cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Peka Tube - ፔካ ቲዩብ

The Great source of Knowledge. You Tube => Youtube.com/@haile12 Telegram Channel 2 - t.me/PekaTube InboX - @HailemichaelDT With Hailemichael Desalegn T.me/EthiopeTowoderos

Mostrar más
Etiopía2 661Amárico2 445La categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
3 888
Suscriptores
Sin datos24 horas
-277 días
-9230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የክሊዮፓትራ ያልተሰሙ 6 አስገራሚ እውነታዎች https://youtu.be/eFoC7ZRw3NU
Mostrar todo...
የክሊዮፓትራ ያልተሰሙ 6 አስገራሚ እውነታዎች - PEKA Tube

የክሊዮፓትራ VII ያልተሰሙ 6 አስገራሚ እውነታዎች - PEKA Tube SUBSCRIBE

https://www.youtube.com/c/HailemichaelDT

Join us on: 𝚃𝚎𝚕𝚎𝚐𝚛𝚊𝚖 =

https://t.me/EthiopeTowoderos

PEKA Tube with Hailemichael Desalegn #Hailemichaeldt #cleopatra #history #ethiopia #ethiopian

ከ1000 በላይ የብራና መጻሕፍት በነጻ የምታገኙባቸው 5 ዌብሳይቶች https://youtu.be/n2g1peyppp8
Mostrar todo...
ከ1000 በላይ የብራና መጻሕፍት በነጻ የምታገኙበት 5 ዌብሳይቶች - Ancient Ethiopian Manuscripts pdf | PEKA Tube

ከ1000 በላይ የብራና መጻሕፍት በነጻ የምታገኙበት 5 ዌብሳይቶች Ancient Ethiopian Manuscripts pdf 📚Link: ◾ British Library:

https://www.bl.uk/manuscripts/BriefDisplay.aspx

◾ Gallica:

https://gallica.bnf.fr/services/engine/search/sru?operation=searchRetrieve&version=1.2&maximumRecords=15&page=2&query=(gallica%20all%20%22ethiopien%22)%20and%20(dc.type%20all%20%22manuscrit%22)

◾ Princeton University Library:

https://dpul.princeton.edu/msstreasures/browse/ethiopic-manuscripts

◾ Cambridge Digital Library:

https://cudl.lib.cam.ac.uk/collections/ethiopianmanuscripts/1

◾ UCLA Library Digital Collections:

https://digital.library.ucla.edu/catalog/ark:/21198/zz0009gx3x

Join us on: 𝚃𝚎𝚕𝚎𝚐𝚛𝚊𝚖 =

https://t.me/EthiopeTowoderos

PEKA Tube with Hailemichael Desalegn #Hailemichael #Ethiopia #ancient

Q1: የላይኛውንና የታችኛውን ግብጽ አንድ አድርጎ በ3100 BCE የገዛ ፈርዖንAnonymous voting
  • Menes (Narmer)
  • Akeneten
  • Khufu
  • Amenhotep III
0 votes
📌 የጥንታዊት ግብጽ ታሪክ - ለጀማሪዎች ሙሉ ትምሕርት 👉Size: 400 KB 👉Page: 6
Mostrar todo...
የጥንታዊት_ግብጽ_ታሪክ_ለጀማሪዎች_by_Hailemichael_D.pdf3.70 KB
📌 የኑሮ ደረጃዎች/ የዕለት ተዕለት ኑሮ በጥንታዊ ግብጽ በጥንታዊ ግብጽ የነበሩትን የኑሮ ደረጃዎች በ6 ከፍለን ከታችኛው ደረጃ እስከ ላይኛው ጫፍ እንመልከት። 1. ባርያና አገልጋይ(Slaves & Servants)፡ ከደረጃው ታች ላይ የምናገኛቸው ሲሆን ባርያዎች ተብለው የሚጠሩት በዋናነት የጉልበት ሥራ ላይ ልክ እንደ ፒራሚድ ግንባታ... ላይ የሚሳተፉ ሲሆን አገልጋዮች ደግሞ ከሩቅ ለፈርዖኑ የተለያዩ ግብርና ገጸበረከቶችን ይዘው የሚመጡትን እንግዶች የሚቀበሉና የሚያስተናግዱ ናቸው። እኒህ እንግዶች በአቅራቢያ ከሚገኙ ግዛቶች የሚመጡ ሲሆን ይዘዋቸው ከሚመጧቸው ገጸበረከቶች ውስጥ መዳብና ተርክዌዝ ከሲና’ይ፤ ወርቅ፣ መዳብና አሜቴስጢኖን ከኑቢያ፤ ወይንና ቅባቶች ከክሬት፤ ጨው፣ ተምርና የቀንድ ከብቶች በአቅራቢያ ከሚገኘው በርሃ...... ተጠቃሽ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም አገልጋዮች ቅባትና የተነጠሩ ቅቤዎችን ከእንግዶች አናት ላይ ያደርጋሉ። ይህም እንግዶችን ለማቀዝቀዝና መልካም መዓዛ እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ ይታመናል። 2. ገበሬዎች(Farmers)፡ እኒህ የአባይን ጎርፍ የሚመጣበትን ጊዜ ጠብቀው በየዓመቱ መልካም ፍሬ እየዘሩ ጥንታዊ ግብጽን በግብርናው ዘርፍ የያዙ ናቸው። መሬቱ በጎርፍ በሚሞላበት ጊዜ የፒራሚድ ግንባታ ላይ እንደሚሳተፉ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ። 3. ሰአሊዎችና ጠቢባን(Craftsman)፡ እኒህ ሰዎች የተለያዩ ሃይውልቶችን፣ ስዕሎችን፣ ቅርጻ ቅርጾችን እንዲሁም ለመገልገያ እንደ ማሰሮ የሚሆኑ እቃዎችን፤ በአጠቃላይ የእጅ ሥራዎች ላይ የሚሳተፉ ናቸው። 4. ጸሐፊዎች(Scribers)፡ እኒህ ሰዎች የጽሕፈት ስራዎች የሚሳተፉ ሲሆኑ ጥንታዊ ግብጽን እንድናውቅ ከረዱን የዘመኑ ነዋሪዎች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው። ይህም የምልክት/ስዕላዊ የጽሕፈት ዘዴ የሆነውን ሂሮግሊፍስ(Hieroglyphs) በመጠቀም በፓፒረስ(Papyrus) ላይ የታዘዙትን ጽሑፍ፣ መልእክት፣ ዜና መዋዕል ይጽፋሉ። • ሂኖግሊፍስ(Hieroglyphs)፡ ይህ ስዕላዊ የአጻጻፍ ዘዴ ጥንታዊ ከሚባሉት ውስጥ ተጠቃሽ ሲሆን ጥንታዊ ግብጻውያን ለግብር ምዝገባ፣ በመቃብርና በግድግዳዎች ላይ መልዕክትን ያስቀምጡበታል። በጥንታዊ ግብጻውያን ሃይማኖትም ይህን የጽሕፈት ዘዴ የጥበብና የጽሕፈት አምላክ የሆነው ቶት(Thoth – god of wisdom and writing) እንደሰጣቸው በሊቃውንቱ ዘንድ ተመዝግቦ ይገኛል። በዘመናችን በተሻለ ሁኔታ የተተረጎመው የሮሴታ ድንጋይ(Rosseta Stone) ከተገኘ በኋላ ነው። • ፓፒረስ(Papyrus)፡ ይህ መጻፊያ ፓፒረስ ተብሎ ከሚጠራ የዛፍ ልጥ ለጽሕፈት ተዘጋጅቶ የሚወጣ ነው። ይህ ዕፅ በሳይንሳዊ መጠሪያው Cyperus papyrus ሲባል ፋሚሊው Cyperaceae ሲሆን በአባይ ወንዝ ዳርቻዎች ላይ የሚበቅል ተክል ነው። በዚህ ልጥ ላይ ብዙ የጥበብ፣ የሃይማኖት፣ የታሪክ... መጻሕፍትን የጻፉ ሲሆን በዋናነት ግን የሚታወቀው በርካታ ገጾች ያሉት የሙታን ግንዘት ጸሎት መጽሐፍ አሁን ድረስ ዓለምን የሚያነጋግር ነው። 5. ቄሶች(Priests)፡ እኒህ በማኅበረሰቡ በጣም የሚከበሩና የሚፈሩ ሲሆኑ በፈርዖኑ ዘንድም ትልቅ ቦታ ይዘጣቸዋል። አንዳንድ ነገሥታትም መንፈሳዊውንም ዓለማዊውን አስተባብረው ይዘው ቄስና ፈርዖን ነበሩ። በርካታ አማልክትን የሚመለኩበትን የጥንታዊ ግብጽን ሃይማኖት በየአማልክቱ ቤተመቅደስ ውስጥ በመግባት ዕጣንና ከርቤን ያጥናሉ። እንዲሁም ከምድር በኋላ ላለው ሕይወት በር ከፋች ነው ተብሎ ለሚታመነው የሙታን የግንዘት ሥርዓት ላይ አስገራሚ የሚባል ጥበብና እውቀትን ተጠቅመው ክንዋኔዎችን ይፈጽማሉ፤ በእጽዋትና ማዕድናት ጥበብም ሳይቀር የተካኑ እንደሆኑ መረጃዎች ይናገራሉ። 6. ፈርዖኖች(Pharaohs)፡ እኒህ ነገሥታት ናቸው፤ ግዛታቸውን በእጃቸው የያዙ የሚፈሩ፣ የሚከበሩና መለኮታዊ ኃይል እንዳላቸው የሚነገርላቸው ናቸው። 📌 የጥንታዊ ግብጻውያን ታላላቅ ሥራዎች ጥንታዊ ግብጽን በርካታ ሊቃውንት ግሪካውያን ፈላስፎችን ጨምሮ የትምሕርት ሀገር(Land of learning) ብለው ይጠሯት ነበር። በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች ከዘመናቸው ቀድመው ጥናቶችን የሰሩ ሕዝቦች ነበሩ። በጽሕፈት፣ በሥነጠፈር፣ በሕክምና፣ በልዕለአካላዊ ጥናቶች ተሳትፈዋል። በጥቂቱ እንመልከት። 👉 በጽሕፈት(Literature)፡ ቅድም እንደጠቀስኩት ከዛፍ ልጥ ፓፒረስ አዘጋጅተው ሂሮግላፊስ በተባለ የጽሕፈት ሥርዓት ጽሕፈቶችን ጽፈዋል፤ ይህ በሰው ልጅ የልውጠት ታሪክ ውስጥ ዋና ስልጣኔ ነው። 👉 ሥነ ጠፈር(Astronomy & Astrology)፡ በርካታ የጠፈር አካላትን በልየታ በመመርመር መረጃዎችን የጻፉ ሲሆን በዋናነት ጊዜን ሚለዩበት ሳይረስ ኮከብ ተጠቃሽ ነው። ሳይረስ(Sirus) - በውሻ የሚመሰል ኮከብ(The Dog Star) ሲሆን፣ ከአባይ ጎርፍ መምጫ ጊዜ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ይታያል፤ በዚህም ለይተው የአባይን ጎርፍ መምጫ ይተነብዩበት ነበር። 👉 ሕክምና(Medicine)፡ በሕክምናው ሳይንስ ዘርፍ ጥንታዊ ግብጻውያን በርካታ ጽሕፈቶችን ጽፈዋል፤ ከነዚህ ውስጥም:- ምን ዕፅዋት ለምን በሽታ እንደሚሆን እንደሌሎቹ ጥንታዊ ሕዝቦች ሁሉ መዝግበው ከዘመናቸው ቀድመው ተራቀውባቸዋል። ለዕለት ተዕለት በሽታዎች መድኃኒቶችን ይጠቀሙ ነበር፤ ይህም ጥንታዊ የእጽዋት እውቀትን(Herbalism) ይጠቀሙ እንደነበር ያስረዳናል። ይህንን የሕክምና መዛግብትንም በኋላ ዘመን ላይ ጥንታዊ ግሪካውያንና ሮማውያን እንደተጠቀሙት ታሪክ ይመሰክራል። ሌላ በዚህ ምድብ ውስጥ መድበን ማየት የምንችለው መሚን ነው። • መሚ(Mummy)፡ ጥንታዊ ግብጻውያን የሞተን ሰው አስክሬን በማድረቅ ሳይበሰብስ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ የሚያደርጉበት ነው። በጥንታዊው ሃይማኖት መሚን የሙታን አማልክት የሆነው አኑቢስ(Anubis – god of the dead) እንደፈለሰፈውና ከምድር በኋላ ላለው ሕይወት በር እንደሆነ ይነገራል። በዚህ ሂደት ውስጥ ጥልቅ የሆነ የሰውን ልጅ የአካል ክፍሎች እውቀት ይጠቀሙ እንደነበር መገንዘብ ይቻላል። ከመሚፊኬሽን በፊት የሚበሰብሱ የሰውነት አካላት(organs) በቀዶ ጥገና ወጥተው በ4ቱ የካኖፒክ¬¬¬¬¬¬ ጃሮች(Canopic Jars) ውስጥ ይቀመጣል። መሚፊኬሽን(Mummification) በአጠቃላይ ከ2-3 ወራትን ይጨርሳል። እያንዳንዱን ሂደት እንይ ብንል ለብቻው ረጅም ቦታን ስለሚይዝብኝ እስከዚህ ከጻፍኩ በቂ ነው። 📌 ውድ የፔካ ቲዩብ ( t.me/EthiopeTowoderos or t.me/PekaTube ) ቤተሰቦቼ ለዛሬው ይህንን ታሪክና እውቀት አጋርቻችኋለሁ፤ ይህ ጽሑፍ የጥንታዊ ግብጽን ታሪክ ለማጥናት እንደጅማሮ መግቢያ ይሆናል ብየ አምናለሁ። ወደ ውስጥ እያንዳንዱን ጉዳዮች ስታጠኑ ግን በጣም ሰፊ ታሪክ፣ እውቀትና ጥበብ እንደምታገኙበት አምናለሁ። ተጻፈ/Written by፦ Hailemichael D.( @hailemichaeldt )
Mostrar todo...
📌 የጥንታዊት ግብጽ ታሪክ ለጀማሪዎች - ሙሉ ትምሕርት...By Hailemichael D. 👉 በዚህ ጽሑፍ ስለ ጥንታዊ ግብጻውያን ከብዙ በጥቂቱ ዋና ዋና የሚባሉ ነጥቦችን እንመለከታለን። ጥንታዊ ግብጻውያን ወይም ጥንታዊት ግብጽ ስንል ወደ አዕምሯችን በርካታ ጉዳዮች ይመጣሉ። ከነዚህም ውስጥ ፒራሚዶች፣ መሚዎች፣ ታላላቅ ፈርዖኖች፣ ሲፊኒክስ፣ ብሉ ናይል(ኒል)፣ የግብጽ አማልክት .... ተጠቃሽ ናቸውና አንድ በአንድ እንያቸው። 👉 ይህ ስልጣኔ መሠረቱን ያደረገው በአባይ ወንዝ ላይ ሲሆን ይህንንም ብዙ አጥኝዎች ይደነቁበታል። “ግብጽ የአባይ ሥጦታ ናት፤ አባይም የግብጽ ሥጦታ ነው።” “ያለ አባይ ግብጽ የሚባል ሥልጣኔ አይኖርም ነበር” (There would be no Egypt without the Nile) ይህም ብቻ ሳይሆን ሃፒ (አፒስ, Hapi-The god of the Nile) ብለው ለሚጠሩት የአባይ ወንዝ አምላክ ሳይቀር ስለ አባይ በጸሎቶቻቸው ምስጋናን እንዲ ብለው ያቀርባሉ “Hail to you, O Nile, who flows from the Earth and comes to keep Egypt alive…” 👉 በመልክአ ምድራዊ ይዞታዋ፤ የግብጽን መሬት በሁለት ከፍለን እናጠናለን። 1. ጥቁር መሬት/Black Land፡ ኬሜት(Kemet) ተብሎ ይጠራል፤ ትርጉሙም ጥቁሩ መሬት ማለት ሲሆን በአባይ ጎርፍ ተጠርጎ ወደ ግብጽ የሚሄደው ለም አፈር ነው። 2. ቀይ መሬት/Red Land፡ ታላቁ በርሃ - እስከ ሳሃራ(Sahara Desert) በርሃ ድረስ ያለው ለሕይወት አስቸጋሪው ስፍራ 👉 ይህ ስልጣኔ 5500 ቅ.ል.ክ/BCE አካባቢ የተመሰረተ እንደሆነ ብዙዎች ሲስማሙ ይኸውም ፈረዖን/ንጉሥ ሜኔስ(Menes) የተከፋፈሉትን አውራጃዎች አንድ አድርጎ በመጀመሪያው ዳይናስቲ ከአሁኒቷ ካይሮ ቅርብ በሆነችው በሜምፌስ(Memphis) ከተማን ገንብቷል። ይህ ስልጣኔ በአጠቃላይ 31 ሥርወ መንግሥታት(Dynasty) ያሉት በጣም ሰፊ የሆነ የታሪክ ጊዜ አሳልፏል። 👉 እኒህን 31 ሥርወ መንግሥታት/ዲናስቲስ በሦስት የታሪክ ጊዜ ክልሎች/Periods ተለይተው ይጠናሉ። 1. የድሮው ሥርወ መንግሥት/Old Kingdom – 2700 BCE – 2200 BCE 2. መካከለኛው ሥርወ መንግሥት/Middle Kingdom – 2040 BCE – 1786 BCE 3. አዲሱ ሥርወ መንግሥት/New Kingdom – 1570 BCE – 1085 BCE 👉 እነዚህን የታሪክ ክልሎች በጥቂቱ እንመልከት። 1, የድሮው ሥርወ መንግሥት/Old Kingdom (2700 BCE – 2200 BCE) C. 2600 BCE የታላቁ የጊዛ ፒራሚድ(The great pyramid of Giza) ግንባታ ተጀመረ። ይህ ፒራሚድ በጊዛ(Giza Complex) ከሚገኙ ፒራሚዶች በሙሉ ትልቁና ጥንታዊው ሲሆን በፈርዖን ክሁፉ(Pharaoh Khufu) እንደተገነባ ይታወቃል። ይህ ፒራሚድ 2 × 106 ብዛት ባላቸው እንዲሁም እያንዳንዳቸው 2000 ክብደት በሚመዝኑና በትክክለኛ ቦታ ላይ ብቻ ከተቀመጡ በሚገጥሙ(ልክ እንደ Puzzle) ድንጋዮች በሚገርም ጥበብ ተሰርቷል። C. 2550 BCE የሲፊኒክ(Sphinx) ሀውልት ግንባታ በጊዛ ተገነባ። ሲፊኒክስ ከወደላይ ያለው አካሉ ግማሽ ሰው የታችኛው አካሉ ደግሞ ግማሽ አንበሳ ሁኖ የተሰራ ሃይውት ነው። በፈርዖን ካፍሬ(Pharaoh Khafra) በ2494 BCE እንደተገነባ መረጃዎች ይገልጻሉ። 2, መካከለኛው ሥርወ መንግሥት/Middle Kingdom (2040 BCE – 1786 BCE) C. 1991 - 1800 BCE ግብጽ እስከ ታችኛው ኑቢያ(Lower Nubia) ድረስ ግዛቷን አሰፋች። C. 1991 - 1800 BCE የስዕልና የጥበብ ጊዜ ነበር። በዚህም ጊዜ የባለሐብቶች ልጆች ወደ ቤተመቅደስ ገብተው መጻፍና ማንበብ ይማሩ ነበር። C. 1878 - 1840 BCE በሴኑስሬት(Senusret III) ታላቅ ጠንካራ መንግሥት ነበራት። c. 1720 BCE ግብጽ በባለ ሠረገላ ተዋጊዎች ሃይኮስ(ሂክሶስ፣ Hykos) ተወራ ነበር፤ ይህ የሆነው በመካከለኛው ኪንግደም መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ኒው ኪንግደም ሲጀምር ግብጽን ለቀው ወጠዋል። 3, አዲሱ ሥርወ መንግሥት/New Kingdom (1570 BCE – 1085 BCE) c. 1503 – 1482 BCE ፈርዖን ሃትሽፕሱት (Hatshepsut- Female pharaoh) የገዛችበት ግዜ c. 1361 – 1351 BCE ፈርዖን ቱት (pharaoh Tut) የገዛበት ጊዜ c. 1290 – 1224 BCE ፈርዖን ራምሴስ 2ኛ(Pharaoh Ramses II) የግብጽን ግዛት አስፍቷል። 📌 ታላላቅ ፈርዖኖች/ The Greatest Pharaohs የጥንታዊ ግብጽ ነገሥታት ፈርዖን ተብለው ሲጠሩ በሕዝቡ ዘንድ እኒህ ፈርዖኖች መለኮታዊ ኃይል እንዳላቸው ተደርጎ ይታመን ነበር። 👉 ቱትሞሲስ 3ኛ (Tuthmosis III) - ይህ ፈርዖን ጦርነት ጥበቡ ታዋቂ ሲሆን ሠራዊቱን ከ17 ጊዜ በላይ ወደ ጦርነት መርቷል። በአገዛዙም ዘመን ግብጽ ታላቅ ሥልጣኔ ነበረች። 👉 አኬኔቴን (Akeneten/ አሜኖፌስ 4ኛ/ 1352-1336 BCE) - ይህ ፈርዖን በጥንታዊ ግብጽ ሃይማኖት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ አድርጎ ነበር። ይህም ብዙ አማልክትን የሚመለክበት(Polytheism) የነበረውን ሥርዓት አንድ የፀሐይ አምላክ(Monotheism) የሚል አስተምሕሮና እምነት ይዞ የተነሳ ፈርዖን ነው። 👉 ሜኔስ(Menes) - የላይኛውንና የታችኛውን ግብጽ አንድ አድርጎ በ3100 የገዛ ፈርዖን ነው። 👉 ራምሴስ 2ኛ(Ramses II) - ከግብጽ ከፍ ብለው ከሚገኙትና ታላቅ ጠላቶች ከሆኑት ከሃይታይቲስ(Hittites) ጋር ከ 30 ዓመት በላይ የተዋጋ ፈርዖን ሲሆን በስተመጨረሻም የሃይታይት ግዛትን ልዕልት አግብቶ ሰላምን አድርገዋል። 👉 ራምሴስ 3ኛ(Ramses III) - ይህ ፈርዖን የመጨረሻው ታላቁ ተዋጊ ፈርዖን ሲሆን ግብጽን ከSea Peoples ጥቃት የጠበቀ ነው። ይህ ፈርዖን ካረፈ በኋላ ግን የጥንታዊት ግብጽ ሥልጣኔ እንየደከመና እየደከመ ሂዷል። ከዛም በተከታታይ በአሦራውያን፣ በኑቢያን፣ በፐርሺያን ተወራለች። በርካታ ፈርዖኖችን መዘርዘር የሚቻል ቢሆንም እንደ መግቢያ ይህ በቂ ይመስለኛል።
Mostrar todo...
🖤 YouTube ላይ የተለቀቁት ቪዲዮዎች[የጥንታዊ ግብጽ ሙሉ ታሪክ፣ ቀመረ ፊደል ሙሉ ትምህርት፣ ጣናና የጣና ገዳማት ታሪክ] በጽሑፍና በPDF አዘጋጅቼ እዚጋ ይለቀቁ ?Anonymous voting
  • እሺ!
  • አይ! የዩቲዩቡ በቂ ነው።
0 votes
ይህ መገጣጠም እንዳያመልጣቹ😊
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.