cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ዚክረላህ ጀመዓ( ذيكرالله )

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? ይህ የዚክረላህ ጀመዓ ቻናል ነው https://t.me/joinchat እንኩዋን ወደ ዚክረላህ ጀመዓ(ذيكرلله ) መጡ

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
165
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

::::::::::::::::::: ➣አላህን ብቻ መገዛት ➣እሱን እንጂ አለመፍራት ➣አምልኮን ለሱ ብቻ ማድረግ ➣እሱን ብቻ እንጂ አለመለመን ➣ወደሱ ብቻ እንጂ ይድረስልን ጥሪ አለማሠማት ➣በሱ እንጂ ያለመመካት ➣በሱ ብቻ እንጂ ያለመስገድ ያለማጎብደድ ➣በስሙ ብቻ እንጂ ያለማረድ ያለመሰዋት ➣በሰሙ ብቻ እንጂ ያለመማል ➣ስራን ለሱ ብቻ ጥርት አድርጎ መስራት ➣ከሱ አስበልጦ ሌላን አካል ያለመውደድ ➣ወደሱ ብቻ ተዉባ ማድረግ ➣ለሱ ብቻ እንጂ ስለት አለማድረግ ➣በደነገገዉ ሸሪዓ መዳኘት ➣ባወረደው ቁረዐን መሥራት ➣በላከው መልዕክተኛ ማመን ✦✦አላህ እንደ አለን ብቻ ነው ስራችን መሞትም በሱ ፍቃድ ነው ህይወታችን✦✦ ========================= 🙏🙏ሼር በማድረግ ተባበሩን🙏🙏 وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? ይህ የዚክረላህ ጀመዓ ቻናል ነው https://t.me/joinchat እንኩዋን ወደ ዚክረላህ ጀመዓ(ذيكرلله ) መጡ
Mostrar todo...
የጽዳት ሥራውን እየሠራ የጌታውን ቃል ያነባል‼ ============================= ✍ ሱጅድ ማድረግን በታዘዘ ጊዜም ባለበት ለጌታው ዝቅ ብሎ ሱጁድ ይወርዳል። ቁርኣንን ለሁሉም ህዝብ ገር ያደረገው አላህ ምስጋና የተገባው ነው። (وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ) «ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን?» [አል-ቀመር: 17] ዘር፣ ቀለም፣ ትንሽ፣ ትልቅ፣ ሴት፣ ወንድ… ሳይል ለሁሉም አግርቶታል። የወረደው በዐረቦች ቋንቋ ቢሆንም በሐበሾችም ይሁን በፈረንጆች ወይም በሌሎች አንደበት ሲነበብ ልብን እንደማረከ ነው‼ ♠ አላህ ልዩ ከሆኑት የቁርኣን ቤተሰቦች ያድርገን። የምንቀራው፣ የምንረዳው፣ የምንማረው፣ የምናስተምረው፣ ትዕዛዙንም የምንፈጽም ያድርገን። || https://t.me/joinchat/h3CVP5d2tDI4N2M0
Mostrar todo...
5.86 MB
~فَإِنِّى قَرِيبٌ (እኔ ቅርብ ነኝ፡፡) وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِى عَنِّى فَإِنِّى قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لِى وَلْيُؤْمِنُوا۟ بِى لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ ( አል- በቀራህ : 186) 🖋 ➷የአሏህ መልዕክተኛ ሰላምና እዝነት በሳቸው ላይ ይሁንና እንድህ አሉ፦ የተባረከውና የላቀው ጌታቹህ (ህያው ና ለጋሽ)ነው። ባሪያው እጆቹን አንስቶ የለመነው እንደሆነ ባዶ እጆቹን ሊመልሰው ያፍራል! ➷! (١) بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው እጀምራለሁ። ➷ብለሀትም ሀይልም በአሏህ ቢሆንጂ የለም። አንተን ብቻ እንገዛለን አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን አንተን ብቻ እናመሰግንሀለን ስለፈጠርከን፣ ሰለለገስከን፣ ቀናውን መንገድ ስለመራከን፣ ስላሳወቅከን፣ ከጥሜት ስለጠበቅከን፣ ኢማንን ስለለገስከን፣ ኢስላምን ስለመረጥክልን፣ቁረአንን ስላወረድክልን፣ቤተሰብን ጤናንና ፀጋን ስለለገስከን፣ አሏህ ሆይ! ምስጋና ይገባህ! ጠላትን የምትገታልን ሪዝቃችንን የምታሰፋልን ደህንነታችንን የምት ጠብቅልን ከመነጣጣል ያደንከን በመልካም የፈወስከን ለጥያቄዎቻችን ሁሉ መልስ የሰጠከን ! ተደራራቢ ምስጋና ይገባህ። በግልፅም በድብቅም ለብቻም ይሁን በህብረት በሂወት ላሉት ለሌሉትም በቅርቡም በሩቁም ላለ በኛ ላይ ለዋልክልን ወዴፊትም ለምትውለው ፀጋህ ጌታችን አሏሆይ ምስጋና ይገባህ ምስጋናችንን እስክትወድልን ከወደድክልንም በኋላ ምስጋና ይገባህ። ➷ አንድሁም በባልደረቦቻቸው ሰላምና እዝነትህ ይውረድ!https://t.me/joinchat/h3CVP5d2tDI4N2M0 ~(2) ይ.....ል...✍
Mostrar todo...
ዚክረላህ ጀመዓ( ذيكرالله جمع)

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? ይህ የዚክረላህ ጀመዓ ቻናል ነው

https://t.me/joinchat

እንኩዋን ወደ ዚክረላህ ጀመዓ(ذيكرلله جمع) መጡ

Mostrar todo...
ዚክረላህ ጀመዓ( ذيكرالله جمع)

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? ይህ የዚክረላህ ጀመዓ ቻናል ነው

https://t.me/joinchat

እንኩዋን ወደ ዚክረላህ ጀመዓ(ذيكرلله جمع) መጡ

✍ ያስተሳሰረን ቃል አለና ነው... 🌹إِنَّمَا ٱلْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌۭ فَأَصْلِحُوا۟ بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ •<<ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡>>• በቅርቡ እየደረሰ ባለው የፍሌስጤማዊያን ጭቆናን ለመቃወም ምን አነሳሳን!?(ከንፁህ ህሊና ባሻገር) 💕ልብ ለልብ ያስተሳሰረን ቃል አለንና ነው ርቀው ላሉ ወንድም እህቶቻችን ልባችን የሚደማው አይናችን ሚያነባው። ቁድስን ለመጠበቅ ዘብ ለቆሙት ጀግኖች ዱአ የምናደርገው! ያስተሳሰረን ቃል አለንና ነው... በሸርቅም በገርብ ስለሙስሊሙ እንባ የሚያስጨንቀን ሀዘናቸው የሚያስከፋን ስኬታቸው የሚያስደስተን! ያስተሳሰረን ቃል አለንና ነው... የየመን ሶሪያውያን የአፍጋን ሊቢያዊያን እንባ በእኛው አይን ሚነባው በእነርሱ ህመም ሀዘን የሚደቁሰን ያስተሳሰረን ቃል አለና ነው! አለም ሁሉ እኛ ላይ እጁን ለማንሳት ሲሞካክር እኛም ወደ ጌትዬ በዱዐ በዚክር እንጠክር ሀያል ነን ባዬችን በረቂቁ ህዋስ እንዲያ ያሸበራቸው ጌትዬ የሚሰሩትን በደል ተመልካች ነውና አብሽሩማ። 🌹وَلَا تَحْسَبَنَّ ٱللَّهَ غَٰفِلًا عَمَّا يَعْمَلُ ٱلظَّٰلِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍۢ تَشْخَصُ فِيهِ ٱلْأَبْصَٰرُ <<አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡>> 🌹مُهْطِعِينَ مُقْنِعِى رُءُوسِهِمْ لَا يَرْتَدُّ إِلَيْهِمْ طَرْفُهُمْ ۖ وَأَفْـِٔدَتُهُمْ هَوَآءٌۭ <<(ወደ ጠሪው መልአክ) ቸኳዮች ራሶቻቸውን አንጋጣጮች ኾነው (ዓይኖቻቸው ይፈጣሉ)፡፡ ዓይኖቻቸው ወደነርሱ አይመለሱም፡፡ ልቦቻቸውም ባዶዎች ናቸው፡፡>> !! 🌹. 🌻.
Mostrar todo...
💍::::::::ትዳር ሃላፊነት ነዉ::::::::::💍 ትዳር ሃላፊነት ነው መስዋዕትነት ይጠይቃል 📌✍! 💍ትዳር ለመመስረት አስበዋልን? ? ማንን❓ ለምን ❓❓ ከጂምሩ በጥያቄ አፈጠጥኳችሁ አይደል አፋዋን ማለት መስወዕትነት፣ ቀሪ ህይወታችንን ከአንድ ሰው ጋር ለማሳለፍ የምንወስንበት ትልቅ የህይወት ዘርፍ ስለሆነ ነው ። የትዳር አጋራችንን በምን መመዘኛ እንምረጥ ??❓❓ ትልቅ ሃገር የሚገነባበት መሰረት ነው፣ መሰረቱ ያላማረ ነገር እድሜ የለው ቶሎ ነው የሚፈርሰው ስለዚህ ኢስላም የትዳር መሰረቱ ጠንካራና በቀላሉ የማይፈር ለማድረግ መሰረቱን በዲን እና አኽላቅ ላይ እንዲገነባ ያስተምራል። በርግጥ የትዳር መሰረቶች የተለያዩ ናቸው ነገር ግን ከዲን እና አኽላቅ ውጪ ያሉት መሰረቶች እድሜ የሌላቸው የትዳር ጠንቅ ናቸው። ነገር ግን ዲን እና አኽላቅ የተቀሩትን መሰረቶች ይዘው ይመጣሉ። ﻭﻗﺪ ﺃﺧﺒﺮ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ، ﻋﻦ ﺫﻟﻚ ﺑﻘﻮﻟﻪ : « ﺗﻨﻜﺢ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻷﺭﺑﻊ ﺧﺼﺎﻝ : ﻟﻤﺎﻟﻬﺎ، ﻭﺟﻤﺎﻟﻬﺎ، ﻭﻟﺤﺴﺒﻬﺎ، ﻭﻟﺪﻳﻨﻬﺎ، ﻓﺎﻇﻔﺮ ﺑﺬﺍﺕ ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺗﺮﺑﺖ ﻳﺪﺍﻙ» ረሱል صلى الله عليه السلام እንዲህ ብለዋሉ፦ “💯ሴት ልጅ ለአራት ነገሮች ትገባለች። 📌ለገንዘቧ፣ 📌ለዘር ክብሯ፣ 📌ለውበቷና 📌ለዲኗ። ✍የዲን ባለቤት የሆነችውን ምረጥ።👌 (ይህን ላደረግክ) እጅህ አመድ አፋሽ ትሁን።” (ቡኻሪና ሙስሊም) ﺃﻓﻀﻞ ﻣﺎ ﻳﻨﺒﻐﻲ ﺗﻮﻓﺮﻩ ﻓﻲ ﺍﻟﺰﻭﺟﻴﻦ، ﻣﻠﺘﺰﻣﺎ ﺑﺸﺮﺍﺋﻊ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﻓﻲ ﺣﻴﺎﺗﻪ ﻓﻼ ﻳﻈﻠﻢ ﺯﻭﺟﺘﻪ، ﻓﺈﻥ ﺃﺣﺒّﻬﺎ ﺃﻛﺮﻣﻬﺎ ﻭﺇﻥ ﻟﻢ ﻳﺤﺒﻬﺎ ﻟﻢ ﻳﻈﻠﻤﻬﺎ ﻭﻟﻢ ﻳُﻬﻨﻬﺎ እጅግ በላጩ ምርጥ ባል ማለት የአላህ ዲን በሚገባ የሚያውቅና ስነ ምግባሩ ያማረ ነው። ዲኑን የሚያውቅ ካገባሽ ከወደደሽ በእጅጉ ያከብርሻል፤ የማይወድሽ ከሆነ አያዋርድሽም ክብርሽን በሚገባ ይጠብቅልሻል። ስለዚህ ዲን ያለው የስነ ምግባር ባለቤት ምርጫሽ ሊሆን ይገባል። በዲናቸው እኩል የሆኑ ሰዎች ለትዳር እጅሽን ከጠየቁ ቤተሰቦቹ መልካም የሆኑትን ምረጪ ምክኒያቱም የእሱ ቤተሰቦች ወደ አንቺ የቀረቡ ናቸውና። ﻟﻘﻮﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﻣﺤﻤﺪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ : (ﺧﻴﺮ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ ﻣﻦ ﺇﺫﺍ ﻧﻈﺮﺕ ﺇﻟﻴﻬﺎ ﺳﺮﺗﻚ، ﻭﺇﺫﺍ ﺃﻣﺮﺗﻬﺎ ﺃﻃﺎﻋﺘﻚ، ﻭﺇﺫﺍ ﺃﻗﺴﻤﺖ ﻋﻠﻴﻬﺎ ﺃﺑﺮﺗﻚ، ﻭﺇﺫﺍ ﻏﺒﺖ ﻋﻨﻬﺎ ﺣﻔﻈﺘﻚ ﻓﻲ ﻧﻔﺴﻬﺎ ﻭﻣﺎﻟﻚ ) }ﺃﺧﺮﺝ ﺍﻟﻨﺴﺎﺋﻲ . የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም “ከሴቶች ሁሉ በላጯ የትኛዋ ናት?” ተብለው ተጠይቀው “ሲያያት የምታስደስት፣ ሲያዛት የምትታዘዝ፣ በነፍሷም በገንዘቡም እርሱ የማይፈልገውን የማትፈጽም” ሲሉ መለሱ። # ትዳር ማለት ሃላፊነት ነው፣ መስዋዕትነት ይጠይቃል! መለያየት የሌለበት ሰላም የሰፈነበት የነፃነት አለም ነው። ትዳር ልክ እንድ ሁለት እጅ ነው። አንድ እጅ ብቻውን አያጨበጭብም ስለዚህ የጭብጨባው ድምፅ ፈፅሞ ወደ ልብ አይደርስም፣ ሁለቱም በጋራ ከተደጋገፉ ግን ፈፅሞ ሊጠፋ የማይችል የደስታ ድምፅ በልባቸው ይገባል፣ በደምስራቸው ይዞራል። ነገ ለሚፈጠረው ጀግና ትውልድ ዛሬ ላይ የሁለታቹ ትልቅ ተፅኖ እጅግ አስፈላጊ ነው ትዳር የጭቅጭቅ መፍትሄ፣ ከጭንቀት ማረፊያ የአይምሮ ሰላም አንድ አዕምሮ ከሚሰራ ሁለት አዕምሮ በጋራ ቢሰራ የሚደመር እንጂ የሚቀነስ ነገር የለውምና 📌ትዳር ማለት ችግርን ወይም ተግዳሮትን ለሁለት የሚያካፍል ፣ ደስታ እና ስኬትን ደግሞ በሁለት የሚያበዛ የልብ ወዳጅ ማግኘት ማለት ነው ትዳር / መጣመር አላህ ከዋለልን ፀጋ አንዱ ነው ስለዚህ ውዶቼ ትዳር እጅግ ከሚያስፈልገን ከዱንያ ነገሮች አንዱ በመሆኑ በፍጥነት ለትዳር እጅ ልትሰጡ ይገባል። 💍ትዳር (ኒካህ) እጅግ ቀለል ያለ እራስን ከዝሙት የመጠበቂያ መንገድ ነው። መመስረት እጅግ ቀላል ነው፣ ዘላቂ ለማድረግ ግን ከፍተኛ ትግል ያስፈልጋል. ስለዚህ ትዳራችን ስኬታማ እንዲሆን አቂዳውን ፣ ዲኑ መስፈርታችን መሆን አለበት 💍:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::💍
Mostrar todo...
ጣፋጭ የአላህ ጥሪ ..... ۞ وَسَارِعُوٓا۟ إِلَىٰ مَغْفِرَةٍۢ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ ۞ ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡ ۞ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ فِى ٱلسَّرَّآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَٱلْكَٰظِمِينَ ٱلْغَيْظَ وَٱلْعَافِينَ عَنِ ٱلنَّاسِ ۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ ۞ ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት ( ተደግሳለች ) ፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል ፡፡ ۞ وَٱلَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا۟ فَٰحِشَةً أَوْ ظَلَمُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا۟ ٱللَّهَ فَٱسْتَغْفَرُوا۟ لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ ٱلذُّنُوبَ إِلَّا ٱللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلُوا۟ وَهُمْ يَعْلَمُونَ ۞ ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለ፡፡ (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት (ተደግሳለች) ፡፡ ۞ أُو۟لَٰٓئِكَ جَزَآؤُهُم مَّغْفِرَةٌۭ مِّن رَّبِّهِمْ وَجَنَّٰتٌۭ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا ۚ وَنِعْمَ أَجْرُ ٱلْعَٰمِلِينَ ۞ እነዚያ ምንዳቸው ከጌታቸው ምሕረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም ናቸው፡፡ የሠሪዎችም ምንዳ (ገነት) ምንኛ አማረች! ፡፡ سورة آل عمران ( 133 - 136 ) 🍂_____________________🍂 🌹. 🌻.
Mostrar todo...
💜💜✨ ጂብሪል ዐ ሰ አንድ ቀን ያለወትሮው ረሱል ሰዐወ ዘንድ ፊቱ ጠቁሮ መጣ። ረሱል ሰ ዐ ወ በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ግዜ፦"አንተ ጅብሪል ምነው ፊትህ እኮ ተቀይሯል?"አሉት። ጅብሪልም፦"አንተ ሙሀመድ አሁን የመጣሁት እሣት የጀሀነም አቀጣጣዮችን አላህ እንዲያቀጣጥሏት ባዘዛቸው ሰዐት ነው። ጀሀነም እውነት መሆኗን ላወቀ፣እሳትም እውነት መሆኗን ላወቀ፣የቀብር ቅጣት እውነት መሆኑን ላወቀ፣የአላህ ቅጣት ትልቅ መሆኑን ላመነ ሰው ከሷ መትረፉን ሳያረጋግጥ መረጋጋት የለበትም" ብሎ መለሰላቸው። ረሱል ሰ ዐ ወ፦"አንተ ጅብሪል እስቲ ስለጀሀነም ንገረኝ" አሉት። ጅብሪልም ዐ ሰ፦"አዎ አላህ ጀሀነምን 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት🔥 ቀይ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት🔥 ነጭ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት🔥 ጥቁር እስክትሆን ድረስ.....አሁን/ጀሀነም ጥቁር ጨለማማ ናት።ነበልባሏ እና ፍሟ አይጠፋም ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ.የመርፌ ቀዳዳ ያህል ጀሀነም ብትከፈት ዱንያ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር። ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ.ከጀሀነምሰዎች ልብስ አንዷ በሰማይና በምድር መሀከል ብትንጠለጠል ከግማቱ የተነሳ ምድር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ ይሞት ነበር። ያ በዕውነት ነቢይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ...አላህቁርአን ላይ የጠቀሰው የጀሀነም ሰንሰለት አንዷ እንኳን በተራራ ላይ ብትቀመጥ ተራራው እስከ ሰባተኛው መሬት ድረስ ይቀልጣል። ያ በዕውነት በላከህ አላህ እምላለሁ.በምዕራብ አንድ ሰውዬ በጀሀነም ቢቀጣ ኖሮ በምስራቅ ያለው ሰው ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር። ሙቀቷ ጠንካራ ነው፣ጥልቀቷ እሩቅ/ስምጥ ነው፣ጌጧ ብረት ነው፣መጠጧም የፈላ ውሀ እና ምግል ሲሆን፣ልብሷም ከእሳት የተለካ ነው። 7 በሮች አሏት። ለያንዳንዱ በር የተለያዩ በሮችም አሏቸው ለሴቶችም ለወንዶችም" ብሎ መለሰላቸው። ረሱልም ሰዐወ፦"እኛ እንደምንጠቀመው አይነት በር ነው?"ብለው ሲጠይቁት ጅብሪልም ዐ ሰ፦" አይ አይደለም ከላይ ወደ ታች የተደረደረ በር ነው።ከአንደኛው በር ወደ ሌላኛው በር ያለው ርቀት 70 አመት ያስኬዳል። እያንዳንዱ በር ከሌላኛው በር ግለቱ በ70 እጥፍ ይበልጣል። የአላህ ጠላቶች ወደጀሀነም ይነዳሉ። ልክ በሯ ላይ እንደደረሱ ዘባኒያ የተባሉ የጀሀነም ወታደሮች በሰንሰለት ይቀበሏቸዋል። ሰንሰለቱን በአፋቸው አስገብተው በመቀመጫዎቻቸው ያስወጡታል። ግራ እጁ ከአንገቱ ጋር ይጠፈራል ቀኝ እጁም ከልቡ ጋር ተጠፍሮ ይታሰራል። እያንዳንዱ ሰው ከሸይጧን ቁራኛው ጋር በሰንሰለት ይጠፈራል። ከዚያም በፊቶቻቸው እየተጎተቱ መላዕክት ደግሞ ከብረት በሆነ መዶሻ ይመቷቸዋል። ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ሲሞክሩ ወደዛው ይመልሷቸዋል"ብሎ መለሰላቸው። ነቢያችንም ሰ ዐ ወ፦"በነዚህ በሮች የሚገቡት እነማን ናቸው?"ብለው ጠየቁት። ጅብሪልም ዐ ሰ፦ "በታችኛው በር የሚገቡት ➺1፦ሙናፊቆች ➺2፦በዒሳ ዐሰ ማዕድ የካዱት ➺3፦"የፊርዐውን ቤተሰቦች...ሲሆኑየበሩ ስም ሀዊያ ይባለል። ሁለተኛው በር ስሙ ጀሂም ሲሆን በሱ የሚገቡት ሙሽሪኮች ናቸው። ሶስተኛው በር ሳብያኖች ነው የሚገቡበት ስሙም ሰቀር ይባላል። በአራተኛው በር ኢብሊስ እና ተከታዮቹ መጁሶችም ይገቡበታል ስሙም ለዟ ይባላል። አምስተኛው በር የሁዶች የሚገቡበት ሲሆን ስሙም ሁጠማ ይባላል። ስድስተኛው በር ስሙ ዐዚዝ ሲሆን የሚገቡበት ክርስቲያኖች ናቸው።"ብሎ ከዘረዘረላቸው በኋላ ሰባተኛውን ለመጥቀስ ፍርሀት ያዘው። ነቢያችንም ሰ ዐ ወ፦"ሰባተኛውን በር ለምን አትነግረኝም?"ብለው ሲጠይቁት ጂብሪልም ዐ ሰ፦"በሱ በር የሚገቡት ካንተ ዑመት የሆኑ ትላልቅ ወንጀሎችን ሰርተው ሳይቶብቱ/ሳይፀፀቱ የሞቱ ናቸው" ብሎ ሲመልስላቸው ረሱል ሰ ዐ ወ እራሳቸውን ስተው ወደቁ። ከዚያም ጅብሪልም የረሱልን ሰ ዐ ወ ጭንቅላት ታፋው ላይ አሳረፈ።ልክ ሲነቁ ቀና አሉና፦"አንተ ጅብሪል ችግሬ በዛ ሀዘኔም በረታብኝ ከኔ ኡመት ጀሀነም ሚገባ አለ እንዴ?"ብለው ሲጠይቁት ጅብሪልም ዐ ሰ፦" አዎን ካንተ ኡመት የትላልቅ ወንጀል ባለቤቶች ይገባሉ"ብሎ መለሰላቸው፣ የዐይናችን ማረፊያ ከእናት ከአባት በላይ ለኛ አዛኝ የሆኑትም ነቢይ ይሄን ሲሰሙ ተንሰቅስቀው ማልቀስ ጀመሩ።ጅብሪልም አብሯቸው አለቀሰ። /ፊዳከ አቢ ውኡሚ ያ ረሱለላህ/ ረሱል ሰ.ዐ.ወይህኔ፦"ያጅብሪል አንተም ታለቅሳለክ?"አሉት ። ጅብሪልም፦"እንዴት አላለቅስ የኔንስ መጨረሻ በምን አውቃለሁ? እብሊስእኮ ከመላእክት በላይ አላህን ይገዛ ነበር አላቸው ። ______________________________ አላህ ይሄን መልዕክት የፃፈውንም ያነበበውንም አንብቦ ለሌላው ያስተላለፈውንም ከዚህ አስፈሪ ቅጣት ይጠብቀውን
Mostrar todo...
  • File unavailable
  • File unavailable
ኮምቦልቻን እንደ አጣዬ⁉️ ================== ✍ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ ውስጥ በህገ ወጥ አደረጃጀት ተደራጅተው ኮምቦልቻን እንደ አጣዬ ለማውደም የመንግስትን የጸጥታ መዋቀር ተጠቅመው ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ ህቡዕ ቡድኖች፤ በህዝብ ትብብር እልህ አስጨራሽ በሆነ ትግል ከመቶ ባላይ አሸባሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የመንግስትን መዋቅር ተጠቅሞ ይህ በህቡዕ የተደራጀ የሽብር ቡድን የሰው ደም ሳያፈስ እና ንብረት ሳያወድም በቁጥጥር ስር መዋሉ ይበል የሚባል እና ለወደፊት ተግቶ እንድሰራ ለደቡብ ወሎ አስተዳደር የማንቂያ ደውል ነው። ቀጣይ ደሴ እና በሌሎች አካባቢ ረብሻ በመፍጠር ንብረት በማውደም እና ሰው በመግደል ምርጫውን ለማደናቀፍ እና ሃገሪቱ እንዳትረጋጋ በማድረግ በመንግስት ላይ ጫና በማሳረፍ በመፈንቅለ መንግስት ሃገረ መንግስቱን ለመቆጣጠር የተለያየ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን ነው የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ። ማህበረሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ከመቼውም ጊዜ በላይ ራሱንና አካባቢውን በንቃት ሊጠብቅ ይገባል። የሚመለከተው የመንግስት አካልም እንዲህ አይነት ሴራዎችን በንቃት እየተከታተለ ተፈጻሚ ከመደረጋቸው በፊት ቀድሞ ማክሸፍ ይጠበቅበታል። በዚህ በተያዙት ቡድኖች ላይ ደግሞ ለሌሎች መቀጣጫ የሚሆን ተገቢ የሆነ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል። በቀላል ነገር ነካክቶ መልቀቅ ለሌላ ህቡዕ ቡድን የልብ ልብ የሚሰጥ ነው። «ሳይቃጠል በቅጠል‼»
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.