cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Annal Muslim

Kaayyoon channel kana ummata islaama hanga dandaamen barsisuudha Ergaawwan qur'ana kessaa Hadisaa rasulaa SAW Da'waalee gara garaa.... የዚህ ቻናል እቅድ ሙስሊሙን ኡማ በተቻለ መጠን ማስተማር ነው።

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
179
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የመጨረሻይቱም ዓለም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 12፥57 *"የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለእነዚያ ላመኑት እና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው"*፡፡ وَلَأَجْرُ الْآخِرَةِ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ "ዱንያ" دُّنْيَا የሚለው ቃል "አድና" أَدْنَى‎ ማለትም "ቅርብ" ለሚለው ተባዕታይ መደብ አንስታይ መደብ ሲሆን "ቅርቢቱ" ማለት ነው፥ “አኺራ” آخِرَةِ የሚለው ቃል "አኺር" آخِر ማለትም "መጨረሻ" ለሚለው ተባዕታይ መደብ አንስታይ መደብ ሲሆን "መጨረሻይቱ" ማለት ነው። ከቅርቢቱ ሰማይ ጀምሮ እስከ ሰባተኛው ሰማይ ድረስ ያለው ዓለም "አኺራ" آخِرَةِ ወይም "የመጨረሻይቱ ዓለም" ነው፦ 12፥57 *"የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለእነዚያ ላመኑት እና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው"*፡፡ وَلَأَجْرُ الْآخِرَةِ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ ሰዎች ሲፈረድባቸው የሚያገኙት ፍዳ እና ሲፈረድላቸው የሚያገኙት ምንዳ የሚቀጠሩበት አኺራ ሰማይ ነው፦ 51፥ 22 *"ሲሳያችሁ እና የምትቀጠሩትም ፍዳ እና ምንዳ በሰማይ ውስጥ ነው"*፡፡ وَفِي السَّمَاءِ رِزْقُكُمْ وَمَا تُوعَدُونَ "ሲሳያችሁም በሰማይ ውስጥ ነው" ማለት ፍራፍሬን ሲሳይ ለማድረግ ከቅርቢቱ ሰማይ የሚወርደውን ውኃ ያመለክታል፦ 40፥13 *"ለእናንተም ከሰማይ ሲሳይን የሚያወርድላችሁ ነው"*፡፡ وَيُنَزِّلُ لَكُم مِّنَ السَّمَاءِ رِزْقًا 2፥22 *"ከሰማይም ውኃን ያወረደ በእርሱም(በውኃ) ከፍሬዎች ለእናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው"*፡፡ وَأَنزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَخْرَجَ بِهِ مِنَ الثَّمَرَاتِ رِزْقًا لَّكُمْ "የምትቀጠሩትም ፍዳ እና ምንዳ በሰማይ ውስጥ ነው" ማለት የምትቀጠሩት ሁሉ በእርግጥ መጪ ነው፥ በፍርዱ ቀን ሰማይም የምትከፈት እና ባለ ደጃፎች የምትሆንበት ቀን ነው ማለት ነው፦ 6፥134 *"የምትቀጠሩት ሁሉ በእርግጥ መጪ ነው፡፡ እናንተም አምላጮች አይደላችሁም"*፡፡ إِنَّ مَا تُوعَدُونَ لَآتٍ ۖ وَمَا أَنتُم بِمُعْجِزِينَ 78፥19 ሰማይም በምትከፈት እና ባለ ደጃፎችም በምትኾንበት ቀን ነው"*፡፡ وَفُتِحَتِ السَّمَاءُ فَكَانَتْ أَبْوَابًا ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 221 አቢ ሁረይራህ”ረ. ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"አንድ የአሏህ ባሪያ ዐበይት ኃጢአቶችን እስከተከለከለ ድረስ ጥርት አድርጎ፦ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" በጭራሽ አይልም፥ ወደ ዙፋኑ እስኪደርስ ድረስ የሰማይ ደጆች የሚከፈቱለት ቢሆን እንጂ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، رضى الله عنه قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَا قَالَ عَبْدٌ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ قَطُّ مُخْلِصًا إِلاَّ فُتِحَتْ لَهُ أَبْوَابُ السَّمَاءِ حَتَّى تُفْضِيَ إِلَى الْعَرْشِ مَا اجْتَنَبَ الْكَبَائِرَ ‏"‏ በኢኽላስ “ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه ያለ ሰው የሰማይ ደጆች ይከፈቱለታል፥ "ኢኽላስ" إِخْلَاص የሚለው ቃል "አኽለሶ" أَخْلَصَ‎ ማለትም "አጠራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን እውነት ለማንገሥ ሐሠትን ለማርከሥ የሚደረግ "መተናነስ" እና ከሙገሳና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአሏህ ውዴታ የሚደረግ "ማጥራት" ማለት ነው። ኢኽላስ ያለው የአሏህ ባሪያ ደግሞ "ሙኽሊስ" مُخْلِص ይባላል፥ የሰማይ ደጆች የሚከፈቱለት እስከ ዐርሽ ሥር እስካለው እስከ ጀናቱል ፊርደውሥ ድረስ ነው። ነገር ግን በአሏህ አናቅጽ ያስተባበሉ እና የኮሩ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም፥ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ ጀናህ አይገቡም፦ 7፥40 *"እነዚያ አንቀጾቻችንን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም፥ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ ጀናህ አይገቡም"*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَاسْتَكْبَرُوا عَنْهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمْ أَبْوَابُ السَّمَاءِ وَلَا يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ الْجَمَلُ فِي سَمِّ الْخِيَاطِ ۚ "የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም፥ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ ጀናህ አይገቡም" የሚለው ኃይለ-ቃል የሚከፈቱት የሰማይ ደጆች የሚገባበት ጀናህ መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። የመጨረሻይቱም አገር ለእነዚያ ለተጠነቀቁት በእርግጥ የተሻለች ናት፦ 12፥109 *"የመጨረሻይቱም አገር ለእነዚያ ለተጠነቀቁት በእርግጥ የተሻለች ናት"* አታውቁምን? وَلَدَارُ الْآخِرَةِ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ اتَّقَوْا ۗ أَفَلَا تَعْقِلُونَ አሏህ የመጨረሻይቱ አገር ከሚገቡት ሙተቂን ባሮቹ ያድርገን! አሚን። Taken from:-✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
Mostrar todo...
قال قتادة بن دعامة السدوسي رحمه الله: ➻ታላቁ ኢማም አቡል ኸጧብ ቀታዳ ኢብኑ ደኣማህ አሰዱሲይ እንደዚህ ይላሉ" الصبر من الإيمان بمنزلة اليدين من الجسد، من لم يكن صابرًا على البلاء لم يكن شاكرًا على النعماء، ولو كان الصبر رجلًا لكان كريمًا جميلًا. ☞ትግስት ለኢማን ያለው አስፈላጊነት ልክ ለአካል ሁለት እጆች የሚያስፈልጉትን ያህል ነው። ➻በመከራ ላይ ታጋሽ ያልሆነ በፀጋ ላይ አመስጋኝ አይሆንም።" ➻ትእግስት አንደ ሰው ቢሆን ኖሮ የተከበረና ያማረ ይሆን ነበር።" 📗መውሱዓህ ኢብኒ አቢ ዱንያ አራተኛ ጥራዝ / ገፅ 59 [موسوعة ابن أبي الدنيا 4/ 59].
Mostrar todo...
☞ "አኼራችሁን አስተካክሉ፣ ዱንያችሁ ትስተካከልላችኋለች" ዑመር ኢብን ዐብዱል ዐዚዝ(ረሒመሁሏህ)
Mostrar todo...
ኢብኑል ቀይም አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይሉ ነበር፡– "ለአሏህ ተብሎ የሚመሰረት ወንድማማችነት ምሳሌው ልክ እንደ አይን እና እጅ ነው አይን ሲያለቅሰ እጅ ይጠርገዋል እጅ በሆነ ነገር ከተጎዳ ለሱ ብሎ አይን ያለቅሳል 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ‏ قال الشيخ صالح آل الشيخ حفظه الله تعالى : "المرأة عليها واجبٌ كبير في الدعوة إلى الله عز وجل لذلك لابد أن تكون متسلحة بالعلم 💎📝". المحاضرات ٥٥٨/٥ .📚
Mostrar todo...
ኢብን መስዑድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነቢዩን ጠየቋቸው፡- ‹‹ከሥራዎች ሁሉ በአላህ ዘንድ ተወዳጅነት ያለው የትኛው ነው? በማለት፡፡ ‹‹ሶላትን በመጀመሪያ ወቅቱ መስገድ›› አሉኝ፡፡ ‹‹ከዚያስ?›› አልኩኝ፡፡ ‹‹ለወላጅ መልካም መዋል፡፡›› ‹‹ከዚያስ?›› ‹‹በአላህ መንገድ መዋጋት (ጂሃድ ፊ ሰቢሊላህ)፡፡›› ዐብደሏህ ኢብን መስዑድ በመጨመር እንደገለጹት፡- ‹‹እነኝህን የአላህ መልዕክተኛ ነግረውናል፡፡ ተጨማሪ ጥያቄ ባቀርብ ኖሮ ሌላም ነጥብ ይነግሩኝ ነበር፡፡›› (ቡኻሪ ዘግበውታል
Mostrar todo...
🎁 Yeroo kamuu Keessa Wanti Argamaa ta'e islaamummaaf gad jechuu dirqama qaba Malee; Islaamummaan Waan Haaraya Argamuuf gad jechuu hin qabu. 📚Dr. Yusuf Al-Qardaawii... يجب إخضاع الواقع للإسلام لا إخضاع الاسلام للواقع 📚 د.يوسف القرضاوى
Mostrar todo...
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُوا۟ رَبَّكُمْ وَٱخْشَوْا۟ يَوْمًۭا لَّا يَجْزِى وَالِدٌ عَن وَلَدِهِۦ وَلَا مَوْلُودٌ هُوَ جَازٍ عَن وَالِدِهِۦ شَيْـًٔا ۚ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّۭ ۖ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِٱللَّهِ ٱلْغَرُورُ እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ወላጅም ከልጁ (በምንም) የማይጠቅምበትን፤ ተወላጅም እርሱ ወላጅን በምንም ጠቃሚ የማይሆንበትን ቀን ፍሩ፡፡ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት አትሸንግላችሁ፡፡ በአላህም (መታገስ) አታላዩ (ሰይጣን) አያታልላችሁ፡፡
Mostrar todo...
ለወሬ ቦታ አንስጥ ﷽ ﺟﺎﺀ ﺭﺟﻞ ﻟﺨﺎﻟﺪ ﺑﻦ ﺍﻟﻮﻟﻴﺪ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻓﻘﺎﻝ ﻟﻪ ﺇﻥ ﻓﻼﻧﺎ ﺷﺘﻤﻚ .. ﻓﻘﺎﻝ : ﺗﻠﻚ ﺻﺤﻴﻔﺘﻪ ﻓﻠﻴﻤﻸﻫﺎ ﺑﻤﺎﺷﺎﺀ አንድ ሰው ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ ጋር መጣና እከሌ ሰድቦሀል አለው... ይህቺ የስራ ሰሌዳው ነች በፈለገው ይሙላት አለው። ﻗﺎﻝ ﺭﺟﻞ ﻟﻮﻫﺐ ﺑﻦ ﻣﻨﺒﻪ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ: ﺇﻥ ﻓﻼﻧﺎ ﺷﺘﻤﻚ .. ﻗﺎﻝ: ﺃﻣﺎ ﻭﺟﺪ ﺍﻟﺸﻴﻄﺎﻥ ﺭﺳﻮﻻ ﻏﻴﺮﻙ . አንድ ሰው ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ ዘንድ መጣና፦ እከሌ ሰድቦሀል አለው… ሸይጧን ካንተ ውጭ ሌላ የሚልከው መልእክተኛ አጣንዴ አለው። ﻗﺎﻝ ﺃﺣﺪﻫﻢ ﻟﺮﺟﻞ .. ﻓﻼﻥ ﺷﺘﻤﻚ ﻓﻘﺎﻝ : ﻫﻮ ﺭﻣﺎﻧﻲ ﺑﺴﻬﻢ ، ﻭﻟﻢ ﻳﺼﺒﻨﻲ ﻓﻠﻤﺎﺫﺍ ﺣﻤﻠﺖ ﺍﻟﺴﻬﻢ ﻭﻏﺮﺳﺘﻪ ﻓﻲ ﻗﻠﺒﻲ . አንድ ሰው መጣና ለአንዱ እከሌ ሰድቦሀል ሲል ነገረው… እሱ ቀስቱን ወደኔ ወረወረው ነገር ግን ቀስቱ አላገኘኝም ነበር ለምን አንተ ቀስቱን አምጥተህ ልቤ ላይ ትተክለዋለህ ትወጋኛለህ? አለው። ﺟﺎﺀ ﺭﺟﻞ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺸﺎﻓﻌﻲ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ: ﻓﻘﺎﻝ ﻟﻪ ﻓﻼﻥ ﻳﺬﻛﺮﻙ ﺑﺴﻮﺀ .. ﻓﺄﺟﺎﺑﻪ: ﺇﺫﺍ ﺻﺪﻗﺖ ﻓﺄﻧﺖ ﻧﻤﺎﻡ ، ﻭﺇﺫﺍ ﻛﺬﺑﺖ ﻓﺄﻧﺖ ﻓﺎﺳﻖ . ﻓﺨﺠﻞ ﻭﺍﻧﺼﺮﻑ . አንድ ሰው ኢማም አሻፊኢ ዘንድ መጣና እከሌ በመጥፎ ያነሳሀል አላቸው…እውነትህን ከሆነ አንተ ወሬ አመላላሽ (አቃጣሪ)ነህ ዋሽተህ ከሆነ ፋሲቅ ነህ አሉት። ሰውየውም አፍሮ ሄደ። ﺃﻗﻮﻝ ﻻ ﺗﺨﺒﺮﻧﻲ ﻋﻤﻦ ﻳﻜﺮﻫﻨﻲ ﺃﻭ ﻳﺘﻜﻠﻢ ﻋﻨﻲ .. ﺍﺗﺮﻛﻨﻲ ﺃﺿﺤﻚ ﻭﺃﺿﺤﻚ ﻣﻊ ﺍﻟﺠﻤﻴﻊ ﻭﺃﺷﻌﺮ ﺃﻥ ﺍﻟﺠﻤﻴﻊ ﻳﺤﺒﻨﻲ، ﻭﻟﻨﺘﺮﻙ ﺍﻟﻘﻴﻞ ﻭﺍﻟﻘﺎﻝ .. ﻓﺮﺳﻮﻝ ﺍﻷﻣﺔعليه الصلاة والسلام ﻳﻘﻮﻝ ﻻ ﺗﻨﻘﻠﻮﺍ ﻟﻲ ﺷﺊ ﻋﻦ ﺃﺻﺤﺎﺑﻲ ، ﻓﺈﻧﻨﻲ ﺃﺣﺐ ﺃﻥ ﺃﺧﺮﺝ ﺇﻟﻴﻬﻢ ﻭﺃﻧﺎ ﺳﻠﻴﻢ ﺍﻟﺼﺪﺭ እኔን በመጥፎ ስለሚያነሳኝ ሰው አትንገረኝ ከሁሉም ጋር በፈገግታ እኖር ዘንድ ተወኝ ሁሉም እኔን እንደሚወደኝ እያወቅኩ ልኑር አለ ....ተባለን ...ከማውራት እንቆጠብ። ነብዩ ﷺ ስለባልደረቦቼ ነገሮችን እያመጣችሁ አትንገሩኝ እኔ ከነሱ ጋር ጥሩ ልብ ይዤ መውጣት መቀላቀል እፈልጋለሁ ብለዋል።
Mostrar todo...
በትክክለኛው ሱና መሠረት ቁጣን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል: 1. በአላህ ዘንድ ከዲያብሎስ ጥገኝነትን ፈልግ ፡፡ ቡኻሪ (ቁጥር 6048) 2. ዝም በል አትናገርም. A-adab A-mufrad (No. 245) 3. ተቀመጥ ወይም ተኛ. Abu Dawud (No. 4782) #ሸር_ያድርጉ @Dr_zakir_Plus
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.