cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

✞Semayawi~tesfa✞

Semayawi~tesfa 👉የዚህገጵዋናአላማ:-መልእክቶች:መጽሀፍቶች:ትምህርቶች:የቅዱሳን ታሪኮቻቸው እንዲሁም ሌሎችንም በተዘጋጁበት ቋንቋ ጥራት እና መጠን ሁሉ በ1ቦታ እንዲገኙ ለማድረግ ነው◈

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
189
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

††† እንኳን ለቅዱስ አባ ሞይስስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ አባ ሞይስስ ጻድቅ ††† ††† ቅዱሱ በኋላ ዘመን ከተነሱ አበው አንዱ ሲሆን ትውልዱ: ነገዱ ከግብፅ ነው:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ ቢሆንም ክርስቲያኖች ጠንካሮች ነበሩ:: አባ ሞይስስ ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: ገና በልጅነት ወደ ትምህርት ቤት ገብቷል:: ††† የዘመኑ ትምሕርት ሁለት ወገን ሲሆን 1ኛው የሃይማኖት ትምሕርት: 2ኛው ደግሞ ፍልስፍና ነበር:: የጻድቁ ምርጫው የቤተ ክርስቲያን ትምሕርት ነበርና ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል:: እንደሚገባ ተምሮ ስለ ነበርም ዲቁናን ሹመውት ተግቶ አገልግሏል:: ከጥቂት ዘመናት በኋላም በተሻለው ጐዳና እግዚአብሔርን ሊያገለግል ተመኘ:: ይህቺን ዓለምም ይንቃት ዘንድ ወደደ:: መልካም ምኞትን መፈጸም ለእግዚአብሔር ልማዱ ነውና የልቡናውን ተምኔት ፈጸመለት:: ከከተማ ወጥቶ: ቁራጭ ጨርቅ ለብሶ ገዳም ገባ:: በዚያም በረድእነት ያገለግል ገባ:: በፍጹም ልቡ በትሕትና እግዚአብሔርን ደስ አሰኘ:: በጉብዝናው ወራት ይህንን መርጧልና:: ገዳሙንም ሲያገለግል ዕረፍትም አልነበረውምና በመነኮሳት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ነው:: ከጊዜም በኋላ "በቅተሃል" ብለው አበው ከአሞክሮ ወደ ምንኩስና: ከምንኩስና ወደ አስኬማ አሸጋግረውታል:: እርሱም ለአሥራ ስምንት ዓመታት አገልግሎቱን ሳያስታጉል: ወጥቶ ወርዶ ገዳሙን ረድቷል:: በእነዚህ ጊዜያት በጸሎት: በጾምና በስግደት ይጋደል ነበር:: በጠባዩም ትእግስትን: ትሕትናን: ተፋቅሮን የሚያዘወትር ነበር:: ጐን ለጐንም ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ይፋጠን ነበር:: በዘመኑ የግብፅ ፓትርያርክ አባ ሚካኤል ይባሉ ነበር:: አውሲም በምትባል አውራጃ ኤጲስ ቆጶስ ዐርፎባቸው "ማንን ልሹም" እያሉ ይጨነቁ ነበርና እግዚአብሔር ስለ አባ ሞይስስ ገለጠላቸው:: አባ ሚካኤልም "ለሕዝቤ የሚጠቅም መልካም እረኛ አገኘሁ" ብሎ ደስ አለው:: ጊዜ ሳጠፋም እርሱን አስጠርቶ "ተሾም" አለው:: አበው ትሕትና ሙያቸው ነውና "አይቻለኝም: ተወኝ ይቅርብኝ" ሲል መለሰ:: አባ ሚካኤል ግን "የምሾምህ መቼ በሰው ፈቃድ ሆነና: በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ" ብሎ ዕለቱኑ ሹመውታል:: እርሱም የአውሲም ጳጳስ ሆኗል:: ቅዱሱ አባ ሞይስስም ወደ ሃገረ ስብከቱ ሔዶ አገልግሎቱን ጀመረ:: በጵጵስና ዘመኑ እንደ ከተማ ሰው መኖርን: የሥጋ ምቾትን አልፈለገምና ጠባቡን መንገድ መርጧል:: በገዳም ሲሰራው ከነበረው ተግባር መካከል ያቋረጠው አልነበረም:: ከብቃቱ የተነሳ ለወደፊት የሚደረገውን ያውቅ ነበር:: እርሱ የተነበየው ሁሉ ተፈጽሟልና:: ሕዝቡን ይመራቸው ዘንድም ተግቶ ያስምራቸው ነበር:: ዘወትርም ከክፋት: ከኃጢአት ይጠብቃቸው ዘንድ ይጸልይላቸው ነበር:: ያዘኑትን ሲያጽናና: በደለኞችን ሲገስጽ ዘመናት አለፉ:: አንድ ወቅት ላይም ስለ ሃይማኖቱ ታሥሮ በረሃብ ተቀጥቷል: ግርፋትንም ታግሷል:: ጻድቁ ጳጳስ አባ ሞይስስ እንዲህ ተመላልሶ የሚያርፍበት ቀን ቢደርስ ሕዝቡን ሰበሰባቸው:: "እኔ ወደ ፈጣሪዬ እሔዳለሁና ሃይማኖታችሁንና ቤተ ክርስቲያንን ጠብቁ" ብሏቸው በትእምርተ መስቀል አማትቦ ዐረፈ:: ምዕመናንም በብዙ እንባና ምስጋና ቀብረውታል:: ከተቀደሰ ሥጋውና ከመቃብሩም ብዙ ተአምራት ታይተዋል:: ††† አምላከ ቅዱሳን ከቅዱሱ አባት በረከት ይክፈለን:: ††† ነሐሴ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ሞይስስ 2.ቅዱስ አብጥልማዎስ 3.ሦስት መቶ ሰማዕታት (የቅዱስ ፋሲለደስ ማኅበር) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ያሬድ ካህን 2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት 3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና 4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ 5.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት ††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" ††† (ሐዋ. ፳፥፳፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Mostrar todo...
""✝ የጾመ ፍልሠታ ትምህርት✝  "" ወላዲተ  አምላክ በገድለ ጻድቃን ኢትዮጵያውያን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ  2011  ክፍል  9⃣  ቀን ፲(10)         ❇️መልከአ ኤዶም ትርጓሜ❇️ ✝በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ ✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር። " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn 🛑የ2011
Mostrar todo...
✝እንኳን አደረሳችሁ!✝ ✝ከፋሌ ባሕረ ተከዚ አቡነ ዓቢየ እግዚእ! ☞መንስኤ ሙታን ☞ፈዋሴ ዱያን ☞መምህር ዘበአማን ☞ምዑዝ ከመ እጣን . . . ❀ተከዜን በየብስ የተሻገራት፥ ፱፻፵፩ አሕዛብን ያጠመቀ፥ ጎንደርን ከአራዊት ይታደጋት ዘንድ ቃል ኪዳንን የተቀበለ! በረከቱ ይደርብን! (ስዕሉ ከጥንታውያኑ አንዱ ነው) https://t.me/zikirekdusn
Mostrar todo...
✝✝✝ እንኳን ለቅዱሳን #ማኅበረበኲር ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ ✝✝✝ ☞ማኅበረ በኲር (ዕብ. ፲፪:፳፫) ማለት ከዓለም ፍጥረት እስከ መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ድረስ የተነሱ/የሚነሱ ቅዱሳን ሁሉ የጋራ መጠሪያ ነው፡፡ ☞እነዚህም አበው፡ ነቢያት፡ ሐዋርያት፡ ጻድቃን፡ ሰማዕታት፡ ደናግል፡ መነኮሳት፡ ባሕታውያን፡ ሊቃውንት፡ ጳጳሳት፡ ካህናት፡ ዲያቆናት፡ ነገሥታት እና ምዕመናን ናቸው፡፡ ☞ታቦታቸው/ቤተክርስቲያናቸው ታች አርማጭሆ #ደብረመጉና (ሞጊና) ውስጥ ይገኛል፡፡ ☞ነሐሴ10 ደገኛ በዓላቸው ነው፡፡ <<< በረከታቸው በዝታ ትደርብን፡፡ >>> ✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊትጉባኤ ዘጎንደር✝ " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Mostrar todo...
††† እንኳን ለካህኑ ሰማዕት አባ ኦሪ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ ††† ††† ይህ ቅዱስ አባት የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ነው:: በዘመኑ (በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ክርስቲያን መሆን ብቻውን ለሞት እንደሚያበቃ ወንጀል ይቆጠር ነበር:: በጊዜው ክርስቲያን ከመሆን በባሰ መንገድ እረኛ ካህን ሆኖ መገኘት በጣም ከባድ ነበር:: ከመነሻውም ያን ጊዜ ክህነት የሚሰጠው በሕዝቡና በሊቀ ጳጳሱ ምርጫ ነበር እንጂ እንደ ዘንድሮ "እኔን ሹሙኝ" ማለት ልማድ አልነበረም:: ምዕመናንም እረኛቸውን ሲመርጡ በጉቦ: በዝምድና አይደለም:: በርትቶ የሚያበረታቸውን: ለመንጋው ራሱን አሳልፎ የሚሰጠውን ይመርጣሉ እንጂ:: ያልሆነ ሰው ለክህነት ቢመረጥ አንድም ክዶ ያስክዳል: ሲቀጥልም ለሕዝቡ መሰናክል መሆኑ አይቀርም:: በጊዜው (በዘመነ ሰማዕታት) የነበሩ ካህናት የቤት ሥራቸውም ማስተማር ብቻ አልነበረም:: በድፍረት በምዕመናን ፊት አንገታቸውን ለሰይፍ መስጠት ይጠበቅባቸው ነበር እንጂ:: ይህንን በገሃድ መፈጸም ከቻሉ አበው አንዱ ደግሞ አባ ኦሪ ቀሲስ ናቸው:: ቅዱሱ ተወልደው ባደጉባት ሃገረ ስጥኑፍ (የግብፅ አውራጃ ናት) መጻሕፍትን የተማሩ: ተወዳጅ እና ደግ ሰው ነበሩ:: አባ ኦሪ ገና ከወጣትነት ቀዳሚ ግብራቸው መንኖ ጥሪት (ምናኔ) ነበር:: በንጽሕናቸው ደስ የተሰኙ ምዕመናንም "ቅስና ተሹመህ ምራን: አስተምረን::" ቢሏቸው አበው ውዳሴ ከንቱን አይፈልጉምና "አይሆንም" አሉ:: ነገሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረና አባ ኦሪ ቅስናን ተሹመው ያገለግሉ ገቡ:: ሕዝቡን በማስተማር: በመምከር: ደካማውን በማጽናት ብዙ ደክመዋል:: ከቅድስናቸው የተነሳ ቅዳሴ ሊቀድሱ ሲገቡ ጌታችን በገሃድ ይገለጥላቸው ነበር:: ሠራዊተ መላእክትም ከበው ይነጋገሯቸው ነበር:: ሥጋውን ደሙን በማቀበልም ተግተው ዘመናት አለፉ:: ቆይቶ ግን ያ በዜና ይሰሙት የነበረ መከራ (ሰማዕትነት) በደጃቸው ደረሰ:: በጊዜው ብዙ ሰው በሰማዕትነት አለፈ:: አባ ኦሪም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ገብተው ስለ ራሳቸውና ሕዝቡ ጽናትን: ደኅንነትን ለመኑና ከቤተ ክርስቲያን ወጡ:: በቀጥታ የሔዱትም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምሥክርነት አደባባይ) ነበር:: በመኮንኑ ፊት ቀርበው "ክርስቶስ አምላክ: ፈጣሪ: የሁሉ ጌታ ነው:: የእናንተ ጣዖት ግን ጠፊ: ረጋፊ: ወርቅ: ብር: እንጨትና ድንጋይ ነው::" ሲሉ በድፍረት ተናገሩ:: መኮንኑም ከአነጋገራቸው የተነሳ ተቆጥቶ ሥቃይን አዘዘባቸው:: ወታደሮቹ ይሆናል ያሉትን ማሰቃያ ሁሉ አባ ኦሪ ላይ ሞከሩ:: በኋላም ወደ ጨለማ እሥር ቤት ወስደው ጣሏቸው:: በእሥር ቤት ውስጥም ድውያንን ፈወሱ: ተአምራትን ሠሩ:: ይሕንን ዜና የሰሙ አሕዛብ ብዙ ድውያንን ሰብስበው መጡ:: ቅዱሱም ሁሉን በጸሎታቸው ፈወሱ:: በዚህ ምክንያትም ብዙ አሕዛብ ወደ ክርስትና መጥተዋል:: በክርስቶስ አምነውም ለክብር በቅተዋል:: ቅዱሱንም ከእሥር ቤት አውጥተው ብዙ ካሰቃዩዋቸው በኋላ በዚህች ቀን ገድለዋቸው ሰማዕትነትን አግኝተዋል:: በአክሊለ ጽድቅ ላይ አክሊለ ካህናትን: በአክሊለ ካህናትም ላይ አክሊለ ሰማዕታትን ደርበዋል:: ††† አምላከ ቅዱሳን በአባቶቻችን ጽናት ያጽናን:: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን:: ††† ነሐሴ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ (ሰማዕት) 2.አባ ጲላጦስ ሊቀ ጳጳሳት ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ) 3.ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) ††† "ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" ††† (፩ቆሮ. ፲፥፲፬-፲፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Mostrar todo...