cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2

SARIS, AKAKI KALITY

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 818
Suscriptores
-124 horas
+197 días
+11730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሐምሌ 6/2016 ዓ.ም ማስታወሻ ለ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ (NATURAL SCIENCE) ተፈታኝ ተማሪዎቻችን በሙሉ፤ (በጥቂት ማስተካከያ በድጋሜ የተለጠፈ) እስካሁን ትምህርታችሁን እያጠናችሁ ቆይታችኋል። አሁን ደግሞ የደከማችሁበትን ወደ ፍሬ የምትቀይሩበት ወቅት በመሆኑ ይህ ጊዜ ለእናንተ ወሳኝ ነው። በፈተና ወቅት የምታከናውኗቸው ተግባራትም የጥናታችሁን ያህል ውጤታችሁ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው። ስለሆነም በዚህ የፈተና ወቅት ማድረግ ያለባችሁንና ማድረግ የሌለባችሁን ጉዳዮች ጠንቅቃችሁ ማወቅ ይጠበቅባችኋል። ለዚህም እንዲረዳችሁ የሚከተሉትን ምክሮችን ከወዲሁ ተረድታችሁ ለመተግበር ዝግጁ ሁኑ! * የትምህርት ቤታችን የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በሙሉ የወረቀት ተፈታኞች ናችሁ። በዩኒቨርሲቲ የምትቆዩት ከነገ ሐምሌ 7 ጀምሮ እስከ ሐሙስ ድረስ ብቻ ነው። ሐሙስ ሐምሌ ሐምሌ 11 ፈተና እንደጨረሳችሁ ዩኒቨርሲቲ መጥተን ወደ ቤታችሁ እንመልሳችኋለን። ስለዚህ ነገ ስትመጡ የምትይዟቸው ነገሮች በጣም ጥቂት የተፈቀዱ ነገሮች ብቻ መሆን አለባቸው። እነዚህም አንሶላ፣ የትራስ ልብስ፣ ብርድ ልብስ፣ ሌሊት የምትለብሱት ቅያሪ ቲሸርት፣ እርሳስ፣ መቅረጫ፣ ደረቅ ምግቦች (ቆሎ፣ ዳቦ ቆሎ ፣ ኩኪስ ሊሆን ይችላል)። በፈተና ቀናት ሁሉ የደንብ ልብስ ለብሳችሁ ስለምትፈተኑ ተጨማሪ ልብስ ያን ያህል አስፈላጊም አይደለም። * በፈተና ዋዜማ ከሚረብሹ ነገሮች ራስን ማራቅ ያስፈልጋል። ሀሳባችሁን ሊሰርቁ ከሚችሉ ማኅበራዊ ሚዲያዎች( ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያለ DSTV ሊሆን ይችላል) መራቅ ይገባችኋል። በዚህ ወቅት ትኩረታችሁን ፈተናችሁ ላይ ብቻ አድርጉ። * በቂ እንቅልፍ ተኙ። በፈተና ዋዜማ ለማንበብ ብላችሁ በፍጹም አታምሹ። በዚህ ቀን ተጨማሪ ሰዓት ከማንበብ ይልቅ ተጨማሪ ሰዓት መተኛት የተሻለ ዉጤት አለው። በቂ እንቅልፍ አለመተኛት በፈተና ወቅት ለድብርትና ለራስ ምታት ሊዳርግና ሥራችሁን ሊያበላሽ ይችላል። ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ብዙ ቡና አለመጠጣት፤ እና ሌሎች አነቃቂ ነገሮችን አለመውሰድ ይመከራል፤ * ጠዋት ማልዶ መነሳት: በጊዜ ተነስቶ መዘጋጀት ከመቻኮል ጋር ተያይዞ ከሚመጣ መታወክ ያድናል። በተጨማሪም ወደፈተናው አዳራሽ በጊዜ ለመድረስ ያስችላል፤ * ቁርስ በአግባቡ መብላት:  ቀለል ያሉ ምግቦችን ተመግባችሁ መሄድ ይኖርባችኋል። *  ወደ መፈተኛ ቦታው ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት በፊት ቀድሞ መድረስ ያስፈልጋል። ይህም ለመረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው፤ * ከቤት ስትወጡ የጽሕፈት መሳሪያዎቻችሁንና የመታወቅያ ካርዳችሁን መያዛችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ይህም ከመንገድ ከመመለስና ከማርፈድ ያድናችኋል። ትርፍ እርሳሶችን እና የእርሳስ መቅረጫዎች መያዝ በጣም አስፈላጊ ነው፤ * ወደ ፈተና አዳራሽ ከመግባት በፊት ወደ መፀዳጃ ቤት መሄድ መልካም ነው። ምናልባት የፈተናው ሰዓት ረዥም ቢሆንና ሽንት ቢይዛችሁ መጨናነቅን ያመጣል። አቋርጣችሁ መውጣት ላይፈቀድላችሁ ይችላል፤ * የመልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ስማችሁን በአግባቡ መጻፋችሁን እርግጠኛ ሁኑ። * የፈተና መመሪያዎችን (instructions) በአግባቡ ማንበብና መተግበር ያስፈልጋል። በእያንዳዱ ፈተና ወረቀት ላይ ወይም የፈተናው ክፍሎች ላይ የሚሰጡትን መመሪያዎች በአግባቡ ማንበብና መተግበር ይኖርባችኋል፤ * አትደንግጡ! በፍጹም መረጋጋት ፈተናችሁን መስራት አለባችሁ። ፍርሃት የተዘጋጃችሁበትን እንኳን በአግባቡ እንዳትሰሩ ያደርጋል። * መልስ መመለስ ከመጀመራችሁ በፊት እያንዳንዱ የፈተና ክፍል ስለያዛቸው የጥያቄ አይነቶች ገረፍ ገረፍ እያደረጋችሁ ብታዩ መልካም ነው። ይህም የተሰጣችሁን ሰዓት በጥያቄው ክብደት ልክ ከፋፍላችሁ ለመጠቀም ያግዛችኋል፤ * አንዱ ጥያቄ ከከበዳችሁ ዝለሉት፤ አንድ ጥያቄ ላይ ተጠምዳችሁ ብዙ ጊዜ የምታጠፉ ከሆነ ቀጥለው ለሚጠብቋችሁ ጥያቄዎች ጊዜ ሊያጥራችሁ ይችላል። ስትዘሉት ግን የጥያቄ ወረቀቱ ላይ ምልክት ማድረጋችሁን  አትርሱ ፤ * ከፈተና ክፍል ቶሎ ለመውጣት አትቸኩሉ፤ ምንም አይጠቅማችሁም፤ ሰዓታችሁን አሟጥጣችሁ መጠቀማችሁን፤ ሁሉንም ጥያቄዎች በአግባቡ መመለሳችሁንና ማጥቆራችሁን አረጋግጡ። ጊዜ ቢተርፋችሁ ጥያቄዎቹን ለመከለስ ተጠቀሙበት፤ * ያልገባችሁ ማንኛውንም ነገር ( ከፈተና ጥያቄ ውጭ) ሲኖር ፈታኞችን ለመጠየቅ አትፍሩ ፤ * ልክ የፈተና ወረቀቱን ከመለሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የዚያ ትምህርት (subject) ነገር ማብቃቱን በመገንዘብ ለቀጣዩ ፈተና እራስን ማዘጋጀት ይገባል እንጂ ስላለፈው ፈተና እያሰላሰሉ መጨነቅ ለቀጣዩ ፈተና በምታደርጉት ዝግጅት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል። * መልካም ሥነ ምግባር መላበስ፦ የተለያዬ አይነት ባሕሪ ያላቸው ሌሎች ተማሪዎች፣ ፈታኝ መምህራን ጭምር ሊያጋጥሙ ይችላሉ። ሁሉንም ጉዳዮች በትሕትና እና በመልካም ሥነ ምግባር ማሳለፍ የግድ አስፈላጊ ነው። በማኅበራዊ ሳይንስ ፈተና ላይ እንደታዘብነው አንዳንድ ተማሪዎች ሌላው ተማሪ ተረጋግቶ እንዳይተኛና ፈተናውን በአግባቡ እንዳይሰራ በመጮህና በመረበሽ፣ ወዳልተመደቡበት ማደሪያ ክፍል በመሄድ፣ ድንገት ከተዋወቋቸውና ሥነ ምግባር ከጎደላቸው ሌሎች ተፈታኞች ጋር በመጣመር ተገቢ ያልሆነ ተግባር ውስጥ የተሳተፉ ተማሪዎች ተገኝተዋል። ይህ ሁኔታ በተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ላይ ፈጽሞ መታዬት የለበትም። አጥፊ ተማሪዎችን ለይቶ መምከርና መገሰጽ ከሁላችሁም ይጠበቃል። የፈተና ወቅት የነገር ሁሉ ፍጻሜ አይደለም። ወደሚቀጥለው የሕይወታችሁ ምዕራፍ መሸጋገሪያ በመሆኑ የምትችሉትን ሰርታችሁ በሰላምና በምስጋና መመለስ አለባችሁ። ስለዚህ የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎቻችን ከላይ የጠቀስናቸውን ጉዳዮች በመተግበር ውጤታማ እንድትሆኑ እንመክራለን። 🍀ነገ በሰዓቱ እንገናኝ! መልካም ፈተና🍀      
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ከሁለት ልጆቻቸው ጋር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱት አይበገሬዋ እናት ** ሰሞኑን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተፈተኑት ጠንካራ እናት ይገኙበታል። ወ/ሮ መይረም ኢስማኢል አሊ ከአፋር ዞን ሁለት፣ ዳሎል መሰናዶ ትምህርት ቤት ነው ከሴት ልጃቸው ጦይባ አብደላ መሀመድ እና ከወንድ ልጃቸው ኢብራሂም አህመድ ሀሰን ጋር ወደ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ያቀኑት። አይበገሬዋ እናት የህይወት ስንክሳር ሳያሸንፋቸው በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናቸውን በስኬት ወስደው አጠናቅቀዋል። (መረጃው የ EBC ነው)
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ከሁለት ልጆቻቸው ጋር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱት አይበገሬዋ እናት ** ሰሞኑን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተፈተኑት ጠንካራ እናት ይገኙበታል። ወ/ሮ መይረም ኢስማኢል አሊ ከአፋር ዞን ሁለት፣ ዳሎል መሰናዶ ትምህርት ቤት ነው ከሴት ልጃቸው ጦይባ አብደላ መሀመድ እና ከወንድ ልጃቸው ኢብራሂም አህመድ ሀሰን ጋር ወደ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ያቀኑት። አይበገሬዋ እናት የህይወት ስንክሳር ሳያሸንፋቸው በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናቸውን በስኬት ወስደው አጠናቅቀዋል። (መረጃው የ EBC ነው)
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
00:34
Video unavailableShow in Telegram
36.77 MB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.