cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

☀️☀️DAILY BREAD🥖🥖

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝ የአስተያየት መስጫ ሳጥን እና የcross @Nemeabbot በየቀኑ ስብከት ይለቀቃል , ለምሳሌ የ ቃል ጥናት ጥቅስ መፀሐፍ ቅዱስአዊ አባባሎኦች Photo ከ መዝሙር ጋር ይሄ ቻናል ከ እግዚአብሔር ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይጨምራል #ተባረኩ ለማነኛዉም አስተያየት @Nemeabbot ያናግሩን.

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Publicaciones publicitarias
196
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

“በአጠገቤ ምንም አታድርጉ፤ የብር አማልክት የወርቅም አማልክት ለእናንተ አታድርጉ።” — ዘጸአት 20፥23
Mostrar todo...
Repost from N/a
ሻሎም ሻሎም ቅዱሳን የጌታ ምህረትና ሞገስ ይብዛላችሁ🙌🙌 ክፍል ሶስት እምነትና ተስፋ እምነት እራሱ የመንፈስ ፍሬ ነው። ያለ እምነት የሚደረግ ሁሉ ሀጢያት ነው። የፀደቅነው በእምነት ነው። የእምነትና የተስፋን ልዩነት ካላወቅን ወደ መታከት፣ ተስፋ ወደ መቁረጥ እንመጣለን። ፨ ተስፋ ማለት፦ ዘወትር በመፅናት ከእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነገርን መጠበቅ ማለት ነው። ዘወትር ማለት የማያቋርጥ የማይቆም ሁልጊዜ ማለት ነው። ተስፋ የሆነ ጊዜ ተስፋ አድርገን የሆነ ጊዜ የምንተወው አይደለም። ፨ ተስፋ የምኞት ሀሳብ አይደደለም ። የእውነት ተስፋ ፦ የተመሰረተው በእውነት ላይ እና በእምነት ላይ ነው። 👉በእውነት ላይ ያልተመሰረተ ተስፋ ምኞት ነው። እምነትና ተስፋን ሁለቱም አስፈላጊ ናቸው። አንዱ አንዱን አይተካም። አንዱም ያለ አንዱ አይሆንም። ✔️እምነት አሁን ነው። ✔️ተስፋ ወደ ፊት ነው። እምነት በልብ ሲሆን ተስፋ ግን በአዕምሮ ነው። እምነትና ተስፋ በጣም የተያያዙና የተሳሰሩ ናቸው። የተስፋና የፍቅር የሁለቱ ውጤት (ፍሬ )ፍቅር ይሆናል። እምነት በተስፋ ተስፋ በእምነት ቦታ አይገባም። " ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 10:10) ሰው በአእምሮ በኩል ሲያምን ተስፋ የተገባለትን ሁሉ መውረስ አይችልም። መውረስ የሚቻለው በልብ ማመን ሲቻል ነው። " እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር፤" (1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:8) ጥሩር፦ ደረት (ልብ)ላይ የሚደረግ ነው። ልብን ይጠብቃል። እንዲሁ እምነት እንደ ጥሩር ነው ልብን ይጠብቃል። የራስ ቁር፦ አእሞሮን የሚሸፍን ነው። ተስፋም እንዲሁ አዕምሮአችንን ይጠብቃል። ✔️እምነትና ፍቅር በልብ ነው። ✔️ተስፋ ግን በአዕምሮ ነው። ሰው በስሜቱ ከተመራ ፦ የስሜት ህዋሳችን contact የሚያደርገው ከዚህ ከሚታየው አለም ጋር ስለሆነ የሚታየው ደግሞ ተለዋዋጭ ስለሆነ አንዴ የመውጣት እና የመውረድ ህይወት ይታይብናል። እምነታችን ግን በእግዚአብሔር ላይ ሲሆን stable የሆነ ክርስትና እንኖራለን። ስሜት፦ ከማስረጃ ከሚታየው ከሚሰማው ከውሸት ሊጀምር ይችላል። እውነት ያለው የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ሲሆን እምነት ደግሞ በእውነት ላይ የሚመሰረት ነው። ከዚህ ውስጥ የሚወጣው በስሜታችን የሚገለጠው ነገር እውነት ይሆናል። ስሜት ከቀደመ ግን እውነት የሆነን ነገር ማግኘት አንችልም ስሜት ተለዋዋጭ ስለሆነ ። በስሜታቸው የሚመሩ ሰዎች ባህሪ፦ ፨ ያልተረጋጉ ናቸው አንዴ ይደሰታሉ፣ አንዴ ይከፋሉ፣ አንዴ ይወጣሉ፣ አንዴ ይወርዳሉ፣ 👉እምነት ኢየሱስ በሰራልን ስራ ላይ መመስረት ሲሆን ተስፋ ደግሞ ኢየሱስ ሊሰራ ያለውን ስራ መጠባበቅ ነው። " ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤" (ወደ ዕብራውያን 3:1) " እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።" (ወደ ዕብራውያን 12:1-2) ✔️ኢየሱስ የእምነት ራስ ነው። ደግሞ ፍፃሜ ነው። የእምነትን መሰረት የጣለው እርሱ ነው። የሚደመድመውም (የሚጨርሰውም) እርሱ ነው። ማለትም፦ ሐዋሪያ ማለት የተላከ ነው። ኢየሱስም ከእግዚአብሔር ተልኮ መሰረት ጥሎልናል። እንደ ሊቀ ካህን ደግሞ እኛን ወክሎ በአብ ፊት የሚታይልን ነው። ኢየሱስ እንደ ሐዋሪያ የጀመረውን ስራ እንደ ሊቀ ካህን ሆኖ ደግሞ ይፈፅመዋል። ተስፋ የራስ ቁር ነው። ከጭንቀት ከግራ መጋባት ፣ ከፍርሃት የሚጠብቅ ነው። ፨ ተስፋ ስናደርግ መጨነቅን እናቆማለን ፨ ተስፋም ሆነ እምነት በመፅሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ መመስረት አለባቸው። " እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28) ፨ እግዚአብሔርን ለሚወዱት ፨ እንደ ሀሳቡ ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። በዚህ ቃል ላይ ከተመሰረትን በእግዚአብሔር መልካምነት ላይ ተስፋ እናደርጋለን። ተስፋ ያደረግነው አያሳፍርም። ተስፋን የሰጠው የታመነ ነውና። ✔️ተስፋ ያደረግነውን ነገር ደግሞ እንድንጨብጥ የሚያደርገን እምነት ነው። እምነት ደግሞ በልብ ነው። ✔️ያመነ ሰው እውነተኛ ተስፋ ነው የሚጠብቀው። ደግሞም ተስፋውን ይወርሳል። " እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።" (ወደ ዕብራውያን 11:1) (ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. 1) ---------- 16፤ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። 17፤ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና። እንግዲህ ቅዱሳን በዚህ ዘመን አፅንተን ልንይዝ የሚገባውን እውነት ጌታ እያስተማረን ነው። እነሱም እምነትና ተስፋ ናቸው። ሰይጣን ሊያስጥለን የሚተጋው እነዚህን ነው። ቅዱሳን ፦ ተስፋ አለን ታላቅ የፀና የሰጠው የታመነ የሆነ ይህን ተስፋ ያመኑ እና በእምነታችሁ የፀኑ ይወርሳሉ። በእምነታችን የምንፀናው በስሜታችን ስንመራ ሳይሆን በመንፈስ ስንመራ ነው። ለዚህ ደግም የውስጥ ሰውነታችሁ እንዲጠነክር ከቃሉና ከመንፈሱ ጋር ህብረት እናድርግ። እምነት በመጨመር ተባረኩ። በእምነት እግዚአብሔርን በማስደሰት ተስፋችሁን በመውረስ ተባረኩ። 👉ይህን የተማራችሁትን አሰላስሉ አጥኑት ተለማመዱት የተማርነው በህይወታችን ሲያፈራ እናያለን። ኢየሱስ ጌታ ነው። በክብር ተመልሶ ይመጣልናል። ተባረኩ 🙏🙏
Mostrar todo...
ሻሎም ሻሎም ቅዱሳን (የያዕቆብ መልእክት ምዕ. 4) ---------- 7፤ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ 8፤ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። " ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።" (ወደ ዕብራውያን 11:6) ለእግዚአብሔር እንገዛ፣ በፍፁምና በሙሉ ልብ ወደ እግዚአብሔር በእምነት እንቅረብ፣ እንከተለው በእውነትና በመንፈስ እናምልከው ለሚፈልጉት የሚገኝ ለሚቀርቡት የሚቀርብ ዋጋንም የሚሰጥ አምላክ ነውና። መልካም ቀን ይሁንላችሁ 🙏🙏
Mostrar todo...
ዛሬ በ አቃቂ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስትያን cornerstone band ጋር የ አምልኮ ጊዜ
Mostrar todo...
Today at akaki mulu wengel bete Christian
Mostrar todo...
cornerstone band.aac37.44 MB
ሻሎም ሮሜ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። ² በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና። ³-⁴ ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ። ⁵ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ⁶ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ⁷ ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤ ⁸ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም። ⁹ እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም። ¹⁰ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው። ¹¹ ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል። ¹² እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ዕዳ አለብን፥ እንደ ሥጋ ፈቃድ ግን እንኖር ዘንድ ለሥጋ አይደለም። ¹³ እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ። ¹⁴ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። ¹⁵ አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። ¹⁶ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ¹⁷ ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን። ¹⁸ ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ። ¹⁹ የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና። ²⁰ ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፤ ²¹ ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው። ²² ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና። ²³ እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን። ²⁴ በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? ²⁵ የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን። ²⁶ እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ²⁷ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና። ²⁸ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ²⁹ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ ³⁰ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው። ³¹ እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ³² ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም? ³³ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? ³⁴ የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ³⁵ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ³⁶ ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። ³⁷ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ³⁸ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ³⁹ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ። @dailybreaddd @dailybreaddd
Mostrar todo...
Alegn Yemilew - Kalkidan Lily Tilahun.mp34.65 MB
Estenfas Alegn - Kalkidan Lily Tilahun.mp35.73 MB
Asdenaki Neh - Kalkidan Lily Tilahun.mp35.18 MB
Sankuwakuwa - Kalkidan Lily Tilahun.mp35.15 MB
Eyulign - Kalkidan Lily Tilahun.mp37.18 MB
Ye Nazretu Eyesus - Kalkidan Lily Tilahun.mp36.53 MB
Gena Sayikefel Bahiru - Kalkidan Lily Tilahun.mp36.14 MB
Amelkihalew - Kalkidan Lily Tilahun.mp36.98 MB
Manew - Kalkidan Lily Tilahun.mp35.09 MB
Tadiya Lemin Metahu - Kalkidan Lily Tilahun.mp34.07 MB