cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

MYS‍💚💛💞

New Music ☺☺☺ Love Music couple pic 💏💏 Jema pic ✌✌ Jobs 😁 Enejoy channel Cross @wizyoyeee @anaolllll Love u guy's

Mostrar mĂĄs
Publicaciones publicitarias
217
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

😂😍😭😁🙇‍♂😔😘😊😡😒☺️😳😄😏😢😃😉🤦‍♂😜😱😞😅😌😋🙄😎😚😅😞😀🤫😆😐😇🙃🙂😗😘🥰😍🥵😓😥😰😨😱😤😠😡🤮🤢🥴😲🥱😴🤤😪😮‍💨😵😮😧😦😯🙄😑🥶🕺🚶‍♂🏃‍♂🧍‍♂ 👩‍❤️‍👨 👆👆👆#Life #of #yonas
Mostrar todo...
ሁለት አይነት ሸክም አለ የመጀመሪያው ጠንክሮ የመስራት ሸክም ነው፤ ሁለተኛው የፀፀት ሸክም ነው። ጠንክሮ መስራት ምናልባት 1 ኪሎ ግራም ቢመዝን ነው፤ ፀፀት ግን 100 ኪሎ ግራም ተሸክሞ እንደመዞር ነው። የቱ እንደሚሻልህ አንተው ምረጥ! ሁላችንም አሁን ካለንበት የተሻለ ነገር እንፈልጋለን፤ በከንቱ ቀንህ ያለፈ ጊዜ👇 "በቃ አይኔ እያየ ምንም ሳልሰራበት ቀኑ አለፈ?" እያልክ ራስህን የወቀስክበትን ጊዜ አስብ፤ አየህ ወንድሜ ጠንክረህ የምትሰራው ከፍ እንድትል ብቻ አይደለም ሁሌም ከራስህ ጋር እንድትስማማ ነው። መሮጥ ጀምር መሮጥ ካቃተህ ተራመድ መራመድ ካቃተህ ተንፏቀቅ ብቻ ግን ትናንት ከነበርክበት ቦታ ተንቀሳቀስ! ጥሩ ጥሩ ነገሮች በሙሉ ለእናንተ መልካም ቀን!
Mostrar todo...
አያቴ የድሮ ሰዎች ግን አሁን ኖሩ ይባላል ? ስል ጠየኩ አያቴም ልጄ ለምን እንደዚህ አልክ ?  አሉኝ አያቴ ድሮ........ መብራት የለ፣ ንጹህ ውሃ የለ፣ ስልክ አልነበረም፣ ፈጣን መኪና የለ፣  ሆስፒታል የለ፣ ውብና ያማረ ቤተክርስትያን የለ...... ታዲያ እነዚህ ኑሮን የሚያቀሉ ነገሮች ሳይኖሩ ሰዎች እንዴት መኖር ቻሉ ? አያቴም መልሰው እሺ መጀመሪያ የኔን ጥያቄ መልስና እኔም የአንተን ጥያቄ እመልሳለሁ አሉኝ። የዚህ ዘመን ሰዎች........ ያለ እምነት፣ ያለ ፍቅር፣ ያለ መልካም ጓደኛ፣ ያለ ደግነት፣ ያለ ተስፋ፣ ያለ ትእግስት፣ ያለ ፈጣሪ እንዴት መኖር እንደቻሉ ንገረኝ አሉኝ እኔም አላውቅም አያቴ አልኳቸው። አየህ ልጄ በድሮ ጊዜ አንተ ያልካቸው ነገሮች ሁሉ አልነበሩም ነገር ግን ከድሮ ዘመን ሰዎች ይልቅ የአሁን ዘመን ሰዎች በእጥፍ እየሞቱ ነው ታዲያ ሆስፒታል ኖሮ ምን ፈየደ ? ትክክል ነህ በፊት ውብና ያማረ ቤተክርስቲያን አልነበረም ፈጣሪ ግን በደሳሳ ጎጆዋችን ውስጥ ከኛጋራ ነበር። አሁን በየደጁ ውብና ያማረ ቤተ/ክርስትያን ቢኖርም የሰዎች ልብ እጅጉን ከመቆሸሹ የተነሳ ከፈጣሪ ጋር ጥሩ ግኑኝነት የላቸውም። በርግጥ ትክክል ነህ የአሁን ሰዎች ንጹህ ውሃ ይጠጣሉ ከድሮ ሰዎች ይልቅ ግን በሽተኞች ናቸው። በአሁን ዘመን እንዳልከው ጥሩ ስልክ አለ የድሮ ዘመን ሰዎች ግን ስልክ ሳይኖራቸውም የወዳጅን ችግር ለመካፈል ከአሁን ሰዎች በጣም ፈጣኞች ነበሩ፤ አየህ እናንተ የዘመኑ ሰዎች የውሸት ኖራችሁ የእውነት ትሞታለችሁ!! ፍቅራችሁ የውሸት ጓደኝነታችሁ የውሸት እምነታችሁ የውሸት ንግግረችሁ የውሸት ታዲያ ከዚህ በላይ የውሸት ኖሮ የእውነት መሞት ምን አለ! ? .............. 🙏🙏 የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ ውዶቼ 🙏🙏
Mostrar todo...
"ሁሉን ነገር መፈለግ፣ ሁሉን መሻት፣ ያለገደብ ለመኖር ማሰብ የዚህ ዓለም ጣጣ፣ የድካም ምንጭ ነው። የምትጠቀምበትን ያክል ብቻ እወቅ፤ የሚያጠግብህን ያክል ብቻ ብላ፤ የሚያረካህን ያክል ብቻ ጠጣ፤ ሁሉን ነገር ማጣት ሰቀቀን ቢሆንም ሁሉን ነገር ማግኘትም ዕዳ ይሆናል፡፡ ምንም አለማወቅ ባዶነት ቢሆንም ሁሉን ማወቅ ደግሞ ሸክምም ይሆናል።"
Mostrar todo...
ልጅ እያለህ መራመድ ማን አስተማረህ ? መንቀሳቀስ እንዳለብህ ከቦታ ቦታ መሄድ እንደምትችል ማነው ያሳወቀህ? እናትህ ፣ አባትህ ፣ ወንድምህ ወይስ አህት ወይስ ሌላ ሰው? በፍፁም ይሄንን የነገረህ የለም ግን ደግሞ አሳይተውኋል አይደል? ሲንቀሳቀሱ አይተህ አንተም መሄድ መቻል እንዳለብህ ተሰማህ ግን እግርህ ለመራመድ ስላልጠነከረ ጉልበትህን መሬቱ ይቆረቁርህ ነበር ቅዝቃዜው ኮሮኮንቹ ብቻ ብዙ ምቾት ሲነሳው የነበረን ነገር ተቋቁሞ ያለማንም እርዳታ ህልምህን ስታሳካ ነበር አይደል ለመቆም ስትጠነክርስ ማን አሳወቀህ? አሁንም ማንም አደል? ግን ብዙ አልወደቅህም? ብዙ አላባበሉህም? ታድያ እንደዛ ስትወድቅ ስትነሳ ስትታመም ተስፋ ቆርጠህ መራመድ ይቅርብኝ ብለህ ትተኸዋል እንዴ? በፍፁም አይደል ድክ ድክ ስትል ውበትህ ይበልጥ የሚያሳሳ የማትጠገብ ሆንክ አይደል አቤት መራመድ የጀመርክ ቀን እማ ማን ይቻልህ እዚም እዛም ስጥሮጥ ስትፈነጭ እንደ አንተ የሚታይ ማን ነበረ! አየህ የህይወትህን የመጀመሪያ ትግል ድል ያደረግኸውና ራስህን ችለህ መቆም የቻልከው እኮ ገና ያኔ ነው እንደዛ ቀን ከዛ በፊት ተደስተህ ቤተሰቦችህን አስደስተህ ታዉቃለህ አታውቅም ያ ቀን ግን ደስታን አስተማረህ የሰው ልጅ የመቀየር የማደግ ለውጥ የመፍጠር የማሸነፍ ፍላጎት አብሮት ተፀንሶ አብሮት የተወለደ ነገር ነው መቼም ቢሆን መቆም አይፈልግም ታድያ ያኔ የነበረህ የልጅነት ጥንካሬ በህመም ውስጥ ማሸነፍ ድል የማድረግ ማንነት በላይ ትምህርት ማሳያ ምን አለ?
Mostrar todo...
Justin Bieber - Intentions ft. Quavo ❤️ 🎙 JOIN US @Music_4_3_3
Mostrar todo...
Justin_Bieber_Intentions_Official_Video_Short_Version_f_3AyMjyHu1bA.m4a3.47 MB
I'm on Instagram as @zlegehare. Install the app to follow my photos and videos. https://instagram.com/zlegehare?igshid=YmMyMTA2M2Y=
Mostrar todo...

አንተን ከምትፈልገው ነገር የሚያገናኝህ የአላማ ፅናት ነው፤ በህይወት የሚያሸንፈው እስከ መጨረሻው የሚጓዝ ሰዉ ብቻ ነው። ወንድሜ ኑሮ ሊያደክምህ፣ ነገሮች ሊሰለቹህ፣ ህይወት ተደደጋሚ ልትሆን ትችላለች፤ የደስታን ጥግ ማየት ከፈለክ ግን ለአላማህ መኖር ከዛ ለአላማህ መሞት አለብህ! ጥሩ ጥሩ ነገሮች በሙሉ ለእናንተ መልካም ቀን!
Mostrar todo...
የተረጋጋ ህይወት እንዲኖርህ መፅሀፍትን አንብብ ብዙ አታውራ ማውራት ሲኖርብህ ግን ዝም አትበል ምክርና አስተያየት ለመቀበል አትፍራ ለተደረገልህ ጥሩ ነገር አመስግን ፤ በቂ እንቅልፍ ተኛ የማታውቀውን ጠይቅ ፤ በየወሩ ካለህ ገቢ ላይ ትኝሽም ቢሆን ቆጥብ ዛሬ መስራት የምትችለውን ዛሬውኑ ስራ። የሠው ልጅ ሲቸግረው ልብሱን የቤቱን  ዕቃ፤ ኩላሊቱንም ሳይቀር ሊሽጥ ይችላል ህሊናውን ከሸጠ ግን በጠና ቸግርታል ማለት ነው።
Mostrar todo...
Man city 6 :3 man un😡👎🤦‍♂
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sĂłlo permite el anĂĄlisis de 5 canales. Para obtener mĂĄs, elige otro plan.