cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

🌹🧕ዘይነብ ነኝ 💚የነብዩና 💖ሙሀመድ ﷺ💘 አፍቃሪ💞💘💓

Publicaciones publicitarias
194
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-430 días
Distribuciones de tiempo de publicación

Carga de datos en curso...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Análisis de publicación
MensajesVistas
Acciones
Ver dinámicas
01
ሙሀዶራ ክፍል 51 በኡስታዝ አብዱሏህ አ/ድ ከዙመር የላይቭ ስርጭት መድረክ የተወሰደ https://t.me/zumer_media
101Loading...
02
Media files
110Loading...
03
Media files
100Loading...
04
Media files
100Loading...
05
Media files
100Loading...
06
ባልሽን ደስተኛ ማድረግ ትፈልጊያለሽ       መልስ አው ከሆነ ተከተይኝ , , እንግዲያውስ  ሀቁን መወጣት ከቻልሽ የሚልሽን ስሚዉ አክብሬዉ💞🏃‍♀ 👍
90Loading...
07
Media files
80Loading...
08
Media files
10Loading...
09
ሰብር ማለት እንባ አይንህን አየሞላው ከአላህ ውጪ ማንም ሳያየው መጥረግ ነው።     @Nebil03😘
80Loading...
10
ሰብር ማለት በአንተ ላይ የሚጨክኑ ሰዎችን ታጋሽ አና ይቅር ባይ መሆን ማለት ነው።   @Nebil03😊
80Loading...
11
Media files
90Loading...
12
አንድ ታዳጊ ጥበብ ሲናገር እንዲ አለ : ❝የበታችነት ከተሰማቹ ጠረጴዛ ላይ ቁሙ ወይ ጣራ ላይ ዉጡ የበላይነት ይሰማቹዋል❞ አስተዉል ወንድሜ ይሄን የመሰለ ጥበባዊ ንግግሬ አንተ ጋር ቆሞ መቆየት የለበትም፤ ወንበር ስጠዉና ይቀመጥ¡
90Loading...
13
ኢላሂ 😔 "ላንተ መንገር ትቼ ለሰው ነገርኩና... ገርቶ የነበረው እንደገና ጠና።" @HALAL_POST
90Loading...
14
ያ አላህ...❤️ ልቤን ላንተ ውሳኔ የተገራች አድርግልኝ ደስታ ማያጣማት ሀዘን የማይሰብራት ነፍስን አድለኝ🤲 🦋حياة يواوا😊🦋 @Halal_post
70Loading...
15
|   በአላህ ይሁንብኝ በዚህች ዱንያ ላይ የአላህን መልዕክተኛ ﷺ ከማየት በላይ ያመለጠን ነገር የለም!💔🥺     | اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه وسلم
80Loading...
16
Audio from Rabia
100Loading...
17
ንም_በዚሁ_ምግባር_እንዲሰለጥኑም_ሲያዝ_ውስጣቸውም_እንዲሰርፅና_የማንነታቸው_አካል_እንዲሆን_ሲጠይቅ ይታያል። መልካም ስነ-ምግባርን የኢማን መገለጫና የእስልምና ጤናማነት መለኪያ አድርጎታል። #ሰናይ_ስነ-ምግባር_ከነፍሳችን_ጋር_ጥልቅ_ማንነትና_የፀና_መሰረት_ያለው_ሲሆን_ፍላጎታችንና_ምርጫችን_በጎና_መጥፎ እንዲሁም ፀያፍም ሆነ ውብ ስራዎቻችን የሚመነጩበት የሕይወታችን ክፍል ነው። ነፍሳችን በባህሪዋ ስለሁሉም ነገረ ምቹ ናት። ይህም ማለት የመጥፎ ወይም የጥሩ ተፅዕኖ ለመቀበል ሁሌም ዝግጁ ነች። ነፍሳችንን ጥቂት ስልጠና ብንሰጣት ሐቅንና መልካምን የመውደድ፤በጥሩ ነገር መነሳሳት፤ ቆንጆን ነገር ማፍቀር፤ መጥፎን የመጥላት ባህሪን እንድትላበስ ማድረግ ይቻላል። ይህ ባህሪዋ መልካምና ተወዳጅ ተግባራትን ያለ ማንም አስገዳጅነት ወደ መተገበር ያሸጋግራታል። ይሄኔ ነፍሳችን “የመልካም ስነምግባር” ባለቤት ትሆናለች። ስነ-ምገባር ከሰው የሚመነጭና ካለማንም አስገዳጅነት የሚፈፅመው ተግባሩ መገለጫ ነው። ለምሳሌ፡- ሆደ ሰፊነትና እርጋታ፤ ታጋሽነትና ቻይነት፤ ቸርነትና ጀግንነት፤ ፍትሀዊነትና በጎነት ወዘተ የመልካም ስነ-ምግባር መገለጫዎች ናቸው። #በተቃራኒው_ነፍስ _ሊደረግላት_የሚገባውን_ማስተካከያ_አልያም_እንክብካቤ_ካልተደረገላት_ወይም በመጥፎ አስተዳደር ካደገች መጥፎውን ጥሩ፤ ቆንጆውን ደግሞ የሚያስጠላ አድረጋ መመልከት ባህሪዋ ይሆናል። ከዚያም ቆሻሻና ርካሽ ተግባራትንና ንግግሮችን ያለምንም አስገዳጅነት ትተገብራለች፤ ትናገራለች። እንድን መጥፎ ስራ በንግግርም ሆነ በተግባር የምንሰራውና ያለማንም አስገዳጅነት የምንፈፅመው ከሆነ መጥፎ ስነ-ምግባር የሚል ስም እንሰጠዋለን። ከነዚህ ስራዎች መካከል እንዴ፣ ሐሰት መናገር፣ ትዕግስት ማጣት፣ ስግብግብነት፤ ድርቅና፤ ፈላጭ ቆራጭ መሆን፤ መጥፎ መናገር፤ ብልግና ወዘተ የመጥፎ ስነ-ምግባር ምሳሌዎች ናቸወ። #ታላቁ_ዓሊም_ሐሰን_አል_በሰሪ_እንዲህ ይላሉ፡- “መልካም ስነ ምግባር መገለጫ የፊትን ገፅታን ፈታ ማድረግ፤ አለመተናኮል ነው።” ዐብደሏህ ኢቡኑ መባረክ ደግሞ፡- “መልካም ስነ ምግባር በሶስት ነገር ይገለፃል ከሐራም ነገር በመራቅ፤ ሐላል ነገር በመፈለግና ቤተሰብን በተገቢው መንገድ መምራት ነው” ይላሉ። ሌሎች ዑለሞቻችን ደግሞ “መልካም ስነምግባር እጅን ከመጥፎ መሰብሰብና የሙእሚንን ምክንያት መቀበል (ሙእሚንን ከነችግሩ መቻል ነው።)” ብለዋል። የመልካም ስነ ምግባር መገለጫዎች ብዙ ናቸዉ፡፡ ከእነርሱ መካከል “ብዙ ይሉኝታና ሐያው ያለው፣ ሰዎችን ከመተናኮል የራቀ፣ መልካም ጎኑ ዘወትር የሚነሳለት፣ ምላሱ ለእውነት የተገራ፣ ንግግሩ ጥቂትና ስራው ብዙ፣ የምላስ ወለምታ (ስህተቱ) ያነሰ፣ የማያስፈልግ ነገር የማያበዛ (በንግግርም በምግብም)፣ ለበጎ ነገር የቀረበ፣ ክብሩን የሚጠብቅ፣ታጋሽና አመስጋኝ፣ የአሏህን ውሳኔ ወዳጅና ሆደ ሰፊ፣ ቃልኪዳኑን ፈፃሚና ጥብቅ የሆነ፣ ተራጋሚና ተሳዳቢ ያልሆነ፣ ነገር አዋሳጅና ሀሜተኛ ያለሆነ፣ ከምቀኝነት ከችኩልነትና ከስስታምነት የፀዳ፣ ፈገግተኛና ዝምተኛ፣ ለአሏህ ብሎ የሚወድና የሚቆጣ … ነው።” #ጀሊሉ_በመልካም_ስብዕና_ያንፀን😥😥 ┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓ በቴሌግራም አድራሻችን👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie በWhatsap ግሩፓችን ለመቀላቀል ከፈለጉ 0936994553 ያናግሩን ┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
50Loading...
18
#ወዳጆቼ_3 አይነት #ጓደኛ አለ። ከአንደኛውና ከሁለተኛው ላይ ትኩረታችሁን ሙሉ በሙሉ አታድርጉት። ሁለ ነገራችሁን ሰጥታችሁም አትንከባከቡት። ነገር ግን #ሶስተኛውን በደምብ ተንከባከቡት ይጠቅማችኋልና። አንደኛው ሁለተኛውና ሶስተኛው የጓደኛ አይነት ምንድን ናቸው? #የመጀመሪያው የጓደኛ አይነት በሆነ ጉዳይ ልናገኘዉ የምንችል ሆኖም ግን ሁሌም የማናገኘው ጓደኛ ነው። ሁለተኛው ጓደኛ ደግሞ እስክንሞት ድረስ አብሮን የሚኖር እኛ ስንሞት ግን አብሮን የማይሆን ነገር ነው። ይህኛው የጓደኛ አይነት የኔ የምንላቸው ሐብትና ቤተሰብ ናቸው። #ሶስተኛው ከላይ ከተጠቀሱት የተለየ የሚያደርገው ከሞትን በኋላም እንኳ አብሮን የሚሆን በዱንያም ብቻ ሳይሆን በአኺራም የማይለየ ጓደኛ ነው። ይህ ጓደኛ ምን እንደሆነ ታቃላችሁ?? #አዎ_ሶስተኛውን_ጓደኛችን በዱንያም ሆነ በአኺራ ከኛው ጋር አብሮን የሚሆነውና ልንንከባከበው የሚገባ ጓደኛችን ነዉ፡፡ እሱም #በዱኒያ ስንኖር የሰራነዉ መልካም #ስራችን ነው። ዱንያ ላይ የምንሰራው ስራ እዚህ ብቻ ሳይሆን በአኺራም አብሮን ነው ሚሆነው። ዱንያ ላይ ጓደኛ አድርገን የያዝነው ስራችን 👉 #ኸይር ከሆነ በአኺራ የምንገናኘው ጓደኛችንም መልካም ነው። ነገር ግን በተቃራኒው ከሆነ ተቃራኒ ሚሆነው፡፡ #አሏህ_ያግዘን! #መልካም_ኸሚስ❤️🥰 ┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓ በቴሌግራም አድራሻችን👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie በWhatsap ግሩፓችን ለመቀላቀል ከፈለጉ 0936994553 ያናግሩን ┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
80Loading...
19
አንድ እውቀትን ፈላጊ ሰው ናቸው! እውቀትን ፍለጋ በሚዞሩ ወቅት ካጋጠሟቸው አስገራሚ አጋጣሚዎች አንዱን እንዲህ ሲሉ ይነግሩናል። « #እውቀትን_ላድን_ከሃገር_ሃገር እዘዋወር ነበር። ታዲያ ሲርበኝ በደረስኩበት አካባቢ ወዳገኘሁት ቤት ጎራ እላለሁ ያበሉ ያጠጡኛል፣ ሲመሽብኛ መስጂድ ውስጥ አድራለሁ። መስጂድ የሌለበት አካባቢ ከሆነ ደግሞ ወዳገኘሁት ቤት ጎራ ብየ እንዲያሳድሩኝ እጠይቃለሁ። ከለታት ባንዱ ቀን ታዲያ ባቅራቢያየ ወዳገኘሁት ቤት ጎራ ብየ ምግብን ጠየኩ። የቤቱ እመቤት ግባ አለችኝ ። ( #ኸልዋ_እንዳይሆን_ስል) ሶስተኛ ሰው መኖሩን አረጋግጨ ገባሁ፣ ምግብም ቀረበልኝ፣ ልበላ እየተሰናዳሁ ሳለሁ አባ ወራው ከች አለ። « #ማን_ነው_ይሄ_ሰው? ሲልም ጮኸ። ሚስቲቱም ደረሳ ነው ። ምግብ ፈልጎ ነው። ምናምን እያለች ልታረጋጋው ሞከረች። ባልዮው ግን በንዴት ፊቱ በርበሬ መስሏል ። #ለምን_ምግባችንን ይበላል ? ሌላ ቤት አጥቶ ነውን? እያለ ማጎምጎሙን ቀጠለ። #አሏህ_ይስጥልኝ_ብየ_ምግቡን ትቼ ወጣሁ። እንዲሁ ደግሞ በሌላ ጊዜና በሌላ ቦታ ወደ አንዱ ቤት ጎራ አልኩ። የቤቱ አባ ወራ አየኝና ግባ ብሎኝ ገባሁ። እኔን ሊያስተናግድ በደስታ ሽር ጉድ እያለ ሳለ በመሃል ገበያ የነበረች ሚስቱ ከተፍ ትላለች። እኔን እንዳየች ፊቷ በርበሬ መሰለ። #ያኛውን_አባ_ወራ_አስታወሰችኝ። ለምን ምግባችንን ይበላል? ሌላ ቤት አጥቶ ነውን? ብላ ስታጎመጉም፣ ያኛው አባ ወራ ፊቴ ላይ ድቅን አለ። አሏህ ይስጥልኝ ብየ ምግቡን ትቼ ልወጣ ስል፣ ባልየው እጄን ይዞ አስቀመጠኝና፣ « #ለምን_ሳትበላ_ትወጣለህ?» አለኝ። እኔም ከዚህ በፊት ያጋጠመኝን አጋጣሚ ቦታውን ሳይቀር እየጠቀስኩ አጫወትኩት። ከዚያም ያጋጣሚ ነገር አይገርምምን? አልኩት እሱ ግን እንዲህ ሲል ይባሱን እኔኑ አሰገረመኝ፦ « #ያ_የተበሳጨብህ _አባ_ወራ_የሚስቴ መንድም ሲሆን ሚስቱ ደግሞ የኔ እህት ነች »፡፡ ዓጂብ ለምን ንፍጉነት?? ሰዉ የሪዝቁን እንጂ ሌላን ላይነካ የምን ማጉረምረም ነዉ!? #አሏህ_ለጋሾች ያድርገን! ┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓ በቴሌግራም አድራሻችን👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie በWhatsap ግሩፓችን ለመቀላቀል ከፈለጉ 0936994553 ያናግሩን ┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
30Loading...
20
الأعمى يتمنى أن يشاهد العالم والأصم يتمنى سماع الأصوات والمقعد يتمنى المشي خطوات والأبكم يتمنى أن يقول كلمات .....وأنت تشاهد...تسمع...تمشي...وتتكلم #ዐይነ አዕማዉ ዐለምን ማየት ይመኛል #መስማት የማይችለዉ ድምፆችን መስማት ይመኛል #ሽባ የሆነ(መራመድ የማይችል) በእግሩ መሄድን ይመኛል መናገር የማይችለዉ(ዱዳዉ) መናገርን ይመኛል! #አንተ_ግን_ታያለህ_ትሰማለህ_ትሄዳለህ_ትናገራለህ! ምን ጎደለህ? ጌታህን አመስግን! #ሁላችንም ይህን ትልቅ ኒዕማ እናመስግን እስኪ!😍 ስፍር ቁጥር ለሌለዉ ፀጋህ ጌትዬ ምስጋና ይገባህ! ┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓ በቴሌግራም አድራሻችን👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie ┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
50Loading...
21
#ልሁንሎት_ፊዳ💚 ያን የረገጡትን አፈሩን ባረገኝ የጫማቸውን ሶል ተለጥፌ እንደገኝ ያን ሲዋካቸውን አረኩን ባረገኝ በረዷማ ጥርሱን ስተሻሽ እንድገኝ ምን አለ በሆንኩኝ ምርኩዝ በትራቸው ጨብጦኝ እንዲውል ልስልስ መዳፋቸው #ብሆን_ኖሮ_ያኔ_ኢስሚድ_ስር_ኩላቸው አልታጣም ነበር ከሰፊው አይናቸው ።።። #ያ_ረሱለሏሂ💚 አንቱን የኔን ህይወት አንቱን የኔን ለዛ እንደው እንደ ዋዛ መተው ያቆሰሎት ያኔ እንደነበሩ ቢደርሰኝ ኸበሩ ሲራዎን ስሰማ ውስጤ መረቀዘ ታመመናም ደማ አንቱ ደም ግባቴ የኔ ጤና ህይወት እንደው እንዲህ በሩቅ በኸበር ከምጨስ ባካል ተገኝቼ ፊዳ በሆንኩሎት የጧኢፍ ቂላቂል ድንጋይን ሊያኖጉ ትልቅ አይቀር ትንሽ ወዳንቱ ሲጠጉ ፊትዎት ተገኝቼ እንደ ሃውልት ቁሜ ውግርት ፍንከታውን ዉጬ ተቋቁሜ በሆንኩ በላይ ካቅሜ እንዲህ ሆነው ነበር መባልኩን ሰምቼ በምፀት ድብደባ እንዲህ ከምጎዳ ስፍራው ላይ ተጥጄ በሆንኩሎት ፊዳ ምን አለ በኖርኩኝ ከውጊያው ከሰልፉ ያኔ አንቱን ሊያጠፉ ሴራ ሲጠልፉ ፍላፃን አስለው ሲያስወነጭፉ ጀሰዴ ገላየ ጋሻ ይሁን መከታ ቀስታቸው ይሰካ በሰይፉም ልመታ ላንቱ ከለል ሆኘ ከቶ ምን ሊያሰጋኝ ኢላማቸው ነቅቶ ውርወራውም ያፍጋኝ ቡጢያቸውም ይዱፍ ጦራቸውም ይውጋኝ #ተሰብሯል_ጥርሳቸው ደምቷል ግንባራቸው ሲባል እየሰማሁ በንዴት ከምጦፍ ባዘን ከምጎዳ ምን አል ያኔ ኖሬ በሆንኩሎት ፊዳ #ያረሱለሏሂ❤️ ምን አል ኖሬ ያኔ ያንቱን ሃዘን እኔ ስቃይዎም ለኔ እንባዎትም ላይኔ ቁስሎ ለጀሰዴ እራቦት ላንጀቴ ሃሳቦት ለሆዴ ተነባብሮ ጎርፎ ባረፈብኝ ባንዴ እንዲህ ሆነው ነበር ሲባል እየሰማሁ እርር ትክን ቅጥል ሰርክ ሌት ማለዳ ብየ ተብሰልስየ ከሰው ሆኘ ባዳ የንዴት እንባየ ዘንቦ ከሚቀዳ ያንቱን ለኔ አድረጎ በሆንኩሎት ፊዳ #የኔ_ግርማ_አርማየ አንቱ ታላቁ ሰው ሰው ሰው መሆኛየ ላንቱ እኔ ላልቅስ ከእንባም አልፎ ደም #ላንቱ እኔ ልራብ ልሰዋ እኔው ልቅደም ,,,,,,, ላንቱ ልጎሳቆል ልጎዳ ልጎዳ ከቶ በስንት ጣሙ ላንቱ መሆን ፊዳ ላንቱ ከሆንማ ከቶ መች ላቅማማ እንኳንስ ሌላውን አባቴን እናቴን ባንድነት ህይወቴን ጠቅልሎስ ብቀማ ስቃዮን ልሰቃይ ቅጣቶን ልቀጣው አዎን አይን አላሽም ላንቱ ሁሉን ልጣው ባተርፍ ነው እንጂ ባንቱ እኔ አልጎዳ እድሉ ይምጣ እንጂ #በሙሉ_ደስታ_ነው_ምሆንሎት_ፊዳ💚 ┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓ በቴሌግራም አድራሻችን👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie በWhatsap ግሩፓችን ለመቀላቀል ከፈለጉ 0936994553 ያናግሩን ┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
40Loading...
22
#መልካም_ስብዕና! መልካም ስብዕና የደጋጎች ዉበት ነዉ፡፡ #መልካም_ስብዕና ከስልጣን በላይ ስልጣን፤ከሀብት በላይ ሀብት ከቁንጅና በላይ ዉበትና ማራኪነት ያለዉ ነዉ፡፡መልካም ስነ ምግባር አጣጥመዉት የማይጠገብ፤አኝከዉት የማይደርቅ፤ረግጠዉት የማይጎረብጥ፤ሳይናገር ማዘዝ የሚችል አብሮ እያለ የሚናፈቅ ሲለዩት የማይረሳ አስገራሚ የኻሊቁ ስጦታ ነዉ፡፡ #መልካም_ስነ_ምግባር_ያለዉ_ሰዉ_አምሳያዉ_ልክ_እንደ_ከረሜላ_ነዉ፡፡ከረሜላ ቢቀጠቀጥ፣ቢቆረጠምና ቢሸራረፍ ጣፋጭነቱን እንደማያሳጣ ሁሉ መልካም ስነ ምግባርን ከጀሊሉ የታደለ ሙእሚንም ሰዎች መጥፎ ቢያደርጉበት፣ቢሰድቡት፣ቢያሙት፣ሒስድ ቢያደርጉበትና ልኩን ሳያዉቁ ቢያስተናንሱት እርሱ ለነርሱ መልካምን ከማሰብና ለእነርሱ በመልካም ከመዋዋል ዉጭ ፀባዩ አይቀየርም፡፡ ብዙ ጊዜ ትንሽ የሆኑ ሰዎችና ስለ ኢስላም አስተምህሮ ጠንቅቀዉ የማያዉቁ አወቅን አወቅን ባዮች መልካም ሰዎችን(ዉስጣቸዉ ንፁህ የሆኑ የዋሆችን) መጥፎ ለማድረግ ቢጥሩም መልካሞች ግን መልካሞች_ናቸዉ፡፡ የሚከተሉት ሸሪዓቸዉ ያመጣላቸዉን ትዕዛዝ እንጅ ነፍስያቸዉን አይደለም፡፡ #ይህ_ነዉ_የመልካም_ስነ_ምግባር_ጥግ፡፡አንድ ሰዉ መጥፎም ሆነ መልካም ዋለልን እኛ አቋማችን ተቀይሮ መጥፎዎች መሆን የለብንም፡፡ አንድ ትልቅ ዐሊም የመልካም ስነ ምግባር ምልክቶች ሶስት ናቸዉ አሉ፦ ➊፦ #የሌሎችን_አዛ_መሸከም_መቻል ➋፦ #ሌሎች ሙስሊሞችን አዛ አለማድረግ እና ➌፦ #መልካምም_ሆነ_መጥፎ ለዋሉልን ሰዎች እኛ ሁሌም መልካም መሆን፡፡ አዎ ትልቅ ሰዉ ማለት እነዚህን ነገሮች ተሸክሞ ማለፍ የቻለና #በነዚህ_ስነ_ምግባሮች_የታነፀ_ጀግና_ነዉ፡፡ قال الله تعالى {وَلَا تَسْتَوِي الْحَسَنَةُ وَلَا السَّيِّئَةُ ۚ ادْفَعْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ فَإِذَا الَّذِي بَيْنَكَ وَبَيْنَهُ عَدَاوَةٌ كَأَنَّهُ وَلِيٌّ حَمِيمٌ} (سورة فصلت 34) “መልካሚቱና ክፉይቱም (ፀባይ) አይስተካከሉም። በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ፀባይ (መጥፎይቱን) ገፍትር። ያን ጊዜ ያ በአንተና በእርሱ መካከል ፀብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ አዛኝ ዘመድ ይኾናል።” (ፋሲለት 34) #ምግባረ_ሰናይ_ሰዉ_በሄደበት_የሚወደድ_በሁሉም_ቦታ_ክብር_የሚሰጠዉና_ከሰዎች_አንደበት_በመልካምነቱ_የማይጠፋ_ሰዉ_ነዉ፡፡አንድ ሙእሚን ኢስላም ያዘዘዉን በመፈፀምና የከለከለዉን በመከልከል በሰናይ ምግባር የታነፀ ከሆነ ታላቅ ብስራት አለዉ፡፡የተስተካከለ ስነ ምግባር ኢስላም ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጣቸው ዐብይ ጉዳዮች አንዱ ነው። عن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما، قَالَ: لَمْ يكن رسولُ الله صلى الله عليه وسلم فَاحِشًا وَلا مُتَفَحِّشًا، وكان يَقُولُ: ((إنَّ مِنْ خِيَارِكُمْ أحْسَنَكُمْ أخْلاَقًا)). متفقٌ عَلَيْهِ. ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ አል-ዓስ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዳስተላለፉት የአሏህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦" #ከመካከላችሁ_መልካሙ_ስነ_ምግባሩ_ከሌሎች_የተሻለ_የሆነዉ_ነዉ"፡፡(ቡኻሪይና ሙስሊም) ታላቁ መልእክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የመልካም ስነ ምግባር ባለቤት ነበሩ፡፡ قَالَ اللهُ تَعَالَى: {وَإنَّكَ لَعَلَى خُلُقٍ عَظِيمٍ} [القلم: 4]. "አንተ እኮ በታላቅ ስነ-ምግባር ላይ ነህ"፡፡(አል_ቀለም፥4) ከሁሉም ፍጡር በላይ መልካም የሆኑት ታላቅ ነቢይ ተከታዮቻቸዉ መልካም እንዲሆኑና ከመጥፎ ባህሪያት እንድርቁ መክረዋል፡፡ #መልካ_ስነ_ምግባር_የትክክለኛ_ኢማን_ውጤት_ነው ። وعن أَبي هريرة رضي الله عنه قَال: قَالَ رسول الله صلى الله عليه وسلم: ((أكْمَلُ المُؤمنينَ إيمَانًا أحسَنُهُمْ خُلُقًا، وَخِيَارُكُمْ خِيَارُكُمْ لِنِسَائِهِمْ)). رواه الترمذي، وقال: (حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحيحٌ). አቡ ሁረይራህ ረዲየሏሁ ዐንሁ ባስተላለፉት ሐዲስ የአሏህ መልእክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ ከሙእሚኖች መካከል ኢማኑ ይበልጥ ምሉዕ የሆነዉ ከመካከላችሁ በስነ ምግባሩ የተሻለ የሆነዉ ነዉ፡፡ከእናንተ መካከል ለሴቶቻቸዉ መልካም የሆኑህ ናቸዉ፡፡(ቲርሚዚይ ዘግበዉታል) በኢማንና በመልካም ስነ ምግባር መካከል ትስስር አለ፡፡የአንድ ሰዉ እምነት ምሉዕ እየሆነ በመጣ ቁጥር ስነ ምግባሩም በዚያኑ ልክ ጥራትና ድምቀት እያገኘ ይሄዳል፡፡ ለሰዎች መልካም በሆነ ቁጥር ከጌታዉም ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ እየሆነ ይሄዳል፡፡ » وعن عائشة رضي الله عنها، قالت: سَمِعْتُ رسولَ الله صلى الله عليه وسلم يقول: ((إنَّ المُؤْمِنَ لَيُدْرِكُ بحُسْنِ خُلُقِه دَرَجَةَ الصَّائِمِ القَائِمِ)). رواه أَبُو داود. የሙእሚኖች እናት የሆኑት ዓኢሻህ ረዲየሏሁ ዐንሃ እንዳስተላለፉት የአሏህ መልእክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ ሙእሚን በመልካም ስነ ምግባሩ የፇሚዎችንና የቋሚዎችን ማለትም የሰጋጆችን ደረጃ ያገኛል፡፡(አቡ ዳዉድ) ቀን በፆም ሌሊት ደግሞ በመስገድ ማሳለፉ ትልቅ ደረጃ አለዉ፡፡ምንዳዉም ከፍ ያለ ነዉ፡፡ይሁንና ሰዉየዉ በመልካም ስነ ምግባሩ ይህን ደረጃ ይጎናፀፋል፡፡በየዉመል ቂያማህ መልካም ስነ ምግባር ከማንኛውም ነገር የበለጠ ክበደት ይሰጠዋል፡፡ وعن أَبي الدرداءِ رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قَالَ: (مَا مِنْ شَيْءٍ أثْقَلُ في مِيزَانِ العبدِ المُؤْمِنِ يَوْمَ القِيَامَةِ مِنْ حُسْنِ الخُلُقِ). رواه الترمذي، وقال: (حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحيحٌ). አቡ ደርዳእ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዳስተላለፉት ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ በየዉመል ቂያማህ ከአማኝ የመልካም ስራዎች ሚዛን ዉስጥ ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የሚከብድ ስራ የለም፡፡(ቲርሚዚይ ዘግበዉታል ሐሰኑን ሶሒሕ ነዉም ብለዉታል) وعن أَبي أُمَامَة الباهِليِّ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رسول الله صلى الله عليه وسلم: (أنَا زَعِيمٌ ببَيتٍ في ربَض الجَنَّةِ لِمَنْ تَرَكَ المِرَاءَ، وَإنْ كَانَ مُحِقًّا، وَبِبَيْتٍ في وَسَطِ الجَنَّةِ لِمَنْ تَرَكَ الكَذِبَ، وَإنْ كَانَ مَازِحًا، وَبِبَيْتٍ في أعلَى الجَنَّةِ لِمَنْ حَسُنَ خُلُقُهُ). حديث صحيح، رواه أَبُو داود بإسناد صحيح. አቡ ኡማመተል ባሂሊይ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዳስተላለፉት የአሏህ መልእክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ እዉነተኛ ቢሆንም እንኳን ክርክርን የተወ ከጀነት ዳርቻ ላይ፣ለቀልድ እንኳን ቢሆን የማይዋሽ ከጀነት እምብርት ላይ፣ለመልካም ስነ ምግባር ባለቤት ደግሞ ከጀነት የላይኛዉ ክፍል ቤት ላይ እንደሚያገኙ ዋስትና እሰጣችኃለሁ፡፡(አቡ ዳዉድ ዘግበዉታል) #ኢስላም_ሰዎችን_ወደ_ጥሩ_ስነ_ምግባር_ጥሪ_ሲያደርግ_ሙስሊሞች
41Loading...
23
Media files
30Loading...
24
#መልካሞቹ💚 قال أحد الصالحين: عندما ترى عيبًا فِيَّ اخبِرني ولا تُخبر غيري فأنا المعنيُّ بتغييره ..ففي الأولى: نصيحة وأجر وفي الأخرى: غيبة ووزر. አንድ መልካም ሰው እንዲህ ይላሉ #በኔ_ላይ_ነውርን_ካየህ_እኔኑ_ምከረኝ፤ ለሌላ ሰው አትናገር። የሚመለከተው እኔን ነውና። የመጀመሪያው ተግባር ጥሩ ምክርንና አጅር የሚያስገኝ ሲሆን ሁለተኛው ተግባር ግን ሃሜትና ወንጀል ነዉ ። ┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓ በቴሌግራም አድራሻችን👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie ┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
40Loading...
25
#በፍቅራቸዉ_ወድቀን_ታሪካቸዉን_ሁሌም የምንናፍቀዉ! ምልጃቸውን ሁሌም የምንከጅለዉ ዕንቁ ነቢይ አንደበታቸው ውበታቸው፣መልካሙና ሰናዩ ስብዕናቸዉ፣ቁጥብነታቸዉ፣አስተዋይነታቸዉ፣ተዋዱዐቸዉ፣ክብር ለሚገባዉ ክብር መስጠታቸዉ...ኧረ ስንቱ……በቃ ሁሉ ነገራቸው ፍጥረቱን በፍቅር አንበርካኪ፣ ሐቢቢ ረሱሉሏሁ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም💚 #ሁለ_ነገራቸዉን_ባስተዋልነዉ_ቁጥር_ዐጃኢቡ_አያሌ_ነዉ! #ሰዎች ላይ እያላገጠ ግጥም በመግጠም አቻ የሌለውን ሐሳን ኢብኑ ሳቢትን ከእለታት በአንዱ ቀን ቁረይሾች ብር ከፍለው ረሱለሏህ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ እንዲያላግጥ አዘዙት። ገጣሚው ሐሳን በረሱል💚 ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም #ገፅታ_ለማላገጥ_ይመቸው ዘንድ በግልፅ ሊመለከት አንዲት ኮረብታ ላይ ቆም ብሎ መምጫቸውን ይጠባበቅ ጀመር። ከዚያም ድንገት ረሱል ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ብቅ አሉ፡፡ ሐሳን ኢብኑ ሳቢት የግጥም ተሰጥኦው በሙሉ ተበታተነ፣ ፈዘዘ፣ ደነዘዘ፣ዉስጡ ተርበተበተ፣ቃል ሳይናገር ወደ ቁረይሾቹ ተመልሶ ሄደ። እንዲህም አለ « #እንኩ_ገንዘባችሁን_እኔ_አልፈልግም_ደግሞ_የላካችሁኝን ጉዳይ ትቼ የሙሐመድን መልዕክተኝነት መስክሬ ተመልሻለሁ።»ሲል አዋጁን አወጀ!አሏሁ አክበር! #የቁረይሽ ሙሽሪኮች በሙሉ በሰሙት ነገር ተደናገጡ ፤ ሐሳንን በዚህ ቅፅበት ምን እንደቀየረው ግራ ቢገባቸው፦ « ሐሳን ምን ሁነሃል? እኛ ለዚህ ነው እንዴ የላክንህ?» አሉት። #ሐሳንም_ያየውን ትዕይንት እንዲህ ሲል ተረከላቸው፦ « #የፊቱን_ነፀብራቅ_ፈንጥቆ ሳየው፤ በእጆቼ አይኖቼን ወድያው ሸፈንኳቸው። #ለአይኖቼ ፈራሁኝ እንዳይጨልሙብኝ፤ #ማልቋቋመውን በአይኔ ስላየሁኝ። ነፍሱ ብርሃን ሁና አካሉ ጨረቃ፤ #ከዚህ_በላይ_ላየው_አይኔም_አይብቃቃ!» 😭😭 ብሎ ቁጭ አለ.... የኛው ነቢይ! የፍጥረተ ዐለሙ ልዩ! ያልናፈቀ ሙእሚን የለም ያንቱን ፊት ማየት! #ሙሐመድ__የመልካም ባህሪይ ባለቤት #ሙሐመድ__የቆንጆዎች ሁሉ መሪ #ሙሐመድ__የጭንቅ ጊዜ ገላጋይ #ሙሐመድ__ጨለማን በብርሀን ቀያሪ #ሙሐመድ__የፍጥረታት ሁሉ እንቁ #ሙሐመድ__የጥበብ ባለቤት #ሙሐመድ__የሩሱሎች መደምደሚያ #ሙሐመድ__የሙእሚኖች ጥንካሬ #ሙሐመድ__የዱኒያ ጌጥ #ሙሐመድ__ የጀነት ቁልፍ! ሶለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ ዐለይህ💚💚 ┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓ በቴሌግራም አድራሻችን👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie ┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
40Loading...
26
Media files
40Loading...
27
Media files
40Loading...
28
#ቁጥቡ_ዘማን_ሸይኽ_ዐብዱሏህ_አል_ሀረሪይን❤️_ዐረቡም_ዐጀቡም ለምን እንደሚወዳቸው ታውቃላችሁ? * ቁርአናዊ መመሪያን አንጸባራቂ፣ ሐዲሳዊ መረጃን አብሪ፣ የአሻዒራና የማቱሪዲያን አርማ.. የማንንም ድስኩር ሳይሰሙ ተክለው ያውለበለቡ የመሻይኹል ሀበሻ ብሎም የዓለም ሱፊይ ሸይኾቻችን መነጽር "ሸይኹል ኢስላም" ስለሆኑ ነው። * እንዴትስ አይወደዱ? ማስመሰል የማይወዱ፣ ሙናፊቅ ጋር "እከክልኝ ልከክልህ" የማይሉ፣ የውሸታምን ጭንብል አውልቀው የቀጣፊን ቅጥፈት አጋልጠው፣ ፍሬውን ከገለባው ለይተው ለኡማው ዒልምን ፈትፈትው የሚመግቡ ሩኅሩህ ሸይኽ ሁነው። እንዴትስ አንውደድዎ ሸይኻችን! ሙሐዲሳችን! * ስንቱን አየነው... ሸይኽነቱን በገንዘብ ሲሸጥ፣ ነጩን ጥምጣም በማስመሰል ሲያጠለሸው፣ ሐቁን በፍርሃት ሲያድበሰብሰው... አንቱ ግን ጽኑ ተራራ.. የማይነቃነቅ ጋር... ነፋሳ የሚያወዘውዘው ግንብ ሁነው... ስድቡንም፣ ቅጥፈቱንም፣ ዛቻውንም ችለው ለኡማው ደረሱለት። * በዒልም ከተባለ ደግሞ በሐዲስ የዱንያ ሙሐዲስ ኖት፣ በተውሒዱም የሙብተዲዓን ምሽግ የነገነጉ ኡሱሊይ ሙተከሊም ኖት፣ በፊቅህም ፋቀሃዎችን ብሎም ሙጅተሂዶችን የተገዳደሩ ፈቂህ ኖት፣ በዓረብኛውም ስር የሰደዱ ሉጘዎይ ኖት፣ በተፍሲሩም አንጥረው የሚያጠጡ ሙፈሲር ኖት... ኧረ በስንቱ?! አንቱ ባሉበት ውሸታም አፉን ሲከፍት አልታየም። እንዴት አልውደዶት ሸይኼ!? ሸይኼ እኮራለሁ! Join👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie
40Loading...
29
💎 #ሴቶች‘ዬ_ክብራችን......💞 #የሴት_ልጅ_ክብር_ዲነል_ኢስላምን_ማክበሯ_ነው! ሴት ልጅ ለዲነል ኢስላም ክብር ካላት እያንዳንዱ ተግባራቷ አሏህን የምትፈራበትን መንገድ ትመርጣለች። ለወንዶች ፊትና ካለመሆን ወንዶችን ትጠብቃለች። በዚህን ሰአት የራሷ ማንነት ከወንዶች ዘንድ የተከበረች ትሆናለች፤ ማንነቷን፣ስሟን አስከብራለች፤ጠብቃለች። ከአሏህ ም ዘንድ የተወደደች ትሆናለች። #ለምሳሌ; ኢስላም ያዘዛትን የሰውነቷን ክፍል (ከ እጇ መዳፍ እና ከፊቷ ሲቀር ) ሒጃብ አሟልታ ስትሸፍን፣ኮስሞቲክስ ሳትቀባባ ብትወጣ) ማንም ወንድ እሷን ሆን ብሎ ሊረብሽ አይሞክርም፤ትከበሪያለሽ። ወንዶችንም ፊትና ላይ ከመጣል ትጠብቂያለሽ። #ሐያእ ይኑርሽ። #ሐያእ፦ ማለት ከኢማን አንዱ እና ዋናው ክፍል ሲሆን ሸሪዓ ባዘዘው መልኩ በመታዘዝ ከፀያፍት ተግባር የመከለከል ልዩ ተግባር ነው። ሐያእ ደግሞ ማድረግ ግዴታሽ ነው። #ሐያእ_ለሴት_ብቻ_ሳይሆን_ለወንድ_ጭምር_ነው። አስተውሉ!📢 ሴት ልጅ ለእኔ እንደ ሃብሃብ🍉ነች። ታዳ ጣፋጭ እና የማይጣፍጥ አለው። ስልሽ… ከገቢያ ቦታ ውስጥ ሃብሃብ እየተሸጠ እያለ አንድኛው የተሰነጠቀ ክፍል አለው በቀላሉ ለገዢዎች ጣፍጭ መሆኑን እና አለመሆኑን ማወቅ ይቻላል። ለየት ይላል በጣም ያምራል ሲያዩት ቀይ መሆኑን ያውቃሉ ግን አንዳቸውም አልገዙትም። ሌላ ያልታየውን እያነሱ ብቻ ይገዛሉ። ለምን እንደሆነ ታውቂየለሽ የማይገዙት የተሰነጠቀ ፓርት ስላለው በዚያ ውስጥ ቆሻሻ በቀላሉ ስለሚገባበት ነው። ማስተላለፍ የፈለኩት፦ 🔉🔉🔉🔉🔉🔉🔉🔉🔉 አንድት ሴት ሚኒ(አጫጭር፣ኢስላም የማይፈቅደውን የሰውነትሽን ክፍል የሚያሳይ) ልብሶች እየለበሽ ሰውነትሽን እያሳየሽ ስትሄጂ ወንዶች ሊማረኩብሽ ይችላሉ። ነገር ግን አንዳቸውም ለትዳር አያስቡሽም። ምክንያቱም ማንነትሽን ክብርሽን በአደባባይ ማሳየትሽ ውስጥሽ ታማኝ አይደለም ብለው እንዲያስቡ አድርጎታል። ـــــــــــــــــــــــــــــــــ …እህቴ ይብቃሽ ከዚህ በላይ በወንዶች አትታለሊ። ከወደደሽ ለጋብቻ ይጠይቅሽ! ┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓ በቴሌግራም አድራሻችን👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie ┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
30Loading...
30
❤️ እማ ♥ እስትፋሷ ሁኖ የህይወት ቀመሬ ከጫንቃዋ ውዬ ከጉያዋ አድሬ ከልቧ ላልጠፋ በደሟ ተፅፌ በመንገዴ ሁሉ ስጋዋ ምንጣፌ ስደክም ስረታ አጥንቷ ድጋፌ አምሳያ የሌላት ጥላ ከለላዬ በቃል የማልገልፃት ባለውለታዬ ❤️ https://telegram.me/nisaulmesharie
30Loading...
31
#የደጋጎች_ፋና💚 ➊ #قال_الإمام_أبو_سليمان الداراني رحمه الله "إني لأخرج من منزلي فما يقع بصري على شيء إلا رأيت لله عليّ نعمة ولي فيه عبرة". #አል_ኢማም አቡ ሱለይማን አዳራኒይ (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይላሉ፦ ከቤቴ ወጥቼ እይታየ አንድ ነገር ላይ አያርፍም አሏህ በኔ ላይ የዋለውን ፀጋ ያስተዋልኩና በርሱም ያስተነተንኩ ቢሆን እንጂ። ሱብሓን አሏህ! #ዓጂብ! #አንድ ክስተትን አንስተን ብናየዉ ወደድኩኝ፡፡ ታሪኩ #ስሙኒ_ይቀራል…ይላል፦ #ከአንድ ሰው በራፍ ላይ ቁጭ ብሎ ድንች የሚሸጥ ምሲኪን ሰው ነበረ። የቤቱ ባለቤት ሁሌም ወደ ውጪ ሲወጣ ይህንን ምስኪን ሰው ይመለከተው ነበረ። ቀኑን ሙሉ ብርድና ጸሀይ እየተፈራረቀበት ኑሮን ለማሸነፍ መድከሙ ስላሳዘነው በአቅሙ ሊረዳው ወሰነ። ነጋዴው አንዷን ድንች በ50 ሳንቲም ነበር የሚቸረችረው። ታዲያ ይህ ሰው ምስኪኑን ነጋዴ ለመርዳት በማሰብ በየቀኑ የአንድ ድንች ዋጋ እየሰጠው ለመሄድ ወሰነ። በየቀኑ 50 ሳንቲሙን እየሰጠው በአንጻሩ ምንም ድንች ሳይቀበል ይሄዳል። ከብዙ ጊዜ በኋላ ይህ ሰው እንደለመደው 50 ሳንቲሙን አኑሮለት ጉዞውን ቀጠለ። ድንገት ከኋላው “ ወንድሜ” የሚል ጥሪ ይሰማል። ዞር ብሎ ሲመለከት ምስኪኑ ነጋዴ ነበር በሩጫ የደረሰበትና የጠራው። ሰውየው በፈገግታ “ከስንት ጊዜ በኋላ ለምን በቀን በቀን 50 ሳንቲም በነጻ እየሰጠሁ እንደማልፍ ልጠይቀኝ ነው ያስቆምከኝ?” አለው ነጋዴው ግን እያለከለከ “አይደለም ኸረ” ሲል መለሰ። ይሄኔ ሰውየው ግራ ገብቶት “እና ለምን አስቆምከኝ?” ቢለው “የድንች ዋጋ 75 መግባቱን ልነግርዎት ነው፤ እናም ስሙኒ ይጎድላል” አለው አሉ። 😛😂😂 ይህንን ታሪክ የሰማሁኝ ቀን በጣም አስቆኝ ነበር። መለስ ብዬ ሳስበው ግን ከቀልድነቱ በላይ የአንዳንድ ሰዎች የአልጠግብ ባይነት ባህሪና ያለ ማመስገን ባህሪ የሚያንጸባርቅ መስሎ ታየኝ። አብዛሀኛው ሰዎች አመስጋኝ ፍጡሮች ናቸው ብዬ አላምንም። ልክ እንደዚህ ምስኪን ነጋዴ ነጻ በሚሰጠን ነገር ላይ እንኳን እንደራደራለን። የእኛ ባልሆነው ሀብት እንሟገታለን። በቸርነት በተሰጠን ነገር ሁሉ ይበልጥ እንጠይቃለን። ሃምሳ ሳንቲም ለምን በነጻ ተሰጠኝ ሳይሆን ለምን ስሙኒ ጎደለ የሚል አመለካከት ስላለን እኮ ነው አብዛኛዎቻችን ባለን ነገር መደሰት የሚያቅተን። ብዙ ጊዜ በየእለት ኑሮዋችን በነገሮች ላይ የምንደራደረው ልክ እንደዚህ ምስኪን ነጋዴ ነው። በነጻ የሚሰጠንን 50 ሳንቲም ሳይሆን የኑሮዋችንን ዋጋ እራሳችን ተምነን ቀሪው ጎደለ ብለን እንሟገታለን። ሰዎች የሚሰጡንን ነጻ ፍቅር፤ ነጻ ክብር፤ ነጻ እምነት ዋጋ የማንሰጠው ቀሪውን ስሙኒ ስለምናስብ ነው። እኛ በባህሪያችን ነጻ የሆነን ነገር ዋጋ አንሰጠውም እንደውም አንድ ተናጋሪ ሰዎች አይምሮዋችንን በደንብ የማንጠቀምበት ነጻ ስለተሰጠን ነው ሲል ሰምቸው ግርምት ጭሮብኝ ነበር። እውነት እኮ ነው፤ የላፕቶፓችንን ያህል አይምሮዋችንን ዋጋ አንሰጠውም። ላፕቶፓችንን ቫይረስ እንዳይነካው የምንጠነቀቀውን ያህል አይምሮዋችን እንዳይበከል አንጠነቀቅም። የሚያስደንቀው ግን የሰው ልጅ በምንም ያህል ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችላቸው ሀብቶቹ በሙሉ በነጻ የሚያገኛቸው ናቸው። በ50 ሳንቲሙ ያልተደሰተና ያላመሰገነ ሰው ስሙኒ ቢጨመርለት ምን ዋጋ አለው? በየቀኑ የሚቸረን 50 ሳንቲም ከበቂ በላይ ነው፤ አንዳንዴ ስሙኒው ይቀራል ብለን ሰጪውን ባናስቀይም መልካም ነበር፤ ነገር ግን ......!!! ብዙ ጊዜ ደስታችንን የሚነጥቀን የ “ስሙኒ ይቀራል” አይነት አመለካከታችን ነው። የተሰጠንስ 50 ሳንቲም? የተሰጠን ነጻ ፍቅር፤ ነጻ ክብር፤ ነጻ እምነት፤ ነጻ ጤንነት፤ ነጻ ተስፋ? ከምንም በላይ ነጻ ህይወትስ?....... ┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓ በቴሌግራም አድራሻችን👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie በWhatsap ግሩፓችን ለመቀላቀል ከፈለጉ 0936994553 ያናግሩን ┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
30Loading...
32
#ትወነጅለዋለህ_ያዝንልሃል! #ረሒሙ_ጌታችን_ጀለ_ጀላሉህ! ታሪኩን ከራሳችን ሕይወት ጋር እናጣምረዉ! ታላቁ አቢድ እና ዛሂድ ዙ ኑን አል ሚስሪይ ( #ሰውባን_ቢን_ኢብራሂም) አንድ እለት ልብሳቸውን ሊያጥቡ ወደ ኒል (ናይል)ወንዝ ወረዱ። ከዚያም አንድ ትልቅ ጊንጥ ወደ ወንዙ ሲመጣ ስላዩ እንዳይነድፋቸው በመጠንቀቅ ሁነቱን መከታተል ያዙ። ጊንጡ ዳርቻው ጋር እንደደረሰ ከወንዙ ትልቅ እንቁራሪት ሲወጣ አስተዋሉ። እንቁራሪቱም ጊንጡ እንዲጋልበው በመመቻቸት ተሸክሞት ወደ ወንዙ ገባ። እሳቸውም የሁለቱን ስራ ማብቂያ ለማየት ጋቢያቸውን ከክንንብ አውልቀው ወንዙን በመዋኘት ተከተሏቸው። ትልቁ ጊንጥ በእንቁራሪቱ እርዳታ ወንዙን አቋርጦ ሌላኛው ዳርቻ ጋር ወረደ። እንቁራሪቱም ባለበት ቆሞ ጊንጡን ይጠብቅ ጀመር። በክስተቱ እጅግ የተደመሙት #አል_ኢማም_ዙ_ኑንም_መጨረሻውን ለማወቅ ጓጉተው በድብቅ ጊንጡን ተከተሉት። ጊንጡም ቅጠሎች የተንዠረገጉባት አንዲት ዛፍ ጥግ ደረሰ። ከዛፉ ስር አንድ ወጣት ተኝቷል ( #ወጣቱ_ጠጥቶና_ሰክሮ_ነው_የተኛውና) ካጠገቡ ባዶ የመጠጥ (የኸምር) ጠርሙሶች ተኮልኩለዋል። ኢማም ዙ ኑን ከመጀመሪያው በተለየ መልኩ ክስተቱን በአፅንኦት ይከታተሉ ይዘዋል። ከዚያም ዛፉ ስር ትልቅ እባብ ወጣ። ሊነድፈው ቋምጦ ወደ ተኛው ወጣት እየተሳበም መጣ። ታዲያ ያ ትልቁ ጊንጥ እባቡ ጭንቅላት ላይ በመሰቀል በመርዙ ነድፎ ገደለውና ወጣቱን ከሞት ታደገው። #ጊንጡ_ይኸን_ሚሽኑን እንደጨረሰ ወንዙ ዳር ወደሚጠብቀው እንቁራሪት በማምራት እሱን እየጋለበ ወደመጣበት ተመለሰ። ዙ ኑን « #ሱብሓን_አሏህ » ሲሉ አግራሞታቸውን ገለፁ። ከዚያም በስካር ሽልብልቦሽ ወደተኛው ወጣት ቀረብ አሉና ከእንቅልፉ ቀስቅሰው ያስተዋሉትን ክስተት አጫወቱት። #ወጣቱም_የጌታውን_እዝነት_አበክሮ_ተረዳውና_ሰቅሰቅ_ብሎ_አለቀሰ፣ መጠጥን እርም ብሎ ትቶ ጥርት ያለ ተውበትን በማድረግ ወደ ጌታው ተመለሰና ትንታግ የአሏህ ባሪያ ሊሆን በቃ! #እዝነቱ_ሰፊ_የሆነዉ ጌታ ከወንጀል ጠብቆ ከእዉነተኛ ባሮቹ ያድርገን! አሚን! ┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓ በቴሌግራም አድራሻችን👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie በWhatsap ግሩፓችን ለመቀላቀል ከፈለጉ 0936994553 ያናግሩን ┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
50Loading...
33
አካል በበሽታ ሲጠቃ የምግብን ለዛ እንደማያገኘው ሁሉ ቀልብም በወንጀሎች ሲጠቃ የዒባዳን ለዛ አያገኝም። #አሏህ ከወንጀል ይጠብቀን😥 ┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓ በቴሌግራም አድራሻችን👇👇 https://telegram.me/nisaulmesharie ┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
30Loading...
34
Media files
40Loading...
ሙሀዶራ ክፍል 51 በኡስታዝ አብዱሏህ አ/ድ ከዙመር የላይቭ ስርጭት መድረክ የተወሰደ https://t.me/zumer_media
Mostrar todo...
record.ogg12.56 MB
ባልሽን ደስተኛ ማድረግ ትፈልጊያለሽ       መልስ አው ከሆነ ተከተይኝ , , እንግዲያውስ  ሀቁን መወጣት ከቻልሽ የሚልሽን ስሚዉ አክብሬዉ💞🏃‍♀ 👍
Mostrar todo...