cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

P H O E N I X B A T C H 2 k 1 2

#School_pics #School_day_pics #School_events #School_vibes_of_2K12 #crazy_class😋 ***********#PHOENIX_BATCH *******🤘😜😍😍😂join😜 Join 🤘join yadergachu Cross bemaderg tebaberun😂😂😂 Send 💬 ur pics @jasif @serendipity2568 @HRRB4 @Mahis_mood

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Publicaciones publicitarias
236
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Mostrar todo...
ORDER FROM TURKEY 🇹🇷

የተለያዩ የቱርክ * የሶፋ ጨርቆች * የአልጋ ልብሶች * የወንድ ሱሪዎች * የህፃናት ልብሶች * የሴቶች ቀሚስ * ብትን ጨርቆች * ሱፎች (በትዕዛዝ) ይዘዙ እናቀርባለን For info @wizbeki7 @Joshwa21

#UPDATED NEWS ♻️እስከአሁን ለፍሬሾች ጥሪ ያደረጉ ገቢዎች👇👇👇👇 1⃣ 🌐#Hawassa_University ♻️በ2013 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች #ምዝገባ_በበየነመረብ ”Online” ከሰኔ 15-20/2013 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ #የመግቢያ_ጊዜ ሰኔ 21-22/2013 ዓ.ም መሆኑን ይገልጻል፡፡ Online_ምዝገባ_ከሰኔ15-20/2013 👇👇👇👇👇 https://portal.hu.edu.et/Home/Freshman 2⃣ 🌐#WollegaUniversity ♻️ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች #ምዝገባ ከሰኔ 28-30/2013 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን መሆኑን እንገልፃለን፡፡ 3⃣ 🌐#DebarkUniversity ♻️በ#2013 ደባርቅ ዩንቨርሲቲ የተመደባቹህ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ግቢ መግቢያ ቀን ከሰኔ 26-30/2013 ድረስ ብቻ በመሆኑ በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ ዩንቨርሲቲው ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ አሳውቋል። 4⃣ 🌐#MekelleUniversity ♻️ዩኒቨርሲቲው የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ከሰኔ 21 እስከ 26/ 2013 ዓ.ም ጥሪ ለማድረግ ጊዚያዊ እቅድ ይዟል። 5⃣ 🌐#Selale_University 📌በ2013 ሰላሌ ዩንቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ነባር ተማሪዎች ከምርጫ በኋላ ግቢ ከተጠሩ በኋላ ማለትም ከሰኔ 21/2013 በኋላ በሳምንቱ ጥሪ እንደሚደረግላቸው የሰላሌ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት መረጃ አድርሰዋል። 6⃣ 🌐#Bahirdar_University ♻️በ2013 የትምህርት ዘመን በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ አዲስ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ሰኔ 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም በመሆኑ በዕለቱ ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታከናውኑ እየገለጽን በምዝገባ ወቅት የ10ኛና የ12ኛ ክፍል የብሄራዊና ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣ 3x4 ስድስት ጉርድ ፎቶግራፎች፣ የመኝታ አልባሳትና የስፖርት ትጥቅ አሟልታችሁ እንድትገኙ እናስታውቃለን፡፡ 7⃣ 🌐 #ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ የአዲስ 🔖 ገቢ ተማሪዎች ጥሪና ምዝገባ ከሰኔ 26 እስከ 30/2013 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አሳውቋል። 8⃣ 🌐#ደብረ_ብርሀን_ዩኒቨርሲቲ 🔖 ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ከሰኔ 25/2013 ዓ.ም በኋላ ጥሪ አደርጋለሁ ብሏል። 9⃣ 💠#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ 🔖 በ2013 የትምህርት ዘመን የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ መርሃግብር ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ሰኔ 23 እና 24 /2013 ነው። 🔟 💠 #አሶሳ_ዩኒቨርሲቲ 🔖 የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 26 እስከ 30/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል። 1⃣1⃣ 💠 #ደብረ_ታቦር_ዩኒቨርሲቲ አዲስ 🔖 ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 26 እስከ 30/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል። 1⃣2⃣ 💠 #አዲስ_አበባ_ዩኒቨርስቲ ለ2013 #አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሰኔ 01 እና 02 2013 ዓ.ም በ http://portal.aau.edu.et በመጠቀም የኦንላየን ምዝገባ እንድታከናውኑ አሳስቧል። 1⃣3⃣ 🌐#Semera_University #ሰመራ_ዮኒቨርስቲ ♻️በ2013 የትምህርት ዘመን በሰመራ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ አዲስ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ሰኔ 26 እና 27 ቀን 2013 ዓ.ም በመሆኑ በዕለቱ ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታከናውኑ እንገልፃለን ። 1⃣4⃣ 🌐#የወሎ _ዩኒቨርሲቲ ♻️አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 28 እና 29/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል። ለአስተያየት ፣አልያም ለጥያቄ👇👇👇 @Entrance_Exambot @yerasulwadjnegn 🔥ትምህርት ነክ መረጃ ለማግኘት👇👇 @Ethio_Entrance_preparation_Exam @Ethio_Entrance_preparation_Exam 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
Mostrar todo...
አምቦ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ በጊዚያዊነት ሰኔ 24 እና 25/2013 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል። ከሰኔ 06 እስከ ሰኔ 20/2013 ዓ.ም ልዩ የምርጫ እረፍት ጊዜ መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ይሁን እንጂ ወደየመጡበት አካባቢ መሄድ የማይፈልጉ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው መቆየት እንደሚችሉ እና የተማሪዎች አገልገሎትም እንደማይቋረጥ የዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መንግስቱ ቱሉ ባላቻ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። ከምርጫው በኋላ የነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ሰኔ 21 እና 22/2013 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
The average adult will spend 34 years of their life staring at screens. #Humans Join and share @SHOCKINGFACT
Mostrar todo...
የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 ጀምሮ እንደሚሰጥ የአ/አ ትምህርት ቢሮ አሳወቀ። በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 23-25/2013 ድረስ እንደሚሰጥ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ አሳውቋል። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
"አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከሰኔ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ" - የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመጪው ምርጫ በኋላ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ የየሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። ከምርጫው በኋላ ሰኔ 21 ሁሉም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ነባር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመጪው ምርጫ ወደደቤተሰቦቻቸው በመሄድ በምርጫው ይሳተፋሉ ብለዋል። "የተማሪዎቹ መሄድ ግዴታ አይደለም" ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው ፤ መምረጥ ለሚፈልጉ ነባር ተማሪዎች እንዲመች ከምርጫው በፊትና በኋላ ያሉ ቀናት የዕረፍት ጊዜ እንደሚሆኑ ገልፀዋል። "ምርጫ ማድረግ መብት እንደመሆኑ፤ መምረጥ የማይፈልጉ ነባር ተማሪዎች በያሉበት ዩኒቨርሲቲ መቆየት ይችላሉ" ብለዋል። ነባር ተማሪዎቹ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ባዘጋጀው የበይነ መረብ የመራጭነት መመዝገቢያ አማካኝነት በምርጫው ለመሳተፍ የመራጭነት ምዝገባ አድርገዋል። ተማሪዎቹ ወደየመጡበት አካባቢ በመሄድ በምርጫው እንዲሳተፉ ምርጫ ቦርዱ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል። ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ : https://t.me/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h @tikvahuniversity
Mostrar todo...
#update የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከ2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ጋር ለቀረቡ ቅሬታዎች የተሰጠ ምላሽ እና የተማሪዎች ዳግም ምደባን ከዛሬ ግንቦት 16/2013 ዓ.ም #ከ10 ሰዓት ጀምሮ በበየነ መረብ መመልከት ይቻላል ብሏል። @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
#ማስታወሻ በ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወስደዉ ቅሬታ ያቀረቡ ተማሪዎች ዳግም ምደባ ከዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በበየነ መረብ መመልከት ይችላሉ። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከ2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ጋር በተያያዘ 23 ሺህ 100 ቅሬታዎች ቀርበውለት ምላሽ ሰጧል። በዚህም • የጤና ችግር ያለባቸውና ማስረጃ ያቀረቡ፣ • አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች፣ • ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናት ተማሪዎች፣ • በፆታ ስህተት የተመደቡ ተማሪዎች፣ • መንትዮች፣ • በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ የሚገኙ ተማሪዎች ያቀረቧቸው በጠቅላላው 1 ሺህ 891 ቅሬታዎች ምላሽ አጊኝተዋል። ከትምህርት ምርጫ ቅያሬ ጋር በተያያዘ (የተፈጥሮ ሳይንስ ተምረው ማህበራዊ ሳይንስ የተመደቡ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተምረው የተፈጥሮ ሳይንስ የተመደቡ) 386 ተማሪዎች ምላሽ አጊኝተዋል። ከተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መራቅና ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ጋር በተያያዘ የቀረቡ ቅሬታዎች ሚኒስቴሩ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ በተመደቡበት እንዲቀጥሉ ወስኗል። ቅሬታ ያቀረቡ ተማሪዎች ከሰኞ ግንቦት 16/2013 ዓ.ም ጀምሮ የቅሬታውን ምላሽ በበይነ መረብ መመልከት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አሳውቋል። ምንጭ:- MoSHE @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
#MoSHE የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተው የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ወደተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ እንደሚደረግ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል። የዘንድሮውን የመመዘኛ ፈተና ካለፉት ከ147 ሺ በላይ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 206 ተማሪዎች በሚፈልጉት የትምህርት መስክ እና የትምህርት ተቋም እንዲመደቡ መደረጉን ተገልጿል። ከምደባ ጋር ተያይዞ ቅሬታ ካቀረቡ 23 ሺህ በላይ ተማሪዎች መካከልም ከ1 ሺህ 800 በላይ የሚሆኑት ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ የምደባ ማስተካከያ ተደርጎላቸዋል። የትምህርት መስክ ምርጫን አስመልክቶ በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተፈጠሩ ስህተቶችን በማረም 386 ተማሪዎች በመረጡት ዘርፍ እንዲመደቡ ተደርጓል ተብሏል። ከፍተኛ የጤና እክል ያለባቸው፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች ፣ ነፍሰ ጡር እና ከሁለት አመት በታች ልጅ ያላቸው እናቶች ፣ አካል ጉዳተኞች እና ከአርብቶ እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ቅሬታን በማየት በቂ ማስረጃ ላቀረቡት አዎንታዊ ምላሽ ተሰጥቷል። በሌላ በኩል ፦ የትምህርት ተቋማትን ምርጫ በሚመለከት ርቀትን፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መሰረት አድርገው የቀረቡ ጥያቄዎችን ውድቅ ማድረጉን ሚኒስቴሩ ማሳወቁን ኢቢሲ ዘግቧል። @tikvahethiopia @tikvagethiopiaBOT
Mostrar todo...