሳችሁኛል።” — ሕዝቅኤል 13፥19 (አዲሱ መ.ት) ቤተክርስቲያንን ለሆዳቸው ከሚያድሩ ሰዎች ወይም አገልጋዮች ለመጠበቅ ሰዎች የሚናገሩበትን መንፈስ በመለየት የሚያገለግሉ መናፍስትን የመለየት ስጦታ የተሰጣቸው ሰዎች ሲኖሩ ነው!!!ጌታ በዚህ ስጦታ ይባርካችሁ!! ይቀጥላል ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ!!! 🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁 https://t.me/acham1583/533 🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕👏👏👏
Mostrar todo...
👑Kingdom Of Heaven Ministry❤️

መንፈሳዊ ስጦታዎች 🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ክፍል 40 ✍✍✍ መናፍስትን የመለየት ስጦታ 🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣 መናፍስትን የመለየት ስጦታ በምድር የሚኖሩ ሰዎችን ከባህሪያቸውና ከድርጊቶቻቸው ተነስተን እንደምለየው የሰውን ውስጣዊ ማንነት በውስጣችን ባለው በሰው መንፈስ አማካኝነት እንደምናውቀው መንፈሳዊውም ዓለም በእግዚአብሄር መንፈስ የሚታወቅ የሚለይ ነው። መንፈሳዊው ዓለም በሁለት ይከፈላል።የእግዚአብሄር አለምና የዚህ ዓለም አምላክ የሆነው የክፋት ሰራዊቶች መንፈሳዊ አለም።የእግዚአብሄር መንፈስ የእግዚአብሄርን አለም ከክፋው ዓለም ለይተን የምናይበትን መንፈሳዊ ዓይን ሰጥቶናል። መናፍስትን መለየት ሲባል ዲያቢሎስ ያለበትን የዲያቢሎስ ስራ ብቻ ማየት ማለት አይደለም ልክ ነው የዲያቢሎስን ስራና አጋንት የተቆጣጠረውን ሰው መለየት አንዱ መናፍስትን መለየት ነው ዳሩ ግን ብቸኛ አገልግሎት አይደለም። መናፍስትን መለየት ማለት የእግዚአብሄርን መገኘት ስራውንና የእግዚአብሄር መንፈስ ያለበትን ከሌለበት መለየት የእግዚአብሄርን መላክና ራሱን የብርሃን መልአክ አድርጎ ከሚለውጠው ክፉ መለየት. መንፈስ ቅዱስ የሞላበትንና የክፉው የሞላበትን በንግግር በእይታ በልዮ ልዮ መንገድ መለየት ነው። መናፍስትን የመለየት ስጦታ ለቤተክርስቲያን እጅግ ጠቃሚ የሆነ ስጦታ ነው።መናፍስትን የሚለይ ሰው በቤተክርስቲያን ውስጥ ካለ በቤተክርስቲያን ውስጥ የኤልዛቤል መንፈስ መሰልጠን አይችልም።ነብይ ሳይሆኑ ነብይ ነን ሐዋሪያ ሳይሆኑ ሐዋሪያ ነን የሚሉ ሰዎች እንደ ልባቸው መፈንጨት አይችሉም። መናፍስትን የሚለዮ ሰዎች መርማሪዎች ወይም ፈታኞች ናቸው። በኤፌሶን ያለችው ቤተ ክርስቲያን የተመሰከረላት በዚህ ነው።“ሥራህን፣ ጥረትህንና ትዕግሥትህን ዐውቃለሁ። ክፉዎችንም ችላ ብለህ እንዳላለፍሃቸው፣ ሐዋርያት ሳይሆኑ ሐዋርያት ነን የሚሉትንም መርምረህ…