es
Feedback
NFSL DVLCA ንፋስ ስልክ ላፍቶ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈ/ቁ /ባ

NFSL DVLCA ንፋስ ስልክ ላፍቶ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈ/ቁ /ባ

Ir al canal en Telegram

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ተሸከርካሪ ተቋማት በማደራጀት፣ አፈፃፀማቸውን ለማሳደግ ክትትልና ቁጥጥር እና የአገልግሎት ማሻሻያ ጥናቶችን በማካሄድ ተደራሽና ውጤታማ የአሽከርካሪና የተሸከርካሪ ብቃት ማረጋገጥና ፈቃድ አገልግሎት ለህብረተሰቡ በተቀላጠፈ መንገድ መስጠት ነው፤

Mostrar más
819
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ ተከበረ፡፡ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡ 17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫ
+5
17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ ተከበረ፡፡ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡ 17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በድምቀት ተከብሯል። የአንድነታች የጋራ ዓርማ የሆነው ሰንደቅ ዓላማችን የኅብረ-ብሔራዊ አብሮነታችን ዋስትና የሉዓላዊነታችን መገለጫ መሆኑ ነው በመርሃ ግብሩ ላይ የተገለፀው፡፡

#ከተቋማችን_መልካም_ዜና! ተቋማችን የቆዩ የህዝብ ጥያቄዎችን በመፍታት ላይ ነው። ባለፉት 6 ዓመታት የመልካም አስተዳደር እና የፍትኃዊነት ጥያቄን ሲያስነሳ የነበረው የሁለት ዓመት እና የአራት ዓመት የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ ምላሽ አግኝተዋል። ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆነ ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአራት ዓመት የሚታደሱ ይሆናል። አዲስ መንጃ ፈቃድም ከሁለት ዓመት የሙከራ በኋላ፣ ባለው ዓሰራር መሠረት በየ አራት ዓመቱ ይታደሳል። ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑት ግን በየሁለት ዓመት የሚታደስ ሆኖ ክፍያው ግን የአራት ዓመቱ ክፍያ ግማሽ (50%) ይሆናል ማለት ነው።

የእሬቻ ዋዜማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅ/ጽ/ቤት በድምቀት ተከበረ። የሠላምና የወንድማማችነት ተምሳሌት የሆነው እሬቻ በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ ያለው ነው። በየዓመቱ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብ
+4
የእሬቻ ዋዜማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅ/ጽ/ቤት በድምቀት ተከበረ። የሠላምና የወንድማማችነት  ተምሳሌት የሆነው እሬቻ በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ ያለው ነው። በየዓመቱ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት ደማቅ ስርዓት ነው። በዋዜማው ዝግጅት ላይ የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ደሳለኝ ተረፈን ጨምሮ አመራሮችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ ።
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ ።

በመዲናዋ በሚከበሩት የመስቀልና እሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ። በ 2017 ዓ.ም በሀገራችን በድምቀት የሚከበሩት የመስቀልና እሬቻ በዓላት የለምንም ፀጥታ ስጋት እንዲከበሩ መንግስት አ
+3
በመዲናዋ በሚከበሩት የመስቀልና እሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ። በ 2017 ዓ.ም በሀገራችን በድምቀት የሚከበሩት የመስቀልና እሬቻ በዓላት የለምንም ፀጥታ ስጋት እንዲከበሩ መንግስት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉንና ሰራተኛውም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተገልጿል። በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት የቅርንጫፍ ጽ/ቤተ ስራ አስኪያጅ አቶ አወቀ ታደሰ ሁለቱም በዓላት በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ የተመዘገቡ መሆናቸውና በድምቀት የሚከበሩ በሆናቸው ለከተማችን ሌላ ገፅታ ያላብሳታል ብለዋል። በርካታ ህዝብ የሚሳተፍባቸውና የጎዳና ላይ እንቅስቃሴ ያላቸው በዓሻ ልንወጣ ት በመሆናቸው ለቱሪዝም እና ለንግድ እንቅሰቃሴ መነቃቃት ትልቅ አስተዋፅኦ አላቸው ሲሉ ተናግረዋል ። በዓሉን በድምቀት እንዲከበር ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።

የተሟላ ስነምግባር የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለአመራሮችና ፈፃሚዎች በስነምግባር ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል። በስነምግባር የታነፀ ፈፃሚ መኖር
+4
የተሟላ ስነምግባር የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለአመራሮችና ፈፃሚዎች በስነምግባር ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል። በስነምግባር የታነፀ ፈፃሚ መኖር ለአገልግሎት አሰጣጡ ቅልጥፍና ጥራት እና ፍትሃዊነት እንዲሁም ለደንበኞች እርካታ መገኘት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተገልጿል። ሞራል እና የስነምግባር ምንነት፣ የስራ ላይ ስነምግባር፣ ስነምግባራዊ አገልግሎት አሰጣጥ፣የኢ ስነ ምግባራዊ አገልግሎት መንስኤና ለማሻሻል በሚያስችሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠናው አተኩሯል።

የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያው የአብሮነትና የወንድማማችነት ቀን
+9
የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያው የአብሮነትና የወንድማማችነት ቀን

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉን ስናከብር የነብዩ መሐመድ የፍቅርና የአብሮነት አስተምሮትን በመተግበር ምንጊዜም እንደምናደርገ
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።  በዓሉን ስናከብር የነብዩ  መሐመድ የፍቅርና የአብሮነት አስተምሮትን በመተግበር  ምንጊዜም እንደምናደርገው ለወገኖቻችን  ያለንን ፍቅር የምንገልፅባቸውን የበጎነት ፣ የልግስናና የቸርነት ተግባራትን በማከናወን ፤ አብሮነትን ፣ ወንድማማችነትንና መተሳሰብን በማጠናከር ሊሆን ይገባል። መልካም በዓል ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

### የመዓድ ማጋራት ### የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅ/ፅ/ቤት ዝቅተኛ ደመወዝ ላላቸው ሠራተኞች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደ
+3
### የመዓድ ማጋራት ### የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ  ፈቃድና  ቁጥጥር ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅ/ፅ/ቤት ዝቅተኛ ደመወዝ ላላቸው ሠራተኞች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ። የቅ/ፅ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አወቀ ታደሰ  አዲሱ ዓመት  የፍቅር፣ የሰላም፣ያሰብነው የሚሳካበት እንዲሆን በመመኘት በዓሉን ስናከብር በመተሳሰብና በመደጋገፍ መሆን ይገባል ብለዋል። ለመላው ሰራተኛ  የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አመራሮች የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ የሪፎርም ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ደሳለኝ ተረፈ
+4
የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ  ፈቃድና ቁጥጥር  ባለስልጣን  አመራሮች የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ የሪፎርም ስራዎችን ተዘዋውረው  ተመልክተዋል። በባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ደሳለኝ ተረፈ በተመራው ጉብኝት በአጭር ጊዜ የተሰሩ ስራዎችን አድንቋል።

#ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ ቤት ዘመናዊ የፋይል አደረጃጀት ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ ነወ። ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በርካታ ተገልጋዮች ያሉት ሲሆን በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ዘርፍ ከ 450 በላይ ለሚ
+4
#ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ ቤት ዘመናዊ የፋይል አደረጃጀት ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ ነወ። ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በርካታ ተገልጋዮች  ያሉት ሲሆን በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ዘርፍ ከ 450 በላይ ለሚሆኑ ተገልጋዮች በየቀኑ አገልግሎት ይሰጣል። አገልግሎት የተሰጠባቸውን መረጃዎች በየዕለቱ ስካን ተደርገው ወደ ሪከርድና ማህደር ገቢ ይሆናል ። የሪከርድና ማህደር ከዚህ ቀደም የነበረውን ደካማ የመረጃ አያያዝ ስር ነቀል ስራዎችን በማከናወን የተገልጋዮችን እንግልት ማስቀረት ተችሏል።

#ሙሉ_ቀን_አገልግሎት_እንሰጣለን የ2016 ጷጉሜ 2 የሪፎርም ቀን እንኳን አደረሳችሁ ። የንፋስ ስልክ ላፍቶ አሽ/ተሽ/ፈ/ቁ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
+8
#ሙሉ_ቀን_አገልግሎት_እንሰጣለን የ2016 ጷጉሜ  2 የሪፎርም ቀን እንኳን አደረሳችሁ ። የንፋስ ስልክ ላፍቶ አሽ/ተሽ/ፈ/ቁ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

#ሙሉ_ቀን_አገልግሎት_እንሰጣለን የ2016 ጷጉሜ 2 የሪፎርም ቀንን ምክንያት በማድረግ በእለቱ(ቅዳሜ) የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን በሁሉም ቅርንጫፎች እና በማእከል ሙሉ ቀ
#ሙሉ_ቀን_አገልግሎት_እንሰጣለን የ2016 ጷጉሜ 2 የሪፎርም ቀንን ምክንያት በማድረግ በእለቱ(ቅዳሜ) የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን በሁሉም ቅርንጫፎች እና በማእከል ሙሉ ቀን አገልግሎት ይሰጣል ።

#ባጃጅ_ተሽከርካሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የባለሶስት እና አራት እግር ወይም ባጃጅ ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ለውጥ ማድረግ እንደሚጠብቅባቸው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያሳውቃል። የአዲስ አ
#ባጃጅ_ተሽከርካሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የባለሶስት እና አራት እግር ወይም ባጃጅ ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ለውጥ ማድረግ እንደሚጠብቅባቸው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያሳውቃል። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ በበላይነት ይመራል፣ ይቆጣጠራል እንዲሁም የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል። ቢሮው አሁን ያለውን የህዝብ ትራንስፖርት የባለሶስት እግር ወይም ባጃጅ ተሽከርካሪዎችን የሕግ ጥሰቶችንና የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል እና አገልግሎት አሰጣጡን ለመቆጣጠር እንዲያስችል ከዚህ ቀደም በህጋዊ ማህበር በመደራጀት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ባለንብረቶች ተሽከርካሪው ከነበረበት ክልል ክሊራንስና  የአዲስ አበባ ነዋሪነት ማረጋገጫ መታወቂያ በማቅረብ ምትክ የአዲስ አበባ ሰሌዳ ማውጣት እንደሚገባ ቢሮው ያሳውቃል። ይህንን አሟልተው እስኪገኙ ማንኛውም የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በከተማዋ ከነሐሴ 26/2016ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ ቢሮው በጥብቅ እያሳሰበ፤ ወደ አገልግሎት ለመመለስ ቀደም ሲል አገልግሎቱን ሲሰጡበት ከነበረው የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አስፈላጊውን ህጋዊ መረጃ በማሟላት ቢሮው በሚያስቀምጠው የአሰራር ስርዓት መሰረት አገልግሎቱን መስጠት እንሚቻል ቢሮው አሳውቋል። ይህንን ተላልፈው በሚገኙ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት የባጃጅ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች በቢሮውና በሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካላት አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን እናሳውቃለን። Transport Bureau