cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ጣፋጭ የብእር ሙዳይ

Poem

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
214
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

@Alishu_t #አንዱ እና #ሌላው .፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ከለታት ባንዱ-ቀን ሳልተኛ ስነቃ የሆነው ገረመኝ የሆነ ጊዜ ላይ አንድ ላይ የነበርን አውን ግን ስነቃ እንዳልነበርን ነን. አንዱ ወደ ሱሱ ሌላው ወደ ራሱ አንዱ ስራ ሰሪ ሌላው ግን ተማሪ አንዱ ተደባዳቢ ሌላው ሰው አክባሪ አንዱ ሰማይ ሲበር ሌላው ውጪ በሮ አንዱ ሴሰኛ ሌላው እስፖርተኛ አንዱ ታስሮ ሌላው አሳሪ ሆኖ ኢሄ ሁሉ ልዩነት ከአንድ ትምርት ቤት እኔ የጨነቀኝ አንዱ-ጋ ነው ሌላው-ጋ የቱጋ እንደነቃው። . . ስነቃ የሆነው እዚጋ ያበቃል ከገጠመላቹ የመጀመሪያ ግጥሜ ኢሄንን ይመስላል።
Mostrar todo...
አሁንስ ......አሁንስ በጣም ከበደኝ መልክ ፈገግታህ አልጠፋብሽ አለኝ ሌት ተቀን ፍቅርህ አሠቃየኝ ስታናግረኝ ራስህ አስታውሰህ በፍቅር አይኖችህ እኔን እያየህ ልቤ ይፈነድቃል ደስ ይሰኛል አሁንም አሁንም አንተን ይመኛል እኔ አልናገርም በጣም ኩሩ ነኝ እባክህ .....እባክህ አሣርፈኝ ፈጠን ብለህ አፈቅርሻለሁ በለኝ ልቤ አንተን ተርቦ ሳይሞት ሳልማቅቅ በፍቅርህ ናፍቆት ገላግለኝ እባክህን ገላግለኝ የኔ ሁኚ ብለህ አሣርፈኝ ከሌላ ስትሆን ስቃጠል በቅናት ልቤን በሃዘን ደጋግመህ ስትፈትናት ከአንተው መስማት እፈልጋለው ገላግለኝ በለኝ አፈቅርሻለሁ @fursatanya @kidapoim @kidapoim
Mostrar todo...
የፍቅር ታሪካችን "ሀብታሙ ጓድሽ ነው ሺበሺ ዘማችሽ ለኔም ይገርመኛል ባዶ እጄን ስወድሽ" ከሚል ሙዚቃ ላይ ስንኙን ወስጄ ሽቅብ በአእምሮዬ አውጥቼ አውርጄ እንደኔ አስተሳሰብ ፍፁም ምልከታ የሰሚ ጆሮ ላይ በመፍጠር ትውስታ የአድማጭ ሀሴት ነው ለዘፈኙ ደስታ! ከቶ አላስደነቀኝ በድምፅ መቀለፁ ስሜትና ሀሳቡን በካሴት መቅረፁ እኔን ያስገረመኝ... የፍቅር ህይወቴን የእኔን መግለፁ! ✍ Ermias Ghiwot @kidapoim @kidapoim
Mostrar todo...
ይድረስ ለማታምኚኝ እገሌ የምባል እኔ ያንቺ አፍቃሪ የዕውነት ለመውደዴ ይሀው ምስካሪ! ከአፌ የሰማሽውን የፍቅር ቃላት የጎን ብገፊያቸው አላምን በማለት ጥቂት ስንኝ ቋጠርኩ የልቤን እውነት! እናምልሽ ውዴ... የፍቅሬን መጠን ቴሌዎችን ጠይቂ ላንቺ በመደወል መዛሌን እወቂ ብሬንም ጨርሼ ብድር መጠቀሜን ለማይሰራ ዳታ ገንዘብ መገበሬን ጨርሰው ይንገሩሽ ላንቺ ስል መኖሬን! አንቺን እንዲሰጠኝ ስለት መደረድሬ ቁልቁል ተንበርክኬ በፊቱ ማቀርቀሬ ዘውትር በየሰርኩ ደጁን መሳለሜ ጉልበቴ እስኪዝል ለፍቅርሽ መድክሜ ካህኑ ራሱ አውቋል ላንቺ እንደሆነ አለሜ! ምስክርም ካሻሽ አውጊ ጓደኞቼን ይንገሩሽ ለፍቅርሽ ሁሉንም መተዌን ፀባዬን ቀይሬ አዲስ ባህሪ አምጥቼ ለያዥ ለገናዥ ሳላመች ቀርቼ ብቻዬን መሆኔን ከሁሉ ተጣልቼ! እነሱን ካላመንሽ ጠይቂ ካሼሪ ላንቺ ስል ማምሸቴን በየግሮሰሪ ጣፈጭ ትዝታሽን እረሳ ይመስል በአረቄ በቢራ ጉበቴን ሳቃጥል መከረሜን ያቃሉ አንቺን ሳብሰለስል! ጎሮቤታችን በር ድድማስጫ ሚውለው ሰፈር በሰጠው ስም ዱርዬ ሚባለው በፍቅርሽ ምክንያት አቅሌን መሳቴ በፊቱ ሳዘግም ብቻዬን ማውራቴ ላንቺ እንደሆነ ያቃል ራሴን ማጣቴ! ከጋሼ ራዲዮ በጀብድ የሚሰማ "ፋኖ ፋኖ" ሚለው የአርበኞች ዜማ እኔ ጆሮ ሲደርስ ለየት ይላል ውሉ አንቺን ለመዋደስ ይመስለኛል ቃሉ ደግሞ ይሄን ስል አበደ ይላሉ! (ያሉትን ይበሉ) ጥያቄው ይብቃሽ! ምን አለፋሽ ውዴ በሀገር ምድሩ ታውቋል በፍቅርሽ ማበዴ! አኚህ ምስክሮች ፍቅርን ካልመዘኑ በሸንጎ ፊት ቆመው ፍርድ ካላቃኑ ሳይሻል አይቀርም ብቸኛ መሆኑ! ተፃፈ በኤርሚያስ @Eromaa ሚያዝያ 2012 @kidapoim @kidapoim
Mostrar todo...
#ስቅለት ወ ኮሮና በእለተ ሀሙስ በፀሎተ ሀሙስ ከቤተክስቲያን መጥቼ በፆም የቆየ ሆዴን እንኳን ምግብ አልሰጠሁትም እንዴት አንድ በሽታ ተፈርቶ ህጉ ተጥሶ እግሬን ሳልታጠብ በረከት ሳለገኝ መጣሁ እያልኩ እየተብሰለሰልኩኝ ነው ዛሬ ይህ ስርዓት እንዴት ይቀራል ዶግማዋ ቀኖናዋ እንዴት ይሻራል እረ ወዲያ...... ታጠቡ ታጠቡ ይሉናል ዛሬ እጠቡን ስንል ደሞ እምቢ ከሳኒታይዘሩና ከሳሙናው በላይ የዛሬ ምንኛ ሚያነፃ በሆነልን ነበር ማቆያ ገቡ የተባሉትን ሰዎች ሰብስቦ በዛሬው ስርአት በወይኑ እና በወይራው ቅጠል ቢታጠቡ አደለም ኮሮና ተብዬ ሌላም ነገር ብን ብሎ ነበር ሚጠፋው ብቻዬን እንደ እብድ ስብሰለሰል የበሬ መንኳኳት ነው ያነቃኝ ልጅ አቤሴሎም ና ጉልባን ብላ ቡናውም ደርሷል የአከራዬ ልጅ ትለፈልፋለች ወጣ አልኩና ወደ አከራዬ ቤት አቀናሁ ምግብ ባልበላ አንጀቴ ኮሮና በሚባል ሰይጣን በጎደፈው ስርአት የተቃጠለው ቆሽቴ ላይ እንባ ሚያራጭ ሚጥሚታ የተቀላቀለበት ጉልባን ቀረበልኝ እሱን አይበላሁ ቡናዬን እየጠጣሁ ከአከራዬ ቤተሰቦች ጋ ወግ ያለው ጨዋታ ስንጫወት አመሸን እኔም ስለደከመኝ ሰላም እደሩ ምኞቴን ተናግሬ ወደ ቀዝቃዛዋ ጎጆዬ ተመለስኩኝ በሬን ዘግቼ አልጋዬ ላይ ተዘረጋሁ ኮሮና ኮሮና ኮሮና ይህን ቃል ቀን በቀን ከመስማቴ የተነሳ ኮሮና ሲባል አቤት ማለት ጀምሬያለሁ ሁለተኛ የአለም ስም ሆኑአል መሳሳም መተቃቀፍ አሁንስ ናፈቀኝ ብሶቴን ማውጫ ገፄን ገንጥዬ መቸክቸክ ጀመርኩ በጌቴ ሴማኒ ይሁዳ ጌታን አሳልፎ ሲሰጥ ምልክት እንዲሆናቸው ዘንድ ጌታን አቅፎ ስሞታል እኔም በዚ በዘመኔ ወደ ጌቴ ሰማኒ ሄጄ ሚመስለኝን እንዲህ አልኩ...... የአለም መከራ የሰው ሁሉ ሀጢያት ማብቂያ ሊያገኝ ሲል መሳሳምና መተቃቀፍ አለም ላይ ይቆማል የአለም መዳኛ በመሳሙ ብቻ ተለይቶ ወቶ ስቃይን ስላየ ትንሳኤው እስኪሆን የዛ ዘመን ሰዎች መሳም መተቃቀፍ ያቆሙ ይመስለኛል ለዛም ነው ትልቅ ደስታ ከፊታችን ሲመጣ ብዙ ፈተናዎች ሚገጥሙን በዚ በኛ ዘመን ትንሳኤን ለማየት መሳሳሙ ቆሙአል በጌቴ ሴማኒ ይሁዳ ጌታዬን ሲስመው ምልክት ሰቶአቸው ይገፉት ጀመረ ፈሪሳውያን በሰውኛ አቅማቸው ጌታ መገፋት ሲጀምር የሰው ሁሉ ሀጢያት ከመዝገቡ ገፅ ይፋቅለት ስለጀመረ አሁንም መሳሳም ያቆምነው መተቃቀፉ የቀረብን ጠግበን ማንጨርሰው ደስታ ከፊታችን እየመጣ ነው ብዬ አስብኩ እነሱን አይመለከትም ወዲ ነው እናንተዬ ይህን ካልኩ ይበቃኛል መስገድም አቁሙ ሳይሉን በፊት ቶሎ ይህን ሳምንት በሰላም ያስጨርሰን በሀሙስ ምሽት ለአርብ አጥቢያ ስለሆነ ተየፃፈው                  መልካም ስቅለት                     ✍ብላቴናው ----Edited---- #ስቅለት ወ ኮሮና በእለተ ሀሙስ በፀሎተ ሀሙስ ከቤተክስቲያን መጥቼ በፆም የቆየ ሆዴን እንኳን ምግብ አልሰጠሁትም እንዴት አንድ በሽታ ተፈርቶ ህጉ ተጥሶ እግሬን ሳልታጠብ በረከት ሳለገኝ መጣሁ እያልኩ እየተብሰለሰልኩኝ ነው ዛሬ ይህ ስርዓት እንዴት ይቀራል ዶግማዋ ቀኖናዋ እንዴት ይሻራል እረ ወዲያ...... ታጠቡ ታጠቡ ይሉናል ዛሬ እጠቡን ስንል ደሞ እምቢ ከሳኒታይዘሩና ከሳሙናው በላይ የዛሬ ምንኛ ሚያነፃ በሆነልን ነበር ማቆያ ገቡ የተባሉትን ሰዎች ሰብስቦ በዛሬው ስርአት በወይኑ እና በወይራው ቅጠል ቢታጠቡ አደለም ኮሮና ተብዬ ሌላም ነገር ብን ብሎ ነበር ሚጠፋው ብቻዬን እንደ እብድ ስብሰለሰል የበሬ መንኳኳት ነው ያነቃኝ ልጅ አቤሴሎም ና ጉልባን ብላ ቡናውም ደርሷል የአከራዬ ልጅ ትለፈልፋለች ወጣ አልኩና ወደ አከራዬ ቤት አቀናሁ ምግብ ባልበላ አንጀቴ ኮሮና በሚባል ሰይጣን በጎደፈው ስርአት የተቃጠለው ቆሽቴ ላይ እንባ ሚያራጭ ሚጥሚታ የተቀላቀለበት ጉልባን ቀረበልኝ እሱን አይበላሁ ቡናዬን እየጠጣሁ ከአከራዬ ቤተሰቦች ጋ ወግ ያለው ጨዋታ ስንጫወት አመሸን እኔም ስለደከመኝ ሰላም እደሩ ምኞቴን ተናግሬ ወደ ቀዝቃዛዋ ጎጆዬ ተመለስኩኝ በሬን ዘግቼ አልጋዬ ላይ ተዘረጋሁ ኮሮና ኮሮና ኮሮና ይህን ቃል ቀን በቀን ከመስማቴ የተነሳ ኮሮና ሲባል አቤት ማለት ጀምሬያለሁ ሁለተኛ የአለም ስም ሆኑአል መሳሳም መተቃቀፍ አሁንስ ናፈቀኝ ብሶቴን ማውጫ ገፄን ገንጥዬ መቸክቸክ ጀመርኩ በጌቴ ሴማኒ ይሁዳ ጌታን አሳልፎ ሲሰጥ ምልክት እንዲሆናቸው ዘንድ ጌታን አቅፎ ስሞታል እኔም በዚ በዘመኔ ወደ ጌቴ ሰማኒ ሄጄ ሚመስለኝን እንዲህ አልኩ...... የአለም መከራ የሰው ሁሉ ሀጢያት ማብቂያ ሊያገኝ ሲል መሳሳምና መተቃቀፍ አለም ላይ ይቆማል የአለም መዳኛ በመሳሙ ብቻ ተለይቶ ወቶ ስቃይን ስላየ ትንሳኤው እስኪሆን የዛ ዘመን ሰዎች መሳም መተቃቀፍ ያቆሙ ይመስለኛል ለዛም ነው ትልቅ ደስታ ከፊታችን ሲመጣ ብዙ ፈተናዎች ሚገጥሙን በዚ በኛ ዘመን ትንሳኤን ለማየት መሳሳሙ ቆሙአል በጌቴ ሴማኒ ይሁዳ ጌታዬን ሲስመው ምልክት ሰቶአቸው ይገፉት ጀመረ ፈሪሳውያን በሰውኛ አቅማቸው ጌታ መገፋት ሲጀምር የሰው ሁሉ ሀጢያት ከመዝገቡ ገፅ ይፋቅለት ስለጀመረ አሁንም መሳሳም ያቆምነው መተቃቀፉ የቀረብን ጠግበን ማንጨርሰው ደስታ ከፊታችን እየመጣ ነው ብዬ አስብኩ እነሱን አይመለከትም ወዲ ነው እናንተዬ ይህን ካልኩ ይበቃኛል መስገድም አቁሙ ሳይሉን በፊት ቶሎ ይህን ሳምንት በሰላም ያስጨርሰን በሀሙስ ምሽት ለአርብ አጥቢያ ስለሆነ ተየፃፈው                መልካም የስቅለትበዓል                     ✍ብላቴናው @kidapoim @kidapoim @kidapoim
Mostrar todo...
Hello hello this is official dagi... we will send you vines funny & series videos amazing photos orginal music voices and also we have competition of music. For any comment @DAGDAN9 , @Bekii8 Subscribe us. Thank you https://t.me/OFFICIAL_DAGII5
Mostrar todo...
ØFFİČĂŁ ĎĂĢÎĪ

Hello hello 🙌 this is official dagi...we will send you vines funny 😁🤣& series videos📽 amazing photos 📸inspirational quote funny vidios 🎥voices 🎙and also we have competition of music🎼 For any comment 🗳@DAGDAN9 , @Bekii8 Subscribe us. Thank you

(እንደ ፈንድሻ ተበተኑ ) ጊዜ ላይ ሳይቆሙ ለስራ እያቅማሙ ከራሳቸው አልፈዉ ፣ ሀገርን አስጠቆሩ ፣ በእኩይ ምግባራቸው ፣ ህፀፅ ተነከሩ ፣ ህይወት ምን ትሁን ምን ፣ ሚስጥር ገመናዋን ፣ ሳያጠኑ ፣ ፍሬያቸውን አጥተው፣ ለፈንድሻ አምሳል ደርሰው ተበተኑ። ✍️ ቤዚቾ @kidapoim @kidapoim @kidapoim
Mostrar todo...
የመከራ ስላቅ ©ሲራክ እንባዬን በስላቅ ገንቡና ከትሩት ወይ መብራት ስሩበት ሲሻችሁ ዋኙበት በደም እዤ ምራቅ.... ሳቅ ደስታችሁ ይድመቅ.. ደሜ ዥረት ሆኖ ታጠቡት ገላችሁን አጥንቴን አውጡና ስሩት አጥራችሁን ይህ ሁሉ ሲሆን ግን..... በህልማችሁ ይሁን -------------//------------- ሲራክ @siraaq _____°°°°°____ @kidapoim @kidapoim @kidapoim
Mostrar todo...
✤✣ይታይሽ የኔ አለም✣✤ ይታይሽ የኔ አለም አዎን ተመልከቺ አስተውይ እናቴ.... የእህቶቼን ሳቅ የልጆችሽን ድምፅ ሳጣው ከሰፈሬ። ፨፨፨፨፨፨ አዎን ኢትዮጵያዬ በወንዞች በሳርሽ በእርሻ ባፈርሽ ቦርቀው ያደጉት እነዛ ልጆችሽ...... ዛሬ ምነው ጠፉ ደብዛ ተሠወረ ማን ቀማሽ ከእጆችሽ። ፨፨፨፨፨፨፨ አዎን የኔ ልእልት የሉም ከቤታቸው ቀዬ መንደራቸው ብቻውን ይጮሃል.. እናትም ተጨንቃ አይኗ አንባን ያነባል። ህፃናት አጥተዋል ጡትን ከአፋቸው.... የእናታቸው መጥፋት እንባ እያስነባቸው። ያልተዘጋው ማጀት ዛሬም አፉን ከፍቷል .... እምዬ ከሌለች እታአለም ካልመጣች አሻፈረኝ ብሏል። ፨፨፨፨ እናም እታለሜ አዎን አስተውዪ የህዝቦችሽን ግፍ የአጥፊዎችሽን ደባ ... የእህቴን በደል የቀሚሷን እንባ። አዎን ተመልከቺ መፍትሔ የሌለው ጩኸቴን አድምጪ ✣✣✣✣✣ እናም ኢትዮጵያዬ እስኪ ጠይቂያቸው ወንዘና ተራራ አእዋፍ ዛፎቹን .. ጋራ ሸንተረሩን መስካመስክ ዋሻውን .. አይቻለሁ ያለ ካለ.. የሲቃን ድምፅ ያደመጠ ... የሀዘንን እንባ የጠረገ... የእምዬን ፍርሀት ተመልክቶ ለእህቶቹ ተቆርቁሮ አንደራሱ የታገለ እስኪ ጠይቂ ካለ !!!!!! ✍ተፃፈ @Mak_bale 23.5.2012 @kidapoim @kidapoim @kidapoim
Mostrar todo...
🍑👌
Mostrar todo...