cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Delicious life

You have to live properly

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
180
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🔥🔥🔥ብዙ ጊዜ ስለምንቀዠቀዥ እግዝአብሄርን የቀደምን የተሻለውንም የያዝን ይመስለናል። 💯እውነቱ ግን እኛ ፈጠንንም ዘገየንም አካሄዳችን ከመለኮት እውቅና የተደበቀ አለመሆኑ ነው። 🙈ያበላሸነውን ሁሉ ያበላሸነው አርፈን ስላልተቀመጥን ነው። 🙏🙏🙏ያውቅልኛል እያሉ እንደመኖር የምያረጋጋ ነገር የለም። #idegulgn betam ♻️♻️ @deliciouslifezz ♻️♻️ ♻️♻️ @deliciouslifezz ♻️♻️
Mostrar todo...
🔋🔋🔋ዛሬ ከተመከርኩት 🔥ዛሬ ቀኑ ከትናንት በኋላ ከነገ ወድህ ነው።ትናንት ማለት ለዛሬ መገኘት ተኝተን ስንፍናን የቆለልንበት ወይም ደግሞ ተንቀሳቅሰን አቅምን 💪💪💪ያጠራቀምንበት እድሜ ነው። 💯ነገ ደግሞ ዛሬ የምንጥለው የስንፍና/የትጋት ዕቁብ ተጠራቅሞ የምንረከበው የዛሬ ግንባታ ነው። ♻️የጊዜ ዋጋን ማወቅ ከመባከንም ከማባከንም እኛን እና የኛ የሆነን ነገር ሌላውንም የመታደግ እውቀትን ያበረክትልናል። 🧠ሰው የምነቃውም የምፈዝዘውም በመረዳቱ ልክ ነው።ሰው ገንዘብ ስላለው ብቻ የፈለገውን ሁሉ ልያገኝ አይችልም፤በአለም ላይ በገንዘብ የማይገዛም ነገር አለና፤ 👉ሰው ሀይል ስላለው ብቻ እንደፈለገው መሆን አይችልም፤ሀይልም የትንሽዬ ቦታ አጥር ባርያ ናትና፤ ✅ሰው እውቀት ስላለው ብቻ የፈለገውን መናገር አይችልም፤እውቀትም በልቃውንት ዘንድ አለማወቅ ይሆናልና። የተሻለው መነፅር ከምለው መፅሀፍ የተወሰደ ♻️idegulgn betam ይቀላቀሉን 👍👍👍👍👍👍👍👍👍 t.me/zelalemzeleke t.me/deliciouslifezz
Mostrar todo...
ዛሬ ምን ተመከርኩኝ?

በውስጥ መስመር ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ ለማቅረብ t.me/zelalemzel ንኩትና ፃፉልኝ

🔋🔋🔋ዛሬ ከተመከርኩት 🌴በቻይና የምገኝ አንድ ባምቡ የተሰኘ ዛፍ አለ።ይህ ዛፍ የመጀመሪያዎቹን አራት አመታት ውሃ 💧💧💧እያጠጡና እየተንከባከቡት ሲያቆዩት ምንም አይነት የዕድገት 🙈🙈ምልክት እንኳን አያሳይም። 💯ነገርግን አምስተኛው አመት ላይ ይህ ዛፍ በስድስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ብቻ ወደ ዘጠና ጫማ ያህል ባንዴ ያድጋል። #አሁን ይህ ዛፍ ለማደግ 6 ሳምንታት ነው አምስት አመታት ነው የፈጀበት? ♻️ይህ የባምቡ ዛፍ ለ4 አመታት ያህል ዕድገት ባያሳይም ቅሉ ሲለማና ውሃ ሲጠጣ ባይቆይ ኖሮ አሁን በስድስት ሳምንታት ጊዜ ይህን ያህል ልያድግ ይቻለው ኖሯል? በፍፁም እንድያውም⚠️⚠️⚠️ ለሞት ይዳረግ ነበር። 💥በእውነት ወዳጆቼ ትዕግስትና እምነቱ ኖሯችሁ ትክክለኛውን ድርጊት ስትከውኑ ከቆያችሁ ውጤቱ የምታይም ይሁን የማይታይ፡ #ከምታይ መድረሻ መድረሻ መድረሳችሁ አይቀርም። ♻️idegulgn betam ይቀላቀሉን 👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍 👉 t.me/deliciouslifezz 👉 t.me/zelalemzeleke
Mostrar todo...
Delicious life

You have to live properly

💯"ብዙ ጊዜ ጭንቀቶቻችን የምመነጩት የሌላ ሰው የችግር ታክሲ ላይ ስንሳፈር ነው።ሰው ኳስ ስወረውርብህ መቅለብ ግዴታህ አይደለም።" ዶ/ር ሪቻርድ ካርሰን ♻️♻️ @deliciouslifezz ♻️♻️ ♻️♻️ @deliciouslifezz ♻️♻️
Mostrar todo...
🔋🔋🔋ዛሬ ከተመከርኩት 🌴በአንድ መንደር ውስጥ የምኖሩ ጠቢብ ሽማግሌ ነበሩ፤በመንደሩ ውስጥ የምኖሩ ነዋሪዎች ጥያቄዎቻቸውን❓❓❓ ይዘው እርሳቸው ጋር ለምክር🗣🗣🗣 ይሄዱ ነበር። 💥አንድ ቀን በመንደሩ የምኖር አንዱ ገበሬ ወደ ጠቢቡ መጥቶ 🙈ግራ በተጋባ ድምፀት እባክዎ ይርዱኝ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነኝ።አንድ በሬዬ ሞተ😭😭😭😭 ስለዝህም የማርስበት የለኝም።ከዝህ የከፋን አይነት ነገር ልኖር ይችላል?"አላቸው።ሽማግሌዉም በእርጋታ ልሆንም #ላይሆንም ይችላል ብለው መለሱለት። #ገበሬውም በጥድፊያ ወደሰፈሩ ተመልሶ ለጎረቤቶቹ ሽማግሌው አብዷል።ከዝህ የባሰ ነገር ምን ልኖር ይችላል እንዴት ይህንን መረዳት ይሳናቸዋል አለ። 🌖በነጋታው ገበሬው እርሻው ውስጥ ፈረስ ይመለከታል።ሰፈሩን ሁሉ ብጠይቅም ፈረሱ ባለቤት አልነበረውምና ምንም በሬ ስላልነበረው በፈረሱ ባርስስ የምል ሀሳብ ይመጣለታል።ከዝያ ፈረሱን ይዞ በእርሱ ማረስ ይጀምራል።ማረስ እንደዛ ቀሎት አያውቅም።ስለዝህም ጠቢቡን ሽማግሌ ይቅርታ ለመቀየቅ ሄደ።ልክ ብለው ነበር በሬን ማጣት የመጨረሻው አስከፊ ነገር አይደለም።እንድያውም በረከት ነው።በሬዬ ባይጠፋ ኖሮ ፈረስ አላገኝም ነበር።🐎🐎ፈረስ ማግኘቴ በጣም ጥሩ ነገር ነው አይደል? ሲላቸው ሽማግሌው በተረጋጋ ድምፀት ልሆንም ላይሆንም ይችላል ብለው መለሱለት። #ገበሬው እንደገና እኝህ ሰው አዕምሯቸውን ስተዋል ብሎ አሰበ። 🌈ነገርግን ገበሬው ቀጣይ የምፈጠረውን አላወቀም ነበር።ከጥቂት ቀናት በኋላ የገበሬው ልጅ ፈረሱን እየጋለበ እያለ 🤕ይወድቅና እግሩ ይሰበራል።ገበሬው እርሻ ላይ ማን ያግዘኛል ብሎ ይጨነቅና ሽማግሌው ጋር ይሄዳል።ፈረስ🐎🐎 ማግኘቴ ምርጥ ነገር እንዳልነበረ እንዴት አወቁ?ልጄ እግሩ ተሰብሯል።እርሻ ላይም አያግዘኝም።ይሄ በእርግጠኝነት እጅግ አስከፊ ነገር ነው።በዝህ መቼም ይስማማሉ? ይላቸዋል። 🔯ሽማግሌው ግን ከዝህ በፊት እንዳደረጉት በእርጋታ #ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ብለው ይመልሳሉ።አሁንስ መሳሳታቸው አይቀርም!ብሎ በንዴት ጥሏቸው ይሄዳል።በነጋታው በመንደራቸው⚔🗡⚔ ጦርነት ታውጆ ወታደሮች አቋማቸው ብቁ የምመስሉ ወጣቶችን ሰብስበው ይዘው ሄዱ።ከመንደራቸው የቀረው የሱ ልጅ ብቻ ነበር።ሌሎቹ ወደሞት ቦታ ስወሰዱ የእርሱልጅ በህይወት በቤቱ ቀረ። #በእውነታው አለም ቀጣይ የምከሰተውን ነገር ማወቅ አንችልም።የምናውቅ ይመስለናል እንጅ አናውቅም። አስታውስ ልሆንም ላይሆንም ይችላል! ♻️በጣም idegulgn 👉ከወደዱት ለ5 ሰው #forward አድርጉልኝ ይቀላቀሉን 👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍 t.me/deliciouslifezz
Mostrar todo...
Delicious life

You have to live properly

🔋🔋🔋ዛሬ ከተመከርኩት In the jungle🌴🌴🌴 which animal is the : biggest ........ Elephant🐘 tallest ........ Giraffe wisest ........ Fox🦊 fastest ........ Cheetah🐆 Yet, the Lion🦁 is the KING of the jungle even without ANY of these qualities.!! Why? Because............... #The Lion is courageous, bold, walks with confidence, dares anything and is never afraid. The Lion believes he is unstoppable. The Lion is a risk taker. The Lion believes any animal is food for him. So.......... What we learn from the Lion ? #in order to be the leader • You don't need to be the fastest. • You don't need to be the wisest. • You don't need to be the smartest. •You don't need to be the most brilliant. # All you need is courage #All you need is the will to try. # All you need is the faith to believe it is possible. # All you need is to believe in yourself, that you can be who God made you and do what He created. "Lion is the leader in jungle because of his Attitude". It's TIME to bring out the Lion in you..! Dr. Myles munoroe "The lion never shout of everything what he see as a dog,but he stare and catch up what he need. so you must be the lion" Dr. Alelgn--- lecture@ aastu በጫካ ካሉ እንስሳቶች ዉስጥ የትኛው ነው : ትልቁ ...............ዝሆን 🐘 ብልጥ............ቀበሮ 🦊 ፈጣን ...........አቦ ሸማኔ🐆 ሆኖም፣እነዚህ ብቃቶች ባይኖሩትም እስካሁን አንበሳ🦁የጫካ ንጉስ ነው !! ለምን? #ከአንበሳው ምን እንማራለን? መሪ ለመሆን •በጣም ፈጣን መሆን አይጠበቅብህም። •በጣም ብልህ መጎን እይጠበቅብህም። • በጣም ብልጥ መሆን አይጠበቅብህም። • በጣም ጀግና መሆን አይጠበቅብህም። ካንተ የሚጠበቀው ጠንካራ መሆን ነው። ካንት የሚጠበቀው ለመሞከር ፍላጎት ነው። ካንት የሚጠበቀው ይህን ማድረግ እችላለሁ የሚል መንፈስ ነው። ካንተ የሚጠበቀው እግዚአብሔር እንደሰራህ መሆንና የተፈጠርህበትን ስራ መስራት እንደምትችል በራስህ መተማመን ነው። "አንበሳ በጫካ ዉስጥ መሪ የሆነው በሁኔታው ወይንም በፀባዩ ነው።" እኛም እንበሳውን በውስጣችን የምንይዝበት ሰአት አሁንኑ ነው። "እንበሳ እንደዉሻ ማንኛውንም ነገር ሲያይ አይጮህም፡ የሚፈልገውን ነገር ለረጅም ሰአት አተኩሮ ካየ በኋላ የሚፈልገውን ይይዛል እንጅ። ስለዚህ እናንተ አንበሳውን ልትሆኑ ግድ ነው።" ዶ/ር አለልኝ--- ይቀላቀሉን 👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍 t.me/deliciouslifezz
Mostrar todo...
Delicious life

You have to live properly

🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁 🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁 🙏🙏🙏እንኳን ለጌታችን እና ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ #የልደት መታሰብያ በሰላም አደረሳችሁ። 🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁 🌍🪐አለማትን በቃሉ የፈጠረው የሰማይና የምድር ታላቁ ጌታ መወለጃ ቦታ አጥቶ በግርግም🐑🐑🐏 የተወለደው የከበረመኖርያ አጥተን ካለንበት ከሀጥአት ግርግም ልያወጣን ነው።የውርደቱ ልክ የውድቀታችንን እና የመውደዱን ርዝመት ይገልጠዋል። 🌱ሽታችን የተቀየረው በበግ ግርግም ያለውን ሽታ ለማሽተት መድሃኒአለም በታላቅነቱ ስላላፈረ ነው። 🎁ገና የምባል ነገር ያለ የገና ስጦታ የለም። ገናችንን ገና ያደረገው ከሰማይሰማያት ከከበረ መኖሪያ ከእግዝአብሄር ለሰው ልጆች የተሰጠ ስጦታ እግዝአብሄር ነው።እግዝአብሄር እግዝአብሄርን በመስጠቱ #ህይወትን አገኘን። በስጦታ ሰላም ሆኖልናል። 💥እንኳን አደረሳችሁ ጌታ ይመስገን ስለ ስጦታው ስለ እየሱስ🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈 t.me/zelalemzeleke 🎈🎈🎈🎈 🎈🎈 t.me/deliciouslifezz 🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈
Mostrar todo...
ዛሬ ምን ተመከርኩኝ?

በውስጥ መስመር ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ ለማቅረብ t.me/zelalemzel ንኩትና ፃፉልኝ

💯እስቲ የምያናድድ ሀሳብ ሳታስብ ለመናደድ ሞክር!እስቲ አሁን ደግሞ የምያጨናንቅ ሀሳብ ሳታስብ ለመጨነቅ ሞክር ወይም የምያሳዝን ሀሳብ ሳይኖርህ ለማዘን ሞክር።አትችልም! እስቲ የምያስደስት ነገር ሳታስብ ተደሰት አይቻልም! ✍አንድ ስሜት እንድሰማህ በቅድምያ እሱን ስሜት የምፈጥር ሀሳብ ሊኖርህ ይገባል። #ደስታንም ሀዘንንም ድብርትንም....የምያንቀሳቅሰው ለማሰብ የምንመርጠው የሀሳብ አይነት ነው።ዶ/ር ሪቻርድ ካርሰን ♻️♻️ @deliciouslifezz ♻️♻️ ♻️♻️ @deliciouslifezz ♻️♻️
Mostrar todo...
💯 በሌሎች አስተያየት ውስጥ እውነትን ፈልግ።ገና የሌሎችን ሀሳብ ከመስማትህ በፊት ከራስህ ሀሳብ ጋር አታወዳድር።የሌሎች ሀሳብ ካንተ ስለተለየ ብቻ ውድቅ አታድርግ።እያንዳንዱ ሀሳብ ጥሩ ነገር ይኖረዋል።ከማንኛውም የሰው አስተያየት ውስጥ ጥሩ ጎን መፈለግን ልመድ። ዶ/ር ሪቻርድ ካርሰን ♻️♻️ @deliciouslifezz ♻️♻️ ♻️♻️ @deliciouslifezz ♻️♻️
Mostrar todo...
🔋🔋🔋ዛሬ ከተመከርኩት 👩‍⚖የ23 ዓመት ወጣት ነች።የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በጥሩ ሁኔታ ካጠናቀቀች በኃላ የኮሌጅ ትምህርቷን ለመከታተል ወደ ተመደበችበት ክፍለሀገር ከሄደች አራት አመት ሆኗታል። 👉ለአባትና እናቷ ብቸኛ ልጅ በመሆኗ ቤተሰቦቿ ለመልቀቅ ተቸግረው ነበር።ይባስ ብሎ ከነበረበት የገንዘብ እጥረት የተነሳ ለትምህርት ከሄደች ጀምሮ ለአራት አመታት ሳትጠይቃቸው ነው የቆየችው።እርሷም ቢሆን የሄደችበት ቦታ በፍጹም አልተሰማማትም ነበር። 🎓በመጨረሻም በጥሩ ውጤት ተመርቃ ከአራት አመታት በኃላ መጣች።ሰፈሯ ግቢዋና የምትተኛበት መኝታ ቤቷ ሳይቀር ናፍቋታል።ከጓደኞቿ ጋር ከተሳፈረችበት አውቶብስ ወርዳ ከእነርሱ ጋር ከተለያየች በኃላ እቤቷ ለመድረስ ልቧ ቸኩሏል።እቤት ስትገባ አባቷ ስራ እናቷ ደግሞ ማሕበራዊ ጉዳይ ስለነበራቸው አላገኘቻቸዉም። 🍂🌴🌱ገና ግቢ ውስጥ ስትገባ ትኩረቷን የሳበው በግቢ ውስጥ የተተከሉት አትክልቶች ናቸው።በተለይ ደግሞ አንድ እጅግ ውብ የሆነ አበባ አየችና አበባውን ለማሸተት በጣም ጓጓች። 🌺🌸🥀🌻ወደ አበባው በመጠጋት በርከክ ብላ ለማሸተት ስትሞክር ከአበባው መዓዛ ይልቅ ለአበባው ልምላሜ ተብሎ አፈሩ ላይ የተደፋው ፍግና የተለያየ የተፈጥሮ ማዳበርያ ጠረን አፍንጫዋን ሰነጠቀው። 😡😡😡ተበሳጨች!እንዴት ይህንን የመሰለ ውብ አበባ እንደዝህ ባለ አስቀያሚ ቦታ ላይ ይተክሉታል?በማለት ለብቻዋ ካልጎመጎመች በኃላ አበባውን ነቅላ ከጠራረገች በኋላ መኝታ ቤቷ ወስዳ አልጋዋ አጠገብ በሚገኘው አነሰተኛ ቆርቆሮ አፈር ሞላ ሞላ አድርጋ ተከለችው። 👨‍👩‍👦ቤተሰቦቿ መጥተውና ናፍቆታቸውን ከተወጡ በኃላ ቀናት አልፋ።አንድ ቀን አባት አትክልት ሊያጠጣ ወጣ ሲል ያንን ውብ አበባ ያጣዋል።ነገሩን ሲያጣራ ልጁ ያደረጋቸውን ገለጠችለት።"እስት አበባውን አሳይኝ"ሲላት ወደ ክፍሏ ወስዳ ስታሳየው አበባው ጠውልጓል። ❓ነገሩ ቢያሰደነግጣትም"ይህንን የመሰለ አበባ ለምን ጥሩ ያልሆነ ቦታ ይተከላል ብዬ ነበረ ያመጣሁት"አለችው።"አየሽ"አላት አባቷ"አበባው የተተከለበት ቦታ ምንም የሚሸትና የማያምር ቢሆንም እንኳን ለአበባው እድገት ወሳኝ ቦታ እሱ ነው። 🔦ለጊዜው የሚመቸውን ቦታ ሰጥተሸው አበባው የተፈጠረለት ግሩም መዓዛ የመሰጠት ዓላማ ከምበላሸበት ለጊዜው በማይመች ስፍራ ሆኖ ነገ ውብ ቢሆን ይሻለዋል"።ከዚያም ጨመር አረገና"በነገራችን ላይ የሰው ልጅ ሕይወትም ሁኔታ እንደዝሁ ነው። 📝የራስሸን የትምህርት ሁኔታ ተመልከችው።ስትሄጂ ደስተኛ አልነበርሸም በዚያም የነበረው ሁኔታ አልተሰማማሸም ነበር ሆኖም አሁን ያለሸበት ደረጃ ለመድረስ ግን በዚያ ሁኔታ ማለፍ ነበረብሸ"። 👉ከማንኛውም ምቹ ነገር በፊት አለመመቸት አለ።ከማንኛውም ትግል በኋላ ደግሞ እረፍት አለ። 👉ይህ የማይለወጥ የሕይወት ሕግ ነው። ይቀላቀሉን 👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍 t.me/zelalemzeleke t.me/deliciouslifezz
Mostrar todo...
ዛሬ ምን ተመከርኩኝ?

በውስጥ መስመር ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ ለማቅረብ t.me/zelalemzel ንኩትና ፃፉልኝ

Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.