cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

eyob fans

@eyob

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
144
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Mostrar todo...
Pis join
Mostrar todo...
hWO8JNx8k7A.mp46.67 MB
​ለመንግስትህ ተገዛ! - ድምጻዊ እዮብ መኮንን ከጌጡ ተመስገን የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ ከደራሲ ሳሙኤል ወልደየስ ሀይሉ ጋር ምጥን ቆይታ አድርገናል። እንሆ ... ጌጡ : "የሬጌው ንጉሥ በኢትዮጵያ" (ስለድምጻዊ እዮብ መኮንን~ አዲሱ መጽሐፍህ ለመጻፍ መነሻ እና መድረሻ ምክንያቶችህ ነበሩህ? ሳሙኤል : አዎን! .. እኛ ኢትዮጵያውያኖች ታሪክ በመሥራት አንደኛ ስንሆን ታሪክ በመጻፍ ግን ወደ ኋላ ቀረት እንላለን፡፡ ሁሌም ስለጀግኖቻችን ማንበብ እና ማወቅ ስንፈልግ በስሚ ስሚ አልያም በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ እንጂ ተፅፈው የተቀመጡ ታሪኮችን አገላብጠን ለማንበብ ብዙ አልታደልንም፡፡ እንደአጋጣሚ ተጽፈው የተቀመጡ ታሪኮች ሲገኙ በውስጣቸው የተጣረሱ ሀሳቦች ይይዛሉ፡፡ በእኔ የንባብ ታሪክ የማነባቸው መጽሐፍት እውነተኛ ታሪክ ላይ ያዘነብላሉ፡፡ በዚህም መሰረት የሀገሬን ታሪክ በዛ ካሉ መጽሐፍት ላይ ሳነብ ጸሐፊዎቹ ያስተላለፉት መልዕክት የሚጣረስ እና ለማመን የሚያስችግር ነበር፡፡ ይህ ግን ሁሉም ጸሐፊያንን አይወክልም፡፡ በሙዚቃው ዘርፍ ደግሞ ታሪክ ከቆየላቸው ድምፃውያን መካከል በጣም ጥቂቶች ናቸው ይህም ነገር ያሳስበኛል፡፡ እናም ይህ ነገር በኔ ዘመን መቆም ስላለበት የራሴን አሻራ ለትውልድ እውነተኛ ታሪክ ለማቀበል ማስቀመጥ እንዳለብኝ ወስኛለሁ፡፡ በሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉትን ታሪኮች ደጋግሜ ለአንባቢ እንደማደርስ ለራሴ ነግሬዋለሁ፡፡ እዮብ መኮንን ደግሞ አራት የነበሩትን ቅኝቶቻችንን ባቲ ፣ አምባሰል ፣ አንቺ ሆዬ እና ትዝታን ወደ አምስት ያሳደገልን ንጉሳችን ነው፡፡ ዛሬ ጃሉድ እና ሳሚ ዳን እንዲህ ፍክት ያሉበትን ሬጌ መስዋዕትነት ከፍሎ ለሀገሬ ህዝብ ያስተዋወቀው አርቲስት እዮብ መኮንን ነው፡፡ በዚህ አጭር ጊዜ ምድር ላይ ለቆየው የሬጌው ንጉሳችን ይህ መጽሐፍ ያንስበታል፡፡ የኔ የመጽሐፉ ደራሲ መድረሻ ደግሞ በዘመኔ ያሉትን ታሪኮች ለትውልድ ማቆየት፤ ማሻገር ነው፡፡ ጌጡ : የመጽሐፉ ይዘትና ቅርፅ ምንድነው? ሳሙኤል : መጽሐፉ የአርቲስት ኢዮበ መኮንን ግለታሪክ ነው (የህይወት ታሪክ)የተፃፈው በሦስተኛው የስነ ጽሑፍ መደብ ሲሆን ባለታሪኩ እኔ እያለ ነው ታሪኩን የሚተርከው። መጽሐፉ 310 ገጽ ሲኖረው በውስጡም ውልደት እና እድገቱ ፣ ስብዕናው፣ የፍቅር እና የትዳር ህይወቱ ፣ ቢሮው (ካልዲስ ኮፊ)፣ ጓደኞቹ ፣ ሊድ ጊታር ፣ ገጠመኙ ፣ ስትሮክ (ለእዮብ ህልፈት ምክንያት) ፣ ምስጢር እና ሌሎች አስደማሚ ታሪኮችን አካቷል።አንባቢያን መጽሐፉንከመጽሐፉ አሳታሚና አከፋፋይ ጃፋር መጽሐፍት መደብር (ከኮሜርስ እና ለገሀር ባለው ዋናው መንገድ አጠገብ) ማግኘት ይችላሉ፡፡ ጌጡ : የእዮብ መኮንን አስደማሚ ታሪኮች ኢዮብ በአንድ ወቅት ውጭ ሀገር ሄዶ ኮንሰርት ሰርቶ ይመጣል። በዛ ሥራው ደግሞ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ሠርቶ ነው የመጣው፡፡ ከውጭ ሀገር እንደመጣ በነጋታው ቦሌ መድኃኒዓለም ፊት ለፊት በሚገኘው ካልዲስ ኮፊ (ቢሮው) ማኪያቶ እየጠጣ ለጓደኛው ለኦሪዮን ስልክ ደወለለትና ጠራው፡፡ (በነገራችን ላይ ጠቆር ያለ ማኪያቶ እዮብ ነብሱ ነው) ኦሪዮንም በፍጥንት መጣና ሰላም ከተባባሉ በኋላ እዮብ ከተቀመጠበት በመነሳትና ግብር እንክፈል እና እንምጣ አለው። ኦሪዮንም የምን ግብር ነው አለውና ተከትሎት መሄድ ጀመረ፡፡ ቦሌ ክፍለ ከተማ ግብር የሚከፈልበት ቦታ እንደደረሱ ኢዮብ ለግብር ተቀባይዋ ውጪ ሀገር ሄጄ ይሄን ያህል ብር ሰርቼ መጥቻለው እና ስንት ነው የሚደርስብኝ ግብር አላት። ግብር ተቀባይዋም ሂሳቡን ሰርታ ከ100 ሺ ብር በላይ ስትለው ምንም ሳያቅማማ ከፍሎ ወጣ፡፡ ኦርዮንም እዮብ ምን እያረክ ነው?! ሲለው በህይወት እስካለህ ድረስ ለመንግስትህ ተገዛ ይላል መጽሐፍ ቅዱስ አለና መለሰለት፡፡ እዮብ በትዳር ቀልድ አያውቅም፤ አይባልግም፤ አያመነዝርም አንድ ጓደኛው የሆነ ወቅት ከሚስቱ ተጣልቶ ሚስቴን ካልፈታው ሲለው እዮብ ጓደኛውን ይኸውልህ ትዳር ከሆነ ትዳር ነው። በሚስትህ ማመን አለብህ የኔን ሚስት አሁን እቤት ሄደህ ብታያት ቦርጯ መሬት እየጎተች ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር የሰጠኝ ስለሆነ እኔም አብሬ እጎትታለው። አለውና ልጁን በማሳቅ መክሮት ትዳሩን ከመፍታት አድኖታል፡፡ ጌጡ : እዮብ መኮንን በጣም የምወደው፤ የማከብረው ድምፃዊ ነበር። ከእዮብ "ሽንገላ አያስፈልግም!" አዘውትሮ የሚናግራት ነገር ነበረች... ሳሙኤል : እዮብ ሰውን መሸንገል፣ የሌለህን አለህ ያልሆንከውን ነህ ማለት አይወድም። "ሽንገላ አያስፈልግም!" በምትል አባባሉ በጓደኞቹ እና በቤተሰቡ ይታወቃል፡፡ አንድ ሰው ለእዮብ መኮንን መጥቶ ስለሌላ ሰው መጥፎ ጎኑን ካወራለት (ካማህለት) እዮብ ሰውየውን ይህንን ለኔ የምትነግረኝን ሂድና ለሱ ንገረው (ለታማው ሰው) አለበለዛም ጸልይለት ይልሃል፡፡ ጌጡ : ምጥን ቃለ መጠይቁን እናሳርገው። ሳሙኤል ወልደየስ እባላለሁ ብለህ ከአንባባቢ ጋር ተዋወቅ? ሳሙኤል : ሳሙኤል ወልደየስ ኃይሉ እባላለሁ። በማኔጅመንት ቢ ኤ በኮምፒውተር ሳይንስ ቢ ኤስ ሲ አለኝ።ለጥበብ በጣም ቅርብ ነኝ።ህይወቴ ያለሙዚቃ እና መጽሐፍት ባዶ ነው። የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረቱ መጽሐፍት ማንበብ እንዲሁም ሙዚቃ ማዳመጥ እወዳለሁ። ጌጡ : ትልቁን ነገር ረስተሃል። እኔ ለእንባቢዎቼ አስተዋውቅሃለሁ። የባለ ታሪኮችን (ታሪክ የሠሩ) ታሪክ ማቆየት አላማው የሆነ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሙያው የፕሮግራም እና የዜና ዳይሬክተር እና ጸሐፊ (ደራሲ) ነው። ሳሙኤል : አመሰግናለሁ።@eyobajegnaya
Mostrar todo...
13_እንዴት_ብዬ_EYOB_MEKONNEN_ALBUM_–.mp38.70 MB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.