cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Rēyhan tube

Aselamu aleykum It is reyhan tube . Created to announce what islam preaches about things like happiness , success and oneness . ♥Islam is the only solution !♥ be a member ! weselamu aleykum

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
616
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Mostrar todo...
ትዳራችን በአንዱ ልጃችን ምክንያት ሊፈርስ ነው

ሁለተኛ ጋብቻ ላይ የሚፈጠር የተለመድ ችግርን የሚዳስስ ጥያቄ ነው

Mostrar todo...
አይደለም የወደፊቱን ቆሜ ላልም ይቅርና የዛሬውን እራሱ መኖር አስጠልቶኛል።ህይወት ከባድ የፈተና መድረክ ነች ሰዎች ደግሞ ተፈታኞቹ!!! የሩቅ ሰው ጭረት ሲያሳርፍብህ የቅርብህ ሰው ግን ያቆስልሃል።አዕምሮ የማሰብያው ልክ ያህል ያስብና ይደክማል።ነገን አሻግሮ ማለም ይሳነዋል።ያን ግዜ ነፍስ ከመኖር መሞትን ትመርጣለች።የነገሮችን ሁሉ ከንቱነት ታስባለህ።የመኖርህ ሚስጥር የመገኘትህ ዓላማ ግር ይልሃል።ህይወት አዙሪት ነች።ጊዜ ተገለባባጭ ነው። ቀን አልፎ ቀን ይተካል ደቂቃዎች ተቆጥረው ሰዓት ይመጣል።አላልፍ ብሎ የታየህ ጥቁሩ ጨለማን ፍንጥቅጥቅ ያለች ፀሀይ ታባርረዋለች።የምታልመውን ደስታ ያገኘኸው ይመስልሃል።እስትንፋስህ ሙሉ ይሆናል።ህይወት ታጓጓሃለች።እያንዳንዳንዷን ቅፅበት የምታልመው ሌላ ጣፋጭ እስትንፋስ ለመሳብ ይሆናል።አዕምሮህ ማስተንተኑን ቀጥሏል።ዙርያህ ያሉት ነገሮች ሁሉ በምክንያት እንደተፈጠሩ ገብቶሃል።ድንገት ቀና ብለህ ሰማዩን ስትመለከት ሰማያዊ ጥርት ያለ ከእንከን የፀዳ፤ ያለምሶሶ የቆመ ድንቅ ተዓምራዊ ጣራ  መሆኑን ትገንዘባለህ።ከሰማዩ ዝቅ ብለው የሚያንዣብቡት አዕዋፋት ለሰማዩ ድምቀት ሰጥተውታል።በዙርያህ ያለው ለምለሙ ምድርና ረጋ ብሎ የሚነፍሰው ንፋስ ምድር እራሷ ገነት ነች ብለህ የማሰብ እድሉን ሰጥቶሃል።ከሰዎች ጋር ያለህ ማህበራዊ ህይወትህ ተስተካክሎ ጣፋጭ ሆኗል።ይህን ሁሉ ደስታ ያገኘኸው ግን በተለየ ቁሳዊ ነገር አደለም።በገንዘብም አይደለም።የነበርክበትን ቦታም ስለቀየርክ አልቀየርክም።ብቻ አንድ ነገር አርገሃል።ከነበርክበት መጥፎ ስሜት አውጥቶ ውስጥህን ሰላምና ደስታን ሰጥቷታል።ከነበርክበት ብቸኝነት ስሜት አውጥቶ ብቻህን እንዳልሆንክ እንድትረዳ አርጎሃል።ዓላማ ቢስ የዋዠቅክ የነበርከውን ሰው አንስቶ የዱንያም የአኺራም ዓላማህን አስታውሶሃል።አላህ አንተን ወዶሃል ዙርያህ ያሉት ፍጡሮችም እንዲወዱህ አድርጓል። እሱም ዚክሩላህ(አላህን በተደጋጋሚ ማስታወስህ ብቻ ነው።) الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ (እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ #ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡13፥28 አንድ ታላቅ ዓሊም እንዲህ ይላሉ፦ዱንያ ውስጥ ጀነት አለች ይቺን ጀነት በዱንያ ሳለ ያልገባ ሰው የአኺራዋንም ጀነት አይገባም። ልቦቻችንን አላህን በማስታወስ እናፅዳቸው።ምክንያቱም ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልቦች ይዝጋሉ ብለውናልና። መልካም ጁምዓ ሰለዋትም እንዳትረሱ አህባቢ😍 ✍محمد عرب BY>> @theamazingquran @theamazingquran
Mostrar todo...
#አንድ ጀርመናዊ ሙስሊም ምሁር ስለ ሽብርተኝነት እና ኢስላም ግንኙነት ሲጠየቅ እንዲ አለ፦ "የመጀመሪያውን የዓለም ጦርነት የጀመረው ማን ነው? ሙስሊሞች አይደሉም !! ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የጀመረው ማን ነው? ሙስሊሞች አይደሉም !! 6 ሚሊዮን አይሁዶችን የጨፈጨፈው ማን ነው? ሙስሊሞች አይደሉም ፡፡ በአውስትራሊያ ውስጥ ወደ 20 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ አቦርጂኖችን የገደለው ማነው? ሙስሊሞች አይደሉም !! ማነው ሄሮሺማ እና ናጋሳኪን ላይ የኑክሌር ቦንቦችን የላከው?? ሙስሊም አይደለም !! በሰሜን አሜሪካ ከ 100 ሚሊዮን በላይ ሕንዳውያን ማን ገደላቸው? ሙስሊሞች አይደሉም !! በደቡብ አሜሪካ ከ 50 ሚሊዮን በላይ ሕንዳውያን ማን ገደላቸው? ሙስሊሞች አይደሉም !! ወደ 180 ሚሊዮን ገደማ አፍሪካውያን ሰዎች እንደ ባሪያ አድርጎ የጨቆነው ከነዚህም 88% የሚሆኑት ሞተው ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የጣለው ማነው? ሙስሊሞች አይደሉም !! አይደሉም!!! ሙስሊሞች አይደሉም !! በመጀመሪያ ፣ ሽብርተኝነትን በትክክል መግለፅ ይጠበርቅባችኋል ሙስሊም ያልሆነ መጥፎ ነገር ከፈፀመ ወንጀለኛ ይባላል። ግን አንድ ሙስሊም ተመሳሳይ ነገር ከፈፀመ እሱን አሸባሪ ትሉታላችሁ። ስለዚህ መጀመሪያ ይህንን ሁለቱን የተዛቡ ደረጃዎች አስወግዱ ከዛ ወደ ነጥቡ መምጣት ትችላላችሁ። እኔ ሙስሊም በመሆኔ እኮራለሁ !! አልሃምዱሊላሂ ዓላ ኒዕመቲል ኢስላም👍 ሼር አርጉ አህባቢ👇👇 By>>@theamazingquran @theamazingquran
Mostrar todo...
👍 17
🎬የሚያደንቁት ዘፋኝ ማንን ነው? | አንድ ነጥብ በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን || One Point | Sheikh Mohammed Hamiddin •HD
Mostrar todo...
የሚያደንቁት_ዘፋኝ_ማንን_ነው_አንድ_ነጥብ_በሸይኽ_ሙሐመድ_ሓሚዲን_One_Point_She_134.mp413.27 MB
🎬የሚያደንቁት ዘፋኝ ማንን ነው? | አንድ ነጥብ በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን || One Point | Sheikh Mohammed Hamiddin •HD 1.1MB only
Mostrar todo...
file_86304.mp4_m2vbot_681208139.opus1.13 MB
አቡ ሁረይራ (አላህ መልካም ስራውን ይውደድለት) እንዳስተላለፈው ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ፦ፀሀይ ከወጣችበት ቀን ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው።በሷ(በጁምዓ) አደም ተፈጠረ በሷ (በጁምዓ) ቀን ጀነትን ገባ በሷ (በጁምዓ) ከጀነት ተባረረ። ☘ሙስሊም ዘግበውታል وعن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: ((من توضأ فأحسن الوضوء ثم أتى الجمعة، فاستمع وأنصت، غفر له ما بينه وبين الجمعة وزيادة ثلاثة أيام، ومن مس الحصى، فقد لغا)). رواه مسلم. አቡ ሁረይራ (አላህ መልካም ስራውን ይውደድለት) እንዳስተላለፈው ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦መልካም ዉዱዕን ያደረገ ከዚያም ወደ ጁምዓ የሄደ ፀጥ ብሎ ኹጥባ ያዳመጠ አሁን ባለውና በሚቀጥለው ጁምዓ መሃከል ያለው ወንጀሉ ይማርለታል 3 ቀንን ጨምሮ(ማለትም የ10 ቀን) ጠጠርን የነካካ በርግጥ መጥፎ ተግባርን ፈፅሟል። ☘ሙስሊም ዘግበውታል قوله: ((وزيادة ثلاثة أيام))، لأن الحسنة بعشر أمثالها. 3 ቀንን ጨምሮ ይማርለታል መባሉ ምክንያቱም አንድ ሀሰና እስከ 10 በመያዟ ነው። وقوله: ((من مس الحصى فقد لغا)) أي: ومن لغا فلا جمعة له. #ጠጠርን የነካካ መጥፎ ተግባርን ፈፅሟል ማለትም በሆነ ነገር መጫወት እንቅቅስቃሴ የሚያበዛ የጁምዓ አጅር የለውም #ከሀዲሱ ኹጥባ በሚደረግ ጊዜ አለማውራት ልክ ሰላት ላይ እንደለን ሆነን መከታተል እንዳለብን እንማራለን
Mostrar todo...
. ▪️ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ 33፥56 አውስ ኢብኒ አውሲን ረ.ዐ እንዳስተላለፉት ረሱልﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ከቀናቶቻችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው።በእኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ።ሰላዋቶቻችሁ እኔ ዘንድ ይቀርቡልኛል። 📚አቡዳውድ ዘግበውታል በዚህ ሃዲስ በጁምዓ ቀን ላይ በነብዩ ላይ ሰለዋትን ማብዛት መወደዱን እንማራለን። اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ ሰሉ አለ ነቢይ😍😍
Mostrar todo...
_️ጁሙዓ_ነው_ሰለዋት_እናብዛ_اللهم_صل_على_محمد_وعلى_آل_محمدﷺ_134.mp48.73 KB
🎬ትፀፀታለህ!!! በጌታዬ ይሁንብኝ ሰላትህን በመተውህ ትፀፀታለህ..... #የሼኽ ኻሊድ አል ራሺድ ትርጉም ዳዕዋ ◉ትርጉም ኢብኑ ኸልዱን ○ድምፅ ሰላህዲን አሊ #ሼር_ማድረግ_እንዳይረሱ ይቀላቀሉን @reyhan1617
Mostrar todo...
ትፀፀታለህ_እስቲ_እንከታተል.133.mp49.60 MB
🎬ትፀፀታለህ!!! በጌታዬ ይሁንብኝ ሰላትህን በመተውህ ትፀፀታለህ.... #የሼኽ ኻሊድ አል ራሺድ ትርጉም ዳዕዋ ◉ትርጉም ኢብኑ ኸልዱን ○ድምፅ ሰላህዲን አሊ #ሼር_ማድረግ_እንዳይረሱ ይቀላቀሉን @reyhan1617
Mostrar todo...
file_85301.mp4_m2vbot_681206686.opus6.30 KB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.