cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Tegbar Elias(ተግባር)

🚶እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጣችሁ 💔 ♨️መንፈሳዊ ጥቅሶች,ትምህርቶችን እና አጫጭር ቪዲዮ ይለቀቃሉ ♨️ለተማሪዎች በብዙ ሰዎች ጥያቄ መሰረት የተለያዩ ኖቶችን፣pdf፣ማትሪክ፣ሞዴል፣ሚኒስትሪ..በአጠቃላይ ትምህርታዊ ነገሮችን .እና አዳዲስ መረጃዎችን የያዘ ቻናል አዘጋጅተናል። እርስዋ ጓደኞቾን በመጋበዝ የ አገልግሎቱ ተጠቃሚ ያድርጉ። የሁሉም ቤት ❤ official channel name T

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
427
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
+330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

አለብኝ ትዝታ በመስቀል ላይ ሞቶ ያዳነኝ ዘማሪ ዮሴፍ ካሳ
Mostrar todo...
ዮሐንስ 9 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³² ዕውር ሆኖ የተወለደውን ዓይኖች ማንም እንደ ከፈተ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አልተሰማም፤ ³³ ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ምንም ሊያደርግ ባልቻለም ነበር። ³⁴ መልሰው፦ አንተ ሁለንተናህ በኃጢአት ተወለድህ፥ አንተም እኛን ታስተምረናለህን? አሉት። ወደ ውጭም አወጡት። ³⁵ ኢየሱስም ወደ ውጭ እንዳወጡት ሰማ ሲያገኘውም፦ አንተ በእግዚአብሔር ልጅ ታምናለህን? አለው። ³⁶ እርሱም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ በእርሱ አምን ዘንድ ማን ነው? አለ። ³⁷ ኢየሱስም፦ አይተኸዋልም ከአንተ ጋርም የሚናገረው እርሱ ነው አለው። ³⁸ እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አምናለሁ አለ፤ ሰገደለትም።
Mostrar todo...
ዘፍጥረት 9 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁸ እግዚአብሔርም ለኖኅና ለልጆቹ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ ⁹ እኔም እነሆ ቃል ኪዳኔን ከእናንተና በኋላ ከሚመጣው ከዘራችሁ ጋር አቆማለሁ፤
Mostrar todo...
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል። በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።  መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው። @tegbarelias
Mostrar todo...
“እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤”   — ኤፌሶን 1፥13
- ይህ ክፍል ሐዋርያው ​​ጳውሎስ ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን በጻፈው ደብዳቤ ላይ የሚገኝ
ስለ የመዳንን ሃሳብ እና መንፈስ  በአማኞች ሕይወት ውስጥ ያለውን ሚና የሚያጎላ ነው።
-
ሲጀምር "እናንተ ደግሞ" በማለት ሲሆን ይህ የሚያመለክተው በቀደሙት ጥቅሶች ውስጥ የተጠቀሱትን የኢየሱስ ክርስቶስ አማኞችን (ተከታዮችን) ነው።
ጳውሎስ ለአይሁድ እና አህዛብ አማኞች ነው እየተናገረ ያለው፣ ✝️ እነርሱም በእግዚአብሔር የድነት እቅድ ውስጥ መካተታቸውን ለመግለጽ ነው።
-"የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል" ፤
✝️እዚህ ላይ፣ ጳውሎስ የወንጌልን መልእክት የመስማት እና የመረዳትን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥቷል።
የእውነት ቃል” የሚያመለክተው በኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኘውን የመዳንን ወንጌል ነው።
- "ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ" ✝️ ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን መዳንን ለማግኘት ወሳኝ እርምጃ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ለኃጢአታችን የሞተው እና የተነሣው በእርሱ ላይ እምነትን ማድረግን ያካትታል። ማመን ኢየሱስን እንደ ጌታ እና አዳኝ የመከተል እና የመተማመን ግላዊ ቁርጠኝነት ነው። - "በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ" ፤ ✝️መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ለተከታዮቹ ቃል የገባላቸው ስጦታ ነው (ዮሐንስ 14፡16-17)። አንድ ሰው በኢየሱስ ሲያምን፣ በመንፈስ ቅዱስ ታትሟል፣ ✝️ይህም ማለት የእግዚአብሔር ንብረት እንደሆኑ ምልክት ተደርጎባቸዋል። መንፈስ ቅዱስ አማኞችን ያድርባቸዋል፣ ይመራቸዋል፣ ያበረታታል እና ህይወታቸውን ይለውጣል። - ስናጠቃልለው  ኤፌሶን 1፡13 የመዳንን ሂደት ያጎላል። ይህ ጥቅስ የሚያጎላው እምነት በክርስቶስ ያለውን ወሳኝ ሚና እና የመንፈስ ቅዱስን በአማኞች ህይወት ውስጥ መገኘት  ነው።
Mostrar todo...
1ኛ ቆሮንቶስ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን። ⁷ ነገር ግን ይህ እውቀት በሁሉ ዘንድ አይገኝም፤ አንዳንዶች ግን ጣዖትን እስከ አሁን ድረስ ስለ ለመዱ፦ ለጣዖት የተሠዋ ነው ብለው ይበላሉና ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳል።
Mostrar todo...
2
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል‼️ 🗣ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል። " በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ " ሲሉ አሳውቀዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው  ፤ ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል። ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል። t.me/great_mission1 @tegbarelias
Mostrar todo...
ማቴዎስ 22 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁵ ከእነርሱም አንድ የኦሪት ሕግ አዋቂ፣ ሊፈትነው ፈልጎ እንዲህ አለው፤ ³⁶ “መምህር ሆይ፤ ከሕግ ሁሉ የሚበልጠው የትኛው ትእዛዝ ነው?” ³⁷ እርሱም እንዲህ አለው፤ “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤’ ³⁸ ይህ የመጀመሪያውና ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ ነው፤ ³⁹ ሁለተኛውም ያንኑ ይመስላል፤ ይህም፣ ‘ጎረቤትህን እንደ ራስህ ውደድ’ የሚለው ነው፤ ⁴⁰ ሕግና ነቢያት በሙሉ በእነዚህ ሁለት ትእዛዛት ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው።”
Mostrar todo...
እኔ ሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በአንድ ልጁ፣ በመንፈስ ቅዱስ በተፀነሰ፣ ከድንግል ማርያም በተወለደ፣
በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን መከራን በተቀበለ፣ በተሰቀለ፣ በሞተ እና በተቀበረ፣
በሦስተኛም ቀን ከሙታን በተነሳ፣ ወደ ሰማይ በወጣ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በተቀመጠ፣
ከዚያም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በሚመለስ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ፣ በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን፣ በኃጢአት ስርየት፣ በሥጋ ትንሣኤ፣ በዘላለም ሕይወት አምናለሁ፡፡
t.me/great_mission1
Mostrar todo...