cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

OBOLE TECH™

✳️በዚህ ቻናል ላይ ✳️ ➡️Android apps📲 ➡️Hacking Tools ➡️Tech News ➡️Software ➡️ComputerTutorial ይገኛሉ ➽ ለማንኛዉም #ጥያቄ , #አስተያየት እንዲሁም #ሀሳብ በዚ ያገኙናል 👇👇👇 @Adu21bot

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
193
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ከ #facebook_ላይ_እንዴት_ቪድዮ_ዳውንሎድ_ማድረግ_ይቻላል ፌስቡክ ላይ የምንፈልገው ዓይነት ቪድዮ እናገኝና ቪድዮውን ዳውንሎድ ማድረግ እንቸገራለን። ቀጥሎ ፌስቡክ ላይ ማንኛውም ቪድዮ ወደ ሞባይል ስልካችሁ ወይም ኮምፒዩተራችሁ ላይ ያለምንም ተጨማሪ አፕሊኬሽን እንዴት ዳውንሎድ ማድረግ እንደምትችሉ እናያለን። 1ኛ፦ ፌስቡካችሁን ትከፍቱና ዳውንሎድ ማድረግ የፈለጋችሁትን ቪድዮ ያለበት ፖስት ከላይ በቀኝ በኩል(...) ምልክትን ክሊክ ማድረግ 2ኛ፦ "Copy Link" የሚል ይመጣል እሱን ክሊክ ማድረግ 3ኛ፦ አሁን ከፌስቡክ ትወጡና(log out ሳታደርጉ)chrome ብራውዘርን ወይም ያላችሁን ብራውዘር ክፈቱ 4ኛ፦ ብራውዘሩን ከከፈታችሁ በኋላ አድራሻ መፃፍያው ላይ ከላይ ኮፒ ያደረጋችሁትን Paste አድርጉት። Paste ስታደርጉት የፈለጋችሁት ቪድዮ ይመጣል። 5ኛ፦ብራውዘራችሁ አድራሻ ላይ ያለውን የቪድዮው አድራሻ ማለትም፦https://www.faceboo...የሚለው አድራሻ ላይ https://www የሚለውን እናጠፋና ባጠፋነው ምትክ mbasic በሚል እንተካዋለን። አሁን አድራሻው፦ mbasic.facebook.com/...የሚል ይሆናል ማለት ነው። በዚህ መልኩ ካስተካከላችሁ በኋላ ኢንተር ወይም Go በሉት። 6ኛ፦ ቪድዮ ይከፈታል። ቪድዮ እንደተከፈተ Play በሉት። ቪድዮ መጫወት ይጀምራል 7ኛ፦ ቪድዮ እየተጫወተ በጣታችሁ ቪድዮው ጫን በሉት።ጫን ስትሉት "Download Video" የሚል ሲመጣ እላዩ ላይ ክሊክ አድርጉት። በቃ አሁን ቪድዮው ዳውንሎድ ማድረግ ይጀምራል።ሲጨርስ የፈለጋችሁትን ቪድዮ አገኛችሁ ማለት ነው። #ሼር_ያደረገ ❤👉join💚 👇 htt// t.me/OBOLE_TECH
Mostrar todo...
OBOLE TECH™

✳️በዚህ ቻናል ላይ ✳️ ➡️Android apps📲 ➡️Hacking Tools ➡️Tech News ➡️Software ➡️ComputerTutorial ይገኛሉ ➽ ለማንኛዉም #ጥያቄ , #አስተያየት እንዲሁም #ሀሳብ በዚ ያገኙናል 👇👇👇 @Adu21bot

#አስደናቂ_አፕሊኬሽን_ልጠቁማችሁ ይህ አፕሊኬሽን Look to Speak ይባላል። የሰው ልጅ ወደ ፊት/ነገ/ከደቂቃዎች በሁዋላ/ ምን እንደሚገጥመው መገመት አይችልም፡፡ዛሬ የሚያየው ዓይኑ ነገ ሊጠፋ ይችላል፡፡ዛሬ የሚናገርበት አንደበቱ ነገ ሊዘጋ ይችላል፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮዋዊ አደጋዎች ወይም በተለያዩ በሽታዎች አማካኝነት የተለያዩ የሰውነት አካላቱ ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ አንድ ሳራ የምትባል ሴት አለች፡፡ሳራ በጣም ታዋቂ አርቲስት ናት፡፡ሳራ በሙያዋ ከፍተኛ ልምድና እውቀት ያላት ትልቅ አርቲስት ናት ፡፡ነገር ግን ሳራ speech and motor impairment በሚባል በሽታ የተጠቃች በመሆንዋ ድምፅዋን አውጥታ መናገር አትችልም፡፡ ስለዚህ ሳራ ድምፅ አውጥታ መናገር ባለመቻልዋ ያካበተችውን ሰፊ እውቀትና ልምድ ለትውልድ ማስተላለፍ አለመቻልዋ ያሳሰባቸው የቴክኖሎጂ ሰዎች Look to Speak አፕሊኬሽንን ለመስራት ተነሱ፡፡ ይህ አፕሊኬሽን እንደ ሳራ ያሉ ድምፅ ማውጣት የማይችሉ ሰዎች በዓየይን እንቅስቃሴ ብቻ ከሰዎች ጋር መነጋገር የሚያስችል አፕሊኬሽን ነው፡፡ አፕሊኬሽኑ በ17 ቁዋንቁዎች የተፃፉ የተለያዩ ቃላቶች የያዘ በመሆኑ ከቃላቶቹ መካከል የበሽተኛውን የዓይን እንቅስቃሴ በመከታተልና በመለካት ለማለት የፈለጉትን ቃላት ይመርጥና አፕሊኬሽኑ እራሱ ድመፁን ከፍ አድርጎ ያነባል፡፡ በዚህ ዓይነት ችግር መናገርና መንቀሳቀስ የማይችሉ አካል ጉዳተኞች በዓይናቸው እንቅስቃሴ በአከባቢያቸው ካሉ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር በቀላሉ ሃሳባቸውን እንዲለዋወጡ ያስችላል፤አፕሊኬሽኑ። እንደ ሳራ መናገር የማይችሉ የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ ካላችሁ ይህንን አፕሊኬሽን እንዲጠቁሙ #ሼር በማድረግ ንገሯቸው። አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ለማድረግ ይህንን ሊንክ ተጠቀሙ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.androidexperiments.looktospeak #Credit_dotcom_tv_show Join👇👇 @OBOLE_TECH @OBOLE_TECH
Mostrar todo...
Look to Speak - Apps on Google Play

Use your eyes to select pre-written phrases and have them spoken aloud.

💧አይበለውና ስልካችን📱ውሃ ውስጥ ድንገት ቢገባ ምን ማድረግ አለብን? ማስተካከያ መንገዶችስ? ➤ አንዳንድ ስልኮች ውሃን በቀላሉ እንዳያሰርጉ ተደርገው የተዘጋጁ ቢሆንም፥ ከውሃው በቶሎ ካላወጣናቸው ውሃው ወደ ስልኩ የውስጠኛ ክፍል ድረስ ዘልቆ ሊገባ ይችላል ። ➩ በየትኛውም አጋጣሚ የሞባይል ስልክዎ ውሃ ውስጥ ቢወድቅብዎ ፈጥኖ ከውሃው ውስጥ ማውጣት ፦ ስልኩ በውሃ ውስጥ በቆየ ቁጥር የሚደርስበት ጉዳት እያከፋ ይመጣል። ⚡️ በመቀጠል 👇 1•📲 ስልኩን ፈጥኖ መዝጋት 2•📲 ከስልኩ መለየት የሚችሉ ለምሳሌ ባትሪውን እና ሲም ካርዱን ፈጥኖ ማውጣት። ➤ በሞባይል ስልኩ ውስጥ እርጥበት ስለሚኖር ይህ ካልተወገደ ስልኩ መስራት አይችልምና። 💧 እርጥበቱን ለማጥፋት ፦ 1•📲 በደረቅ እና ነፋስ ሊያገኝ በሚችል ስፍራ ማስቀመጥ፣ 2•📲 ከ100 እስከ 110 ዲግሪ ፋራናይት ሙቀት እንዲያገኝ በሚችል ስፍራ ማስቀመጥ። ➤ ስልኩ የአፕል ምርት ከሆነ ደግሞ፥ ኩባንያው እስከ 115 ዲግሪ ፋራናይት ሙቀት ሰጥቶ እርጥበቱን ማስወገድ ይቻላል። 📲የሞባይል ስልኩ እስከሚደርቅ ድረስ ጥቂት ስአት ማቆየት ይኖርብናል ። 🔅 ስልኩን ሩዝ ውስጥ ማስቀመጥ ሌላኛው አማራጭ ነው። ለዚህም ውሃ ውስጥ የወደቀውን የሞባይል ስልክ በጥሬ ሩዝ ውስጥ በመክተት ማቆየት። ➩ ይህ ደግሞ ሩዝ በተፈጥሮው እርጥበት የመሳብ ባህሪ ስላለው በስልኩ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመምጠጥ እንዲደርቅ ያደርገዋል። 📢: ✅Credit :- @OBOLE_TECH JOIN👉@OBOLE_TECH 📤 ➩ ሀሳብ/አስተያየት :↩️ 📣: @Adu21bot ⚡️Share And Support Us.
Mostrar todo...
✳️ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የህፃናት የአእምሮ እድገት ======================= ▫️ባለንበት ክፍለ ዘመን የተሻለ የመረዳት እና የአስተሳሰብ ችሎታ እንዲኖር ከፍተኛውን አስተዋፅኦ እያደረጉ የሚገኙት የቴክኖሎጂ ውጤቶች መሆናቸውን በተለያዩ መንገዶች መመልከት ይቻላል፡፡ ቴክኖሎጂን መጠቀም የሰው ልጅን የአዕምሮ ተግባራት ውስን እንዲሆን አድርጓል የሚል አመለካከት በብዙዎች ቢኖርም፤ እንደዘርፉ ባለሙያዎች ገለፃ ከቴክኖሎጂ ውጭ መኖር በማይቻልበት በዚህ ዘመን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በአግባቡ እንዲጠቀሙባቸው በማድረግ በልጆች የአዕምሮ እድገት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ማሳደር እንደሚቻል ይገልፃል፡፡ የአስተሳሰብ ወይም የአረዳድ ችሎታ የሰው ልጅ ካለው የእውቀት፣ የግንዛቤ እና የአስተዳደግ ሁኔታ ጋር የሚያያዝ መሆኑን የተለያዩ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ ይህ ደግሞ የሚጀምረው በልጅነት እድሜያችን በአካባቢያችን ከምናየው፣ ከምንሰማው እና ከምንማረው ሁነቶች ነው፡፡ በመሆኑም በልጅነታችን አልፈነው የምንመጣው ልምምድ አሁን ለሚኖረን ማንነት እና ማህበራዊ ግንኙነት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው እሙን ነው፡፡ ▫️ቴክኖሎጂን አግባብነት ባለው መልኩ እና አትራፊ በሚያደርገን መንገድ ከተጠቀምነው ለልጆች ሁለንተናዊ እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ብዙ ማሳያዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ በዘርፉ ባለሙያዎች የተሰሩት አብዛኞቹ ጥናቶች እንዳሳዩትም በቴክኖሎጂ መስፋፋት የተነሳ ህፃናት አዕምሯቸውን ፈጣን እንዲሆን፣ የተሳትፎ መጠናቸው እንዲጨምር እና በጥልቀት ማሰብን እንዲለማመዱ የተክኖሎጂ እገዝ ቀላል እንደማይሆን በብዙ መንገድ ተገልጦ ይገኛል፡፡ ▫️ለምሳሌ ቀደም ባለው ትውልድ ልጆች ጊዜያቸውን በንባብ ሲያሳልፉ የተፃፈውን ብቻ የሚያነቡ እና ተሳታፊ ከማያደርጋቸው ነገሮች ጋር የሚውሉ በመሆናቸው ትኩረታቸው እንዲከፋፈል፣ በአንድ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ እንዲሁም ምናባዊ እንዲሆኑ ያደርጋቸው ነበር፡፡ ▫️በሌላ በኩል ግን በቴሌቭዥን፣ በኢንተርኔት እና በሌሎችም የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚዘጋጁ የተለያዩ ቪዲዮዎች፣ ጌሞች እና መሰል ነገሮች ላይ የሚሳተፉ ልጆች በእያንዳንዱ ተግባራት ተሳታፊ በመሆናቸው የተከፋፈለ ትኩረትን እና ምናብን ከመፍጠር ይልቅ የማስተዋል፣ ችግርፈቺ የመሆን፣ ምክንያታዊ የመሆን፣ በትኩረት የማሰብ፣ የተሻለ የቋንቋ አጠቃቀም የመኖር እንዲሁም ብልህ እና ፈጣን እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡ ይህም በአዕምሮ እድገታቸው ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ይታመናል፡፡ በመሆኑም የተመረጡ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በአግባቡ በመጠቀም የልጆቻችንን የአዕምሮ እድገትን ማፋጠን እና ነገን የተሻለ መድረግ ከወላጆች የሚጠበቅ ትልቅ ሃላፊነት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ምንጭ፡ Psychology ════❁✿❁ ═══════ 🎮▩♦️. @OBOLE_TECH 🎯▩♦️. @OBOLE_TECH 🚀▩♦️. @Adu21bot #ሁሌም_ከኛ_ጋ_ወደ_ፊት 🏃🏃‍♀ ══════❁✿❁════════ 🅣🅔🅒🅝🅞🅛🅞🅖🅨
Mostrar todo...
ኢትዮጵያ ፌስቡክንና ትዊተርን ሊተካ የሚችል የማህበራዊ ትስስር ገጽ ስራ ላይ ልታውል ነው!! የራሳችንን የማህበራዊ ትስስር platform እንፍጠር የሚለው ጥያቄያችን ተሰምቷል! 🇪🇹🇪🇹 በኢትዮጵያ ውስጥ የለሙ የተግባቦት (የኮሙዩኒኬሽን) ፕላትፎርሞች አሁን ላይ ወደ ሙከራ መግባታቸውን የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል። ፌስቡክና ትዊተር ኢትዮጵያዊ የሆነ እውነት የያዙና ተጽእኖ የሚፈጥሩ መልእክቶች ካሉ በአስቸኳይ እንዲጠፉ እያደረጉ ነው ብለዋል። @OBOLE_TECH @OBOLE_TECH
Mostrar todo...
🌎 በአለም ላይ እስካሁን ከተሰሩት የሞባይል ስልኮች በትልቅነት አቻ ያልተገኘለት በ #ክሪኬትና በ #ሳምሰንግ ድርጅቶች የተፈበረከው Samsung Model SCH-r450 ነው:: 📱 ይህ የሞባይል ስልክ የተሰራው በፈረጆቹ 2009 ሲሆን የሚገኘውም በምድረ አሜሪካ ቺካጎ ነው በተጨማሪም SCH-t450 የተባለው ትልቁ ሞባይል (15 ጫማ ርዝመት) : (13 ጫማ ከፍታ) እና (3 ጫማ ጥልቀት) በጋራ ይዟል 📱ይህ ግዙፍ ሞባይል ለእይታ ሲቀርብ ለጎብኝዎች የማያቋርጥ የድምፅ እና የመልክት አገልግሎት ይሰጥ ነበር... - ከአለምም ትልቁ ሞባይል በመባልም በጊነስ ወርልድ ሪኮርድሰ መዝገብ ላይ ሰፍሯል። JOIN👉 @OBOLE_TECH JOIN👉 @OBOLE_TECH 📤 ➩ ሀሳብ/አስተያየት :↩️ 📣: @Adu21bot ⚡️Share And Support Us.
Mostrar todo...
📍ሳይንስን በስልካችን📍 - በእጆቻችን ላይ የሚገኙ ስማርት ስልኮቻችን ብዙ ነገሮችን እንድንከውን በሚያስችሉን ረቂቅ ቴክኖሎጂዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ - ታድያ ስልካችንን ለፎቶ ማንሳት እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ፍጆታ ከማዋል ባለፈ ተከታዮቹን መተግበሪያዎች ተጠቅመን ሳይንስን በተለየ መነፅር መመልከት እንችላለን፡፡ 1. #eBird - በስነ-አዕዋፍ (Ornithology) ጥናት ላይ በተሰማራ ቤተ-ሙከራ የሚተዳደረው ይህ መተግበሪያ የተለያዩ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንድናውቅና እንድንመረምር ከማስቻል ባለፈ ከዘርፉ ተመራማሪዎች ጋር ጭምር መረጃውን እንድንለዋወጥ ያደርገናል፡፡ በመተግበሪያው አድራሻችንን በማስገባት በዙሪያችን ያሉ ዝርያዎችን ማየት ስንችል የወፍ መገኛ ስፍራዎች ላይ በአጋጣሚ ከተገኘንም ያሳውቀናል፡፡ ታድያ ከበይነ መረብ ውጪም ስለሚሰራ ገጠራማ ቦታዎች ላይ አንቸገርም፡፡ 2. #Star_Walk - Star Walk በአመሻሹ ሰማይ ካሜራችንን ወደ ከዋክብት እንድናማትር በማድረግ ብቻ በእይታችን ስለገቡትን ከዋክብት እና ፕላኔቶች ገለፃ ያደርግልናል፡፡ ከማርስ የፀሐይ መውጫና መጥለቂያ ሰዓት አንስቶ እጅግ የበዙ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ያቀብለናል፡፡ 3. #NASA_Globe_Observer - ይህ መተግበሪያ ከቀድሞዎቹ በተለየ ወደ ረጂነት ይለውጠናል፡፡ በዳመና ሽፋን፣ መሬት ሽፋን እና ወባ ትንኝ ዙሪያ መረጃን የሚሰበስብ ሲሆን እኛም ቢሆን የምንመለከተውን ዳመና ፎቶ በማንሳት ለናሳ እንድናደርስና የአየር ፀባይን በመረዳት ረገድ ሚና እንድንጫወት ያደርገናል፡፡ 4. #MyShake - ለምርምር ታስቦ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተሰራ ሲሆን በዙሪያችን እና በዓለም ዙሪያ ያሉ የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴዎችን ያሳውቀናል፤ እኛ ላይ ቢከሰቱ ምን ማድረግ እንዳለብንም ይነግረናል፡፡ ሌላኛው የዚህ መተግበሪያ ስራ ስልካችን ላይ ተፅዕንዖ ሳያደርስ ያለንበትን ስፍራ የመሬት መንቀጥቀጥ ሁናቴ በመገምገም ምሁራኑ ግምቶችን እንዲያስተካክሉና ህይወትን እነዲያድኑ መረጃ ያቀብላል፡፡ 5. #The_Elements (በክፍያ) - iOS በሚጠቀሙ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲሆን Periodic Table ላይ የሚገኙትን ንጥረ-ነገሮች አካላዊ ቅርፅ ከመረጃ ደብሎ ያደርሰናል፡፡ ለምሳሌ እያንዳንዱን ንጥረ-ነገር ዙሪያውን ባሻን አቅጣጫ እንድንቃኝና ብሎም ስለ ይዘቱ፣ የግኝት ታሪኩ፣ ጥቅሙ፣ የገበያ ዋጋው ወዘተ… ጥልቅ ትንታኔ ይሰጠናል፡፡ 6. #Wolfram_Alpha (በክፍያ) - በድረ-ገፁ አማካኝነት የምናገኘው ይህ መተግበሪያ የፊዚክስ እና ኬሚስትሪ ቀመሮችን፣ የቁሶችን ይዘት፣ የምድራችን ንብርብሮችን መረጃ፣ የከዋክብት ካርታን እና ሌሎች መረጃዎችን ያቀርብልናል፡፡ በተጨማሪም ውስብስብ የሂሳብ ኢኩዌዥኖችን የማስላትና የአየር ሁኔታንም የማሳወቅ ስራ ይሰራል፡፡ 7. #Science_Journal - ይህ የጎግል ምርት በዙሪያችን ያሉ ሁቴዎችን እንድንመዘግብ ያደርገናል፡፡ ለምሳሌ፡- የስልካችንን ሴንሰሮች በመጠቀም ብርሃን፣ ድምፅ፣ ግፊት፣ እንቅስቃሴን ያነባል፡፡ በብሉቱዝ አማካኝነት ከሌሎች ማሳሪያዎች ጋር በመቀናጀትም ይሰራል፡፡ ውጤቶችን በፎቶና ፅሁፍ ሲያስቀርልን እነዚህን መረጃዎች ወደ ሌሎች መሳሪያዎች በማስተላለፍ መጠቀም እንድንችልም ያደርገናል፡፡ 📢: ✅Credit :- @OBOLE_TECH 📤 ➩ ሀሳብ/አስተያየት :↩️ 📣: @Adu21bot 📌Share And Support Us
Mostrar todo...
Tech News ▫️አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰው ልጅ ታላቁ ግኝት እንደሚሆን የጉግል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተናገሩ፡፡ ▫️የጉግል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሱንዳር ፒቻይ ከቢ.ቢ.ሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኳንተም ኮምፒዩቲንግ እና ስለ ተቋማቸው ተፅዕኖ ፈጣሪነት አብራርተዋል፡፡ ▫️በቀጣዮቹ 25 ዓመታት ውስጥ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኳንተም ኮምፒዩቲንግ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ አብዮታዊ ለውጥ እንደሚያመጡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይገልጻሉ፡፡ ▫️ሱንዳር ፒቻይ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ተዓምራዊ ለውጥ አምጥተዋል ከሚባልላቸው የእሳትና እና ኤሌክትሪክ ግኝቶች ጋር አመሳስለው ገልጸውታል፡፡ ▫️ኳንተም ኮምፒዩቲንግን አስመልክቶ በሰጡት ገለጻ አዲስ የመፍትሔ አማራጭን ይዞ የመጣ መሆኑን በቆይታቸው አብራርተዋል፡፡ ©Tech21 ═════❁✿❁ ═══════ 🎮▩♦️. @OBOLE_TECH 🚀▩♦️. @Adu21bot 🔶ቻናላችንን JOIN በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇 @OBOLE_TECH @OBOLE_TECH 📣#Mute ያደረገችሁ #Unmute በማድረግ መረጃዎችን ቶል ያግኙ✅ ══════❁✿❁════════ ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ ◈◂▴△ @OBOLE_TECH | | ▽▴▸◈ 🅣🅔🅒🅝🅞🅛🅞🅖🅨
Mostrar todo...
❝ስማርት ስልካችሁ ላይ ሊኖር ግድ ይላል❞ 🛃#አቀናባሪ ኖት? የተለያዩ #ስቶሪ ለመስራት ፈልገዋል? ወይስ #ቫይን ተጫዋች ኖት? የፈለጉትን ይሁኑ ብቻ ዛሬ አንድ መተግበሪያ ከእናንተ ጋር ሊተዋወቅ ግድ ብሎታል! ✅ዩቲዩበር፣ ብሎገር፣ ስቶሪ ሜከር፣ ወይም ተራ ኤዲተር ልትሆኑ ትችላላችሁ! 🎦ያም ሆነ ይህ ዛሬ የማሳያችሁ መተግበሪያ እናንተ ስማርት ስልክ ላይ ለ' መጫን ቋምጦ ተነስቷል!😘 〽️የሶፍትዌሩ መገለጫ #Power #Director ይባላል የተለያዩ ፊልሞች፣ ዶክመንታሪዎች፣ አስተማሪ ትምህርቶችን ለመስራት የሚያገለግል ምርጥ መተግበሪያ ነው! 〽️የፈለኩትን አይነት ቪዲዮ መስራት ስፈልግ የምጠቀመው መተግበሪያ ነው! 〽️ከሁሉም መተግበሪያዎች ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር የተለያዩ ፊልም ለመስራት ከምንጠቀምባቸው መሳሪያዎች አንዱ #Green #Screen በውስጡ አካቶ መያዙና 〽️በሺዎች የሚቆጠሩ ቪዲዮ ኤዲቲንግ ስታይል (Store) በውስጡ አቅፎ የያዘ በመሆኑ ነው! 🔰ቀጥታ #PlayStore (ለመስራyStore) ላይ ገብታችሁ ያለ ምንም ክፍያ መጫን ትችላላችሁ! ⚠️ቻናላችንን ለሌሎች ማጋራት አትርሱ እንዲሁም የቻናላችንን #Notification #On በማድረግ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ! ═════❁✿❁ ═══════ 🎮▩♦️. @OBOLE_TECH 🎯▩♦️. @OBOLE_TECH
Mostrar todo...
🖥 በኮምፒውተራችን ላይ #DELETE ሳይደረጉ #HIDDEN 🤷‍♂️ የሆኑ ፉይሎች እና ፎልደሮች ለማግኘት ወደነበረበት ለመመለስ ምን ማድረግ እንዳለብን ከዚህ ቀጥሎ በቅደም ተከተል የተቀመጡትን መንገዶች በመከተል የኮምፒውተርዎን ቅንብር ያስተካክሉ፡ – 1. Start የሚለው ምልክት በመጀመርሪያ እንመርጣለን 2. በመቀጠል ኮንትሮል ፓናል (Control Panel) 3. ከሚቀርቡለን ምርጫ ውስጥ Appearance and Personalization የሚለው ላይ ክሊክ እናደርጋለን... 4. ቪው (View) የሚለውን እንጫናለን ከዚያ አድቫንስድ ሴቲንግ (Advancing Setting) እናገኛለን.... 5. በመጨረሻም Show Hidden Files, Folders, Anddrives ክሊክ ካደረግን በኋላ ok የሚለውን መርጠን እናጠናቅቃለን፡፡ - ወይም:- Start >run >cmd> f:attrib -r -s -h /s /d 👉 በመቀጠል ተደብቀው የነበሩ ፋይሎቻችንን የምናገኝ ይሆናል. ✅Credit @OBOLE_TECH 📤 ➩ ሀሳብ/አስተያየት :↩️ 📣: @Adu21bot ⚡️Share And Support Us.
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.