cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

[መንሀጁል አንቢያዕ]

▪ قال ابن القيم: ( والجهاد بالحجة واللسان مقدم على الجهاد بالسيف والسنان )" 🔺ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ እንዲህ አሉ፦ በመረጃ ና በአንደበት ትግል ማድረግ በሰይፍ ና በመሳሪያ ትግል ከማድረግ ቀዳሚ ነው አሉ!! 📜 مقدمة منظومته الكافية الشافية ص/ 19

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 061
Suscriptores
-124 horas
-37 días
-1730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🔹አዲስ የተጀመረ የሸይኽ ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) ኪታብ የኪታብ:- አልጃሚዕ ሊሹብሃት አል-ሙመይዐህ ⏱ማታ ከዒሻእ በኋላ በሸይኽ አህመድ አወል (ሀፊዘሁላህ) በዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም ቻናልም ይተላለፋል 👇👇 https://t.me/DarASSunnah1444 https://t.me/DarASSunnah1444
Mostrar todo...
الجامع لشبهات المميعة ودحضها.PDF.pdf7.34 KB
በአንድ ቀን ፆም የአመት ወንጀል… ——— የዓሹራ ቀን ፆም ትሩፋት! ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- قال النبي صلى الله عليه وسلم: "صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ " رواه مسلم “የዐረፋ ቀን ፆም ከፊቱ ያለውን (አንድ) አመት እና ከኋላው ያለውን (አንድ) አመት ወንጀል ያስምራል (ያሰርዛል) ብዬ በአላህ ላይ እገምታለሁ። #የዓሹራ_ፆም_ከፊቱ_የነበረችውን_አመት_ወንጀል_ያስምራል (ያሰርዛል) ብዬ በአላህ ላይ እገምታለሁ።” ሙስሊም 1162 ዘግበውታል። عن أبي قتادة رضي الله عنه – في صفة صوم النبي صلى الله عليه وسلم وهو حديث طويل – قال : وسئل عن صوم يوم عاشوراء فقال : " يكفر السنة الماضية " أخرجه مسلم , والترمذي , وابن ماجه አቢ ቀታዳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ስለ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፆም ሁኔታ በረጅም ሀዲስ የሚከተለውን ብሏል:- ነቢዩ ﷺ ስለ ዓሹራ ፆም ተጠይቀው ሲመልሱ “ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያስምራል (ያሰርዛል)።” ብለዋል። [ሙስሊም፣ ትርሚዚይ፣ እና ኢብን ማጃ ዘግበውታል።] ይህ አላህ ለኛ የዋለው ትልቅ ውለታ ነው!። በአንድ ቀን ፆም ምክንያት የአመት ትናንሽ ወንጀሎች ይሰረዛሉ። በመሆኑ በአላህ ፈቃድ ይህን ፆም የወፈቀው ሰው 9ኛውን ቀን ሰኞ ሙሀረም 9/1446 ዓ.ሂ: እንዲሁም በኢትዮ ሐምሌ 8/2016: በፈረንጆች ደግሞ ጁለይ 15/2024 ስለሆነ ሰኞን ፆሞ ማክሰኞን 10ኛውን ቀን ለመፆም እንዲዘጋጅ ሁላችንም በተቻለን መጠን እናነቃቃ፣ (እናስተውስ)። በመልካም ነገር ላይ በማስታወስ ተጨማሪ አጅር ከአላህ ዘንድ ለማግኘት መሽቀዳደም ነው። ✍🏻ኢብን ሽፋ: ሙሀረም 8/1446 ዓ. ሂ #Join ⤵️ የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Mostrar todo...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

የዓሹራ ቀን አጿጿም እና በዕለቱ የሚከሰቱ ቢድዓዎች ————— እንደሚታወቀው የዓሹራ ቀን ፆም ማለትም ሙሀረም 10ኛውን ቀን መፆም ከታላላቅ ሶናዎች ነው። ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- (أَفْضَلُ الصِّيَامِ بَعْدَ رَمَضَانَ شَهْرُ اللَّهِ الْمُحَرَّمُ) رواه مسلم “ከረመዷን በኋላ በላጩ ፆም የሙሀረም ወር ፆም ነው።” [ሙስሊም 1163 ዘግበውታል።] ይህ ፆም የረመዷን ወር ከመደንገጉ በፊት ግዴታ ነበርም ተብሏል። የሚፆምበትን ምክንያት:- በመሰረቱ እንደ ሙስሊም ማንኛውም በቁርኣን እና በሶሂህ ሀዲስ የመጣን መልካም ስራ፣ ትእዛዝም ይሁን ክልከላ ምክንያቱን አወቅነውም አላወቅነውም መተግበርና መቀበል ግዴታችን ነው። በግልፅ ማስረጃ የመጣ ነገር እስከሆነ ድረስ መተግበር ነው። የዓሹራ ፆም ምክንያት አለው። በሚከተለው ሀዲስም ተብራርቷል:- عن ابن عباس ((قَدِمَ النَّبِيُّ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ- المَدِينَةَ فَرَأَى الْيَهُودَ تَصُومُ يَوْمَ عَاشُورَاءَ فَقَالَ مَا هَذَا؟ قَالُوا: هَذَا يَوْمٌ صَالِحٌ، هَذَا يَوْمٌ نَجَّى اللَّهُ بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنْ عَدُوِّهِمْ فَصَامَهُ مُوسَى، قَالَ فَأَنَا أَحَقُّ بِمُوسَى مِنْكُمْ فَصَامَهُ وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ)).  في صحيح البخاري ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ:- “ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና በገቡ ጊዜ አይሁዶች የዓሹራን ቀን (ሙሀረም 10ኛውን ቀን) ሲፆሙ አዩዋቸው፣ ነቢዩም ለአይሁዶች ይህ ምትፆሙት ምንድነው? አሉዋቸው፣ ይህ ምርጥ ቀን ነው፣ ይህ ቀን አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ከጠላታቸው የገላገለበት ቀን ነው፣ ሙሳ ፆሞታል። አሉ፣ ነቢዩም እኔ ለሙሳ ከናንተ የበለጠ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው ፆሙት፣ እንዲፆምም አዘዙ።” [ቡኻሪ ዘግበውታል።] አጿጿሙን በተመለከተ:- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- (( لَئِنْ بَقِيتُ إِلَى قَابِلٍ لَأَصُومَنَّ التَّاسِعَ )) ، أخرجه مسلم “ወደፊት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም (ቀን) እፆማለሁ።” [ሙስሊም ዘግበውታል።] በዚህ መሰረት ዘጠነኛውንና አስረኛውን ቀን እንፆማለን ማለት ነው። ይህም ከምንም አይነት ጭቅጭቅ ነፃ የሆነው አጿጿም ነው። 10ኛው እና 11ኛው??? ዘጠነኛው ቀን ያመለጠው 10ኛውን እና 11ኛውን መፆሙን በተመለከተ ግን የተወሰኑ ጭቅጭቆች አሉበት። እንደ ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) ያሉ ሊቃውንቶች 10 እና 11 መፆም ይቻላል ሲሉ የሚከተለውን ሀዲስ ማስረጃ ያደርጋሉ:- (صُومُوا يَوْمَ عَاشُورَاءَ ، وَخَالِفُوا فِيهِ الْيَهُودَ ، صُومُوا قَبْلَهُ يَوْمًا أَوْ بَعْدَهُ يَوْمًا). رواه أحمد في مسنده “የዓሹራን ቀን ፁሙ፣ አይሁዶችን በመቃራንም ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን ፁሙ።” ኢማሙ አሕመድ በሙስነዳቸው የዘገቡት ሲሆን አልባኒን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ ዓሊሞች ዷዒፍ ነው ብለውታል። የዚህን ሀዲስ ዷዒፍነት ያመኑ ዑለማዎች ሆነው ዘጠነኛው ቀን ያመለጠው ሰው 11ኛውን ለመፆሙ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "በሚቀጥለው ካደረሰኝ 9ኛውን እፆማለሁ።” ማለታቸው፣ ምክንያቱ ለ11ኛው ቀንም ይሆናል። ይላሉ፣ 9ኛውን ቀን እፆም ነበር ያሉበት ምክንያቱ አይሁዶችን ለመቃረን ነውና። 9ኛውን እና 10ኛውን ቀን ብቻ መፆም ነው፣ 9ኛው ካመለጠ ደግሞ 10ኛውን ብቻ መፆም ነው እንጂ 11ኛው የለም የሚሉት ደግሞ፣ "9ኛውን ቀን እፆም ነበር" ያሉበት ምክንያት አይሁዶችን ለመቃረን ቢሆንም  11ኛውን ለመፆም ማስረጃ አይሆንም ብለዋል። 1ኛ, ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በወቅቱ 10ኛውን ፆመው ነው ያቆሙት እንጂ 11ኛውን አልፆሙም። 2ኛ, በሚቀጥለው ካደረሰኝ 9ኛውን ወይም 11ኛውን እፆማለሁ ሳይሆን ያሉት 9ኛውን ብቻ ነው ከ10ኛው ጨምረው እንደሚፆሙት የተናገሩት። በነዚህ ምክንያቶች አንድ ሰው 9ኛው ካመለጠው 10ኛውን ብቻ ነው የሚፆመው ይላሉ። እንደ ማስረጃው አመዛኝነት ግን ከጭቅጭቁ ለመውጣትም በተቻለ መጠን 9ኛው እንዳያመልጥ ጥረት አድርጎ 9 እና 10 መፆም፣ 9ኛው ካመለጠ ግን ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንም 9ኛው አምልጧቸው 10ኛውን ብቻ ስለ ፆሙ 10ኛውን ብቻ መፆም ነው። ወላሁ አዕለም!! የዓሹራ ቀን ቢድዓዎች። ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:- “መኳኳልን እና መጋጌጥን፣ በቀኑ ለየት ያለ ሶላትን መስገድም ሆነ ሌሎች ለየት ያሉ ተግባሮችን በላጭነት አስመልክተው የመጡ ሀዲሶች በጠቅላላ ዷዒፍ ናቸው። የዚያን ቀን ከመፆም ውጭ ሌሎችን ነገሮች የሚጠቁም አንድም ትክክለኛ ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተረጋገጠ ሀዲስ የለም። "የዓሹራ ቀን ባለው አቅም ሰፋ አድርጎ ያመቻቸ ሰው፣ የሌሎችንም አመታት አላህ ሰፋ ያድርግለት።” የሚለው ሀዲስ ኢማሙ አሕመድ ሶሂህ አይደለም ብለውታል። የዚያን ቀን እለቱን አስመልክቶ መኳኳል፣ መቀባባት፣ ሽቶ መጠቀም፣ ውሸታሞች ያስቀመጡትና ሌላውም ተቀብሏቸው ከሀዘን ወደ ደስታ የሽግግር ቀን ብለው መጋጌጫ አድርገው የያዙት ነው። ይህን ያደረጉት ሙብተዲዕና ከአህሉ ሱንና ያፈነገጡ ጭፍሮች ናቸው። አህሉ ሱንናዎች ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያዘዙበትን የሚፈፅሙና ሸይጧን ያዘዘበትን ቢድዐ የሚጠነቀቁ (የሚርቁ) ናቸው።” [አልመናር አልሙነይፍ ፊ ሶሂሂ ወዷዒፍ 89] የሳዑዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴም "ይህን ቀን በመጋጌጥም ሆነ በምግብ ለየት ማድረግ አይፈቀድም። እንዲሁም ሺዓዎች እንደሚያደርጉትም የሀዘን ቀን አድርጎ ራስን በስለት መሰል ነገር መጉዳት አይፈቀድም። በዚያን ቀንም ሆነ በሌሎች ቀኖች ፋጢማን መለመን አይፈቀድም፣ በተውበት እንጂ አላህ ከማይምረው ከትልቁ ሺርክም ነው። ” ብሏል። [ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ቁ. 22177] ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሃዲ ዑመይር አልመድኸሊ (ሀፊዘሁላህ) በዚያ ቀን ለዕለቱ ብሎ ለየት ያለ ምግብ አዘጋጅቶ መብላት ይፈቀዳል ወይ? ተብለው ተጠይቀው፣ ሲመልሱ:- "በዓሹራ ለየት ያለ ነገር መዘጋጀት አለበት፣ ወደ አላህ ያቃርባል የሚል እምነት ኖሯቸው ከሆነ የሰሩት ይህ ቢድዓ ነው። ባረከላሁ ፊኩም።” ብለዋል። በሀገራችን በዚህ ቀን የተለያዩ ቢድዐዎች በተለይ ሱፊዮች ዘንድ ይፈፀማልና በዚህ ቀን ከፆም ውጪ ምንም አይነት ለየት ያለ ተግባር እንደሌለ አውቀን ከተለያዩ ቢድዐዎች ተጠንቅቀን ልናስጠነቅቅ ይገባል!!። ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) #Join ⤵️  የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Mostrar todo...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

👉 ዓሹራእና ምንዳውዓሹራእ ማለት የሙሐረም ወር 10ኛ ቀን ሲሆን ከነብዩላሂ ሙሳ አስገራሚ ታሪኮች አንዱን የሚያስታውሰን ቀን ነው። ➧ ነብዩላሂ ሙሳ ፊርዓውን ህፃናቶችን በሚያርድበት ዘመን ተወልደው በራሱ ቤት እንዲያድጉ አላህ ያሻውን ሰሪ የሆነው ጌታ አደረገ። ይህም ፊርዓውን በይተል መቅዲስ አካባቢ የተነሳ እሳት የግብፅን ምድር ሲያጠፋ በህልሙ ያይና ለጠንቋዮቹና ድግምተኞቹ ሲነግራቸው ከእስራኤላዊያን የሚወለድ ህፃን የንግስናው  መጥፊያ ሰበብ እንደሚሆን ነግሩት። ፊርዓውንም ከሚወለዱት ህፃናት ሴቶቹ ቀርተው ወንዶቹ እንዲታረዱ አዘዘ።ይህ ነገር አገልጋይ እንዳያሳጣቸው የፈሩት ግብፃዊያን ፊርዓው ዘንድ ሄደው አቤቱታ ሲያቀርቡ አንድ አመት የሚወለደው ተትቶ በሌላኛው አመት የሚወለደው እንዲታረድ አዘዘ። የአላህ ፍላጎት ሆነና ነብዩላሂ ሙሳ ወንድ ህፃናቶች በሚታረዱበት አመት ተወለዱ። የእስራኢላዊያን ህፃናት መወለድ የሚጠባበቁ ሰራዊቶች በመኖራቸው የነብዩላሂ ሙሳ እናት ጊዜዋ በመድረሱና አመቱ ወንድ ህፃናት የሚታረዱበት በመሆኑ ጭንቅ ውስጥ ገባች። የተፈራው አልቀረም ህፃኑ ተወለደ። እናት ምን ይዋጣት!!!? ↪️ አላህ ሁሉን ቻይ መሆኑን ሊያሳያት በሳጥን አድርገሽ ወደ ቀይ ባህር ወርውሪው የሚል መልእክት እንዲመጣላት አደረገ። ወረወረችውም። ወደ አላህም ፍፁም ተማፀነች። አላህም ልጇን እንደሚመልስላት ቃል ገባላት። ባህሩ ሳጥኑን ወደ ፊርዓውን ቤተመንግስት እየነዳ አደረሰው። የፊርዓው አገልጋይ ሴቶች ሳጥኑን አገኙት ሲከፍቱት የሚያምር ህፃን ነው!!!። ወደ ቤተመንግስት ተወሰደ። ኣሲያ የፊርዓው ባለቤት የአይናችን ማረፊያ ይሆናል ልጅ አድርገን እንያዘው አትግደለው አለችው ተቀበላት።     ➲ ረሃብ ይዞት ሲያለቅስ የሚቀርብለት ጡት በሙሉ እንቢ አለ። ምናልባት የሚስማማው ጡት ከተገኘ ብለው ሴቶችን ሲፈለጉ እህታቸው ማንነቷን ደብቃ አንድ ህፃናት በሙሉ ጡቷን የሚጠቡላት ሴት ላመላክታችሁ ወይ ብላ ጠየቀች አው አሉ። እናታቸው ወደ ቤተመንግስት መጣች!!!። ሱብሃናላህ በፊርዓውን ቤተመንግስት በእሱ ተንከባካቢነት በእናታቸው ጡት እንዲያድጉ አላህ አደረገ። በወቅቱ እስራኤላዊያን በቂብጦች የመከራ ገፈት ይጎነጩ ነበር። አላህ በሙሐረም 10ኛ ቀን ፊርዓውንን ከነሰራዊቱ አጥፍቶ እሳቸውንና ህዝቦቻቸውን ነጃ አወጣ። የአላህ መልእክተኛ ነብዩ ሙሐመድ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ወደ መዲና ሲሄዱ አይሁዶች ይህን ቀን ሲፆሙ አገኙዋቸው። ለምንድነው የምትፆሙት ብለው ሲጠይቁዋቸው ይህ ቀንማ አላህ ፊርዓውን አጥፍቶ ሙሳን ያዳነበት ቀን ነው። ለዚህ ነው የምንፆመው አሉዋቸው። እሳቸውም ለሙሳማ እኔ ከናንተ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው መፆም ጀመሩ ተከታዮቻቸውንም እንዲፆሙ አዘዙ። ያለውንም ምንዳ ሲናገሩ እንዲህ አሉ:– "صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ"     رواه مسلم   ( 1162). "የዓረፋ ቀንን መፆም ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የዓሹራእ ቀንን መፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።" ♻️ አዩዶችን ለመኻለፍ አላህ ካቆየኝ የሚመጣውን አመት ዘጠነኛውን የሙሐረም ቀን እፆማለሁ ብለው ነበር። ከዚህ በመነሳት የሙሐረምን ዘጠነኛና አስረኛ ቀን መፆም ይወደዳል። አብዛኛዎች ፉቀሃዎች ዘጠነኛ አስረኛና አስራ አንደኛውን ቀን መፆም ሱና ነው ይላሉ። ነገር ግን ከመረጃ አንፃር ዘጠነኛና አስረኛው ነው። ይህ ካልተቻለ አስረኛና አስራ አንደኛውን በመፆም አይሁዶችን መኻለፍ ይቻላል።         አላህ ይወፍቀን። ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር በድጋሚ የተለቀቀ። http://t.me/bahruteka
Mostrar todo...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

ልዩ እና ገራሚ ሙሐደራ 🔍🔍🔍🔍🔍🔍 እያንዳንዱ ሰው ስላለበት አማና ✅ አደራን የመወጣት አስፈላጊነት ➜ ይህ ሙሐደራ    ➧ ኡስታዝ ያለበት አደራ    ➧ ሚስት ያለባት አማና    ➧ ዶክተር ስላለበት አማና    ➧ ተማሪ ስላለበት አደራ    ➧ ሰራተኞች ስላለባቸው አማና    ➧ የሀገር አስተዳዳሪ ስላለበት አማና    ➧ በየትኛውም ሙያ፤ እድሜ ሁኔታ ወዘተ ያለ ማንኛውም ሰው ስላለበት ሀላፊነት በዝርዝር ተዳሷል።    ➹ ሌሎችም በሚገርም አቀራረብ ተካተዋል። 🎙 በተከበሩ ሸይኽ አቡ ዐብዱልሃሊም ዐብዱልሐሚድ ብን  ያሲን አል'ለተሚይ አሱኒይ አስሰ'ለፊይ አላህ ይጠብቃቸው 🏝 ይሄን ሁሉ ትንታኔ ያቀረቡት ሸይኹ በሂፍዛቸው ነው። በጣም ትልቅ ብቃት አላህ ሰጥቷቸዋል። በጣም አስገራሚ አሊም ናቸው። ▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴ ⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩ 🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣  ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️ https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy ሀሳብ  ካለዎ  ⤵️⤵️⤵️⤵️ https://t.me/AbuImranAselefybot
Mostrar todo...
የዲን አማናዎችን መጠበቅ.mp327.58 MB
🔊 የሙስሊም እህቱ ጭንቀት ለሚያሳስበው ሁሉ የእርዳታ ጥሪ 🔊 አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ ውድ ሙስሊም  ወንድምና እህቶች እነሆ "በዚህች ምድር የወንድሙን (ወይም የእህቱን) ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የርሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ  ﷺ ነግረውናል ። የሱና እህታችን ሹክሪቴ ዐብደሏህ ትባላለች ። እነ ኡስታዝ አብራር አወል ቅራት አለም ኢያሉ(ኢየቀሩ) ቅራት የጀመረች ስትሆን ሙሃዷራቸውን ትታደም ነበር  በኡስታዝ ቃሲም ሱልጣንም ቂራት አለም ኢያሉ (ኢየቀሩ) ቀርታለች በአሁኑ ሳት ደሞ በኡስታዝ አቡ ሀሳን ሙሀመድ ኪርማኒ  ትቀራ ነበር የዛሬ ሰባት አመት አከባቢ ባጋጠማት አደጋ ምክኒያት በአሁኑ ሳት ቅራቷን አቁማ ከመኝታዋ አትንቀሳቀስም አደጋውም ከቆጥ ወድቃ ብዙ አመታትን ታማለች   በሳአቱ የሚገባ ህክምና ባለማግኘቷ ሚክኒያት ብዙ በሽታዎችን አስከትሎባታል የኩላሊት ቁስለት የነጭ ደምሴሏ ከ 12000 በልጦ በሽታን አለመቋቋም ሌሎችም በሽታዎች አሉ❗️ ወደ ኢስፒሻሊስት ሃኪም ሄዳ እንድትታከም ዶክተሩ ተናግሯል ሆኖም የሚያግዛት ቤተሰብ የለም ከብችኛዋ እናቷ ጋር ባንዲት ጎጆ ቤት ነው ምትኖረው እንኳን የህክምና ብር ማግኘት ይቅርና ለጥቃቂት ሃጃቸው እንደሚቸገሩ ነው የማቀው እህታችን ወደናንተ መቅረብ በጣም ቢከብዳትም መፍትሔ ስታጣ ግዜ ተገዳለች ስለዚህ ይህችን የሱና እህታችን ካለችበት አደጋ ለማትረፍ ወደ ቂራቷ  ለመመለስ የኛ የወንድምና የእህቶቿ እገዛና እርዳታ ያስፈልጋታል 📌 ኒዕማ የሚታወቀው ከተወገደ ቦሃለ ነውና ያለችበትን ጭንቀት እሷ ናት ምታቀው ✅ ውድ ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች ፣  ለዚህች ለተጨነቀች እህታችን ትንሽ ትልቅ ሳንል የህክምና ወጪዋን በመሸፈን ካለችበት ጭንቀት ወጥታ ወደ ጤንነቷና ወደ ቂራቷ እንድትመለስ የአቅማቹህን እንድታበረክቱ  ስንል ለሁላቹሁም የእርዳታ ጥሪያችንን   እናስተላልፋለን በገንዘብ መርዳት ባትችሉ share በማድረግ ተባበሩት። የእህታችን አካውንት ቁጥር :- የኢትዮ ንግድ ባንክ        #1000237129524   # ስም :- ሹክሪቴ ዐብደላ ሀሰን ለበለጠ መረጃ ስልክ:     #0966849050 "በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ  ﷺ ነግረውናል ። ይሄንን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሁሉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ በተለያዩ ቻናሎች ግሩፖች ሸር እንድታደርጉልን https://t.me/ye_selefiyoch_eht
Mostrar todo...
👉 አዲስ pdf 👉 40 ሐዲሶች عنوان: الأربعون المكية في التوحيد والسنة .pdf ርእስ:- አርባዎቹ መኪይ (መካ ላይ የተዘጋጁ) በተውሒድና በሱንና ላይ የሚያተኩሩ ሀዲሶች بقلم الشيخ الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله السلطي حفظه الله ✍🏻አዘጋጅ:- ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ) ከሳዑዲ ዐረቢያ መከህ ቴሌግራም ቻናል ⤵️ https://t.me/HussinAssilty 🔹እነዚህ በተውሒድና በሱና ላይ የሚያጠነጥኑ ከሶሂህ ሀዲስ የተውጣጡ ለጀማሪ ተማሪዎች ለሽምደዳ የሚቀሉ ወሳኝና አንገብጋቢ ሀዲሶች ናቸው፣ በተለይ በክረምቱ በየ ቦታው የሚያስተምሩ ኡስታዞች ለልጆች እነዚህን ሶሂህ ሀዲሶች ብታሸመድዱ የተመረጣና መልካም ነው። የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Mostrar todo...
الأربعون_المكية_في_التوحيد_والسنة_للحفظ.pdf7.17 KB
Photo unavailableShow in Telegram
🏝 ❝አስደሳች ዜና❞ 📚 አዲስ ኪታብ በተለይ ለኡስታዞችና ለዲን ተማሪዎች 📖 ⚙️ የታላላቅ መሻይኾች ተማሪ የሆነው ዓሊም ሸይኽ ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አል-ኢትዮጲ አስ-ስልጢይ (ሀፊዘሁላህ) ከተዘጋጁ ኪታቦች አንዱ የሆነው « እስልምና ዒሳን {ዓለይሂ ሰላም} ማላቁ እና ከእስልምና ሀይማኖት የመካድ ምክንያቶች» በሚል በዐረቢኛ የተዘጋጀ አዲስ ኪታብ በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል ኢንሻ አላህ!!! 📮 📔 تعظيم الإسلام لعيسى عليه السلام وأسباب الارتداد عن دين الإسلام 📝 إعداد وجمع:-             🔑 الشيخ حسين بن محمد بن عبد الله الإتيوبي السلطي 📝  አዘጋጅ:- ሸይኽ ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አል-ኢትዮጲ አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ) የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/shakirsultan/1860 📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ 👇👇👇 🌐 https://t.me/shakirsultan
Mostrar todo...
ተጀመሯል የኡሱል አስ-ሱንና ሊል ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሀንበል (ረሂመሁላህ) ሸርህ (ሉዙም አስ-ሱንነህ) የኩታቡ pdf 👇👇 https://t.me/DarASSunnah1444/7031 በሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) ቀን:- ጁምዐህ፣ ቅዳሜና እሁድ ሰኣት:- ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ገባ ገባ በሉ👇👇👇 https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=bea2443f610277d234
Mostrar todo...
ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel

👉 አዲስ ኪታብ pdf عنوان:- لزوم السنة في شرح أصول السنة ሱናን አጥብቆ መያዝ በሚል ርእስ የተዘጋጀ የኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሀንበል (ረሂመሁላህ) ኡሱል አስ-ሱንና ኪታብ ማብራሪያ للشيخ الفاضل الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله الإتيوبي السلطي حفظه الله ✍🏻አዘጋጅ:- የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ እና የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ዐሊ ኣደም ተማሪ የሆኑት ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ) ከሳዑዲ ዐረቢያ መከተ'ል መከረመህ 🔸በዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም ቻናል በonline ጁምዓ፣ ቅዳሜና እሁድ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በሸይኹ በራሳቸው እየተቀራ ነው በአማርኛ ስለሚብራራ ሁሉም መከታተል ይችላል ቴሌግራም ቻናል ⤵️

https://t.me/HussinAssilty

https://t.me/HussinAssilty

(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት) የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ

https://t.me/DarASSunnah1444

https://t.me/DarASSunnah1444

ተጀመሯል كتاب صحيح البخاري بفضيلة الشيخ الدكتور حسين بن محمد السلطي حفظه الله ገባ ገባ በሉ 👇👇👇 https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=868d1b19d75c2d7dfe
Mostrar todo...
ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel

ይህ የዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው مركز دار السنة لتعليم الشريعة الإسلامية Dar As-Sunnah Sharia Knowledge Center አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን ከድልዲዩ በስተቀኝ እንገኛለን። ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031

Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.