cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

የ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች Yasin Nuru "ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ) "የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም "   የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7} ለአስተያየት👇👇 @Hasabbbbot ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ👇👇 @yasin_nuru_hadis

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
25 977
Suscriptores
+4624 horas
+2327 días
+49930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ሱብሃንአላህ => ጂንን የሚፈራው ቀበሮ ሳይሆን፤ ጂን ቀበሮን እንደሚፈራ ያውቃሉ?!! => ግመል የበደለውን እንደማይረሳ ያውቃሉ?!! => ንስር አሞራ በህመም ምክንያት እራሱን በማጥፋት እንጂ በኖርማል ሁኔታ እንደማይሞት ያውቃሉ?!! => ቀጭኔ በቀን ሶስት ጊዜ፤ በጥቅሉ ለ9 ደቂቃዎች ያህል ብቻ እንደምትተኛ ያውቃሉ?!! => ዝሆን ሀዘን ሲሰማው እንደሚያለቅስ ያውቃሉ?!! => ፈረስ ጅራቱ ከተቆረጠ እንደሚሞት ያውቃሉ?!! => ዶልፊን ሲተኛ አንድ አይኑን ብቻ እንደሚጨፍን ያውቃሉ?!! => አዞ ሲደሰት እንደሚያለቅስ ያውቃሉ?!! => አንበሳ የአውራ ዶሮ ጩኸትን እንደሚፈራ ያውቃሉ?!! => ጉንዳን ስታስነጥስ እራሷን እንደምትስት ያውቃሉ?!! በመጨረሻም ኀያሉ ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ጥራት ይገባው ማለት ይገባናል፡፡ #ሱብሃነላህ!! @yasin_nuru @yasin_nuru @yasin_nuru
Mostrar todo...
👍 58😍 8 4🥰 3😁 3❤‍🔥 1🔥 1🤯 1
«እነዚህን መሰል ሴቶች ለትዳር ከመምረጥ ተጠንቀቅ! ይህ የኢስላም ሳይሆን የኢንስታግራም ዲን ነው። ይህ ኒቃብ ሳይሆን ፋሽናዊ አለባበስ ነው። «ኪዩት ሙስሊም» ይባሉ ዘንድ ሂጃብን ሴክሹዋላይዝድ  አድርገውታል። ይህ ሐራም ነው ሒጃብ አይደለም ፣ወንድ ጋር መቀላቀል አለበት ወዘተ ስትላት ከራሷ ላይ ለመከላከል የማታመጣው ሎጅክ የለም።አንዷንም ማሳመን አትችልም።ፌሚኒዝምን በኢስላም ካባ ማራመድ የምትፈልግ ሆና እንጅ አታገኛትም! ሸይጣን የፈበረከላቸው አንድ አባባል ደግሞ አለ «ኒቃብ ከምንም አያግድም!» ይሉሃል። ከምንም ላያግድማ አልተደነገገም።የአላህ ህግ አይደለም፡  የሰው ልጅ ህግ እንኳን ያለ አላማ አይደነገግም! እግር ኳስ ላይ ተቀላቅላ በመዋኛ ገንዳ ውስጥ ተዘፍቃ ኒቃብ ከምንም አያግድም ትላሀለች። እስኪ በአላህ!?  ልብስ ውሃ ሲነካው ሰውነት ላይ ተለጥፎ መቀመጫና ታፋን እንደሚያሳይ ህፃን ልጅ ራሱ የሚስተው ሀቅ ነው ??! ደግሞ በቅርብ ርቀት ነን ሙስሊም ወጣቶች ያዩዋቸዋልኮ!  እንደዚህም ሆኖ ኒቃብ ከምንም አያግድም ¡ ይሄንንም ኢስላማዊ ዳሌ ይሉት ይሆናልኮ!  ያችኛዋ በታይት ዳሌዋን አሳየች ይችኛዋ በኒቃብ አሳየችው ታዳ ልዩነቱ ምንድን ነው?  የልብሱ ድንጋጌ ስም ብቻ ይመስሏችኋል? እነዚህን አምሳያዎች ካገባህ ቤትህ ውስጥ አቂዳና አኽላቅ እንደሌለ እወቅ ሂጃብ በሚመስል ልብስ ፌሚኒዝም ተጠቅልሎ ቤትህ እንደገባ እወቀው! አላህ ሀቅና ባጢልን ከለየ በኋላ ምርጫውን ለህሊና ነው የሰጠው። ሂጃብ በእይታ እንኳን ትክክልና ሀሰት መሆኑን ህሊና ይፈርዳል!  ከዚህ ሁሉ በኋላ ትመጣና ፦ አንተ ለምን ታያለህ?  አይንህን አትሰብርም?» ትልሀለች ። ወላሂ በይ?  ፎቶ አንስተች የለቀቅሽው እኛ አይናችንን አጨፍነን ስክሮል እንድናደርገው ነው?  ጉዳዩ ወዲህ ነው ፦ ስሜታዊ ዝንባሌን ሸይጣን በዲን ስም ከሽኖ ሲያቀርበው ነው!ውሃና ጥመት ሲወስድ እያሳሳቀ ነው።» ኢስማዒል ኑሩ @yasin_nuru @yasin_nuru
Mostrar todo...
👍 79 28😭 5👏 3👌 3👎 1🤔 1
#የ25ቱ_ነቢያት_ስም_ከነአመጣጡ_እና_ሀገራቸውን !!! 👉ካነበባችሁ በኋላ ለሌሎች ማስተላለፍ አትርሱ👈 #1=አደም(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ9 ሱራዎች በ25 አንቀጾች ውስጥ 25 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #2=ኢድሪስ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ2 ሱራዎች በ2 አንቀጾች ውስጥ 2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #3=ኑሕ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ30 ሱራዎች በ50 አንቀጾች ውስጥ 50 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #4=ኢብራሒም(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ25 ሱራዎች በ63 አንቀጾች ውስጥ 69 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #5=ሉጥ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ14 ሱራዎች በ27 አንቀጾች ውስጥ 27 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #6=ኢስማዒል(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ8 ሱራዎች በ12 አንቀጾች ውስጥ 12 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #7=ኢስሐቅ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ12 ሱራዎች በ16 አንቀጾች ውስጥ 17 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #8=የዕቁብ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ10 ሱራዎች በ10 አንቀጾች ውስጥ 16 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #9=ሁድ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 3 ሱራዎች በ7 አንቀጾች ውስጥ 7 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #10=ሷሊሕ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ9 ሱራዎች በ25 አንቀጾች ውስጥ ለ 25 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #11=ሹዐይብ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ10 አንቀጾች ውስጥ 11 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #12=ሙሳ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ34 ሱራዎች በ131 አንቀጾች ውስጥ 136 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #13=ሀሩን(ዐለይሂ ሰላም)፡-  ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ13 ሱራዎች በ20 አንቀጾች ውስጥ ለ 20 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #14=ዳዉድ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርአን ውስጥ በ9 ሱራዎች 16 አንቀጾች ውስጥ ለ 16 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #15=ሱለይማን(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ7 ሱራዎች 16 አንቀጾች ውስጥ ለ 17 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #16=ኢልያስ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 1 ሱራ በ2 አንቀጾች ውስጥ ለ 2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #17=አዩብ( ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ4 አንቀጾች ውስጥ ለ 4 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #18=ዩኑስ(ዐለይሂ ሰላም)፡-  ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ4 አንቀጾች ውስጥ ለ 4 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #19=ዩሱፍ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 3 ሱራዎች በ26 አንቀጾች ውስጥ ለ 27 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #20=በአል-የሰዕ(ዐለይሂ )፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ2 ሱራዎች በ2 አንቀጾች ውስጥ ለ 2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #21=ዙል-ኪፍል(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ  በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ2 ሱራዎች በ2 አንቀጾች ውስጥ ለ ስም2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #22=ዘከሪያ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ6  ውስጥ ለ 7 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #23=የሕያ(ዐለይሂ ሰላም)፡- አንቀጾችይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ5 አንቀጾች ውስጥ ለ 5 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #24=ዒሳ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ11 ሱራዎች በ25 አንቀጾች ውስጥ ለ 25 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ #25=ሙሐመድ(ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ4 አንቀጾች ውስጥ ለ 4 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ⬇➡➡~የነቢያቶች ሀገር 👇👇 1.. አደም (ዐ.ሰ) = ስሪላንካ (Sirilanka) 2.. ኑህ (ዐ.ሰ) = ጆርዳን (Jordan) 3.. ሹዓይብ (ዐ.ሰ) = ሶሪያ (Soria) 4.. ኢብራሂም (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain) 5.. ኢስማኤል (ዐ.ሰ) = ሳኡዲ (Saudi) 6.. ያእቆብ (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain) 7.. ያህያ (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain) 8.. ዘከሪያ (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain) 9.. ኢስሃቅ (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain) 10.. የሱፍ (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain) 11.. ሉጥ (ዐ.ሰ) = ኢራቅ (Iraq) 12.. ኢዩብ (ዐ.ሰ) = ጆርዳን (Jordan) 13.. ሁድ (ዐ.ሰ) = የመን (Yemen) 14.. ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) = ሳኡዲ (Saudi)  ( ከሁሉም በተለየ መልኩ የተላኩት ለአለም ህዝቦች ነው )     15.. ሙሳ (ዐ.ሰ) = ግብፅ (Egypt) 16.. ሀሩን(ዐ.ሰ) = ግብፅ (Egypt) 17.. ሷሊህ (ዐ.ሰ) = የመን (Yemen) 18.. ሱለይማን (ዐ.ሰ) = ግብፅ (Egypt) 19.. ኢሊያስ (ዐ.ሰ) = ጀሩሳሌም (ፍልስጤም) 20.. ዳውድ (ዐ.ሰ) = ኢራን (Iran) 21.. ኢሳ (ዐ.ሰ) = ጀሩሳሌም (ፍልስጤም) 22.. ኢድሪስ (ዐ.ሰ) = ኦማን (Oman) 23.. ዩኑስ (ዐ.ሰ) = ኢራን (Iran) 24.. ዙልኪፍል (ዐ.ሰ) = ጆርዳን ( Jordan ) 25.. አልየስእ (ዐ.ሰ) = ሶሪያ ( Soria) የአላህ እዝነት እና ሰላም በሁሉም ላይ ይስፈን ሳታነብት እንዳታልፉ @yasin_nuru @yasin_nuru
Mostrar todo...
👍 152 43👌 7🥰 5 4👎 4
ትንሽ ፈገግ በሉ‼ ============ ✍ «… ወሎ ውስጥ ነው አሉ። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ  ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል። * ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ። "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት። ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ አይቶ ተመለሰ። ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው። "ይሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ። "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤ እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ። አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ። የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል። * "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው። "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት። * "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ። "አዎ" አሉት። · ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:– "እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!" ©: የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው። @yasin_nuru @yasin_nuru
Mostrar todo...
😁 111👍 75🤣 51 23👌 9 5🥰 5😢 1😇 1
ትንሽ ፈገግ በሉ‼ ============ ✍ «… ወሎ ውስጥ ነው አሉ። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ  ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል። * ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ። "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት። ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ አይቶ ተመለሰ። ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው። "ይሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ። "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤ እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ። አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ። የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል። * "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው። "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት። * "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ። "አዎ" አሉት። · ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:– "እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!" ©: የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው።
Mostrar todo...
ጁሙዓን የት ሃገር፣ የት መስጅድ ሰገዳችሁ? ኹጥባው ስለምን ነበር? ለሌሎችም እንዲጠቅም ከሰማችሁት ውስጥ የኹጥባውን ጭብጥ በአጭር አስፍሩት። @yasin_nuru
Mostrar todo...
👍 85 29🥰 7🔥 4😍 4😁 3
«አንዱ አረብ ሒሳብ አዋቂ ተጠየቀ .... . ... ስለ ሴት ምን ታስባለህ? . ፈከረ . 'ሴት' አለ ... ...   እምነት ካላት 1 ነጥብ አላት ...   ውበት ካላት  0 ከጎኑ ጨምር ...ዘሯ ካማረ ሌላ 0 አሁንም ጨምር ... ሀብትም ካላት 0 ጨምር ከኋላ . ሁሉም ካላት 1000 ነጥብ አላት ... የመጀመሪያው ከጎደለ ግን ምንም ናት! . ምገርም ነው! ምደንቅ ነው! ሐዲሱም እንዲያ ነው!» ቢን ዓሊ @yasin_nuru @yasin_nuru
Mostrar todo...
👏 98👍 69 30👌 14😁 11🥰 7
በዚህ ታሪክ ውስጥ አላህ ምን ያህል ለባሮቹ ሩህሩህ፣ ያሻውን የሚያደርግ ኃያል ጌታ እንደሆነ እንረዳ ዘንድ እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ Mahi Mahisho ውልደታቸው በፓኪስታን ዋና ከተማ ነው። በዘመናችን አንቱታን ያተረፉ ከኒውሮሎጂ የህክምና ዘርፍ ጠበብቶች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ  ስመ-ጥር ስፔሻሊስት ናቸው። ሕክምና ለመስጠት ከሀገር ወደ ሀገር ከከተማ ወደ ገጠር ስለሚዘዋወሩ በስራቸው ባህሪ ከባድነትና እረፍት አልባነት ጋር ተደማምሮ ህመምተኞች እሳቸውን በቀላሉ ለማግኘት ይቸግራቸዋል። ከስድስት ወራቶች እስከ ዓመት ቀጠሮ መጠበቅ ግድ ይላል። እነሆ ዛሬ እዛው ፓኪስታን ውስጥ በሽተኞችን ለማከም ቀጠሮ ይዘዋል። ካሉበት ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ለመሄድ በአውሮፕላን ጉዞ ጀምረዋል። ብዙም ሳይርቁ የተሳፈሩበት አውሮፕላን በገጠመው ጭጋጋማና መጥፎ የአየር ሁኔታ በአንድ ትንሽ ከተማ አየር ማረፊያ ለማረፍ ተገደዱ። ከአውሮፕላኑ ወርደው የአየር ሁኔታው እስኪሻሻል ቢጠብቁም እንዳሰቡት ሳይሆንላቸው ቢቀር የአውሮፕላኑን ፓይለት የጉዟቸው መዳረሻ ወደሆነችው ከተማ ለመድረስ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ጠየቁት። ፓይለቱም ሶስት ስዓት እና ከዛ በላይ እንደሚሆን ነገራቸው። ዶክተሩ አንድ የሚያስጨንቃቸው ነገር አለ።  ብዙ ህመምተኞች የእሳቸውን እርዳታ በመፈለግ በቀጠሯቸው መሰረት የሳቸውን መምጣት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው አሳስቧቸዋልና በዚህ ሁኔታ ለማደር አእሞሯቸው አልፈቀደም። መኪና ይዘው ጉዟቸውን ለመቀጠል ይወስናሉ። ግና ትንሽ ከተጓዙ በኋላ ከባድ ዝናብ መንገዳቸውን ገታው። መንገዱ ጭቃማ ስለሆነ  መኪናቸውን መንቀሳቀስ ባለመቻሏ አሁንም በድጋሚ ባሉበት ስፍራ ለመቆየት ተገደዱ። አሁን ያሉበት መንደር ደግሞ በጣም ሩቅ የሆነ ገጠራማ መንደር ሲሆን ዝናቡ እስኪያባራ ከመኪናቸው ወርደው ሰላት ለመስገድ አሰቡ። ውሃ እና መስገጃ ፍለጋ ወደ አንድ ቤት አቀኑ። በሩን በዝግታ አንኳኩ። እድሜያቸው  ገፋ  ያለ አንዲት  አዛውንት በሩን ከፈቱ። ምን ልርዳችሁ በማለት ጠየቁ። ዶክተሩም ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ ሰላት ለመስገድ ስለፈለኩኝ ጥቂት  ውሃ እና መስገጃ ፈልጌ ነው በማለት ጠየቁ። መርሃባ ግቡ በማለት ውሃ እና መስገጃ አቀረበችላቸው። ሰግደው እንደጨረሱ ሙስልሟን ሴት አመስግነው ሊወጡ በመራመድ ላይ ሳሉ አልጋ ላይ የተኛ ሰው ተመለከቱ “ምነው?.. ምን ገጥሞት ነው?” ብለው ጠየቁ።  ሴትዮዋም ታሪኩን ታወጋ ጀመር “እዚህ ቤት ውስጥ የምንኖረው እኔና ይህ የምትመለከቱት ልጄ ነው። ለረጅም ጊዜ በያዘው ህመም በመሰቃየት ላይ ነው። በተደጋጋሚ የተለያዩ ሐኪሞች ጋር በመሄድ ሕክምና እንዲያገኝ ብሞክርም ሳይሳካ ቀረ። ዶክተሮች ወደ ታዋቂ ስፔሻሊስት ዶክተር እንድሄድ በሰጡኝ ጥቆማ መሠረት ወደተባለው ዶክተር ዘንድ ሄጄ ነበር። ነገር ግን ዶክተሩ ብዙ በሽተኞች ስለሚያስተናግዱ እሳቸውን ማግኘት እንደማይቻልና ከ6 ወር በሃላ እንድንመለስ ቀጠሮ ተሰጥቶን ወደ ቤት ተመለስን” አሉ አዛውንቷ ትክዝ ብለው መሬት እንዳቀረቀሩ ንግግራቸውን ቀጠሉ “እኔ አቅመ ደካማ አዛውንት ነኝና ልጄን ይዤ ወደ ቤት ተመለስኩ። አላህን ቀንና ማታ እየለመንኩት ነው። አልሀምዱሊላህ እስካሁን ነብሱ አለች...” አሉ አዛውንቷ እምባ እየተናነቃቸው። ዶክተሩ  የሴትዮዋን ንግግር በጥሞና አድምጠው ሲጨርሱ ”ማን የሚባል ዶክተር ጋር ነው ዶክተሮች እንድትሄዱ የነገሯችሁ?” አሉ። “አንድ ታዋቂ የሆነ ስሙ ዶ/ር ኢሻም የሚባል ሀኪም ዘንድ እንድሄድ ነበር የተነገረኝ” በማለት ለዶክተሩ ምላሽ ሰጡ። የሰሙትን ነገር ለማመን የከበዳቸው ዶክተር እራሳቸውን መቆጣጠር ተስኖዋቸው  እምባቸውን ማፍሰስ ጅመሩ። አስከተሉና "አላህ ዱአዎትን ሰምቶ ምላሽ ሰጥቷል” አሉና ንግግራቸውን አስከተሉ “ህመምተኞችን ለመርዳት ወደሌላ ከተማ ቀጠሮ ነበረኝ። በአውሮፕላን ጉዞዬን ጀመርኩ ግን በመጥፎ የአየር እክል ምክንያት ሳይሳካ ቀረ እንደገና በመኪና ጉዞዬን ለመቀጠል ሞከርኩ። በከባድ ዝናብ እና ጭቃ እዚህ መንደር ለመቆየት ተገደድኩ ...” በማለት ተናገሩ። ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪኩን ስሰማ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር ይላሉ ታሪኩን የተረኩልን ሙፍቲ ሜንክ። አላህ ይህን ውድ ዶክተር የዚህችን አቅም አልባ እና ልጇን ምታስታምም አዛውንት ቤት ድረስ አምጥቶ በራቸውን እንዲያንኳኩ ሲያስደርግ፣ ሩቅ እና ገጠራማውን መንደር አቆራርጦ አላህ በችሎታው ቤት ድረስ ሲያመጣው ከማየት በላይ ሚያስደንቅ ነገር አለመኖሩን እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ። አላህን የያዘ ምን አጣ አላህንስ ያጣ ምን አገኘ @yasin_nuru @yasin_nuru
Mostrar todo...
137👍 80🥰 9🤗 4🤓 1
በዚህ ታሪክ ውስጥ አላህ ምን ያህል ለባሮቹ ሩህሩህ፣ ያሻውን የሚያደርግ ኃያል ጌታ እንደሆነ እንረዳ ዘንድ እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ Mahi Mahisho ውልደታቸው በፓኪስታን ዋና ከተማ ነው። በዘመናችን አንቱታን ያተረፉ ከኒውሮሎጂ የህክምና ዘርፍ ጠበብቶች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ  ስመ-ጥር ስፔሻሊስት ናቸው። ሕክምና ለመስጠት ከሀገር ወደ ሀገር ከከተማ ወደ ገጠር ስለሚዘዋወሩ በስራቸው ባህሪ ከባድነትና እረፍት አልባነት ጋር ተደማምሮ ህመምተኞች እሳቸውን በቀላሉ ለማግኘት ይቸግራቸዋል። ከስድስት ወራቶች እስከ ዓመት ቀጠሮ መጠበቅ ግድ ይላል። እነሆ ዛሬ እዛው ፓኪስታን ውስጥ በሽተኞችን ለማከም ቀጠሮ ይዘዋል። ካሉበት ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ለመሄድ በአውሮፕላን ጉዞ ጀምረዋል። ብዙም ሳይርቁ የተሳፈሩበት አውሮፕላን በገጠመው ጭጋጋማና መጥፎ የአየር ሁኔታ በአንድ ትንሽ ከተማ አየር ማረፊያ ለማረፍ ተገደዱ። ከአውሮፕላኑ ወርደው የአየር ሁኔታው እስኪሻሻል ቢጠብቁም እንዳሰቡት ሳይሆንላቸው ቢቀር የአውሮፕላኑን ፓይለት የጉዟቸው መዳረሻ ወደሆነችው ከተማ ለመድረስ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ጠየቁት። ፓይለቱም ሶስት ስዓት እና ከዛ በላይ እንደሚሆን ነገራቸው። ዶክተሩ አንድ የሚያስጨንቃቸው ነገር አለ።  ብዙ ህመምተኞች የእሳቸውን እርዳታ በመፈለግ በቀጠሯቸው መሰረት የሳቸውን መምጣት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው አሳስቧቸዋልና በዚህ ሁኔታ ለማደር አእሞሯቸው አልፈቀደም። መኪና ይዘው ጉዟቸውን ለመቀጠል ይወስናሉ። ግና ትንሽ ከተጓዙ በኋላ ከባድ ዝናብ መንገዳቸውን ገታው። መንገዱ ጭቃማ ስለሆነ  መኪናቸውን መንቀሳቀስ ባለመቻሏ አሁንም በድጋሚ ባሉበት ስፍራ ለመቆየት ተገደዱ። አሁን ያሉበት መንደር ደግሞ በጣም ሩቅ የሆነ ገጠራማ መንደር ሲሆን ዝናቡ እስኪያባራ ከመኪናቸው ወርደው ሰላት ለመስገድ አሰቡ። ውሃ እና መስገጃ ፍለጋ ወደ አንድ ቤት አቀኑ። በሩን በዝግታ አንኳኩ። እድሜያቸው  ገፋ  ያለ አንዲት  አዛውንት በሩን ከፈቱ። ምን ልርዳችሁ በማለት ጠየቁ። ዶክተሩም ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ ሰላት ለመስገድ ስለፈለኩኝ ጥቂት  ውሃ እና መስገጃ ፈልጌ ነው በማለት ጠየቁ። መርሃባ ግቡ በማለት ውሃ እና መስገጃ አቀረበችላቸው። ሰግደው እንደጨረሱ ሙስልሟን ሴት አመስግነው ሊወጡ በመራመድ ላይ ሳሉ አልጋ ላይ የተኛ ሰው ተመለከቱ “ምነው?.. ምን ገጥሞት ነው?” ብለው ጠየቁ።  ሴትዮዋም ታሪኩን ታወጋ ጀመር “እዚህ ቤት ውስጥ የምንኖረው እኔና ይህ የምትመለከቱት ልጄ ነው። ለረጅም ጊዜ በያዘው ህመም በመሰቃየት ላይ ነው። በተደጋጋሚ የተለያዩ ሐኪሞች ጋር በመሄድ ሕክምና እንዲያገኝ ብሞክርም ሳይሳካ ቀረ። ዶክተሮች ወደ ታዋቂ ስፔሻሊስት ዶክተር እንድሄድ በሰጡኝ ጥቆማ መሠረት ወደተባለው ዶክተር ዘንድ ሄጄ ነበር። ነገር ግን ዶክተሩ ብዙ በሽተኞች ስለሚያስተናግዱ እሳቸውን ማግኘት እንደማይቻልና ከ6 ወር በሃላ እንድንመለስ ቀጠሮ ተሰጥቶን ወደ ቤት ተመለስን” አሉ አዛውንቷ ትክዝ ብለው መሬት እንዳቀረቀሩ ንግግራቸውን ቀጠሉ “እኔ አቅመ ደካማ አዛውንት ነኝና ልጄን ይዤ ወደ ቤት ተመለስኩ። አላህን ቀንና ማታ እየለመንኩት ነው። አልሀምዱሊላህ እስካሁን ነብሱ አለች...” አሉ አዛውንቷ እምባ እየተናነቃቸው። ዶክተሩ  የሴትዮዋን ንግግር በጥሞና አድምጠው ሲጨርሱ ”ማን የሚባል ዶክተር ጋር ነው ዶክተሮች እንድትሄዱ የነገሯችሁ?” አሉ። “አንድ ታዋቂ የሆነ ስሙ ዶ/ር ኢሻም የሚባል ሀኪም ዘንድ እንድሄድ ነበር የተነገረኝ” በማለት ለዶክተሩ ምላሽ ሰጡ። የሰሙትን ነገር ለማመን የከበዳቸው ዶክተር እራሳቸውን መቆጣጠር ተስኖዋቸው  እምባቸውን ማፍሰስ ጅመሩ። አስከተሉና "አላህ ዱአዎትን ሰምቶ ምላሽ ሰጥቷል” አሉና ንግግራቸውን አስከተሉ “ህመምተኞችን ለመርዳት ወደሌላ ከተማ ቀጠሮ ነበረኝ። በአውሮፕላን ጉዞዬን ጀመርኩ ግን በመጥፎ የአየር እክል ምክንያት ሳይሳካ ቀረ እንደገና በመኪና ጉዞዬን ለመቀጠል ሞከርኩ። በከባድ ዝናብ እና ጭቃ እዚህ መንደር ለመቆየት ተገደድኩ ...” በማለት ተናገሩ። ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪኩን ስሰማ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር ይላሉ ታሪኩን የተረኩልን ሙፍቲ ሜንክ። አላህ ይህን ውድ ዶክተር የዚህችን አቅም አልባ እና ልጇን ምታስታምም አዛውንት ቤት ድረስ አምጥቶ በራቸውን እንዲያንኳኩ ሲያስደርግ፣ ሩቅ እና ገጠራማውን መንደር አቆራርጦ አላህ በችሎታው ቤት ድረስ ሲያመጣው ከማየት በላይ ሚያስደንቅ ነገር አለመኖሩን እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ። አላህን የያዘ ምን አጣ አላህንስ ያጣ ምን አገኘ ለአስተያየትዎ @Strong_iman_bot ይጠቀሙ @yasin_nuru
Mostrar todo...
ቢስሚላሂ ረሕማኒ ረሒም - መልካም ምክሮች 1- ቀንህን ከምትጀምርባቸው ነገሮች ሁሉ ዚክር እና ሶላት ምርጦቹ ናቸው!! 2- ወንጀል ብትሰራም ባትሰራም ምላስህ ሌት ተቀን አላህን እስቲግፋር ከመጠየቅ አይቦዝን! 3- በዱዐ አትዘናጋ ለመዳን ወሳኙ መሳሪያ እሱ ነውና!! 4- ከመናገርህ በፊት ቃላቶችህን የሚፅፉ መላኢካዎች አጠገብህ እንዳሉ አትዘንጋ!! 5- ትልቅ ማእበል ቢያጋጥምህ እንኳ አሁንም መውጫ እንዳለህ አስብ!! 6- አለንጋ ጣቶችህ የበለጠ የሚያምሩት ዚክር ላይ ሲሳተፉ ነው!! 7- ለዱዐ ምላሽ የምታገኝበትን እድል ሐራም በመብላት አትዝጋው!! 8- የመጥፎ ጥርጣሬ አባዜ ከሌለብህ ደስተኛ ሁነህ ትኖራለህ!! 9- በጋዜጣና በሞባይል ፍቅር ከመውደቅህ በፊት በቁርአን ፍቅር ውደቅ!! 10- የሰው ልጅ ነፍሱ አመፀኛ ናትና በአላህ ትዛዝ ላይ አስገድዳት!! 11- ያንተ አሮጌ ልብሶች ለድሃ አዳድሶች ናቸው!! 12- ምድርን ስትሰናበት ካንተ ጋራ መቃብር የሚገባ ስራ ይኑርህ!! 13- ሀሜተኛ ሰው ካጋጠመህ 'አላህን ፍራ' ለማለት አትፍራ!! 14- ህይወት በተፈጥሮ ውብ ናት፣ ከኢማንና ከተስፋ ጋር ደግሞ እጅግ ውብ ናት!! 15- የምትቸኩልለት ነገር ሁሉ ከሶላት የሚበልጥ አይደለምና ተረጋግተህ ስገድ!! 16- ህይወት እኛ ከምንገምተው በላይ በጣም አጭር ናትና ከዚህም ከዚያም ጋር አትጋጭ!! 17- የጭንቀት ሁሉ መንስኤው ከአላህ ﷻ መራቅ ነውና በተቻለህ አቅም ከአላህ ላለመራቅ ሞክር!! @yasin_nuru @yasin_nuru
Mostrar todo...
👍 133 65😁 3👏 1😭 1