cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የኢቅራ መስጂድ ጀመዓ

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
189
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሴቶች ከበፊት ጀምረው በመሠረቱ በአለባበሳቸው የተሰተሩ ነበሩ። ንግስት ሰበእ በሱለይማን ቤተ መንግስት በገባች ጊዜ ወለሉ ላይ ውሃ ያለ መስሏት እንዳይነካት ልብሷን ከእግሯ ከፍ አደረገች መባሉ፤ እስከ ታች ድረስ የተሸፈነች መሆኑን የሚያሳይ ነው። ታዲያ አንቺ የነቢዩ ኡማ ሆነሽ የምትገላለጭው እህቴ ሆይ! ምን ነክቶሽ ነው? ከሴትነት መሠረታዊ ጉዳዮች እየተቃረንሽ ነው'ኮ! 🔸 ‏قال ﷲ ﷻ : { قيل لَهَا ادخُلِي الصَّرحَ فَلَمّا رَأَتهُ حَسِبَتهُ لُجَّةً وَكَشَفَت عن ساقَيها } . ✍ قال ابن عثيمين - رحمه الله - : " المرأة مِن قديم الزمان شيمَتُها التَّسَتُّر لأنَّ قوله: (وَكَشَفَت عَن ساقَيها) دليلٌ على أنَّ الأصل أنَّها مَستورة ". 📗 تفسير سورة النمل ( 248 ) . (قِيلَ لَهَا ادْخُلِي الصَّرْحَ ۖ فَلَمَّا رَأَتْهُ حَسِبَتْهُ لُجَّةً وَكَشَفَتْ عَن سَاقَيْهَا ۚ قَالَ إِنَّهُ صَرْحٌ مُّمَرَّدٌ مِّن قَوَارِيرَ ۗ قَالَتْ رَبِّ إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِي وَأَسْلَمْتُ مَعَ سُلَيْمَانَ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ) «ሕንጻውን ግቢ ተባለች፡፡ ባየቺውም ጊዜ ባሕር ነው ብላ ጠረጠረችው፡፡ ከባቶችዋም ገለጠች፡፡ «እርሱ ከመስተዋት የተለሰለሰ ሕንጻ ነው» አላት፡፡ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩ» አለች፡፡» [አል-ነምል: 44]
Mostrar todo...
«#ይህችን_ሴት_አትሁኝ . 1. በቴሌግራም ሀይ አለሽ 2. ሳትመልሺ ወደ profilu አቀናሽ 3. አለባበሱም ሆነ አቁዋሙ ያምራል 4. በድጋሜ ሀይ አለሽ 5. አሁን ግን በደስታ መለሽለት 6. መልክት መለዋወጥ ተጀመረ.. 7. በአካል ለመገናኘት ቀጠሮ ተያዘ 8. ጥሩ ልብስ ለበሰሽ ሽቶ ተቀብተሽ አምሮብሸ ሄድሽ 9. ወድ የሆነ መዝናኛ ቦታ ወሰደሽ 10. ጥሩ የምትሉት ጊዜ ማሳለፍ ጀመራቹ 11.… በቀልዱ ያስቅሻል 12. … ፈገግታ ይመግብሻል 13. ብዙ ትውውቅ ያላቹ ያህል ተሰማሽ 14. ክፍል እንድትይዘ ጠየቀሽ ተስማማሽ 15. ምቾት እንዲሰማሽ አደረገ 16. … 17. ትክክል አለመሆኑ ቢገባሽም ደስታ ተሰምቶሻል 18. … 19. ለመቃወም አቅሙን አጣሽ 20. ሌላዉ ቢቀር መከላከያ ለመጠቀም ሀሳብ አቀረብሽ 21. ሊሰማሽ አልቻለም 22. ነገሩን ወደድሽው 23. ከፍሪጅም ቀዝቃዛ ዉሀ አምጥቶ እራሱ አጠጣሽ 24. የሚያሳይሽ ክብር እጅጉን ማረከሽ 25. ራስሽን እድለኛ አርገሽ ቆጠርሽ 26. የምትፈልጊውን ወንድ እንዳገኘሽ ተሰማሽ 27. ልብሰሽን ለባበስሽ 28. ወደ ቤት ሸኘሽ 29. … የደሰታ ጊዜ ማሳለፉን ገለፀልሽ 30. ለጉዞሽም ገንዘብ በእጅሽ አስጨበጠሽ 31. ከልብሽ ፈገግ በማለት ነገ እንገናኝ አልሽው 32. እሱ ግን መልስ አልሰጠሽም 33. በደስታ ፈገግ እንዳልሽ ተጉዘሽ እቤት ደረሰሽ 34. በሰላም እቤት እንደደረሽ ሜሴጅ ላክሽለት 35. online ቢሆንም መልስ አልመለሰልሽም 36. ግራ ተጋብተሽ ድጋሜ ፃፍሺለት 37. አሁንም መልስ የለም 38. ከደቂቃዎች ብሀላ ስታይው ቴሌግራም ላይ ብሎክ ተደርገሻል 39. ብሎክ መደረግሽ ታወቀሽ 40. ቀናት ሳምንት ወራት አለፉ 41. ህመም ይሰማሽ ጀመር ድካም ክብደት መቀነስ.. 42. ወደ ሆስፒታል በመሄድ ምርመራ አደረግሽ 43. ከቆይታ ቡሀላ ነርሶ ውጤት ይዛ መጣች 44. HIV ፖዘቲቭ እና እርጉዝ እንደሆንሽ ተነገረሽ 45. እንዴት??? 46. ከእውነቱጋ ተጋፈጥሽ 47. ጭንቀት ነገሰብሽ በፍርሀት ተዋጥሽ 48. ተስፋ ቢስነት ስሜት አልባነት ተሰማሽ 49. ሞት ወደ አንቺ መቃረቡ ተሰማሽ 50. ሁኔታዎች ወደ ኃላ ተመልሰው ብታድሻቸው ተመኘሽ 51. ግን ምን ዋጋ አለው እረፍዶል 52. ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ ፀሎት አደረስሽ! • ይህችን ሴት አትሁኝ • በስሜት አትመሪ • በሀብት በንዋይ ሰውን አትመዝኚ • ሴት ልጅሽ እንድትሆንልሽ የምትመኚውን አይነት ሴት ሁኚ» منقول
Mostrar todo...
👑አንድት ሴት ከመገላለጥ👑 💍 ትጠንቀቅ 💍 መነበብ ያለበት ✍🏻 አንቺ ውዷ እህቴ ሆይ ዛሬ ላይ ብዙሃን ሴቶች እያደረጉት ያለው ድርጊት ከትልልቅና አፀያፊ ወንጀል ተደርጎ ይወሰዳል፦ ከቤታቸው ሌሎችን አማላይና ለራሳቸው የማለሉ ሆነው ተቀባብተው ተውበው መውጣታቸው ትልቅ የፊትና በር ከፋቾች ሆነዋል። ➖ ያም ጌጥን ውበትን መገላለጥ ሸቶ መቀባባት የተላያዩ ፈታኝ የሰውነት ክፍሎችን ማሳየት ወንዶችን መቀላቀል ይህ አስቀያሚ ድርጊት ይፈፅማሉ በራሳቸውም ላይ የአሏህን ቁጣ ያረጋግጣሉ። ◽قال الله تعالى: - (وَمَا ظَلَمْنَاهُمْ وَلَٰكِن ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ٍۖ ) هود (101) ◽ አሏህ እንድህ አለ፦ 【እኛ አልበደልናቸውም ነገር ግን እነሱ እራሳቸውን በደሉ።】 ሱረቱል ሁድ [101] ◽ والله عز وجل يقول : " وَقَرْنَ فِي بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ الْجَاهِلِيَّةِ الْأُولَى " [سورة الأحزاب، الآية : 33]. ◽አሏህ እንድህ አለ፦ ((ቤታችሁ ተቀመጡ የቀደምት የመሀይማንን አገላለጥ አትገላለጡ))። ሱረቱል አህዛብ [33] ◽ ويقول سبحانه : " وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ " [سورة النور، الآية : 24]. ◽ሉኡሉ ጌታችን ይላል፦ ((ጌጣቸውን ግልፅ አያድርጉ)) ሱረቱ ኑር [24] 📋وقال النبي صلى الله عليه وسلم «صنفان من أهل النار لم أرهما : قوم معهم سياط كأذناب البقر يضربون بها الناس، ونساء كاسيات عاريات مائلات مميلات رءوسهن كأسنمة البخت المائلة، لا يدخلن الجنة ولا يجدن ريحها، وإن ريحها ليوجد من مسيرة كذا وكذا» 📙 رواه مسلم وغيره 📋 የአሏህ ነብይ እንድህ አሉ፦ «ሁለት አይነት ሰዎች የእሳት ናቸው አሁን አላያቸውም ፤ ሰዎች ናቸው ከነሱ ጋር ሰዎችን የሚደበድቡበት የከብት ጅራት መሰል አለንጋ ያላቸው ፣ እናም ለብሰው ያለበሱ ለራሳቸው የሚማልሉ ሌሎችንም የሚያማልሉ ሴቶች ናቸው ፀጉራቸው እንደተዘነበለ ግመል ሻኛ ነው ጀነት አይገቡም ሽታዋንም አያገኙም…።» ሙስሊምና ሌሎችም ዘግበውታል 💢 አንድት ሙስሊም የሆነች ሴት ጠባብ ዘርዛራ የሰውነት ቅርፅን ከሚያሳይ የሰውነትን ውበት ከሚያጋልጥ ልብስ መራቅ ይኖርባታል። ➖ እንድሁም ከመሰባበር ድምፅን ከማቅለስለስና በአካሄድ ሰዎችን ከመፈተን ልትጠነቀቅ ይገባታል። ➖ ከራሷ ላይ ሂጃብ ማንሳት ከደረት ከክንድ ከባት መሰል የሰውነት ክፍሎችን መግለጥን ትጠንቀቅ። ◼ ጋጠ ወጥ የሆኑ ሴቶች የሚለብሱትን አይነት አጫጭር ልብስ ከመልበስ ልትጠነቀቅ ይገባታል። ይህ አሏህ እርም ክልክል ካደረገው ነገር ስለሆነና እንድሁም ለአደገኛ ፊትና ስለሚያጋልጥ። 📋قال العلامة ابن باز رحمه الله : 💢فالواجب الحذر من ذلك، والمرأة عورة وخطرها عظيم على نفسها وعلى غيرها، فالواجب عليها أن تكون بعيدة عن أسباب الفتنة بالتحجب ولبس الجلباب الذي يسترها ... 📋 ኢማም ኢብኑ ባዝ አሏህ ይዘንላቸው እንድህ ነበር ያሉት፦ 💢 «ግዴታው ከዚህ ልትጠነቀቅ ነው ፣ ሴት ሰውነቷ በሙሉ ሃፍረተ ገላ ነው ፣ አደጋዋም በራሷም ሆነ በሌሎች ላይ የከፋ ነው ፣ ግደታው እሷነቷን ልሸፍን የሚችለውን ጅልባብ በመልበስ ከፊትና ምክናየቶች የራቀች ልትሆን ነው…።» ◼ ሴት ሰውነቷ በሙሉ ሊገለጥ የማይገባው ሃፍረተ ገላ ነው ወደ ሱቅ ስትወጣ ሸይጧን ይክባታል። ➖ ለዚህም ልትሸፈንና ሂጃቧን አጥብቃ ልትይዝ ይገባታል ይህ የሰላም ምክናየት ስለሆነ። ◽ والله يقول سبحانه في كتابه العظيم: (وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَاعًا فَاسْأَلُوهُنَّ مِنْ وَرَاءِ حِجَابٍ ذَلِكُمْ أَطْهَرُ لِقُلُوبِكُمْ وَقُلُوبِهِنَّ )[الأحزاب:53]، ◽አሏህ በተከበረው ቃሉ እንድህ አለ፦ 【እቃን ስትጠይቁ ከመጋረጃ ጀርባ ሆናችሁ ጠይቁ ይህም ለናንተም ሆነ ለነሱ ልብ ንፅህና የተሻለ ነው።】 ሱረቱል አህዛብ [53] እህቴ በመሸፈንሽ የሌሎችንም የራስሽንም ልብ ከተለያዩ በሽታዎች ትጠብቂያለሽ። እህቴ አሏህ ይዘንልሽ እነዚያ ምርጥ ቆነጃጅት የነብዩ ምርጥ የነብዩ ባልደረቦች የነበሩት ጀግና ሴቶችን ሞደል አድርጊ ፤ እነዚህ ዛሬ ላይ ክብራቸውን ማንነታቸውን አርግፈው የጣሉ ክብራቸው መደፈሩ የማያሳስባቸው የዝንብ መዋያ የሆኑ ሴቶች እስታይል እንዳይሸውድሽ ስልጣኔ መስሎች የስልጣነውን ማማ የስልጣነውን ሰገነት አውልቀሽ አልሰለጠነው አውሬነት እንዳትመለሽ። #ጥቅሙ ለራስሽ ነዉ እህቴ ምክንያቱም አእምሯቸዉ መጥፎ የሚያስብ ሰዎች እንደ ዝንብ ለወሩሽ ይችላሉ። ማለትም አንቺ ላይ ጉዳት ለማድረስ ይህን መጥፎ የሆነ አለባበስ በምትለብሽ ጊዜ ማለት ነዉ። ## ስለዚህ እህቴ እስልምና ሴትን አይጨቁንም እንዳዉም አለባበስሽን በማስተካከል ነጻነት ተሰምቶሽ እንድትኖሪና እንዲሁም ክብርሽን እንድትጠብቂ ያደርግሻል። የነበባቹህ በሙሉ ሼር የሴት ልጅ መስተካከከል ለኢስላም ኡማ ቁልፍ ነዉ ለሂዳያ ስበብ አንሁን ለወድ እህቶቼ አድርሱልኝ SHARE 🔗SHARE ╔════════════╗ ☪ JOIN: @yasin_nuru         ☪ ☪ JOIN: @yasin_nuru         ☪   ╚════════════╝
Mostrar todo...
ወንድም እህቶቼ ለምን ለሀይማኖታችን ቦታ አንሰጥም? እኛ የተፈጠርነው እኮ አምሳያ የሌለውን ብቸኛውን አምላካችንን አንድንገዛ ነው ! እስኪ ደሞ የኛን ሁኔታ መለስ ብለን እንመልከት እህቴ አለባበስሽ እውነት አላህ ባዘዘሽ መልኩ ነው? ወንድሜስ እስኪ አዋዋልክን ተመልከት። በእህትክ ወይ በ እናትክ ላይ እንዲፈፀም ማትፈልገውን ነገር ለምን በ ሙስሊም እህትክ ላይ ትፈፅማለክ። እህቴስ ለምን ወንድምሽን ትፈትኛለሽ! ለምን አላህን አንፈራም? ሁላችንም እኮ በሰራነው ነገር ነገ የውመል ቂያማ ተጠያቂዎች ነን። ለምን ሞትን አናስታውስም? ለምን ቂያማን አናስታውስም? አው ለምን የ ቂያማን ቀን አናስውስም? ያን ቀን እኮ አካላችን በሙሉ እኛ ለይ ይመሰክራሉ። ወንድም እህቶቼ በ እጃችን ምንድን ምንሰራው? ስልኮቻንስ በምንድነው የተሞላው? በስልካችንስ ምንድነው ምንሰማው? ምንድን ምናየው? በ እግሮቻችንስ የት ነው ምንሄደው? ወደ መስጂድ? ወይስ ወይስ ካልተፈቀደልን ሰው ጋር ነው ጊቢውን ምንዞረው? #ተው ግን አላህን እንፍራ።። #እውነት ነብያችንን እንወዳለን???? ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እኛን ለማየት ይናፍቁ ነበር እኛ ግን አለባበሳችን ፣ አነጋገራችን ፣ አዋዋላችን አረ እንደውም ሁሉ ነገራችን ከነሱ ተቃራኒ ሆኖዋል እኮ። ታዳያ ለምን እንወዳቸዋለን ብለን ምንሞግት ከሆነ ለምን ያዘዙንን አንታዘዝም? ከከለከሉን ነገርስ ለምን አንከለከልም? እውነት አላህን ምንወድ ከሆነ ረሱልን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንድንከተል አላህ አዞናል።። ወዳጅ እኮ ለሚወደው አካል ታዛዥ ነው! አውነት ነቢዩን ምንወድ ከሆነ እስኪ ያዘዙንን እንታዘዝ የከለከሉንንም እንከልከል።።። በተለይ አዲስ ተማሪዎች አላህ አኮ ለ ሊትን የፈጠረልን በውስጡ እንድናርፍ ነው። ታዲያ ለምን ከሰው መደበቂያ እናደርገዋለን? አሁን እዚህ ቤተሰቦቼ የሉም ደግሞም ጨለማነው እያልን ለምን ከሙስሊም የማይጠበቅ ነገር እንሰራለን? ያ ከሱ ምንም የማይደበቀው አምላካችን እያየን እንደሆነ ረስተነው ከሆነ ይሀው አኔንም እናንተንም አሁን ላስውሳቹ። ማስታወስ ለምእመናን ይጠቅማልና! እባካችሁን ወደ አላህ እንመለስ። ያ ወደሱ ለተመለሱት ወንጀልን ወደሚምረው! ጊዜ የለንም ብላችሁ እባካችሁን #### #ከዳዕዋው አንዳትቀሩ።
Mostrar todo...
....ለልቤ..... --------------------------------- ተውሒድ ባይተዋር ሲሆን ሸርክ ቢዲአ ነግሶ፡ ጥመት ስር እየሰደደ ምርቱን ለህዝብ ለግሶ፡ የሀቅ ዘበኛው ግን ባይተዋርነትን መርጧል፡ በተራ ነገር እየተባላ እጅ አጥፎ ተቀምጧል፡ ---------------------------------------------------- ድካም እየተሰማኝ መንፈሴን ብርታት ሲነሳው፡ በጨለማ ዳዴ እያለ ፀሃይ ውስጤን ሲያሳሳው፡ የጎኔ ጥንካሬ አቅም በንደት እየደቀቀ፡ የማይሰንፈው ልቤ ግን ተስፋ የሚል ቃል ሰነቀ፡ --------------------------------------------------- ጠላቴ አድማስ አስፍቶ በጥላቻ ሲከተለኝ፡ ባልሰራሁን እየከሰሰ በውሸት ሲወነጅለኝ፡ እልኸኛ ሆነና ልቤ አልደፈርም አለኝ፡ 👉#እናም__!! ሱናችን አንገት ሲደፋ፤ ቢዲአ ደፍሮ ሲያቅራራ፡ ከውሸት ላይ ቁጭ ብሎ፤ ውሸት በውሸት ሲያብራራ፡ በጠጠር ሊጥል ሲታገል የሱናውን ተራራ፡ ሀቅን ልዋጋ ብሎ በማይችለው ሲንጠራራ፡ ሽርኩን ደፍሮ ሲያስተምር ሱፍያና አሻኢራ፡ ......✍️#ይህኔ_!! ተውሒዲና ሱናን ለውስጤ ቀልቤ፡ አብሽር አይዞህ ብዬ ነገርኩት ለልቤ፡ --------------------------------------------- ✍️ኑረዲን አል አረቢ ---------------------------------------------- https://t.me/nuredinal_arebi
Mostrar todo...
شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن

#ሰለፍያ_ቀጥተኛ_የሀቅ_መንገድ_ብሎም_አይነኬ_ፅኑ_ተራራ_ነው ለአስተያዬትና እርማት @Nuredin_al_arebi_Bot

👉#ለዑስታዝ_ኸድር_ከሚሴ_ሀፊዞሁሏህ_!! ........................................................... 👉#እኛ_እናውቅሀለን___!! --------------------------------- የጣልንህ መስሏቸው ምን ብዙ ቢያዜሙም፡ አሏህ የሰጠህን ክብርህን አይቀሙም፡ ኢኽዋን ቢያሴርብህ ሱፍያ ቢያቅራራ፡ ጃሒል መሀይም ነው ብትል ሐጃዊራ፡ ባድስ ቢዘምትብህ ደግሞም ባለተራ፡ ማንም ምንም ቢልህ ያወራ ቢያወራ። በግልፅ ይስተዋላል የሰራኸው ስራ፡ --------------------///------------------- ያለ ምንም አድሎ ያለ ድንበር ማለፍ፡ አሁን ባለህ አቋም አብሬህ ብሰለፍ፡ ሁጃህ ያሳምናል ፋና አለው ከሰለፍ፡ አስተውሎ ላዬ ስሜት ሳይጋልበው፡ አሶብያ ይዞት ሀፍረት ሳይሻብበው፡ ሁጃ መርህህን ሰርፆ ላነበበው፡ ሀቅ ለሚፈልግ ደሊል ነው ሚያጠግበው፡ -------------------------//------------------ 👉#ከቶ_ለምን_ይሆን!? ኢኽዋን በሀገርህ ላይ አስሮ የሚፈታህ!? አህባሽ ውሸት ሰብቆ ሁሌ እሚያንገላታህ!? ባልፈፀምከው ክስተት፤ ሁሉም ስሜተኛ አንተን የሚመታህ!? #ከቶ_ለምን_ይሆን_!? የጥፋት ማሽኖች ስምክን የሚያነሱት!? ባልፈፀምከው ስህተት አንተን የሚከሱት!? በጥላቻ ብቻ ደፍረው የሚነሱት!? #ከቶ_ለምን_ይሆን!? ወይ መረጃ ጠቅሰው በአደብ አይነግሩን!! ወይ እውቀት የላቸው ሀቅ አያስተምሩን!! ከመሀል ላይ ቆመው አደነጋገሩን!! ስድብና ትችት ወቀሳ አስተማሩን!! --------------------------------------------- 👉#ለነገሩማ_!! ቁስላቸው ሲነካ፤ እሪ ዑዑ ቢሉ ለነገሩ አይገርምም፡ እውነት ነው አውቃለሁ፤ ችግር ካልተነካ ንግግር አያምም፡ ተባይ ካልፈጠረ፤ አረም ካላወጣ ሰብል አይታረምም፡ በሁጃ ካልሆነ፤ የሰገጤ መንጋ አይገረመምም፡ በደንብ ካልፈጩት፤ ጣዕሙ መራራ ነው አንከርዳድ አይልምም፡ 👉#ደግ_አደረካቸው__ --------------------------------------------------- በውሸት ዘመቻ በስሜት ስም ማጥፋት፡ አይቻልምና ባጢልን ማስፋፋት፡ ስህተቱን በሁጃ ያጋለጥከው ሁሉ፤ ወቀሳ ቢያበዛ እኛን አይገርመንም፡ በደሊል ነው እንጂ፤ በቀረርቶ ብዛት ቲፎዞ አንሆንም፡ #ደግሞ_ላንተም_ቢሆን፤ #ሀቅ_ላይ_ካልፀናህ_ተዐሱብ_የለንም፡ ----------------------------------------------------- 👉#አወና__ የፀሃዩን አቋም፤ በወረቀት ሰፈር አንሶ ብታየውም፡ ወረቀትን አምነህ፤ ያንን ትልቅ ፀሃይ ትንሽ አትለውም፡ በቀለማ ቀለም ፤ የጊዜው ሰአሊ ሲያስውብ ሲተለትል፡ በመሀይምነት፤ በመሚመቸው መጠን ቃል ሲጎነታትል፡ አንተም እሱን ሰምተህ ዘወትር ብትባትል፡ በእርግጥ አይገርመኝም፤ ብሩሹን አምነኸው አናሳ ነው ብትል፡ ~~~~ ያንን ያክል ግዝፈት፤ በብዕር ተስሎ ላይን ቀርቦ ሲታይ፡ ድሮስ ቢሆን ታዲያ፤ በወረቀት ሜዳ ላይቀል ነው ፀሃይ?? #ለማንኛውም____! በውሻሸት ተረት፤ በድምፀ-ሞቅታ በሚያፈስ ታዛ ያለ በቂ ደሊል፤ አንተን አንጠላህም ጩኸት ስለበዛ፡ ለመዘሀበል ሀቅ፤ በመታገል ላይ ነህ አወ እንወድሀለን፡ ሳንርቅ በቅርበት ልፋት ጥረትህን፤ እቅድ ፕላንህን ፀባይ አቋምህን እንረዳሀለን፡ የማያውቁህ ያውሩ፤ ይበሉ እንዳሻቸው እኛ እናውቅሀለን፡ ------------------------------------------------ 👉#በኑረዲን_አል_አረቢ_10/02/14_!! ------------------------------------------------- http://t.me/nuredinal_arebi
Mostrar todo...
አስተማሪ ታሪክ «ለሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል-ሙነጂድ (ሐፊዘሁሏሁ ተዓላ) የቀረበላቸው አሳዛኝ የፈታዋ ጥያቄ ለሁላችንም በዚህ ወቅት ራሳችንን እንድንፈትሽ አስተማሪ ታሪክ ነው ይጠቅመናል ብዬ አቀረብኩት.......... «ጠያቂዋ....... ■« እኔ በጣም ታዋቂ የሆኑ ቤትሰብ ልጅ ነኝ። በሥነ-ምግባርና በዐደብ አሳድገውኛል በዚህም ባሕሪዬ ይመሰክሩልኛል። ነገር ግን ይህንን ወጣት እንድተዋወቀው ምን እንደገፋፋኝ አላውቅም። እኔ ግን ልረዳው ፈልጌ ነበር የቀረብኩት ምክንያቱም ይህ ወጣት አባቱ መሞትና ስለ እናቱና ስለ ወንድሞቹ ኃላፊት ሲወድቅበት የአዕምሮ መረበሽና መቃወስ በሽታ ተፈጠረበት። ከዚያም መጥፎ ጓደኞችን አፈራ የእነሱን መንገድ ተከተለ። እኔ በመልካም ኒያ ልመክረው ቀረብኩ እሱን ካለበት ጣጣ አዘቅጥ ውስጥ መመለስ ግዴታዬ ነው ብዬ ለራሴ አሰብኩ። ከቀናት በኋላ በምክሬ ተስተካከለ መጥፎ ጓደኞቹን ሁሉ ተለያቸው ሙሉ በሙሉ ተቀየረ። «እናቱ በድንገታዊ ባሕሪ መስተካከሉ ተደናግጠው ምክንያቱን ሲጠይቁት ስለ እኔ ያጫውታቸዋል። እናቱ በዚህ ልጃቸውን መጥፎ ባሕሪ ታግሼ ስለቀየርኩላቸው እጅግ ተደስተው በጣም አመሰገኑኝ። አንድ ቀን ሊያየኝ ለዚያራ መጣ ለምን እንዳላመነታው ራሱ አላውቅም ልክ እንደ ወንድሜ እንደሆነ ብቻ ተሰማኝና ወጥቼ ተቀበልኩት። ብቻችንን የምንጫወትበት ብዙ ሰዓት አገኘን በዚሁ ቅጽበት ዝሙት ላይ ወደቅኩኝ። ከዚያም በውስጤ እጅጉን አዘንኩኝ። «አሁን ደሞ እሱ ለትዳር ቤትሰቡን መላክ ይፈልጋል። ነገር ግን ይህ በፍፁም የሚሆን ነገር አይደለም። ሦስት አመት እበልጠዋለሁ፣ ዜግነታችንም አንድ አይደለም፣ በተጨማሪ ደሞ እኔ አርግዣለሁ ወደ ጌታዬ ተውባ ማድረግ እፈልጋለሁ። ትልቅ ወንጀልን እንደሰራሁ ይገባኛልል። በደንብ ልትወቅሱኝ ተገቢ ናችሁ እርዱኝ መፍትሔ እፈልጋለሁ። (ጠያቂዋ ወጣት) «በባዕድ ሴትና ወንድ መካከል ያለው ያልተገደበ ግንኙነት ለኸይር ፣ ለምክር፥ ሰዎችን ወደ ሐቅ ለመመራት እስከሆነ ድረስ ችግር የለውም ብለው በሸሪዓው ስም ለሚደበቁ ወስላቶች እንደዚህ አይነቱ ተጨባጭ ታሪክ ያንን ለኸይር ምናምን የሚለውን የሰይጣን መሸሸጊያ ግርዶሽ ገደል ይከተዋል። እዚህ ታሪክ ላይ ይችን ጨዋ ቀናዒ እንስት ከዝሙት ባሕር አዘቅጥ ውስጥ ለመጨመር ሙሉ ሕይወቷን ለማቃወስ ሰይጣን(ለዐነሁሏህ) «በኸይር ስም» የተከተላቸውን ወጥመዶች ማስተዋል ብቻ በቂ ነው። ለዚህ ነው አሏሁ(ሱወ) ዝሙትን "አትሥሩ" ሳይሆን አስለን "አትቅረቡት" ያለን ስለዚህ መቅረብ ማለት ደሞ ልክ ይች እሕት እንደወደቀችበት ወጥመድ "ለኸይር ነው" "መልካም ኒያ" ነው ያለኝ የሚሉት የሰይጣን ወጥመዶች ናቸው። አሏህ ከሰይጣን ተንኮልና ከብልሃት ሴራው ይጠብቀን። «ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ! (17/32) https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/12169
Mostrar todo...
ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

አስተማሪ ታሪክ «ለሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል-ሙነጂድ (ሐፊዘሁሏሁ ተዓላ) የቀረበላቸው አሳዛኝ የፈታዋ ጥያቄ ለሁላችንም በዚህ ወቅት ራሳችንን እንድንፈትሽ አስተማሪ ታሪክ ነው ይጠቅመናል ብዬ አቀረብኩት.......... «ጠያቂዋ....... ■« እኔ በጣም ታዋቂ የሆኑ ቤትሰብ ልጅ ነኝ። በሥነ-ምግባርና በዐደብ አሳድገውኛል በዚህም ባሕሪዬ ይመሰክሩልኛል። ነገር ግን ይህንን ወጣት እንድተዋወቀው ምን እንደገፋፋኝ አላውቅም። እኔ ግን ልረዳው ፈልጌ ነበር የቀረብኩት ምክንያቱም ይህ ወጣት አባቱ መሞትና ስለ እናቱና ስለ ወንድሞቹ ኃላፊት ሲወድቅበት የአዕምሮ መረበሽና መቃወስ በሽታ ተፈጠረበት። ከዚያም መጥፎ ጓደኞችን አፈራ የእነሱን መንገድ ተከተለ። እኔ በመልካም ኒያ ልመክረው ቀረብኩ እሱን ካለበት ጣጣ አዘቅጥ ውስጥ መመለስ ግዴታዬ ነው ብዬ ለራሴ አሰብኩ። ከቀናት በኋላ በምክሬ ተስተካከለ መጥፎ ጓደኞቹን ሁሉ ተለያቸው ሙሉ በሙሉ ተቀየረ። «እናቱ በድንገታዊ ባሕሪ መስተካከሉ ተደናግጠው ምክንያቱን ሲጠይቁት ስለ እኔ ያጫውታቸዋል። እናቱ በዚህ ልጃቸውን መጥፎ ባሕሪ ታግሼ ስለቀየርኩላቸው እጅግ ተደስተው በጣም አመሰገኑኝ። አንድ ቀን ሊያየኝ ለዚያራ መጣ ለምን እንዳላመነታው ራሱ አላውቅም ልክ እንደ ወንድሜ እንደሆነ ብቻ ተሰማኝና ወጥቼ ተቀበልኩት። ብቻችንን የምንጫወትበት ብዙ ሰዓት አገኘን በዚሁ ቅጽበት ዝሙት ላይ ወደቅኩኝ። ከዚያም በውስጤ እጅጉን አዘንኩኝ። «አሁን ደሞ እሱ ለትዳር ቤትሰቡን መላክ ይፈልጋል። ነገር ግን ይህ በፍፁም የሚሆን ነገር አይደለም። ሦስት አመት እበልጠዋለሁ፣ ዜግነታችንም አንድ አይደለም፣ በተጨማሪ ደሞ እኔ አርግዣለሁ ወደ ጌታዬ ተውባ ማድረግ እፈልጋለሁ። ትልቅ ወንጀልን እንደሰራሁ ይገባኛልል። በደንብ ልትወቅሱኝ ተገቢ ናችሁ እርዱኝ መፍትሔ እፈልጋለሁ። (ጠያቂዋ ወጣት)…

ብሄርተኝነት ጣኦት ነው! ~~ * የሃይማኖት አጥር የማይከበረበት፣ * ሙስሊም ወገን የሚታረድበት፣ ንብረቱ የሚነጠቅበት፣ የሚቃጠልበት፣ * "ሃይማኖት አይከፋፍለንም" እያሉ የሚሰበክበት፣ * ጣኦታዊ በአላት የሚታደሙበት፣ አማራነት፣ ኦሮሞነት፣ ትግሬነት፣ አፋርነት፣ ... ወሎየነት፣ ጎንደሬነት፣ ሀረሪነት፣ ወለጋነት፣ ... ጣዖት ነው። * {እሷ የሸህ ልጅ ናት እኔ የመምሬ ምን ያስጨንቀኛል ወሎ ተፈጥሬ} የምትዘፍንበት ወሎየነት ቆሻሻ ነው። * የእምነት የለሾች ውጤት በሆነችው ሉሲ ላይ ተመርኩዞ "አፋር የሰው ዘር መገኛ" እያሉ በክህደት እንዲጀነኑ የሚያደርግ ብሄርተኝነት ገዳይ ነው። * ታቦት እስከሚሸኙ፣ መስቀል እስከሚጣዱ፣ ገና እስከሚያደምቁ፣ ... የደረሰ የአማራ ብሄርተኝነት ነቀርሳ ነው። * ኢሬቻ እስከሚካፈሉ፣ ሙስሊም ወገኖች ዘራቸው እየታየ እስከሚጠቁ፣ ... የደረሰ የኦሮሞ ብሄርተኝነት አጥፊ ነው። ጥፋት በማንም ቢፈፀም ጥፋት ነው። በዘርና በቋንቋ በሚመስሉህ ሰዎች ስለተፈፀመ ወግነህ አትከራከር። ወገኔ ሆይ! ከምንም በላይ ኢስላምህን አስቀድም። ያንተ ዘር ከዐረብ አይበልጥም። ዐረብ እንኳ አላህን መፍራት ከሌለው በስተቀር በሌላው ላይ ብልጫ የለውም። ዘርህ ከመተዋወቂያነት ባለፈ ስሙኒ ታክል ዋጋ የለውም። ስለዚህ አትኮፈስ፣ አትሸማቀቅ። ዘርን መሰረት አድርገህ በጅምላ አትውድድ፣ በጅምላ አትጥላ። ሁሌም አኺራህን አስቀድም። በቃልም በፅሁፍም የዘር ጥላቻ እንዳትቀስቅስ ተጠንቀቅ። ጊዜው የሰው ህይወት የረከሰበት ጊዜ ነው። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጅህ ላይ የሰው ደም እንዳይኖር ፍራ። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
Mostrar todo...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

ይህን ሂጃብ አለባበስ አንዳድ እህቶች ባለማወቅና በቸልተኝነት ሲጠቀሙት ይታያል ። ዉድ እህቶች ፀጉርን እንዴ ግመል ሻኛ አቁሞ ሂጃብ መልበስ ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሀራም አድርገዉታል። አቡ ሁረይራ በዘገቡት ሀዲስ ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ስለ ሁለት አይነት የጀሀነም ሰዎች ሲናገሩ። አንደኛወቹ ጅራፍ አዘጋጅተዉ ሰዎችን የሚገርፉ ሲሆኑ ሁለተኛወቹ ደግሞ ሴቶች መሆነቼዉንና ፀጉራቸዉን እንደ 🐪ግመል ሻኛ የሚያቆሙ ናቼዉ። እህቶች ጥንቃቄ አድርጉ። https://t.me/MTUEQRAMESJID
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.