cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

አቡ ሱሀይል

ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢِ "ﺍﻗْﺮَﺃْ ﺑِﺎﺳْﻢِ ﺭَﺑِّﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺧَﻠَﻖَ" "አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታ ስም" አል ዐለቅ ምእራፍ/1 በዚህ ገፅ ላይ የተለያዩ ኢስላማዊ መልእክቶችና፣በተለያየ ዘርፍ የሚሰጡ ት/ቶችን በድምፅና በቪዲዮ ያገኙበታል።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
2 022
Suscriptores
+324 horas
+77 días
+5030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የዐቂደቱ–ጠሓዊያ፟ህ ደርስ ሊጀምር ነው፣ተቀላቀሉ👇👇👇 https://t.me/almaewacharity
Mostrar todo...
አል መእዋ ኢስላማዊ በጎ አድራጎት ድርጅት

ይህ የአል መእዋ ኢስላማዊ በጎ አድራጎት ድርጅት ግሩፕ ነው።

Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር መረጃ * በዛሬው እለት 9/11/16 በአአ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሸኽ ፈትሁዲን ሀጂዘይኑ አማካኝነት የጎሮ አንቢያእ መድረሳን በተመለከተ ስብሰባ የተጠራ መሆኑ ይታወቃል። ከአልዒምራን የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምህርት ተቋም ዋና ስራአስኪያጅ ኡስታዝ አስለም ዩሱፍ ፣ ኡስታዝ አህመድ ኢስማዒል ፣ኡስታዝ አንዋርአህመድ ፣ኡስታዝ ዓብዱልገኒይኸድር እና የአካባቢ ሽማግሌዎች የተገኙ ሲሆን ከምክር ቤቱ ሀላፊዎች ምክትል ፕሬዝዳንት ሸኽ ፈትሁዲን ሀጅ ዘይኑ ፣ ዋና ፀሀፊ ሸኽ ሁሴን በሽር ፣ ከስራ አስፈፃሚዎች ኡስታዝ ሀሺም ፣ ኡስታዝ ሀሰን ዓሊ እና የምክር ቤቱምክትል ስራ አስኪያጅ ጋር በተደረገ ውይይት የሚከተሉት ሶስት ውሳኔዎች ተላል ፈዋል 1ኛ የአዲስ አበባ መጅሊስ በፈረሰው የመድረሳ ክፍሎች ምትክ ለተማሪዎች  መማሪያ እና ማረፊያ የሚሆኑ ክፍሎችን ሰርቶ ያስረክባል። 2ኛ በቀጣይም  የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንትበተገኙበት ከአል ዒምራን  ተቋም የበላይ ሀላፊዎች  ጋር ውይይት በማድረግ የመድረሳው እጣፈንታ የሚወስን ይሆናል። 3ኛ የመድረሳው ሙዲር ኡስታዝ ኸድር ተማምን በተመለከተ  የአዲስ አበባ መጅሊስ ከመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር  ሀላፊነት ወስዶ  ያስፈታል። በቀጣይ የሚኖረውን የውሳኔ አፋፃፀም እየተከታተልን የምናሳውቅ ይሆናል።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
# መርሀ ህይወት ___ ኢማም አል ሻ፟ፊዒይ( ረ.ዐ) ስለ መሠረታዊ የግንኙነት መርህ ሲናገሩ፡- زِن مِن وَزَنكَ بِما وَزَنكَ وَما وَزَنكَ بِهِ فَزِنهُ مَن جا إِلَيكَ فَرُح إِلَيــهِ وَمَن جَفاكَ فَصُدَّ عَنهُ مَن ظَنَّ أَنَّكَ دونَهُ. فَاِترُك هَواهُ إِذَن وَهِنهُ وَاِرجِع إِلى رَبِّ العِبادِ فَكُلُّ ما يَأتيكَ مِنهُ በመዘነህ ልክ አንተም መዝነው የሰጠህን ቦታ መልሰህ ስጠው ወዳንተ ለመጣው ወደርሱ ሂድለት ፊቱን ላዞረብህ አንተም ዙርበት ከርሱ አሳንሶ ለተመለከተህ ድክመቱንና ስሜቱን ትተህ ወደ ሰዎች ጌታ፣ተመለስ ወዳ’ላህ ከርሱ ነውና፣ኹሉ ሚመጣህ <<<<<>>>>> እስልምና መጥፎን በበጎ መልሰህ፣ክፋትን በመልካም ገፍትረህ ከሌሎች ልቀህና ተሽለህ እንድትገኝ የሚያነሳሳ ሐይማኖት ከመሆኑም ጋር፣እንዲህ ያሉ ግብረ መልሶችን የሚሹ፣በአምሳያና በፍትሓዊነት ለግንኙነትህ ወሰን ልታበጅላቸው የሚገቡ፣አንዳንድ ሰዎች እንዳሉ እነዚህ ስንኞች ያመላክታሉ። አዎን! ትእግስትህን ፍርሀት፣እንዳላወቀ መሆንህን ሞኝነት፣ይቅር ባይነትህን እንደ ልምምጥ የሚቆጥር፤ፊት ስትሰጠው ቫዝሊን ሚለቀልቅህ፣ስትቀርበው ከርሱ ውጪ መኖር የማትመስለው በበዛበት ወቅት እንዲህ መሰሉን ቀይ መስመር ማስመር፣ድንበር ሳታልፍ ድንበር ማበጀትና፣በፊት ወደነበረት ቦታው መመለስ የግድ ነው፤አልያ የልብህ ትርፉ ጉዳት ነው። __ t.me/hamidabuhamid
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
#የዓሹራእ ፆም __   ያለንበትን(የሙሐረምን)ወር አስረኛ ቀን(ዓሹራእ)መፆም የተወደደና የላቀ ምንዳ እንደሚያስገኝ እንዲሁም ያለፈውን የአንድ አመት ወንጀል እንደሚያስምር ጠንካራ በሆኑ በነብያዊ ሀዲሶች ተገልፀዋል። ኢብኑ አባስ(ረዐ)የአላህ መልእክተኛ(ሰዐወ)መዲና ሀገር በመጡበት ሰዓት አይሁዶች የአሹራእን ፆም ሲፆሙ ተመለከቷቸውና ለምን እንደሚፆሙ ሲጠይቋቸው:ይህ ቀን በጎ ቀን ነው:አላህ(ሱወ)የኢስራኢል ልጆችን ከጠላቶቻቸው ያዳነበት ቀን ነው:ነብዩላህ ሙሳም ይፆሙት እንደነበረ ተናገሩ:በዚህ ጊዜ ነብዩ(ሰዐወ)እንደዛማ ከሆነ ከናንተ የበለጠ እኔ ለዚ የተገባሁ ነኝ በማለት:እሳቸውም ፆሙት:ሰዎችንም አዘዙ"። ይህ ቀን አላህ(ሱወ)ብዙ ተዓምራቶችን ያሳየበት ቀን ነው:አንባገነኑ ፊርዐውን ከነ ወታደሩ የሰጠመበት:የነብዩላህ ኑህ(ዐሰ) መርከብ ከዛ ከባድ ማዕበል በዃላ የተረጋጋችበት ቀን ነው:ስለዚህ ይህን ቀን በመፆም ምስጋናችንን እንግለፅ:ለኛም በዚ ሰዐት የናፈቀንን ፍቅር ሰላም አንድነትን እንዲሰጠንና:አዛ ያረገንን ጥላቻና ዘረኝነትን እንዲያነሳልን አስበን እንፁም.......ወዳጆቼ የምንም አይነት ችግር መፍትሄ ሚገኘው ከአላህዬ ነው:ወደሱ በመቅረብ:እሱን በማስደሰት ችግራቸን ይወገዳል:አልገራ ያለው ይገራል።       ይህን ቀን መፆም ሌላውና ትልቁ ትሩፋት ባሳለፍነው አመት ሰይጣንም ይሁን ነፍሳችን አሳስቶን የሰራናቸውን ወንጀሎች እንዲታበሱልን ያደርጋል:ይህን ታላቅ ብስራት ነብያችን(ሰዐወ)በሀዲሳቸው ገልፀውልናል።   በዚሁ አጋጣሚ ዘጠነኛውንም ቀን(ታሱዐእ) አያይዘን መፆም ይወደዳል:ነብዩ(ሰዐወ)እስከሚቀጥለው አመት አላህ ካቆየኝ ዘጠነኛውንም እፆማለው ብለው ነገር ግን በመሀል ሚቀጥለው አመት ሳይደርሱ ወደ አኼራ ሄዱ።    ኢማሙ ነወዊ(ረዐ)ዘጠነኛውን ቀን የምንፆምበት ምክንያቶች ሲጠቅሱ በመጀመሪያ ደረጃ እንደ ዋና ምክንያት ያስቀመጡት ከአይሁዶች ጋር ላለመመሳሰል ነው:እነሱ አስረኛውን ብቻ ነጥለው ስለሚፆሙ ማለት ነው። (ዓሹራእ) ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ማለት ነው፤ነገር ግን አስቀድሞ ከ9 ኛው አልያ አስከትሎ ከ 11ኛው ቀን ጋር መፆም ይወደዳል ____ # ለሌሎች አስታውሱ ! ማስታወስ ለምእመናን ይጠቅማል !
Mostrar todo...
📌 ነገር ወደ አለባለቤቱ ሲጠጋ …   በጠርዘኝነትና በጥላቻ አዕምሮው ሳይታወር፣እውነትንና እውነትን ብቻ ለሚሻ፣የተከተከበ ማስታወሻ!! __ “ ጉዳዩ ወደ አለባለቤቱ የተሰጠ ጊዜ፣የዓለምን ማብቂያ  ተጠባበቅ ” ____ ረሱለላ፟ህ ﷺ   ⭕️ ብቁ ሆነህ እንኳን ሹመትን አትፈልግ በሚል አስተምህሮ አድገህ፣ብቃት ሳይኖርህ ለሹመት እዚና እዛ መኳተን፣ አላማህ(ምላስህ እንደሚለፍፈው)ለዲን ሳይሆን ለግላዊ ጥቅምና የነፍሲይያን ፍላጎት ለማሟላት እንደሆነ በግልፅ ያሳብቃል፤ማንኛውም ሀላፊነት ከበስተጀርባው አላህ ፊት ተጠያቂነት እንዳለው ግን ቆም ብለን አስበነው እናውቃለን!!!    መቼስ ይህን የማይዘነጋ አዕምሮ ምንም እንኳን ብቁ ቢሆን የሀላፊነት ቦታውችን ተፈልጎ እንጂ ፈልጎ አይቀርብም፤ያው ይህ ሽሽት በሁሉም ሁናቴና ቦታ ላይ ሚተገበር ባይሆንም!!!   ግና  ብቁ ሳይሆኑ በምንም አይነት ሁኔታ  በሙስሊሞችን ጉዳይ ላይ ለመሾም መቋመጥ  አንድም ከስር ያገለግሉናል ብሎ ለታመነላቸው ማህበረሰብ ንቀት፣ሁለትም ለዲን ኻዲም(አገልጋይ) ሳይሆኑ ሃዲም(አፍራሽ) መሆንን ያስከትላል።   እውነት ኢስላምንና ሙስሊሙን ማህበረሰብ ማገልገል ዐለማው ያደረገ ሰው ብቁ ባልሆነበት ጉዳይ ላይ "እኔ ብቁ አይደለሁም" በማለት ለተገቢው አካል ማስረከብ ነው ያለበት፤ይህን ሳያደርግ ቀርቶ ብቁ ባልሆነበት ቦታ ላይ(ሊያውም ፈልጎት)መሾሙ ዐለማው ዲንን ማገልገል እንዳልሆነና ከበስተጀርባ ሌላ ግላዊ(ምድራዊ)ጥቅምን ማሳካት እንዳሰበ ነው ሚያመላክተው። ✅  ኢስላም ከሰሃባዎች ዘመን አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ብቃትን ያልቃል፤በየመስኩ ያሉ ልዩ ባልተቤትነትን ያከብራል፤ሰዪዳችን ﷺ ከናንተ መሀከል ስለ ሐላልና ሐራም አዋቂው እከሌ፣ስለ ውርስ ህግጋት አዋቂው እከሌ፣በቁርኣን አነባበብ ደግሞ በጣም የተካነው እከሌ፣ሰዎችን በሶላት መምራት ያለበት እንዲህ፣እንዲህ የሆነ ነው... እያሉ መጠቆማቸው ለምን ይሆን ብለን ስንጠይቅ ፤ለሁሉ ነገር ባልተቤት እንዳለውና በዛ ጉዳይ ላይ ጥልቅ እውቀትና ብቃት እንዳለው ያስረዳናል፤እናም ተራው ማህበረሰብ ለሚያስፈልጉት ማንኛውም ጉዳዮች በመንገዱ ላይ ያገኘውን ሁላ መጠየቅ እንደሌለበትም ያሳያል።    እስልምና በተዋረድ ከትውልድ ትውልድ የተላለፈውም በዚሁ አስተማማኝ መርሖ ነበር፤ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለዲኑ ይሰጥ ከነበረው ላቅ ያለ ቦታ ማንን መከተል እንዳለበት ጠንቅቆ ያጤናል፤ባልተቤቶቹንም ሲያገኝ ያከብራል፤ያሉትን ይሰማል፤በጠቆሙት ይጓዛል፤በመሰለኝና በደሳለኝ አይመራም፤በዚህ መልኩ ሁሉም ዘርፉን ለይቶ ለኢስላም አሻራውን ጥሎ አልፏል። ⛔️  ግና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ አካሄድ መስመሩን መልቀቅ ያዘ፤ዲን እንደ ዋዛ የሚያይ ማህበረሰብ ተፈጠረ፤ከዲኑ ይልቅ ለነፍሳዊ ዝንባሌያቸው ቅድሚያ የሚሰጡ ለእውቅናና ለክብር ውለው ያደሩ የዲን ነጋዴዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ፤ተራው(ዐዋሙ)ማህበረሰብም  ዳዒውን ኡስታዝ፣ኡስታዙን ሸይኽ፣ሸይኹን ሙፍቲ እያደረገ ነኝ ላለው ሁላ ነህ የሚል እውቀና መስጠትን ተያያዘው፤ብቁ ሳይሆን የግል ጥቅሙን በዚህ መንገድ ማስፈፀም የወሰነውም የነፍሲያ ባሪይ ሳይሆን ነህ ሲሉት፣አይ! እኔ ለዚህ ብቁ አይደለሁም በማለት ፈንታ ነህ ብሎ የፈረመለትን ሚስኪን ማህበረሰብ በደስታ ተቀበለ፤ያኔ ነው እንግዲ ትልቁ ውድቀት የጀመረው፤እውነተኛ ባልተቤቶች እየተገፉና ከማህበረሰቡ እየተቆረጡ እንደ ባዳ መታየት ጀመሩ፤ከነሱ ይልቅ ጥራዝ ነጠቁ አፈ ቀላጤ ይሰማ ጀመር፤የነሱ አመለካከትና አካሄድ እንደ ስህተት የሚቆጠር ሆነ።   ይህ ምን አይነት ማህበረሰብ ፈጠረ?!ብለን በሚዛናዊነት ስናስተውል፤የሀሳብ ልዩነትን የማያከብር፣ከገዛ ሙስሊም ወንድሙ ጋር እንኳን መኗኗር የተሳነው ፅንፈኛ፣ጠርዘኛ፣ገፊ የሆነ፤የዑለማእን ክብር የማያውቅ፤ለኢስላም ትልቅ ውለታ የዋሉ ቀደምት ሊቃውንትን የሚረግም፤እንደኔ ካላየህ እውር ነህ ብሎ የሚደመድም ጭፍን ማህበረሰብ፤ያለ እውቀቱ መተቸቱ ሳያሳፍረው በክብር ላይ የሚረማመድ .... ብቻ ትንሽ ወደዃላ ዘመን መለስ ብለን የምናገኘውን ወርቃማ፣ልበ ሰፊ፣አርቆ አሳቢ፣አቃፊ ሙስሊም ማህበረሰብን እንብዛም ማየት ተስኖን ያለንበት ተጨባጭ ላይ ነን .... አላህ ይድረስልን 🤲   ይህን ነባራዊ ሁኔታ ስታዘብ ብዙ ነቢያዊ ትንቢቶችን ያስታውሰኛል:– “ አንድ ጉዳይ ባልተቤቱ ወዳልሆነው ይሰጣል፣እውቀት እእየተነሳ መሀይምነት ይስፋፋል፣ሰዎች መሀይማንን መሪ አድርገው ይይዛሉ፣ያለ እውቀታቸው ተጠይቀው ጠመው ያጠማሉ .... የሚሉ ሐዲሶች እየተፈፀሙ እንዳሉ ይሰማኛል።😭    ብቻ አሁንም ጊዜው አረፈድምና ሁላችንም ቀድመን ነፍሳችንን ቀጥሎ ቤተሰቦቻችንና ትውልድን እንታደግ፤በጭፍን እየተጓዝንበት ያለውን መንገድ ቆም ብለን እንመርምር፤መልካም መናገር ባንችል ዝምታን እንምረጥ፤ለእውነት መቆም ቢያቅተን ለውሸት አናጨብጭብ፤ከምንም በስተፊት አላህ ፊት ስንቆም በማናፍርበት አቋም ላይ እንሁን!!!👌 _ ወላሁ አዕለም 🙏
Mostrar todo...
#ጭፍን ለሆነ መንጋ ሺ ማስረጃዎች ምንም ናቸው !!!
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የፊታችን ሰኞ (ሐምሌ/8) የሚጀምር ይሆናል፤ሊንኩን በመጫን ወደ ቻናሉ ይቀላቀሉ፤ለሌሎችም በማጋራት የመልካምነት አሻራዎን ያሳርፉ። https://t.me/almaewacharity
Mostrar todo...
# ሐስቡነላ፟ሁ ወኒዕመል–ወኪል ዲንን ያገለግላል፣ሙስሊሙን ማሕበረሰብ በፍትህ ያስተዳድራል፣ኢስላማዊ ተቋማትን ያለ ልዩነት ያግዛል ብለህ የመረጥከው … ይኸው የቁርኣን መዳሪሶችን እያፈረሰ፣ልጅነታቸውን መስዋዕት አድርገው፣ከተለያዩ የሀገራችን ክልሎች የመጡ፣የነገው ትውልድ ተስፋ የሆኑ የዲን ተማሪዎችን እየበታተነ፣ትውልድ አና፟ፂ ኡስታዞችን እያሳሰረ ይገኛል !!! ማያልፍ የለም፤ኹሉንም አላህ ይመለካታል፤የጊዜ ጉዳይ እንጂ ባለው ጊዜያዊ ስልጣን ተመክቶ የበደል አለንጋውን የመዘዘ ኹላ የአላህን አፀፋዊ ምላሽ በቅርቡ ያገኛል !!! #ሁሌም ከሐቅና ከፍትሕ ጎን የቆመ በሁለቱም ዓለም ይድናል !!!
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.