cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

All about businesses in Ethiopia 🇪🇹

የስራና መገበያያ ገፅ #ስራ እና ስራነክ የሆኑ ጠቃሚ የቢዝነስና የስራ ፈጠራ መረጃዎች የሚለጠፉበት ገፅ ነው

Mostrar mĂĄs
Publicaciones publicitarias
6 380
Suscriptores
-624 horas
-67 dĂ­as
-22330 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Business 104 | ቢዝነስ ፩ ፩   ብራንድን አቅልለህ አትየው ። በዚህ ዘመን በየትኛውም      ቢዝነስ ውስጥ ብራንድ ትርጉም አለው ።የምትመነዝረው       የማይታይ ሃብት ነው ። intangable assets       ቢዝነስህን  ከጀመርክ ቀን ጀምሮ አስበህም ሆነ       ሳታስበው ብራንድህ   ላይ ኢንቨስት እያደረክ ነው ።       ታድያ ይህ በየእለቱ ወጪ እያወጣህበት ያለውን      ብራንድን አስበህበት አቅደህ ለምን አትገነባውም  ?       ትርፍህ ያለው እዛ ላይ ነውና አስብበት እያወራሁህ       ያለሁት Nurture Brand Advocates ስለሚባለው       ነገር ነው ። ፪  ገበያን መፍጠር የምትችለው አንተ ነህ። ገበያ ወደ አንተ      አይመጣም ። አንተ ነህ ወደ ገበያው መሔድ ያለብህ ።     ገበያውን ለ ቢዝነስህ እንዲመቸው አድርገህ ፍጠረው ።      ደሃና ገበያ አይገናኙም የሚባለውን አባባል ተወው ።      ሰላሳ ቀን እንዴት unlucky ትሆናለህ ? አመቱንስ ሙሉ      ሰርተህ እድል ላይኖርህ ይችላል ? አሰራርህን ግን       መቀየር አለብህ ። በተመሳሳይ መንገድ እየሰራህ       የተለየ ነገር አትጠብቅ ።    ጥሩ  ገበያ ማለት የ አራት ነገሮች ውህድ ነው ። ምርት     ወይንም  አገልግሎቱ ፣ ቦታ ፣ ዋጋ እና  ፕሮሞሽን ።      እነዚህም 4P በመባል  ይታወቃሉ ። product , place      price and promotion .በጥሩ ቀመር አዋህዳቸው። ፫    ደስተኛ ያልሆኑ ደንበኞች ትልቅ እውቀት የምናገኝባቸው       ትምህርት ቤቶቻችን ናቸው ። ቢዝነስ ማለት       የደንበኞችህን  ህመም እና ችግር ፈትተህ እንዲደሰቱ        የምታደርገው ስራ ነው ። ወይንም ግንኙነት ማለትም        ልንለው እንችላለን ።        ከእያንዳንዱ ደበኞችህ ጋር የምታደርጋቸው ግብይት       ከተከናወነ በኋላ ግንኙነትህ ተጠናቋል ማለት መሆን       የለበትም ። እንዲህ እንዲሆን በጭራሽ  አትፍቀድ ።       የግብይት መዝጊያ ማለት የግንኙነት መጀመሪያ       መሆኑን  እወቅ ። ለምን መሰለህ ቢዝነስ ማለት        ግንኙነት ማለት  ነው ። Business is all about a        relationship .        ሰኑይ የሆነች ሰኞ ትሁንላችሁ ! Engineer Kefe Haylu
Mostrar todo...
Business 104 | ቢዝነስ ፩ ፩ ብራንድን አቅልለህ አትየው ። በዚህ ዘመን በየትኛውም ቢዝነስ ውስጥ ብራንድ ትርጉም አለው ።የምትመነዝረው የማይታይ ሃብት ነው ። intangable assets ቢዝነስህን ከጀመርክ ቀን ጀምሮ አስበህም ሆነ ሳታስበው ብራንድህ ላይ ኢንቨስት እያደረክ ነው ። ታድያ ይህ በየእለቱ ወጪ እያወጣህበት ያለውን ብራንድን አስበህበት አቅደህ ለምን አትገነባውም ? ትርፍህ ያለው እዛ ላይ ነውና አስብበት እያወራሁህ ያለሁት Nurture Brand Advocates ስለሚባለው ነገር ነው ። ፪ ገበያን መፍጠር የምትችለው አንተ ነህ። ገበያ ወደ አንተ አይመጣም ። አንተ ነህ ወደ ገበያው መሔድ ያለብህ ። ገበያውን ለ ቢዝነስህ እንዲመቸው አድርገህ ፍጠረው ። ደሃና ገበያ አይገናኙም የሚባለውን አባባል ተወው ። ሰላሳ ቀን እንዴት unlucky ትሆናለህ ? አመቱንስ ሙሉ ሰርተህ እድል ላይኖርህ ይችላል ? አሰራርህን ግን መቀየር አለብህ ። በተመሳሳይ መንገድ እየሰራህ የተለየ ነገር አትጠብቅ ። ጥሩ ገበያ ማለት የ አራት ነገሮች ውህድ ነው ። ምርት ወይንም አገልግሎቱ ፣ ቦታ ፣ ዋጋ እና ፕሮሞሽን ። እነዚህም 4P በመባል ይታወቃሉ ። product , place price and promotion .በጥሩ ቀመር አዋህዳቸው። ፫ ደስተኛ ያልሆኑ ደንበኞች ትልቅ እውቀት የምናገኝባቸው ትምህርት ቤቶቻችን ናቸው ። ቢዝነስ ማለት የደንበኞችህን ህመም እና ችግር ፈትተህ እንዲደሰቱ የምታደርገው ስራ ነው ። ወይንም ግንኙነት ማለትም ልንለው እንችላለን ። ከእያንዳንዱ ደበኞችህ ጋር የምታደርጋቸው ግብይት ከተከናወነ በኋላ ግንኙነትህ ተጠናቋል ማለት መሆን የለበትም ። እንዲህ እንዲሆን በጭራሽ አትፍቀድ ። የግብይት መዝጊያ ማለት የግንኙነት መጀመሪያ መሆኑን እወቅ ። ለምን መሰለህ ቢዝነስ ማለት ግንኙነት ማለት ነው ። Business is all about a relationship . ሰኑይ የሆነች ሰኞ ትሁንላችሁ !
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
2016 ዓ.ም. የቢዝነሥ ሃሣብ #007 ኬኔቶ ሠርቶ አሽጎ መሸጥ። ኮካኮላ፣ፔፕሢ፣ጁሥ፣ማልት ወዘተ ፋብሪካዎች ተደራሽነታቸውን ያሠፉት በ 'bottel it' ማርኬቲንግ እሥትራቴጂ ነው። ኬኔቶ ከአልኮል ነጻና በተለየ መልኩ በብዛት ማህበረሠባችን እየተጠቀመውና እየተለማመደው ያለ የመጠጥ አይነት ነው።በምግብ የጎለበተ ማድረጉን እንዳትረሡ።በተረፈ የምግብ፣የጤና ወዘተ ባለሙያ ምክርን /እገዛን ተጠቀሙ። በዘመናዊ መልክ ገብሡን አበጥረን ፣ቆልተን፣ፈጭተን፣ቀቅለን፣የተለያዩ ግብአቶችን በመጨመር (እንደየ ቅመማው ይለያያል) ወዘተ... በማጣራት በ ካርቦን ዳይኦክሣይድ ጋዝ በጠርሙሥ ወይም በ PET bottel በማሸግ ወደገበያ ማሥገባት ነው።ድግሦች፣ሆቴሎች፣ሡቆች፣ ወዘተ ገበያችሁ ይሆናሉ። በማሽን የታገዘ ምርት ቢኖራችሁ ደግሞ የማምረት አቅማችሁ ይጨምራል። ለምሣሌ.... ማበጠሪያ፣ ማጠቢያ፣መቁያ፣መፍጫ፣መቀቀያ፣ ሪአክተር(optional)፣መቀላቀያ፣ሤትለር፣መቀመሚያ፣ማጣሪያ እና ማሸጊያ ማሽን በጥቂቱ ያሥፈልጋችኋል። የካርቦን ዳይኦክሣይድ ግብአት በቀላሉ ሥለምታገኙ ጋዙን መሥሪያ ለጊዜው አያሥፈልጋችሁም።ኦግዝለሪ ኢኪውፕመንት ቦይለር፣ኮምፕረሠር፣ጀነሬተር እና የውሣ ማጣሪያ መረሣት የለበትም።ሢአይፒ ሢሥተማችሁን ተመልከቱት። ለምሣሌ በቀን 5,000 ሊትር የተጣራ ኬኔቶ ለማምረት 100kw 3phase የኤሌክትሪክ ሃይል፣15m by 10m በ5m ከፍታ የማሽን ቦታ ይፈልጋል። አሥፈላጊውን ህጋዊ ፍቃዶች እንዳትረሡ። በመደራጀት መሥራት ብትችሉም አሪፍ ነው።ቦታ ያለው፣እውቀት ያለው ፣ገንዘብ ያለው፣ጉልበት ያለው ተደራጅቶ መሥራትም ይቻላል። በርቱ!
Mostrar todo...
ቢዝነስ 102 ፩ ደንበኛህን እንደ ተቆጣጣሪዎችህ ተመልከት ። መመልከት ብቻ ሳይሆን ከልብህ አክብር ። ማክበር ብቻ ሳይሆን ገና ከቤቱ ሳይነሳ እንዳውም ገና ሳታውቀው ጭምር ውደደው ። ለምን መሰለህ ? ደሞዝህን የሚከፍለው እሱ ነው ። ማክያቶ የሚጋብዝህ ልጆችህን ትምህርት ቤት የሚከፍልልህ ነዳጅ የሚችልልህ ኧረ ስንቱ የቢዝነስህ ሞተር እሱ ስለሆነ ነው ። ደንበኛ ከሌለ ቢዝነስ የሚባል ነገር የለም ። ፪ የደንበኞችን ፍላጎት እግር በእግር ተከታተል ። የምትሸጥለት አንተ የምትፈልገው ሳይሆን እሱ የሚፈልገው መሆኑን አረጋግጥ ። በደንበኞች አገልግሎት ውስጥ ሁለት ነገሮችን አትርሳ የደንበኛህን ችግር ወይንም ህመም ማውቅ እና ለዚህም መፍትሄ አምጥቶ ማርካት የሚባሉትን ነገሮች ( pain and satisfaction . ፫ የደንበኞች ፍላጎት በየጊዜው እንደሚቀያየር ተረዳ ። የጥሩ ነገር ፍላጎት እየጨመረም የሚመጣ ጉዳይ ነው ። አዲስ አገልግሎት አዲስ ምርትም እንዲሁ ። እነ ሳምሰንግ እና አፕል አዳዲስ ነገር በየጊዜው ይዘው የሚመጡት እና ደንበኞቻቸውን ሰርፕራይዝ የሚያደርጉት ለምን ይመስልሃል ? የደንበኞች ፍላጎት የሚቀያየር እና የሚጨምር ስለሆነ ነው ።
Mostrar todo...
ቢዝነስ 101 ፩ እጅግ በጣም ካልተቸገርክ በስተቀር ቢዝነስ ለመስራት ስታስብ አየር ባየር አድርገው ። ምክንያቱም መሬት ለማውረድ ስትሞክር በጣም አስቸጋሪ ነው ። ፪ ካፒታል እንደሚያስፈልግህ ግልፅ ነው ። ካፒታልን ፍለጋ ባንኮችን ምርጫህ ማድረግ ግን አያዋጣም ። ምክንያቱም ባንኮች ባንተ ገንዘብ ካፒታል ሊሰሩ እንጂ ካንተ ጋራ ሊሰሩ ፍላጎት የላቸውም ። ይልቁንም እቁብን የመሳሰለ አማራጭን ተጠቀም ። ፫ የታክስ ከፋይ ቁጥር ማውጣት ማለት በራስህ ላይ ሰላይ እንደመጥራት ሊሆን ይችላል ። እንዲሁም ስህተት ፈልጎ እስር ቤት ሊወረውርህ እና አስፈራርቶ ገንዘብ ሊቀበልህ የተዘጋጀ ጦርን መጋበዝ መሆኑን አውቀህ ጥንቃቄ አድርግ ። ሊረዱህ ወይንም ምን ቸገረህ እናግዝህ ብለው አይደለም ። ለፍልሚያውም ህጋዊ ሆነህ ተዘጋጅ። ማሳሰቢያ አየር ባየር ማለት Asset light የሚለውን እንግሊዝኛ ለመተካት ነው ።
Mostrar todo...
ህይወትህን እያባከነህ እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች እና እንዴት ማስተካከል እንደምትችል። 1. በማህበራዊ ሚዲያ የዜና መጋቢ ውስጥ ያለ አላማ በማሸብለል በስማርትፎንዎ ላይ ብዙ ጊዜ ያሳልፋሉ 2. Netflix/TV፣ TikTok እና Facebook አስቂኝ ቪዲዮዎችን በመመልከት ከመጠን በላይ ተጠምደዋል 3. ቅዳሜና እሁድን በሙሉ ድግስ ያደርጋሉ 4. ስልክዎን ከእንቅልፍዎ በኋላ ለአንድ ሰአት ወይም ከዚያ በላይ ይጠቀማሉ እና ልክ እንደሰነፍ ይሰማዎታል 5. ሰዓትህን በመስመር ላይ የሌሎች ሰዎችን ህይወት በመመልከት ታጠፋለህ 6. ሁል ጊዜ የወሬ ዜናዎችን ፣የታዋቂ ሰዎችን ወሬዎችን ፣የአዳዲስ ወሬዎችን እና የማህበራዊ ሚዲያን በመታየት ላይ ይገኛሉ። 7. በመስመር ላይም ሆነ ፊት ለፊት ሐሜትን በተደጋጋሚ ትፈፅማለህ 8. ያለአቅጣጫ በሕይወታችሁ ውስጥ በእንቅስቃሴዎች ውስጥ ብቻ ነው የምታልፉት 9. ለቀጣዩ ቀን ምንም የታቀደ ነገር ስለሌለ በእውነቱ ቀኑ እንዲያልቅ አይፈልጉም 10. በመጨረሻ, ጊዜዎን በተሻለ መንገድ ባለማሳለፍዎ ውስጥዎ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማዎታል አሁን፣ ህይወትዎን ለመቀየር እነዚህን ሁሉ አሉታዊ ምልክቶች እንዴት ማስተካከል ይችላሉ? አንብብ፡- 1. በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምታጠፋውን ጊዜ በእጅጉ ገድብ። የጊዜ ገደብዎን ሲያልፉ ለማስታወስ በስልክዎ ውስጥ የሰዓት ቆጣሪን መጠቀም ይችላሉ። የሶሻል ሚዲያ የስራዎ ወይም የንግድዎ አካል ካልሆነ በስተቀር። 2. ተዛማጅነት የሌላቸውን የመስመር ላይ ይዘቶች ፍጆታዎን ለግል እድገትዎ በማንበብ ይተኩ። ብዙ ያንብቡ ወይም እዚያ በሚሆኑበት ጊዜ ህይወትዎን በተሻለ ሁኔታ ለመለወጥ አቅም ያላቸውን ጠቃሚ ይዘቶች ያንብቡ። 3. በፓርቲ ላይ ከመጠን በላይ ከመጠመድ ይልቅ ቅዳሜና እሁድን በጎንዎ ላይ ለመስራት ወይም አንዱን ለማግኘት፣ አዲስ ክህሎት ለመማር፣ ስፖርት ለመጫወት ወይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያሳልፉ። ይሁን እንጂ ድግስ አልፎ አልፎ ጥሩ ነው. 4. በማለዳ ከእንቅልፍዎ ሲነቁ የሚከናወኑትን ስራዎች ዝርዝር የቀደመውን ምሽት ወይም የመጀመሪያ ነገር ይፍጠሩ እና ወዲያውኑ ማለዳዎን ለእራስዎ በተዘጋጀ ጥራት ባለው የጠዋት ስራ ያበረታቱ። 5. ስሜት ቀስቃሽ ዜናዎችን መመልከት አቁም እና እንደ ፖለቲካ፣ ንግድ፣ የስራ እድል፣ ፋይናንስ፣ ኢኮኖሚ ወዘተ ባሉ ጠቃሚ ዜናዎች እራስህን አዘምን። ራስህን እየታገልክ ታሪካቸውን በማሳየት ታዋቂ ሰዎችን ማበልጸግ አቁም። 6. ከሰዎች ጋር የምታደርጉትን ውይይቶች እርስ በርስ ወደ ሚበረታቱ ርዕሶች፣ ማሻሻያዎች፣ እድሎች ቀይር እና የተሻለ እንድትሆን የሚያነሳሱ ማህበራዊ ክበቦችን ይፍጠሩ። 7. እቅድ ያውጡ, ቀንዎን ያቅዱ እና ሳምንትዎን ያዘጋጁ; የታቀደው ይከናወናል፣ ያልታቀደው በቀላሉ ይዘለላል ወይም ይረሳል። 8. ከላይ ያሉትን ሁሉ ያድርጉ እና በዚህ አመት ምን ያህል ርቀት መሄድ እንደሚችሉ ይመልከቱ.

"If you want to move to a new level in your life, you must break through your comfort zone and practice doing things that are not comfortable." ~ T. Harv Eker
Mostrar todo...
"Selling is not convincing. Selling is helping." - Mark Cuban #marketing
Mostrar todo...
What is Business? | ንግድ ምንድን ነው? ንግድ በአጭር አገላለጽ ሰዎች የሚፈልጉትን ዕቃ ወይም አገልግሎት ለገበያ አቅርቦ ከተገዛበት ወይም ከተመረተበት ዋጋ በላይ በትርፍ መሽጥ ነው። ከዚህ አገላለጽ እንደምንረዳው በንግድ ውስጥ ያሉ 4 ቁልፍ ጉዳዮች አሉ። 💢 አንደኛው ምርቱን ወይም አገልግሎቱን የሚፈልጉትን ሰዎች መለየት ነው። [ ምርትና አገልግሎትህ የሚስማማው ለማን ነው? ማንን አስበህ ነው ያመረትኸው? የማንን፣ የትኛውን ችግር ነው ልትፈታ ያለምከው? "ለሁሉም!" የሚባል መልስ የለም። ያ የሰነፍና የግዴለሽ መልስ ነው። የደንበኛ ዒላማህን ገና ከመነሻህ ለይ! ዳቦን እንኳ ሁሉም አይበላም። ኮካኮላን ሁሉም አይጠጣም። ዒላማዎችህን ገና ከመነሻው ለይና ፍላጎታቸውን እወቅ። ዒላማ እንዴት ይለያል? ፍላጎቱስ እንዴት ይታወቃል? የባለሙያ እገዛ ተጠቀም።] 💢 ሁለተኛው ምርትና አገልግሎትህን ለገበያ ማቅረብና ከሌሎች ተለይቶ መመረጥ መቻል ነው። [ ሥራህን ለገበያ አቅርበሃል? ሥራህ ለገበያ ካልወጣ የሙዝየም ዕቃ ወይም ለኤግዚቢሽን ትዕይንት የቀረበ ነውና ክፍያ አታገኝም። ሥራህን ለገበያ አውጣ፣ አስተዋውቅ። ሰዎች አንተን ለምን ይመርጡሃል? ምርትህና አስተሻሸጉ፣ አገልግሎት አሰጣጥህና ደንበኛ አቀባበልህ ማራኪ ነው? ከሌሎች ተለይቶ የሚመረጥ ነው? ዋጋህ ለምርትና ለአገልግሎትህ ተመጣጣኝ ነው? ቦታህስ አመቺና ጽዱ ነው? በምን ትመረጣለህ?] 💢 ሦስተኛው ጉዳይ አትራፊ ዋጋን መተመን ነው። [ ለመሆኑ የምትሸጠውን ዕቃ ይሁን አገልግሎት ዋጋ እንዴት ትተምናለህ? ወጪህ ስንት ነው? የምትጠብቀው ትርፍ ስንት ነው? ሌሎች ተፎካካሪዎችህ በስንት ይሸጣሉ? ገዢዎችህስ በስንት የመግዛት ዓቅም አላቸው? ይህንን መፈተሽ ለትርፋማነትህ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ይህንን የዋጋ ትመና ጉዳይ ብዙዎች በዘፈቀደና የተፎካካሪን ዋጋ በመከተል ሲተምኑ ይታያል። ያ አደገኛ አካሄድ ነው። ለነገሩ ዋጋ መተመን የሚችል ብዙ ባለሙያም የለም። አንተ ግን ሁነኛ ባለሙያ ፈልግ። ይህንን የዋጋ ትመና ሥራ በዘፈቀደ ማሠራት ኋላ ከፍ ያለ ፀፀት ያመጣልና ተጠንቀቅ!] 💢 አራተኛው የምታመርተውን ምርት መሸጥ ነው። [የምትሸጠውን ዕቃ እንዴት ትገዛለህ? እንዴት ታመርታለህ? እንዴት ታጓጉዛለህ? እንዴት ታከማቻለህ? እንዴት ትደረድራለህ? እንዴት ትሸጣለህ? ማን ገንዘብ ይቀበል? ማን ይጫን? ማን ሥራውን ይምራ? ማን ገንዘቡን ባንክ ያስገባ? ማን ታክስ ይክፈል? ጥሩ የሥራ ክፍፍል፣ አደረጃጀት፣ ብቁ ሠራተኞችና ጥሩ የሠራተኛ አያያዝ ካለህ ሥራህ ላንተም፣ ለሠራተኞችህም ለደንበኞችም ሳቢና አስደሳች ይሆናል።] እናስ? የቱን አሟልተህ ይዘሃል? የቱ ጎድሎሃል? በል እንግዲህ ደንበኛህን ለይ •አቅርቦትህን ተመራጭና ተከታታይ አድርግ •ተመጣጣኝ ዋጋ ተምን •ቀልጠፍ ብለህ በፈገግታ ያለ ግርግር ሽጥ።
Mostrar todo...