cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ALL IN ALL ዜና

We use it for all and all!!!

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
183
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ከአማራ ክልል መንግሥት የተላለፈ ጥሪ፡፡ ነሐሴ 30/2013 ዓ.ም በሁሉም የህልውና ዘመቻ ግንባር አካባቢ ላለው ህዝባችን፤ አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በልዩ ኀይል፣ በሚሊሻ፤ ፋኖ እና በመላው ሕዝባችን እየተወሰደበት ባለው ከባድ ምት እና እርምጃ ጠላት እየተበታተነ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የሕዝብ ጠላት የሆነው የአሸባሪው እና ወራሪው ትህነግ ቡድን የዘረፈውን የሕዝብ እና የመንግሥት ሃብት ይዞ እንዳይወጣ በየአካባቢው ተደራጅተህ እርምጃ እንድትውሰድ የክልሉ መንግሥት ጥሪ ያቀርባል። በተለይም በመርሳ ግምባር ሚሌና ጊራና አካባቢ፣ ከመርኮታ ወደ ፋጂ የባቡር መስመሩን ተከትሎ፣ ከጎኃ ጀምሮ ወደ ሚሌ አቅጣጫ፣ በመቄት ግምባር ከገረገራ ጀምሮ እስከ ድልብ ደረስ፣ በላስታ፣ ላሊበላ እና መጃ አካባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ጎንደር በማይጠብሪና አካባቢው ጠላት በከፍተኛ ሁኔታ እሸሸ ስለሆነ የጠላት ቡድን አባላትም ሆኑ አንድም የሕዝብ እና የመንግሥት ሃብት ይዞ እንዳይወጣ ሁሉም በአካባቢው እየተደራጀ የሚሸሸው ቡድን ላይ እርምጃ እንዲወስድ እና አስፈላጊን መረጃ ለጸጥታ አካሉ እዲሰጥ የአማራ ክልል መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮቪድ-19 በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ባሳደረበት በዚህ ወቅት 50 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ ክትባት በመላው አለም ለሚገኙ ከ28 በላይ ሀገራት በማጓጓዝ በየትኛውም የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች ያልተሞከረ ስኬት ከማስመዝገቡም በላይ ወረርሽኙን ለመከላከል በሚደረገው አለም አቀፍ ጥረት ላይ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
Mostrar todo...
ቁጥሮች ! ባጠናቀቅነው ነሀሴ ወር በይፋ የተገለፁ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሮች ፦ - መነሻውን ከጋምቤላ ያደረገ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-15074 አ/አ በሆነ ዶልፊን ህዝብ ማመላለሻ ሲዘዋወር የነበረ ህገወጥ መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በዚህ ወር ተይዟል፤ የተያዘው መሳሪያ በቁጥር 12 ክላሽንኮቭ እና 5 ጥይት መያዣ ነው። - የሰሌዳ ቁጥር A76390 በሆነ ቪትዝ መኪና 5 ክላሽንኮቭ ከ132 ጥይት ጋር ሲዘዋወር በድንገተኛ ፍተሻ ተይዟል (እንደ ጎንደር ከተማ ፖሊስ መረጃ) - በሀመር ወረዳ በዚህ እያጠናቀቅን ባለነው ወር ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 10 መሳሪያ፣ 14 ክላሽ ጥይት፣ 3 የክላሽ መጋዘን ተይዟል። - በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው ውሃ ልማት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው አምባሳደር ፔንሲዮን ውስጥ 10 ባለሰደፍና 10 ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች እና 17 የክላሽንኮቭ ጥይት ካርታዎች ተይዘዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 2 ግለሰቦች ተይዘዋል። - በባህር ዳር ከተማ በአፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ በአንድ ግለሰብ ቤት በተደረገ ፍተሻ 1 ሺህ 669 የብሬን ጥይት በዚህ ወር ተይዟል። - ከከሚሴ ወደ አ/አ ሊዘዋወር የነበረ 53 ህገወጥ ጩቤ ፣ 30 የጥይት መያዣ ካርታ፣ 30 እንግብ፣ 30 የትጥቅ መያዣ ቀበቶ ሸዋ ሮቢት ላይ ተይዟል። - በገንደውሃ ከተማ አንድ ግለሰብ 30 የክላሽ ካዝናዎችን በህገወጥ መንገድ በኩርሲ ወንበሮች ይዞ ሲንቀሳቀስ ተይዟል። - በከፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ በኬላ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 634 ፍሬ የክላሽ ጥይትና 50,055 ብር ከነተጠርጣሪዎቹ ተይዟል። NB : ከላይ የተጠቀሱት የህገወጥ መሳሪያ ዝውውሮች በዚህ ወር ከተሰሙት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው ፤ ሌሎች ተዳራሽ ያልሆኑ ሊኖሩ ይችላሉ #ጥንቃቄ
Mostrar todo...
የቁም እንሰሳት ወጪ ንግድ የሚገኘው ገቢ ከዓመት ዓመት እያሽቆለቆለ ነው። የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ በ2013 ባወጣው መረጃ መሰረት 70.2 ሚሊዮን የዳልጋ ከብት፤ 42.9 ሚሊዮን በጎች፤ 52.5 ሚሊዮን ፍየሎች እና 8.1 ሚሊዮን ግመሎች አሏት፡፡ ሀገራችን በሀብታምነት ከምትጠራበት የቁም እንሰሳት ወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ ግን ዝቅተኛ መሆኑ ሳያንስ ጭራሽ ከዓመት ዓመት እያሽቆለቆለ ነው፡፡ በ2013 በጀት ዓመት የተገኘው 44.169 ሚሊዮን ዶላር ከጠቅላላው የወጪ ንግድ ከተገኘው 3.64 ቢሊዮን ዶላር 1.788 በመቶ ብቻ ድርሻ አለው፡፡ ሰሞኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ችግሮች ምንድንናቸው እንዴትስ እንፍታቸው ሲል ከቁም እንስሳት ላኪዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አድርጓል፡፡ ኮንትሮባንድ፣ ህገ-ወጥ ንግድ፣ የቁም እንስሳት ላኪዎች ከሃገር ውስጥ የቁም እንስሳት የመሸጫ ዋጋ በታች ወደ ውጭ የመላኪያ ዋጋ ማስመዝገብ/Under invoice/ ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ እንዲቀንስ ያደረጉ ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል። ''የውጪ ሀገር ዜጎች ሀገር ውስጥ ገብተው ህገ-ወጥ የግብይት መረብ በመዘርጋት የቁም እንሰሳት ወጪ ንግዱን ስለተቆጣጠሩት አኛ ህጋዊ ነጋዴዎች ከገበያው እንድንወጣ እየተገደድን ነው” ሲሉ በውይይቱ ላይ የተገኙ የቁም እንሰሳት ላኪዎች ምሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ ችግሮቹን አጥንቶ ከነመፍትሄያቸው የሚያቀርብ 9 አባላት ያሉት ግብረ-ሀይል ተቋቁሞም ወደ ሥራ ገብቷል ተብሏል። ከዘርፉ በጀት ዓመተ 263,138 በግና ፍየል፣ 58051 የዳልጋ ከብት፣ 46,205 ግመል በድምሩ 367,394 የቁም እንሰሳት በመላክ እንደየቅደም ተከተላቸው 18.19፣35.20፣ 36.46 በድምሩ 89.85 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል፡፡ ALL IN ALL ዜና
Mostrar todo...
የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር መጠናቀቁ ተገለፀ! የ2013 የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር በስኬት መጠናቀቁን ተገለጸ፡፡የመርኃ ግብሩ ማጠቃለያ ስነ ስርዓት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ተካሂዷል፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ባስተላለፉት መልዕክት መርኃ ግብሩ ባስቀመጥነው ግብ መሠረት ተግባራትን “ጀምሮ የማጠናቀቅ ብሔራዊ አቅማችንን” የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡“የትኛውም ፈተና ሳይበግረን የኢትዮጵያን ልማትና ብልጽግና እናረጋግጣለን”ም ነው ዶ/ር ዐቢይ ያሉት።በዘንድሮውና በሶስተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 6 ነጥብ 8 ቢሊዮን ችግኝ መተከላቸውን አንስተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው “የገጠሙንን ፈተናዎች እጅ ለእጅ ተያይዘን በመሻገር የኢትዮጵያን ከፍታ ማረጋገጥ አለብን”ሲሉ ተናግሯል።መርኃ ግብሩ በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ያለመ ቢሆንም፣ በ3 ዓመታት ብቻ ከ18 ቢሊየን የሚበልጡ ችግኞች ተተክለዋል።በአዳማ ከተማ በተካሄደው መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝቷል፡፡
Mostrar todo...
በኮሎራዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 100 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረጉ ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ ኮሎራዶ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 100 ሺህ ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ገንዘቡን ካዘጋጇቸው ልዩ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮች ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ገልጿል።
Mostrar todo...
Mostrar todo...
ETHIO_Alibaba.com®

ሰላም! ከ alibaba ወይም ከ aliexpress ኦርደር ማረግ አስበዋል አንግዲያውስ በነዚህ ሊንኮች 👉 www.alibaba.com 👉 www.aliexpress.com ያሰቡትን እቃ ለኛ በ ሊንክ አልያም ፎቶውን ይላኩት በ ፍጥነት በ USD ወይም በ ETB ዋጋውን እንልክሎታለን በነዚህ አድራሻ ያገኙናል 👇👇👇 👉 @alibaba_admins

Mostrar todo...
ETHIO_Alibaba.com®

ሰላም! ከ alibaba ወይም ከ aliexpress ኦርደር ማረግ አስበዋል አንግዲያውስ በነዚህ ሊንኮች 👉 www.alibaba.com 👉 www.aliexpress.com ያሰቡትን እቃ ለኛ በ ሊንክ አልያም ፎቶውን ይላኩት በ ፍጥነት በ USD ወይም በ ETB ዋጋውን እንልክሎታለን በነዚህ አድራሻ ያገኙናል 👇👇👇 👉 @alibaba_admins

Subscribe the channel
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.