cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

እንኳን መጣቹ ወደቻናላችን 👍 ስለንባብ እንሰብካለን 👉አዲስ መፅሐፍ እንጠቁማለን 👉pdf እንልክላችዋለን 👉ግጥም 👉ከመፅሐፍ የተወሰዱ ታሪኮች 👉የታላላቅ ሰዎች አባባሎች 👉አስገራሚ ፎቶዎች ያላቹን አስተያየት 👉 ይንንአስተላልፍል የምትሉት ላኩልኝ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል @nbab2

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
204
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

፡ ተስፋ ብቻ አድርግ…         እንደ ድንገትም ቢሆንይህን እያነበብክ ከሆነ ወዳጄ እቺን መልክት ልነግርህ ወደድኩ …ምን አልባት…አሁን ላይ በህይወትህ ከባዱን እና ደስ እማይለውን ጊዜ እያሳለፍክ ይሆናል…በሀገርህ፣በቤተሰብህ፣በምታፈቅራት ሴት እና በራስህ ደስተኛ አደለህ ይሆናል…እምታየውም ነገር ሁሉ አልጥምህም ብሎህም ይሆናል…እኔም በርግጥ ብዙ ነገር አይጥመኝም…        ምን አልባትም ደሞ…ስራ ፈልገህ አተህ ይሆናል፣ እራስንም በሱስ ደብቀህ ይሆናል፣ በማትፈልገውም መንገድ እየሄድክ ይሆናል፣ የቀደመውን ፍቅርህንም እረስተህ በሀሰት ጐዳና ላይ እየተመላለስክ ይሆናል…          ግን ወዳጄ! …ያልነጋ ጨለማ እና ያላባራ ዝናብ የለም…ተስፍ እንዳትቆርጥ…የፈለገ ቢደክምህ እና ቢሰለችህም እረፍት አድርግ እንጂ እንዳታቆም…አንድ እውነትም አለ… እሱም ምንድን ነው መሰለህ…ሁሌም ደስታ የለም…ይህን እንዳትረሳ…ሁሉም መልካም ይሆናል።     @nbab2 @Ragxo44
Mostrar todo...
2
፡    አንቺስ ምን ትያለሽ?…🖤       ብዙዎች…እሱ መጥፎ ሰው ነው…የሚያወራውንም አይኖርም…አስመሳይ እና ውሸታም ሰውም ነው…እሱ እኮ ዱርዬ ነው…ሀጥያተኛ እና በደለኛም ሰው ነው ይላሉ…አንቺስ ግን ምን ትያለሽ?…ለአንቺስ ምን አይነት ሰው ነኝ?…    እንደሚሉኝ አይነት ክፉ ሰው ነኝ?…ወይስ መልካም ሰው …ቤተሰቡን እሚወድ እና እሚያከብር ሰው እናም ፈርሀ እግዛብሔር ያለው ሰው…            አንቺስ ምን ትያለሽ?…🤎          🌹💔🌹💔🌹💔🌹💔🌹 @nbab2 @Ragxo44 🌹💔🌹💔🌹💔🌹💔🌹💔
Mostrar todo...
👍 2
🌹🌿 አንድ የማውቀው ታሪክ ልንገራችሁ...ልብ ብለው ያንብቡ በጣም ሚዋደዱ ሁለት ፍቅረኛሞች ለመጋባት ይወስናሉ፡፡ ቀለበት ሊያስሩ ጥቂት ወራት ሲቀራቸው ልጅቱ የመኪና አደጋ ይደርስባት እና ፊቷ ሙሉ በሙሉ ተበላሸ፡፡ "ቀሪ ህይወቴን መልከ-ጥፉ እና አስጠሊታ ሁኜ መኖሬ ግድ ሆኗል፡፡ ከእንግዲህ ላንተ የምገባ ሴት አደለሁም፡፡ ሌላ ቆንጆ ወጣት ሴት ፈልገህ አግባ፡፡" ብላ ለልጁ ፃፈችለት፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ እንዲህ ሚል ደብባቤ ደረሳት... "ውዴ ማፈር ያለበት ሰው ካለ እኔ ነኝ ማፈር ያለብኝ፡፡ በአይን ህመም ምክንያት ማየት እንደማልችል ዶክተር ነግሮኛል፡፡ እንዲህ ሁኜ የምታገቢኝ ከሆነ እኔ አንቺን ለማግባት እፈልጋለሁ፡፡" ወዲያው ተጋቡ፡፡ ልጁ ጭራሽ ማየት አይችልም ነበር፡፡ ለ 20 አመታት በፍቅር በደስታ በመተሳሰብ ኖሩ፡፡ እሷ የአይኑ ብርሃን ሁና እየመራችው ፍቅራቸው ፈክቶ በሀሴት ኖሩ፡፡ ከ20 አመት ቆይታ በኋላ ሴቷ በጠና ታመመች፡፡ በባዶ ጨለማ ትቼው ልሞት ነው ካለኔ ማን አለው እያለች ትጨነቅ ነበር፡፡  ሞት አይቀርምና ወደማይቀርበት አለም ሄደች፡፡ ሚስቱ የሞተችበት እለት ሰውየው አይኑን ገልጦ ማየት ጀመረ፡፡ ሰው ሁሉ ተገረመ ደነገጠ "አይነ ስውር አልነበርኩም.... የተበላሸውን ፊቴን አየብኝ ብላ እንዳትሳቀቅ ብዬ ነው አይነ ስውር መስዬ የኖርኩት፡፡" አለ፡፡ የታሪኩ "ሞራል" እዉነተኛ ፍቅር አካላዊ ውበትን ሳይሆን ሚመለከተው ውስጣዊ ውበትን ነው፡፡ ምክንያቱም እውነተኛ ፍቅር በአይን ሳይሆን በልብ ነው ሚመለከተው፡፡ 🌹💔🌹💔🌹💔🌹💔🌹💔🌹 @nbab2 @Ragxo44 🌹💔🌹💔🌹💔🌹💔🌹💔🌹
Mostrar todo...
🥰 1😡 1
"አውቃለሁ እንደምታፈቅሪኝ ግን አሁን ቢከብድሽም አንድ እንድታቂው ምፈልገው ነገር አለ" "ምንድነው ? ልቤ እየፈራ ነው አንተም እንዳለፉት ግዚያት እንደነበሩት ልትተወኝ ነው?በምን....በምንስ ጥፋቴ ልትሸሸኝ ነው....መጥፎ ሰው ነኝ እንዴ" "መጥፎ ስለሆንሽ አይደለም ምንተውሽ አንዳንዴ ጥሩነትሽ ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ይሆናል ምንተውሽ....ጥሩ ግዜ እንደነበረን አውቃለሁ እርሺኝ እኔ አዲስ ቤት ልገነባ ነው አዲስ ህይወት ውስጥ ልሄድ ነው" "እርሺኝ ለአፍ ቀላል ሆነ እንዴ በአንዴ ምረሳህ" "አታልቅሺ አንቺ ጥሩ ሰው ነሽ እኔ ነኝ መጥፎ እላይሽ ላይ ሌላ ቤት ለመሄድ የከጀልኩ አፉ በዪኝ ከአሁን በኋላ እያገኘሁሽ ቁስልሽ ላይ ጨው አላልከፈክም ደህና ሁኚ ውዴ ከሳምንት በኋላ የሰርግ ደብዳቤ ይደርስሻል አደራ እንዳትቀሪ" "ተሞሽረህ ስትሸኝ እልል ብዬ ልሸኝህ ወይስ አልቅሼ ልሰናበትህ ይሁን ጥሪህ የፀጋዬን ዘፈን የሰርግህ እለት ብዬ ላንጎራጉር ነው ጥሪህ....." "ብቻ አደራ አደራ እንዳትቀሪ የተሞሸርኩ እለት ደህና ሁኚ ውዴ" የሰርጉ ደብዳቤ "የኔ ፍቅር ህይወት በፍቅራችኝ ገብታ አንቺ ወይ እሷን መምረጥ እንዳለብኝ ጠየቀችኝ ቀድማ አንቺን እንዳትነጥቀኝ ከአነቺ እሷን መረጥኩ ህመሜ በሽታዬን ደበኩሽ ታምሜ አብረሽኝ እንዳትታመሚ በስብራቴ እንዳትሰበሪ ነበር መሄዴ ነው ያልኩት ቀጠሮዬ ደርሷል ንግስቴ በሌላኛው ቤት ልሞሸር ነው አደራ አደራ እንዳትቀሪ የተሞሸርኩለት"......
Mostrar todo...
🤯 3
ጊዜ እና ሠው 👉በጣም ብዙ ጊዜ ሰዎች ጊዜ እያለፈ ነው ጊዜውን መጠቀም ያስፈልጋል።ጊዜ ካለፈ አይመለስም ሲሉ ይስተዋላሉ። እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፦        ጊዜ በሰው ውስጥ ያልፋል ? ወይስ የሰው ልጅ ነው ጊዜ ውስጥ እያለፈ ያለው? 👉እውነት ለመናገር ሰው በጊዜ ውስጥ ያልፋል እንጂ ጊዜ በሰው ውስጥ አያልፍም። ጊዜውን በአግባቡ መጠቀም ያለብን እኛ አላፊ ስለሆንን እና ያለፍነውን የትላንቱን ማንነት መድገም ስለማንችል ዛሬን በአግባቡ ለመጠቀም ነው።  ስለዚህ አንድ እውነት እንዲገባችሁ እወዳለሁኝ። በጣም በፍጥነት በጊዜ ውስጥ እየተጓዝን እንደሆነ ይግባን። እና በጣም በፍጥነት እየጠፋን እንደሆነም ይግባን። ስለዚህ ጊዜውን በአግባቡ እንጠቀም ስንል ጊዜው እንዳያልቅብን ሳይሆን እኛ በፍጥነት እያለቅን እንደሆነ በመረዳት ውስጥ መሆን አለበት። እወዳችሁዋለሁ ሰናይ ቀን።        @nbab2 Jonah 🙏🙏🙏
Mostrar todo...
🫡 1
🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
👉ይሄ ያንተ አይምሮ ነው። ማንም ሰው እንደፈለገ እንዲመራው አትፍቀድለት። መኪና ከገዛህ በሁዋላ መኪናህን መንጃ ፈቃድ አውጥተህ እራስህ እንደምትነዳው የገዛ ጭንቅላትህንም እራስህ ሾፍረው። ወንድሜ አጎቴ እናቴ አክስቴ አባቴ እያለክ ሰበብ እየፈለክ አይምሮህን ላገኘኸው ሁሉ አትስጥ!!! ስራ የፈታ አይምሮ የሰይጣን መጫወቻ እንደሚሆን አስተውል። 👉 @Ragxo44🙏🙏🙏 @nbab2
Mostrar todo...
🔥 1
በጧት ተነስታ ሚሥት ቁርስ ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ ትላለች ባል ተብየው ሓልጋው ላይ ጋደም ብሎ ከአሑን አሑን ልነሳ አልነሳ እያለ ሑለት ልብ ላይ ነው ። የሚሥቱ ስልክ ላይ ሚሴጅ ሲገባ ሠመው ስልኩን አነሳ ፖተርኑን ከፈተ ሚሤጁን ማንበብ ጀመረ ! ሀይ ሠላም አደርሽ የኔ ልእልት አሁን ወፎቹ ላንቺ እየዘመሩልሽ ነው የጠዋትዋ ፀሀይ ደግሞ አንቺን ለማየት ተጠድፋ ደጅ ደጃችሁን ታያለች ጨረቃዋ በቅጡ ሳይነጋ ቶሎመሽቶ ላንቺ ብቻ ለማብራት ተጣድፋለች የሠፈራቹ መንገዶች ባንቺ ብቻ መረገጥን ይሻሉ።እኔ ግን ፀሀይዋንም አልሖንኩ ወፎቹንም አልሆንኩ አልያም መንገዱን ግን...ልክ እንደ ፀሀዯ አንቺን ለማየት እሻለሁ እጓጓለሁ ግን ስለሚያፈቅረኝ ነው ብለሽ እንዳታስቢ አንቺን ካላየሁ መኖር ስለማልችል ነው። ባል ሜሴጁን አልጨረሰውም ቤቱን ጦር ሜዳ አደረገው። ነይ አንች !አንችን እኮ ነው! አንች ዘልዛላ! ማለቱን ተያያዘው ሚሥት ባሌን ምነካው ብላ እሩጣ መጥታ በሥሥት ማየት ጀመረች ባል የንዴቱን አንድ ግዜ በጥፊ ቸቧ አደረጋትና ማንጋር ነው የምትዘላዘይልኝ እስኪንገሪኝ ብሎ የሥልኩን ሚሤጅ አሣያት በጋራ አነበቡት መጨረሻላይ እነዲሕ ይላል እንዲሕ አይነት አሪፍ መጣጥፍ በየጌዜው እንዲደርሠዎ ወደ 82*** A ብለው ሚሤጅ ይላኩ !! ቀናተኛ መሆን እዳ ነው!
Mostrar todo...
👍 3👎 1 1😨 1
#ኢነርጂህን_የሚያበላሹ_3ቱ_አስተሳሰቦች #1_ሰዎች_ምን_ይሉኛል_ማለት ለስኬትህ ከሌሎች ሰዎች ማረጋገጫ የምትፈልግ ከሆነ በሕይወትህ ውስጥ እውነተኛ እርካታን አታገኝም። ውስጥህንም ከማዳመጥ ይልቅ ሰዎች ሁን የሚሉህን ትሆናለህ። ስኬት ትዳር መያዝ ነው ሲሉህ ታገባለህ፣ ስኬት መኪና መግዛት ነው ሲሉህ ተበዳድረህም ቢሆን መኪና ትገዛለህ። አንተን ከአንተ በላይ የሚያውቀው የለምና የአእምሮ ኢነርጂህን በመጠቀም በተቻለህ አቅም የራስህን መንገድ ወስን #2_ፍጹምነት "ሁሉም ነገር በፍፁምነት ካልተሰራ ምን ዋጋ አለው" ብሎ ማሰብ አጥፊ ነው። ፍጹም ለመሆን ስትጥር አላስፈላጊ እና ጥቃቅን በሆኑ ነገሮች ላይ ትወጠራለህ፣ መነቃቃትህ እና ተነሳሽነትህም ይዳከማል። ጊዜህንም በከንቱ ታባክናለህ። ፍጹም ለመሆን ከመጣር ይልቅ ከስህተቶችህ መማርን ምረጥ። የአእምሮ ኢነርጂህን ፍጹምነት ላይ ብቻ እንዲያተኩር አታድርገው፤ ከስህተቶችህ ተማር! #3_ለውጥን_አለመፈለግ ሁሌም በምናውቀውና በለመድነው መንገድ መጓዝን እንፈልጋለን። አዳዲስ እድሎችን ለመሞከር እንፈራለን፣ መለወጥ አንፈልግም። ህልምህን እውን ለማድረግ የአእምሮ ኢነርጂህን በመጠቀም ካለህበት መፋዘዝ ውስጥ መንቃት አለብህ። ባለበት የረገጠ የትም አይደርስምና ለውጥን አትፍራ፣ በምትችለው ሁሉ መለወጥን ከዛሬ ጀመር። አይዞህ በርታ! አንተ በአስደናቂ ኢነርጂ የተሞላህ ነህ፤ ከሚመርዙህ ነገሮች ራስህን መከላከል የምትችለው #የአእምሮ_ኢነርጂ መጽሐፍን በማንበብ ነው፡፡ ስለ አእምሮህ አስደናቂ ኢርጂና እንዴት እንደምትጠቀምበት ያስተምርሀል፡፡ ምንጭ #የአእምሮ_ኢነርጂ መጽሐፍ @Ragxo44 @nbab2
Mostrar todo...
👍 1