cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Owners for ourselves(የራስ ሊቅ)

If u wanna know about urself ,then u are in the right channal. " Stay with us."

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
151
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#የፈረሱ_እና_የ_ፍየሏ_ታሪክ አንድ ገበሬ የሚወደው ፈረሱ ይታመምበትና ወደ እንስሳት ሀኪም ጋር ይዞት ይሄዳል። ሀኪሙም ፈረሱ ጉረኖ ድረስ በመሄድ በሚገባ መረመረው። ለገበሬውም - "ተላላፊ በሽታ ስላለበት ለሶስት ቀን መድሀኒት እንስጠውና ካልተሻለው ወደሌሎቹ ፈረሶች እንዳይዛመት እንገለዋለን" ብሎት ሄደ። ይሄንን ሲያወሩ ፍየል ተደብቃ ሰምታቸው ኖሯል ለፈረሱ እያለቀሰች ያወሩትን ነገረችውና "እንደምንም ብለህ ተነስ! ያለበዛ ይገሉሀል" እያለች ተንሰቀሰቀች። የመጀመርያው ቀን ሀኪሙ መጥቶ መድሀኒቱን ሰጥቶት ወጣ። ወድያው ፍየል ለምለም ሳርና አተላ ይዛለት መጣች ና "እንደምንም ተነስ!" ብላ ተማፀነችው። በሁለተኛውም ቀን ሀኪሙ ሲመጣ ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም መድሀኒቱን ወግቶት እስከ ቀጣዩ ቀን ጠብቆት ካልተሻለው እንደሚገለው ለገበሬው ነግሮት ሄደ። ይሄን ግዜ ፍየል ለምለም ሳር ፈልጋ ለፈረሱ በማምጣት አፅናናችው። የመጨረሻ ቀን ሀኪሙ ሲመጣ አሁንም ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም ይሄን ጊዜ ከገበሬው ጋር ቢገሉት እንደሚሻል በር ላይ ቆመው ሲያወሩ ፍየል ቀስ ብላ ተደብቃ ፈረሱ ጋር ገብታ እየተንሰቀሰቀች- "በናትህ አኔንም ጓደኛ አታሳጣኝ ካልተነሳህ ይገሉሀል" ብላ አለቀሰች። ፈረሱ በፍየሏ ግፊት ቀስ ብሎ ተነሳ። ፍየል ደስ አላት። "ጎበዝ አስኪ እሩጥ" እያለች አበረታችው። ፈረሱ በወኔ በፊት ከሚሮጥበት ፍጥነት በላይ ሮጠ። ይሄን ጊዜ ፍየል በደስታ ጮኸች። ገበሬውና ሀኪሙ የምን ጩኸት ነው ብለው ሲያዩ ያዩትን ማመነን አቃታቸው።ፈረሱ በሓይል አየሮጠ ነው። ገበሬው በደስታ ብዛት ሀኪሙን አንቆ ሳመው። እረኛውን ጠርቶት "ዛሬ እኔ ቤት ትልቅ ድግስ አለ! ስለዚህ ቶሎ በሉ ፍየሏን እረዱልኝ! ምሳ እዚህ ነው" አለ። ✍አንዱ የሌላው መሰላል ነው። ለአንዱ ሂወት ለሌላው ሞት ነው። ለሀብታም ሂወት የደሀው ችግር ግድ ነው። ለአንዱ ማለፍ የሌላው ውድቀት ወሳኝ ነው። አለም የምትመራበት ህግ ነው።
Mostrar todo...
Hodo
Mostrar todo...
ልጂቷ ከፍቷታል ጎንበስ ብላ እያለቀሰች ነው ሀሳብ ውስጥ ነች ላናግራት ፈለኩ ደሞ ልቤ አመነታ እናት ሰላም ነው አልኳት ቀና አለች ያየሁትን አላመንኩም ልጅቷ ፍቅረኛዬ ሁና አገኘሁዎት ደነገጠች ደነገኩ ተርበተበተች ግራ ገባኝ አቀፍኳት አቀፈችኝ ምን ሆነሽ ነው አልኳት ምንም ብላ መለሰችልኝ። አንድ ነገር ግን እወቅልኝ አለችኝ ምንድነው እሱ አልዃት እወደሀለሁ በሙሉ ልቤ በሰውነቴም በነፍሴም ጭምር አለችኝ እኔም እወድሻለሁ ብዬ አቀፍካት። አሁን ተለያይተናል የተለያየነው በምን መሰላችሁ ያኔ ችግሯን ምንም አልሆንኩም ስትለኝ ሳልረዳት አይዞሽ ንገሪኝ ብዬ ወንድነቴን ሳልጠቀም ወንድ ሳልሆንላት ያለፍኩት ችግሯ ነበር ምክንያታችን አየህ ሴት ልጅ ምንም ስትል የሆነ ነገር አለ ማለት ነው። (ኤሊያስ እንድሪስ)
Mostrar todo...
Ene wedehewalw👍👍👍👍👏👏
Mostrar todo...
🎙አርቲስት: ዘሪቱ ከበደ 🔈ርእስ: የወንድ ቆንጆ [2006] ሚስትህ በጣም ፉንጋ ናት ፉንጋ ከኔ የባሰች አንተን መሳይ አደላት ቀድማ ስላልፈረደች አንተ በጣም ቆንጆ ነህ ቆንጆ ቃሉ ያንስሃል እስከምቶን ምሳሌ ማንም ይስማማብሃል እንደሱ ሳታውቀኝ በፊት ሳይሞላልህ መፋቀር ስለዚህ የፍቅር ጉዳይ አነጋግረኸኝ ነበር ሁለመናሽ ደስ አለኝ አፈቀርኩሽ ስትለኝ አላመንኩህም ጭራሽ ስትቀልድ ነው የመሰለኝ ሲባል እማውቀው ደሞ የወንድ ቆንጆ ልቤም ሲፈራ እንዳልጎዳ ደሞ የወንድ ቆንጆ እንዳትኮራ ሲባል እማውቀው ደሞ የወንድ ቆንጆ ልቤም ሲፈራ እንዳልጎዳ ደሞ የወንድ ቆንጆ እንዳትኮራ ሚስትህ እጅግ ፉንጋ ናት አንተ አልታየህ እንደዛ ሆዴን እስኪያመኝ ቀናሁ አልፌህ እንደዋዛ አንተ በጣም ቆንጆ ነህ በሚያነጋግር አይነት በእውነት ግራ ይገባል አንተን ከሷጋ ማየት ወደኋላ መለሰኝ አሳሰበኝ ስለኛ የፈላለከኝ ሰሞን እንድሆንህ ፍቅረኛ ቆንጆ ወንድ ማቅረብ ትርፉ አልባ ብዬ መከራ ልቤን ተከላክዬው ኮራሁብህ ሳትኮራ ሲባል እማውቀው ደሞ የወንድ ቆንጆ ልቤም ሲፈራ እንዳልጎዳ ደሞ የወንድ ቆንጆ እንዳትኮራ ሲባል እማውቀው ደሞ የወንድ ቆንጆ ልቤም ሲፈራ እንዳልጎዳ ደሞ የወንድ ቆንጆ እንዳትኮራ እሷ ግን አመነችህ ትንሽነት ሳይሰማት ፉንጋ ሳለች ስታምርህ ተማምና እንደምትገባት እሷ ግን አመነችህ ከሽፋኔ አልፋ አየችህ ሚዛንህም ተረታ አንተንም በዛው ሰፈረችህ ኧረሱ ቆንጆ ነው ልቤ ፈራ ፈራ ፈራ ቆንጆ ቆንጆ ነው ልቤ ፈራ ፈራ ፈራ ሲባል እማውቀው ደሞ የወንድ ቆንጆ ልቤም ሲፈራ እንዳልጎዳ ብዬ ደሞ የወንድ ቆንጆ አንተም እንዳትኮራ ሲባል እማውቀው ደሞ የወንድ ቆንጆ እንዳልጎዳ ብዬ ደሞ የወንድ ቆንጆ እንዳትኮራ ደሞ የወንድ ቆንጆ ደሞ የወንድ ቆንጆ ልቤ ፈራ ፈራ ፈራ ልቤ ፈራ ፈራ ፈራ Share ur best friend🙏 Only @ArifmusicI @ArifmusicI
Mostrar todo...
★★★.....ተኖረና....★★★ ላለ-ለሌለ...... እየታለ......እየተሌለ በመሸ-ነጋ-መሸ...... እንደነበረ እንዳለ... እንዳደረ እንደ-ዋለ "ህይወት"እንደ...ዋለለ እንዲሁ...... እንደዋተተ "መኖር"ን እንደ ሞገተ "ኗሪ" ሳይኖር ኖረ....ኖረና......ሞተ:: ተኖረ-ተኖረና ተሞተ ተሞተና ተለቀሰ ዕንባ------እንደ ጅረት ፈሰሰ ደረት------እንደ አፈር ፈረሰ ምድረ ቡቱቷም......ጭርንቁስ-ደሀ! ተቃቀፈና አነባ ለምንም......ምንም......ላይረባ! ግና!......ያረፈ...... እንዳላረፈ ............አረፈ አየ......አየና.....አለፈ፣ "ትቢያ" ነበር ......"ትቢያ" ለበሰ ለሟች ኗሪ...... ለኗሪ ሟች...... ...................ወግ ደረሰ
Mostrar todo...
​​​​..... "ምን ያክል ነው ፍቅርሽ? ብለህ ብጠይቀኝ ❤️❤️ ምን ያክል ልበልህ? ምኑን አውቀዋለሁ፣ እኔ አምላክ አይደለሁ፣ ብቻ ግን... ማንም ጓደኛዋን ከምትወደው በላይ፣ ማንም ፍቅረኛዋን ከምታፈቅረዉ በላይ፣ ውስጤን ገዝተከዋል ቦታ አለህ ልቤ ላይ፡፡ 😍😍😍 ብታምንም ባታምንም፣ እውነቱን ልንገርህ ፍቅሬ አንተን አልዋሽም፣ እስከ ዘላለሙ እኔ አላፈቅርህም፣ እንደ ሞኝ አፍቃሪ የዘላለሜ ነህ ብዬ አልደልልህም፣ ምክንያቱም... ዘላለም የሚኖር ሠው ተፈጥሮ አያውቅም፡፡ አንተም እኔም ሁሉም ማንም ቢሆን ማንም፣ ዘላለም አፍቅሮ ዘላለም አይኖሮም፡፡ ግን... እስከ'ድሜዬ ክልል እስከ ሂወቴ ጫፍ፣ መቼም አይሰለቸኝ አንተና ፍቅርህን አዝያችሁ ብከንፍ፡፡ አፈቅርሃለሁ 💖💖ትላንትም ዛሬም ነገም አስካለው በምድር ፣ከዛም በኋላ ❤️❤️
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.