cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ

“ነገር ግን #ወንጌልን አደራ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር የታመንን ሆነን እንዳገኘን መጠን፥ እንዲሁ እንናገራለን፥ ልባችንን የሚመረምር እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ደስ እንደምናሰኝ አይደለም።”1ኛ ተሰሎንቄ 2፥4 1. መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ መልኩ መረዳት 2. መንፈሳዊ መጽሐፎችን በsoft copy ለመንፈሳዊ እድገታችሁ የሚጠቅሙትን ማቅረብ። For comments:- @Christlove_bot

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
523
Suscriptores
Sin datos24 horas
+47 días
+1430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በሞባይ ለአጠቃወም ምቹ የሆመ መጽሐፍ #Just_Uploaded #Praise_God! ❤🥰🥰🙏 Preconditions - #Device: Android (IOS ተጠቃሚዎችን ይቅርታ ለማለት 'ወዳለሁ 🙏፤ ወደፊት ከብዙ ማሻሻያ ጋር ብቅ እላለሁ ☺️) - #Version: >4.4 <መሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮ> Version 1.0 አዘጋጅ፡ ፋንታሁን በየነ ወርሐ 25/09/2012 ዓ.ም   #ለወዳጅ_ዘመዶ' ያጋሩ! Please!! 🙏🙏 #አመሰግናለሁ! #መልካም_ንባብ!
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የአምልኮ ታላቅነቱ ከውስጥ ከውስጥ የመነጨ ለአምላክ ብቻ የሚገባ የፍቅር፣ የአክብሮትና የምስጋና መግለጫ መሆኑ ነው። በሌላ በምንም መንገድ መግለጽ የማይቻል የጠለቀ ውዳሴ በአምልኮ ይገለጻል። እግዚአብሔርን ባወቅነው መጠን አምልኮአችን ከውጫዊ ሥርዓት አልፎ በሁለንተናችን ለእርሱነቱ የምናቀርበው የተቀደሰ መሥዋዕታችን ይሆናል። የልባችን ዓይኖች በጸጋው ተከፍተው እግዚአብሔርን እንደ እግዚአብሔርነቱ ማለትም:- ♦ በፈጣሪነቱ ♦ በሁሉን ቻይነቱ ♦ በመሐሪነቱና በፍቅሩ መጠን ወዘተ. መረዳት ስንጀምር ከውስጣችን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በአምልኮ ብቻ የሚገለጽ የውዳሴ፣ የቅኔና የምስጋና ምንጭ መፍለቅ ይጀምራል። ይህ በጌታ ጸጋና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚወጣ አምልኮ የእግዚአብሔርን ልብ ደስ ከማሰኘቱም በላይ ለአምላኪው የልብን ደስታና የሕይወትን እርካታ ያበዛለታል። የመንፈስንና የስሜትን ፈውስ ያመጣል። እግዚአብሔርን የማወቅ፣ የማክበር፣ የመፍራት፣ የመውደድንና ለእርሱ ክብርና ምስጋና ብቻ የመኖርን ናፍቆትና ፍላጎትን ያሳድጋል። https://t.me/spiritualbookss 👈 ይህን ሊንክ ተጭነው በመግባት ሙሉ መጽፍፉን ማውረድ እዲሁም ሌሎች መንፈሳዊ መጽፈረት እንድታነቡት በጌታ ፍቅር አሳስባችኋለሁ🙏 ለጓደኞችዎ Share ያድርጉ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት 7. የአዲስ ኪዳን ስሞች ሀ. ክርስቶስ የተቀባ መሢህ ንጉሥ (ሐዋ 2:36 ፣ሮሜ 6፡ 23 ፣ቲቶ 2፡13) ለ. ጌታ ጌታ የተከበረ (ሉቃ 1፡46 ሐዋ 2፡36 ይሁዳ 4) ሐ. ቲዎስ ይህ ኤሎሂም ከሚለው ከዕብሪ ይስጡ - ስም ጋር ይመሳሰላል በአዲስ ኪዳን ለጌታ መጠሪያ ሲውል ዕውነተኛ አምላክ የሚል ትርጉም ይይዛል (ሉቃ 14 ዮሐ 20:28 ቲቶ 2፡13) መ. አባት ይህ ስም በብሉይ ኪዳንም የነበረ ሲሆን በይበልጥ ግን እግዚአብሔር በዚህ ስም የተጠራው በአዲስ ኪዳን ነው ስሙ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት አስገኝነት ያመለክታል (ዮሐ 4:23 ሮሜ 8 15፣ ኤር 314 ! 1ኛ ቆሮ 8፡6 ዕብ 12:9 ያዕ 1፡17) እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን የእሥራ ኤል አባት እንደሆነ ሁሉ በአዲስ ኪዳንም የአማኞች አባት ነው፡፡ ይህ ስም በብሉይ ኪዳን 15 ጊዜ በአዲስ ኪዳን 24 ጊዜ ተገልጿል። የወዳጆ፣ በተለያዩ group Share በማድረግ መሰረታዊ የክርስትና አስተምሮ አውቀው እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ የበኩሎን ይወጡ🙏 ተባረኩ ወንድሞቼና እህቶቼ አገልጋይ ወንድማገኝ 👉https://t.me/spiritualbookss 👉https://www.facebook.com/profile.php?id=100064178855381
Mostrar todo...
💯Amaizing spiritual Book💯          Author: Yared Tilahun (Evangelist)✔️ ርዕስ፦ #እግዚአብሔርን_መምሰል «እግዚአብሔርን መምሰል» የሚለው ርዕስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠንካራ ጽሑፎች አንዱ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለምን እንደምክንያት ከሚጠቀሱት አንዱ የቋንቋ ጉዳይ ነው።      ምንም እንኳን የርዕሱ ጽንሰ ሃሳብ በብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ በስፋት የሰረፀ ቢሆንም በዋነኝነት የተወሳው በአዲስ ኪዳን ውስጥ ነው፡፡ የአዲስ ኪዳን ጸሐፍት ይህን መንፈሳዊ ሃሳብ ለመገለጽ አዲስ ኪዳንን ከጻፉበት የግሪክ ቋንቋ ‹‹ዮሰቢያ» የሚለውን የግሪክ ቃል ተጠቅመዋል፡፡
Mostrar todo...
ትምህርት 6. 2ኛው የእግዚአብሔር መጠሪያ ስም "ያህዌ"      ያህዌ ማለት ነፃ፣ ራሱ በራሱ የሚኖር ፣ እንዲኖር ሌላ ኃይል ወይም ምክንያት የማያስፈልገው ዘለዓለማዊ አምላክ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱን የገለጸው «ያለና የሚኖር» ብሎ ነው (ዘዳ 3፡14) እሥራኤላውያን ያህዌ የሚለው ስም የማንነቱን ከፍታ መግለጫ የከበረ ስለሆነ አለቦታው አይጠራም ብለው ስለሚያስቡ በምትኩ «አዶናይ» በሚለው ስሙ ይጠሩታል፡፡     ከተፈጸሙ ድርጊቶች ጋር በመያያዝ ያህዌ በሚለው ስም ተያይዘው የእግዚአብሔር ስም መግለጫ የሆኑ ስሞች የሚከተሉት ናቸው:- 👉ሀ. ያህዌ- ይርኤ- እግዚአብሔር ያዘጋጃል (ዘፍ 22:8 -14) 👉ለ. ያህዌ- ንሲ- እግዚአብሔር ዓላማዬ (አርማዬ) (ዘጸ 17:15) 👉ሐ. ያህዌ ሻሎም- እግዚአብሔር ሰላሜ (መሳ 6፡ 24) 👉መ. ያህዌ- ጸባዖት- እግዚብሔር የሠራዊት ጌታ (1 ሳሙ 17: 45 : መዝ 24፡ 10) 👉ሠ. ያህዌ- ማካዶሽ- የሚቀድስ እግዚአብሔር (ዘጸ 31፡ 13) 👉ረ. ያህዌ- ሮይ- እግዚአብሔር እረኛዬ ነው (መዝ 23፡ 1) 👉ሰ. ያህዌ ጽድቅኑ- እግዚአብሔር ጽድቃችን (ኤር 23፡ 6፣ 33፡16) 👉ሽ. ያህዌ ኤልጌሞላህ- እግዚአብሔር የሚክስ አምላክ (መካሻዬ) (ኤር 51፡56) 👉ቀ. ያህዌ ናካህ- እግዚአብሔር ተበቃይ (ሕዝ 7:9) 👉በ. ያህዌ-ሻማህ- እግዚአብሔር በዚያ አለ (ሕዝ 48:35) 👉ተ. ያህዌ ራፋ- እግዚአብሔር ፈዋሻችን ዘጸ 15:26) 👉ቸ. ያህዌ ኤሎሂም- እግዚአብሔር ሃያል (መሳ 5:3፣ኢሳ 17 ፡6) ንጉሥነቱን ፣ ፍፁምነቱን የሚገልጽ (ዘጸ 5:9) 3ኛው. አዶናይ       አዶናይ የሁሉ ጌታና ባለቤት በሁሉ ላይ የሚገዛ ማለት ነው (ዘፍ 19:2፣ 40:1፣ 1ሳሙ 1፡15፣ኢሳ፣5፡14፣ኢሳ 6:8-11):: የእግ/ርንም የሚገልጽ ስም ነው (ዘፀ 4፡10-12 ፣ኢያ 7:8-11)፡፡ ተባረኩ አገልጋይ ወንድማገኝ 👉https://t.me/spiritualbookss 👉https://www.facebook.com/profile.php?id=100064178855381
Mostrar todo...
📚Spiritual Books📚(መንፈሳዊ መጻሕፍት)

Provided for all #More than #1000 spiritual books I recommend you to read. Share your friends. Get yourself fit by #downloading small, KB and mb soft copy spiritual books.

Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት 5. የእግዚአብሔር ስሞች       የእግ/ር ስሞች የማንነቱ መግለጫ ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ በተፃፈበት በዕብራይስጥ ቋንቋና በግሪክ የእግ/ርን ስም ፍቺ መረዳት ስለ እግ/ር ያለንን ዕውቀት ይጨምራል። የእግ/ርን ስም መጥራት እርሱን ማምለክ ነው (ዘፍ 21፡33)። ጌታ ባስተማረው ፀሎት «ስምህ ይቀደስ» በሉ ብሏል (ማቴ 6፡9)፡፡ 5.1. የብሉይ ኪዳን ስሞች      በብሉይ ኪዳን እግ/ር በዋናነት የሚጠራባቸው ስሞች ኤል (ኤሎሂም)፣ያህዌ እና አዶናይ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን እነዚህን ስሞች እና ከእነዚህ ስሞች ጋር በተያያዥነት የሚጠሩትን በዝርዝር እናያቸዋለን:- 1ኛው. ኤል (ኤሎሂም)       "ኤል ኤሎሂም ማለት ታላቅ ኃያል አምላክ ማለት ነው፡፡ ይህ የእግ/ር ስም ሁሉን ገዥነቱን (ኢሳ 54:5 : ኤር 32፡ 27 ነህ 2፡4፣ ዘዳ 10፡17)፡፡ የመፍጠር ሥራውን (ዘፍ 1፡1 ፣ኢሳ 45፡18 ' ዮና 1፡9) ፈራጅነቱን (መዝ 50፡6 መዝ 58፡11)፡፡ ይገልፃል፡፡ «ኤሎሂም»ወይም «ኤል» ከተሰኘው ስም ጋር በመያያዝ እግ/ር የሚጠራባቸው ሌሎች ስሞች የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ስሞች ከአንዳንድ ሁኔታዎችና ከተፈጸሙ ድርጊቶች ጋር በተያያዘ መንገድ የተጠራባቸው ስሞች ናቸው፡፡ 👉ሀ. ኤል-ሻዳይ - ሁሉን ቻይ እግ/ር (ዘፍ 17፡1)፡፡ 👉ለ. ኤል-ኤልዮን ብርቱና ሃያል አምላክ የሁሉ ገዥ ማለት ነው (ዘፍ 14፡18)፡፡ ልዑል እግ/ር (ዘኁ 24፡16)፡፡ 👉ሐ. ኤል-ሮኢ- እግ/ር ያያል በዘፍ 16፡13) 👉መ. ኤል-አለም- እግ/ር የዘላለም አምላክ (ዘፍ 21፡33 ኢሳ 40፡28) 👉ሠ. ኤል- ኤሎሄ እሥራኤል- የእሥራኤል አምላክ እግ/ር. 2ኛው... ያህዌ በቀጣይ ቀን እንመለከተዋለን ተባረኩ አገልጋይ ወንድማገኝ 👉https://t.me/spiritualbookss
Mostrar todo...
ትምህርት 4. የሚወራረሱ (የሚሸጋገሩ) ባሕርያት        የሚወራረሱ (የሚሸጋገሩ) ባህርያት ሰውና መላዕክት ከእግ/ር በተወሰነ መጠን የሚካፈሏቸው ናቸው፡፡ ሰውም በእግ/ር አምሳል ነው የተፈጠረው ሲባል፣ እግ/ር በግዙፍ አካል የተገለጠ ሥጋና አጥንት አለው ማለታችን ሳይሆን በቅድስና፣ በዕውቀትና፤ በገዥነት ባሕርይው ከእግ/ር የወረሰው ወይም የተሰጠው ለሌሎች ፍጡራን ያልተሰጠ ባህርይ አለው ማለታችን ነው፡፡      ሀ. የማወቅ ባሕርያት (ዕውቀትና ጥበብ) እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ምንም ሳይቀር ያውቃል ዕውቀቱ ከዘላለማዊ ማንነቱ ነው፡፡ (ሐዋ 15፡18፤ ዳን 2:22፣ ኢሳ 29:15 1ዮሐ 3:20፣ ዮሐ 2፣24)፡፡ የማንኛውም ዕውቀት ምንጭ እግ/ር ነው፣ የጥበብም ሁሉ መዝገብ እርሱ ጥበበኛ አምላክ ነው፡ ተፈጥሮን በየዓይነቱ መፍጠሩ (መዝ 104:24፣1ቆሮ 15፡41)፡፡ ለ. የሞራል ባሕርያት (ፍትህ ፣ ፅድቅ ' ቸርነት ፣ ፍቅር ፣ ቅድስና)        እግዚአብሔር ፍትሃዊ ነው በፍርዱ ፃድቅ ስለሆነ የሰውን ፊት አይቶ አያደላም፣ የአርሱ ፍትህ በሁኔታዎች አይዛባም፣ ጽድቅ ማለት ትክክል ፣ ያልተዛነፈ፣ ስህተት የሌለበት ሃሳብ ወይም ተግባር ማለት ነው እርሱ ለኃጢአት ተገቢውን ዋጋ ቅጣት በመስጠቱ ፃድቅ ነው፡፡ (ሐዋ 10፡34-35 ፣ሮሜ 2፡11፣ዳን 9፡7፣ ኤር 9:24፣ ዘፍ 18፡25)። እግዚአብሔር መልካም ነው ቸርነቱንም በብዙ መንገዶች ገልጿል (ያዕ 1፡17 ፣መዝ 145፡ 15-16፣ ማቴ 5፡45)፡፡ ሐ. የገዥነት ባሕርያት         እግዚአብሔር ሁሉን ገዥነቱን የገለፀው፣ በመፍጠር ተግባሩ 33:49 ኢሳ 40፡ 12-17) በተፈጥሮ ሥርዓት ላይ (መዝ 107፡ 25- 29)፡፡ በሰው ልጆች ላይ (ዘፀ 5:2 ፣ዳን 4:30-37)፡፡ በመላዕክት ላይ (ዕብ1፡6):: በወደቁ መላዕክት ላይ (2 ጴጥ 2:4) ሁሉ ነው፡፡        በመጨረሻም የእግዚአብሔር ባሕርያት ከሰው መረዳት በላይ ነው፡፡ በመሆኑም የማይወረሱ ባህርያት የእግዚአብሔር የግሉ የመለኮትነት መግለጫ ባህርያት እንጂ የትኛውም ፍጡር ሰውንም ጨምሮ ሊለማመዳቸው ወይም ሊወርሳቸው አይችልም፡፡ በአንፃሩ ግን የሚወረሱ ባህርያትን በክርስቶስ የዳኑ ሰዎች ሁሉ በዕለት ኑሮአቸውና አገልግሎታቸው ሊተገብሩት የተገባ ነው (2 ጴጥ 1፡4 ዮሐ 14፡12)፡፡ ተባረኩ አገልጋይ ወንድማገኝ 👉https://t.me/spiritualbookss 👉https://www.facebook.com/profile.php?id=100064178855381
Mostrar todo...
📚Spiritual Books📚(መንፈሳዊ መጻሕፍት)

Provided for all #More than #1000 spiritual books I recommend you to read. Share your friends. Get yourself fit by #downloading small, KB and mb soft copy spiritual books.

Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት 3. የእግዚአብሔር ባሕርይ       የእግዚአብሔርን ባህርያት በሁለት ከፍሎ ማየት ሲቻል እነርሱም የማይወራረሱ /የማይሸጋገሩ እና የሚወራረሱ የሚሸጋ ናቸው፡፡ 1ኛ. የማይወራረሱ (የማይሸጋገሩ) ባሕርያት:- ስንል ከእግዚአብሔር ወደ የእግዚአብሔር ብቻ የሆኑ ናቸው። እነርሱም ሀ. እራስ በራስ መኖር (Self existence)      እግዚአብሔር ራሱን በራሱ ችሎ የሚኖር ነፃ የሆነ ገዥና ሉዓላዊ ነው። ለመኖርም የማንንም እርዳታ አይፈልግም (መዝ 33፡11፣ ኤፌ 1:21፤ ዳን 4:35፣ ሮሜ 11፡33-34)፡፡ ለ. አለመለወጥ (Immutability)       እግዚአብሔር በእርሱነቱ፣ በሕልውናው፣ በተስፋው፣ በዕቅዱ፣ እና በባህርይው በጊዜና በዘመን የማይለወጥ ሃሳቡንም የማይለውጥ ነው (መዝ 102፣24-28)፡፡ እግዚአብሔር አይለወጥምና (ዘኁ 23፡19)፡፡ "እግዚአብሔር በራሱ ላይ አንዳች ነገር አይጨምርም፣ አይሻሻልም፣ አይማርም አይመራመርም (ሚል 3፡6፣ ያዕ 1፡17)፡፡ ሐ.  አለመወሰን (Infinity)        እግዚአብሔር የመጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘላለማዊ አምላክ በመሆኑና በአንድ ጊዜ በሁሉም ሥፍራ የሚገኝ፣ ስለሆነ ወሰን የለውም፣ እግዚአብሔር የጊዜና የቦታ ወሰን ስለማይዘው ከገደብ ውጪ ነው (1ነገ 8:27፤ ኢሳ 66:1፣ መዝ 145፡31 1ጢሞ 6፡10)፡፡ መ. ሁሉን ቻይነት (Omnipotent)        እግዚአብሔር ሁሉን ለማድረግ ሙሉ ኃይልና ችሎታ የሚሳነውና የሚያቅተው ነገር የሌለ አምላክ ነው (ዘፍ 17፡2)፡፡ 2ኛወ. ነገ ማለዳ አብረን በዝርዝር እናየዋለን loading... ተባረኩ አገልጋይ ወንድማገኝ 👉https://t.me/spiritualbookss 👉https://www.facebook.com/profile.php?id=100064178855381
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት 1. እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔር መኖር (ሕልውና)፡- እግዚአብሔር ቃሉ ከግእዝ የተገኘ ነው። እግዚእ ጌታ፣ ብሔር ደግሞ ዓለም ሲሆን፥ እግዚአብሔር ማለት የዓለም ጌታ ማለት ነው። እግዚአብሔር ግዑዝ የሆነ ኃይል ወይም የማይጨበጥ ምናባዊ እሳቤ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሰዎች ህልውናውን ወይም መኖሩን ፈልገው ሊያገኙት የሚችሉትና ራሱንም ለገለጠላቸው ህብረት ሊያደርግ የሚችል ህያው አምላክ ነው (ዮሐ 17፡3)፡፡ የእግዚአብሔር መኖር በምን ይታወቃል:- 1ኛ. በዕምነት ይታወቃል (ዕብ 11፡1፣3፣6፣ መክ 3:11) በእምነት ካልሆነ በስተቀር ራሱን እግ/ርንም ሆነ የሠራውን ሥራ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ማወቅ አይቻልም። 2ኛ. ራሱን በመግለጡ ይታወቃል እግ/ር ራሱን የገለጠባቸው ሁለት ዋና መንገዶች "አጠቃላይ መገለጥና" "ልዩ መገለጥ" ናቸው፡፡ i. አጠቃላይ መገለጥ እግ/ር ራሱን ለሰው ልጆች ሁሉ በሁሉም ጊዜና ሥፍራ ያሳወቀበት መንገድ ነው፡፡ ይህም መገለጥ ወደ ሰው የመጣው በቃል በንግግር ሳይሆን በተፈጥሮ(ሮሜ1፡20፣መዝ 19፡1-4) በሰው የውስጥ ህሊና(2 ቆሮ 5:11፣ሮሜ 9:1-4) እና በታሪክ (ጸዘ 9፡13-18|ኢሳ 10:12-19) አማካኝነት ነው፡፡ ii. ልዩ መገለጥ እግ/ር በልዩ መገለጥ ራሱን የገለጠው በሥጋ በመጣው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ(ዕብ 1፡2፣ ዮሐ 1፡14-18፣ዮሐ 14፡9) እና በእግ/ር ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ(ዮሐ 20፤30-35፣ዘዳ 29:29፣ሉቃ24፡44፣ዮሐ1፡18) በኩል ነው፡፡ ተባረኩ አገልጋይ ወንድማገኝ 👉https://t.me/spiritualbookss 👉https://www.facebook.com/profile.php?id=100064178855381
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ትምህተ መግቢያ: ክርስቲያናዊ አስተምህሮ    አስተምህሮ ሲባል ሰፊና ብዙ ተጓዳኝ ነገሮችን ሊጠቀልል እንደሚችል ይታመናል። ስለሆነም ስርዓተ ትምህርትን፣ መመሪያን፣ የሃይማኖት ስርዓትንና አስተዳዳራዊ ጉዳዮችን ሁሉ አጠቃሎ የሚይዝ ነው። ክርስቲያናዊ አስተምህሮ አስመልክቶ ለምንናገረው ነገር ሁሉ መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡   የእግዚአብሔር ቃል ያመንነውን እንድናውቅና ባመንበትም ጌታ በምንም ነር ሳንናወጥ ፀንተን እንድንቆም በብዙ ይመክረናል፡፡ በአንጻሩም የምናምነውን ነገር አጥርተን እንዳናውቅ ብዥታ የሚፈጥሩብንና ከእምነታችንም ወደ ኋላ እንድናፈገፍግ የሚያደርጉን ብዙ ፈተናዎችና መሰናክሎች የምናልፈው ራሳችንን፣ ዓለምን፣ የመኖራችንን ትርጉምና ዓላማ እንዴት እንደምንረዳ በጠቅላላ የተሳሰረው ከእግዚአብሔር ማንነት ጋር መሆኑን ስንረዳ ነው፡፡   በዚህ ቻናል ለተከታታይ ቀናት ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል፣ ስለ ሰውና ኃጢአት፣ ስለ ድነት፣ ስለቤተክርስቲያን፣ ስለመላእክት፣ እንዲሁም የመጨረሻው ዘመንና የጌታ ዳግም ምጻት መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምራቸው ነገሮች ሁሉ መሰረት በማድረግ እንማራለን።      በመጨረሻም የትምህርቱ ዋናው ዓላማ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ዳግመኛ የተወለደ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንደሚያገኝ እና ከእግዚአብሔር ጋር ለዘለዓለም እንደሚኖር ማመን(ዮሐ 1:12) ሲሆን ቤተክርስቲያን ምዕመናኖቿ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እንዲችሉና እምነታቸውን ጥንቅቅ አድርገው እንዲያውቁና በጽናት እንዲናገሩና እንዲኖሩበትም ጭምር ለማስቻል ነው። ዕብ 6:19 አገልጋይ ወንድማገኝ 👉https://t.me/spiritualbookss 👉https://www.facebook.com/profile.php?id=100064178855381
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.