cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የአባቶቼን ርስት አልሰጥም

💒💒ለምጠፋ መብል ሳይሆን ለዘለዓለም ሕይወት ሊሆን ይገባል 💒💒💒የሐ.፫፥፭ እግዚአብሔር አምላካችን የዘለዓለም ሕይወት በምናገኝበት ጽኑ ክርስትና ራሳችንን የምንመረምርበት ንጹሕ ልቡና በምክረ ካህን በምንኖርበት ትህትና እንዲያጸናን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አስተየት መልዕክት ካለዎት በዚ ቦት ያገኙኝ 👇👇👇👇 @Tadeyedingelbot https://t.me/yeabatoch 👆👆👆👆

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
381
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

፰ ተዐቀብ ከመ ኢትኩን ዘክልኤ ነገሩ ሁለት ነገርን ከመናገር ተከልከል ለአንዱ አንድ ለአንዱ አንድ። (፩) ማታ አንድ ጧት አንት ከመናገር ተከልከል በጧት የተናገረውን በማታ አይደግምም እንዲል \ሐተታ\ መናፍቃን በጉባኤ ከተረቱ በኋላ ወደ ከተማ ገብተው ለአንዱ አንድ ነገር ለአንዱ አንድ ነገር ማታ አንድ ጧት አንድ ነገር የሚናገሩ ሁነዋልና /አቋምም እርጋታም ፅናትም የለላቸው ሁነዋል/ እንዲህ አለ ሁለት ስራ ከመስራት ተከልከል ማለት አንድ ጊዜ ጽድቅ አንድ ጊዜ ኃጢአት አንድ ጊዜ ወደ ገዳም አንድ ጊዜ ወደ ዓለም አትበል። ሐሰተኛ እንዳትሆን። ነገረ ሠሪ አትሁን ሁለት ነገር ከመናገር ተከልከል/በአንድ ራስ ሁለት ምላስ አትሁን/ \ሐተታ\ ምነው ? ይህን ነገርማ ከላይ ተናግሮት አልነበረም ስለምን ? ደገመው ቢሉ ያ የምግባር ይህ የሃይማኖት ነው በሃይማኖት አንደ አንተም ነኝ ለሌላውም እንደአንተም ነኝ ማለት አለና /ይህም የተገባ አይደለም/። ፱ ወኢታንሶሱ ዘእንበለ ዳዕሙ በተዐቅቦ ያለተዐቅቦ አትኑር (፩) ተዐቅቦ/ራስን ገዝቶ መሰብሰብ/ የሌለው አነዋወር አትኑር። ሰነፍ አውታታ አትሁን። ሰውን የማታፍር እግዚአብሔርን የማትፈራ አትሁን። ፊት አይተህ የምታዳላ አትሁን ክፉ ነገርን የምትናገር አትሁን።
Mostrar todo...
በሐሰት አትመሥክር። አትበድል። ፫ ተዐቀብ እምነ ማውታ ሙቶ የተገኘውን ከመብላት ተከልከል በወጥመድ በወፈንጠር የተያዘውን (፩ም) በደም የታፈነውን አትብላ ሐተታ \ አንገቱን ከልለው በጭራ ገመድ አስረው ደሙን ያጠጡታልና የላላው እንዲጸና የጸናው እንዲላላ:: (፩ም) በደም ይላል በቁሙ ደም ከመብላት ተከልከል አርግተው አዝግነው ይበሉታልና ይህ ሁሉ የአሕዛብ ስራ ነውና። (፩ም) ብርንዶ ስጋ ከመብላት ተከልከል ደም አይለየውምና። ፬ ነጽር ወዑቅ ወኢያስህትከ መኑሂ ከመ ትትገኀስ እምዛቲ ሃይማኖት:: ከዚህች ሃይማኖት ትለይ ዘንድ ማንም እንዳያስትህ ዕወቅ ምነው የያዝከው የምግባር አይደለምን ? ስለምን ሃይማኖት አለ ቢሉ የሃይማኖት መግለጫው ምግባር ነውና። (፩ም) በቁሙ የሃይማኖት ሥራ አለበትና ይህ ካልሆነ ግን ከእግዚአብሔር አንድነት ትለያለህ። ፭ ወእሉ እሙንቱ ኀጣውእ ክሡታን በኦሪት ፥ በሲኖዶስ፥በግብረ ሐዋርያት የታወቁ ኃጣውእ እሊህ ናቸው። በኦሪት ፥ በሲኖዶስ፥በግብረ ሐዋርያት ያልታወቁ/ ያለተገለጹት/ ንዑሳን ትዕዛዛትም አሉ። እኛ የነሱን ነገር እንናገራለን።
Mostrar todo...
ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት በዚህች ዕለት በዚህች ሰዓት የዓለም መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ለአዳም ልጆች ድኅነት በመስቀል ላይ ሆኖ በታላቅ ድምፅ ጮሆ “ኤሎሄ ኤሎሄ” ብሎ “ሁሉ ተፈጸመ” በማለት በባሕርይው ሞት የሌለበት አምላክ ነፍሱን በፈቃዱ ለሞት አሳልፎ ሰጠ። “ቀትር በሆነ ጊዜም በስድስት ሰዓት ፀሐይ ጨለመ፤ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስም ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ። ፀሐዩም በጨለመ ጊዜ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከመካከሉ ተቀደደ። ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አባት ሆይ፥ ነፍሴን በአንተ እጅ አደራ እሰጣለሁ”’ ብሎ ጮኸ፤ ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።” (ሉቃ.፳፫÷፵፬-፵፮)
Mostrar todo...
"የሰይጣንን ኃይል ያደከምክ እውነተኛ ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ በሦስት ሰዓት በጵላጦስ ፊት ለቆሙ እግሮችህ እጅ እየነሳሁ ምስጋና አቀርብልሃለሀ።" መልክዓ ሕማማት
Mostrar todo...
Mostrar todo...
እንኳን ለሰሞነ ሕማማት አራተኛ ቀን ለጸሎተ ሐሙስና ለሕጽበተ እግር በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ        አሜን   ✥••••• ●◉ ✞ ◉●•••••✥ እንኳን ለሰሞነ ሕማማት አራተኛ ቀን ለጸሎተ ሐሙስና ለሕጽበተ እግር በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን   ✥••••• ●◉ ✞ ◉●•••••✥ ሰሞነ ሕማማት ዘዕለተ ሐሙስ የዕለቱ ዜማ

#ሠሉስ(ማክሰኞ) የሰሙነ ህማማት ሠሉስ(ማክሰኞ) "የጥያቄ ቀን" በመባል ይታወቃል ምክንያቱም ሹመትን ወይም ስልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኞ ባደረገው አንጾሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታት በማን ስልጣን ታደርጋለህ? የሚል ነበረ። ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኃለው የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? አላቸው እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም?  ይለናል ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል እንደ መምህርም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸው ሁሉ በራሱ ስልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል እንደማይገባን ነው በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል  ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምረን ነው። #እምበለደዌ_ወሕማም፤ ✞✞✞ #እምበለ_ጻማ_ወድካም ✞✞✞ #አመ_ከመ_ዮመ_ያብጸሐነ፤ ✞✞✞ #ያብጸሐክሙ_እግዚአብሔር_በሰላም። ✞✞✞
Mostrar todo...
ጸሎተ አባ ጊዮርጊስ የሰባቱ(፯ቱ) ጊዜያት የአባ ጊዮርጊስ ጸሎት
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.