cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

✞ ኤፍታህ በማለዳ

📣ይህ ✞ ኤፍታህ በማለዳ የተባለው ኦርቶዶክሳዊ ዕውቀትን መማማሪያ እንዲሁም ስለሀይማኖታችን እንድናቅና "የሰው ጠላት የለኝም" በማለት ጠላታችን ዲያብሎስን በመቃወም ከክርስቶስ ጋር በመሆን ለበረከትና ለፀጋ በመትጋት መንግስትቱን ለመውረስ የምንማማርበት ነው። እግዚአብሔር ይርዳን። በተከከታታይ የማንቂያ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን በኤፍታህ ይጠብቁን። @Eftah_bemaleda

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
687
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም ተነስቷል በዚህ የለም #መድኃኔዓለም @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸዉ አምስቱ ችንካሮች (ሚስማሮች) ስም፦ #1ኛ ሳዶር #2ኛ አላዶር #3ኛ ዳናት #4ኛ አዴራ #5ኛ ሮዳስ አምስቱ የእመቤታችን ኃዘናት፦ #1ኛ ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉክ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነዉ።ሉቃ 2÷34 #2ኛ ሁለተኛዉም ሦስት ቀን በቤተ መቅደስ ባጣሁህ ጊዜ ነዉ።ሉቃ 2÷41 #3ኛ ሦስተኛዉም እጅህን እግርህን አስረዉ በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነዉ።ዮሐ19÷1 #4ኛ አራተኛዉም በዕለተ አርብ እራቆትህን ቸንክረዉ በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀልኩ ባሰብኩ ጊዜ ነዉ አለችዉ። ዮሐ19÷17 #5ኛ አምስተኛዉም ወደ ሐዲስ መቃብር ዉስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነዉ።ዮሐ 19÷38 ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈፀሙ 7ቱ ተአምራት፦ #1ኛ ፀሐይ ጨልሟል #2ኛ ጨረቃ ደም ሆነ #3ኛ ከዋክብት እረገፉ #4ኛ ዓለቶች ተሰነጠቁ #5ኛ መቃብር ተከፈቱ #6ኛ ሙታን ተነሱ #7ኛ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ ሰባቱ የመስቀል ላይ ንግግሮች፦ #1ኛ አምላኬ አምላኬ ለምን ተዉከኝ።ማቴ 27÷46 #2ኛ አባት ሆይ የሚያደርጉት አያዉቁምና ይቅር በላቸዉ። ሉቃ 23÷34 #3ኛ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእዉነት እነግረሃለሁ። ሉቃ 23÷43 #4ኛ እነሆ ልጅሽ አነዃት እናትህ።ዮሐ 19÷26 #5ኛ ተጠማሁ።ዮሐ 19÷28 #6ኛ አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ።ሉቃ 23÷46 #7ኛ የተፃፈ ሁሉ ደረሰ ተፈፀመ አለ።ዮሐ19÷30 የአምላካችን ቸርነትና የእመቤታችን ምልጃ አይለየን አሜን ፫ ❤️ @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
" ሕማማት መስቀል" ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦ 1. በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የኋሊት መታሰሩ 2. ከአፍንጫው ደም እስኪውጣ ድረስ 25 ጊዜ በጡጫ መመታቱ 3. 65 ጊዜ ከግንድ ማጋጨታቸው 4. 120 ጊዜ በድንጋይ ፊቱን መመታቱ 5. 365 ጊዜ በሽመል መደብደቡ 6. 80 ጊዜ ጽህሙን መነጨቱ 7. 6666 ጊዜ መገረፉ 8. አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ መደፋቱ 9. 136 ጊዜ በምድር ላይ መውደቁ 10. ሳዶር፡ አላዶር፡ ኤዴራ፡ ዳናትና ሮዳስ በሚባሉ 5ቱ ቅንዋተ መስቀልበችንካር መቸንከሩ 11. መራራ ሐሞትን መጠጣቱ 12. መስቀሉን ተሸክሞ መንገላታቱ 13. በመስቀል መሰቀሉ ናቸው። 💛 @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
ሕማምህን ላስብ ከእኔ ምን አይተህ ነው እንዴት ብትወደኝ ነው ግርፋቴን ወስደህ አንተ የተገረፍከው ከኔ ምን አይተህ ነው እንዴት ብትወዳኝ ነው እኔ እንድናገር አንተ ግን ዝም ያልከው እንዴት ብትወደኝ ነው ማንስ ለጠላቱ ይህን ያህል ይደክማል እራሱንስ ለሞት አሳልፎ ይሰጣል ያንተ ግን ይለያል ያንተ ግን ይደንቃል ከርስት ልትመልሰኝ የህማም ሰው ሆነሀል ህማምህን ላስብ ሞትህን ልናገር የከፈልክልኝን የመዳኔን ነገር በለሷ ለምልማ በቅጠል ብታምር ፍሬ ግን የላትም ላንተ ሚሆን ነገር አንተ ግን ስለኔ ብዙውን ሆነሀል እርቃንህን ተሰቅለህ እኔን አልብሰሀል ህማምህን ላስብ ሞትህን ልናገር የከፈልክልኝን የመዳኔን ነገር እንዳላየ አልፎኛል ሌዋዊውም ካህኑ አለም እንደዚህ ናት ከጨለመ ቀኑ በዘይት ጠገንከኝ በወይንህ አከምከኝ በያሪኮ መንገድ ቆስየ ብታየኝ ህማምህን ላስብ ሞትህን ልናገር የከፈልክልኝን የመዳኔን ነገር ፍቅርህ ይበረታል ፍቅርህ ይለውጣል ያየሁት መዳፍህ ልቤን ቀስቅሶታል ይህ ሁሉ ለእኔ ነው መከራ ህማሙ እንደ አዲስ ፈጥሮኛል በከበረ ደሙ ህማምህን ላስብ ሞትህን ልናገር የከፈልክልኝን የመዳኔን ነገር @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
_ሕማምህን_ላስብ_ዘማሪት_ሲስተር_ዮርዳኖስ_ምስጋናው_ቤተ_ቅኔ_Beta_QeneMP3_70K.mp36.24 MB
Photo unavailableShow in Telegram
ሰሙነ ሕማማት @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
ያለን #አንድ ነው፤ ነገር ግን ሁሉን መሆን ይችላል!! እርሱም፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ❝ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን #ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።❞ ሐዋርያት 3፥6 Join - @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
መጋቢት ፳፯ በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ! "ሊቃነ መላዕክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት!" Join - @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
ማን ያምናል አሁን የእኛን መዳን በአለም እርኩሰት ለሚያውቀን እንዲሁ ነጻ ናችሁ ያልከን ተባረክ ፈቅደህ የባረከን ኑሮአችን ነበር የጨለማ ምንቀኝ የአልምን ዜማ ሳንጠፋ ሳንገባ ከጥልቁ ተማርን ታይቶልን ሰንደቁ Join - @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
ምህረቱ ለዘላለም ነውና ቸርነቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመሰግኑ ከመከራ ዘመን መራመጃ ሆኖ ልጆቹን ያወጣ በግርማው ሸፍኖ ይጋር ሰሀዶታ የጸጥታ ወደብ ወደ ተጨቆኑት በፍትህ የሚቀርብ የእስራኤልን ቅዱስ አመስግኑ መልካሙን እረኛ አመስግኑ ለድሆች የሚፈርድ አመስግኑ እውነተኛ ዳኛ አመስግኑ @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
“…እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ ታለቅሳላችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ፥ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፥ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል። ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም። እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ገና አያችኋለሁ ልባችሁም ደስ ይለዋል፥ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።” ዮሐ 16፥ 20-23 @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...