cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

(በአላህ ፍቃድ የሸይኽ ኢልያስ አህመድ (ሀፊዘሁላህ) ደርሶች : ሙሀደሮች በዚህ ቻናል እናቀብሎታለን ። አስተያየት ካላቹ በጉሩፑ ዙሪያ በሩ ክፍት ነዉ ከታች ባለዉ ሊንክ አሳዉቁኝ https://t.me/mesud16

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
6 061
Suscriptores
+224 horas
+287 días
+11930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ለሐጅ የተመዘገባችሁ ወገኖች ~ 1ኛ፦ ሐጅ በግምት አይተገበርም። በዚህ ላይ የተዘጋጁ ትምህርቶችን ተከታተሉ። እዚያ ሄደው ልክ ይሁን አይሁን ሳያውቁ ሌሎች የሚፈፅሙትን ሁሉ የሚፈፅሙ አሉ። ይሄ ደግሞ አላህ የሚጠላቸው ነገሮች ላይ ሊጥለን ይችላል። 2ኛ፦ መውጫ እለት ደርሶ መዋከብ ከሚገጥም አስፈላጊ የሚባሉ ነገሮችን ከወዲሁ ዝግጁ አድርጉ። 3ኛ፦ መረጃዎችን ከወዲሁ ተለዋወጡ። የአዲስ አበባ መጅሊስ ለሑጃጅ መረጃ የሚያስተላልፍበት፣ እንዲሁም የሑጃጅ ጥያቄ የሚመልስበት የቴሌግራም ግሩፖች እንዳሉ አይቻለሁ። ነገር ግን ብዙ ሑጃጅ መረጃው ላይኖረው ስለሚችል ቢታሰብበት መልካም ነው። 4ኛ፦ በሐጅ ላይ አጉል ንትርክ የተወገዘ ነው። ስለዚህ እርስ በርስም ይሁን ከመጅሊስ የሐጅ አስተባባሪዎችም ጋር ይሁን አጉል ንትርክ ውስጥ ከመግባት ተጠንቀቁ። ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ቅሬታ ካላችሁ በአደብ ተነጋገሩ። ሐጃችሁን አደጋ ላይ እንዳትጥሉ። 5፦ መረጃ በመለዋወጥ፣ ደካሞችን በማገዝ፣ የተቸገረን በመርዳት፣ በመስተንግዶ፣ ወዘተ. ተጋገዙ። አላህ በሰላም ደርሳችሁ የምትመለሱ ያድርጋችሁ። ትልቁ ነገር ደግሞ አላህ ሐጃችሁን ይቀበላችሁ። ኣሚን። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Mostrar todo...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ለቀብሩ እና ለዕለተ-ትንሳኤ መልካም ጓደኛ የፈለገ ኢስቲግፋር ያብዛ።
Mostrar todo...
ኹጥባ በተቻለ መጠን፡ * ቃላቱ የተከሸነ፣ * መጠኑ የተመጠነ፣ * መልክቱ ወቅቱን ያማከለ፣ * አቀራረቡ ታዳሚውን ያልዘነጋ ቢሆን መልካም ነው። ኸጢቦች ሆይ! ሌላው ቢቀር ቢያንስ ሰዎች ውጭ ላይ ከባድ የቀትር ፀሐይ ቃጠሎ ሲያንቃቃቸው ወይም ዝናብ ሲዘንብ እንኳ ርህራሄ ቢኖራችሁ መልካም ነው። ሰዎች እየተከፉ ዒባዳቸውን እንዲፈፅሙ አታድርጉ። "ከናንተ ውስጥ አስበርጋጊዎች አሉ" የሚለውን ሐዲሥ አስታውሱ። = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor
Mostrar todo...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

Photo unavailableShow in Telegram
አንዳንዱ የሚከላከልልህ ያስመስላል። እሱ ግን መጥፋትህን እንጂ አይሻም። =
Mostrar todo...
👆👆👆 🔖 ከበሽታ እንዲፈውሱን ረሱልን ﷺ መለመን ይቻላል የሚሉ ሰዎች ብዥታና ምላሾቹ ✅ ዐብደላህ ቢን ኡመር እግሩን በደንዘዘው ሰዓት ያ ሙሐመድ ብሎ ተሽሎታል? ✅ አንድ ሰው ችግር ሲያጋጥመውወይም ሲያመው ረሱል ከዚህ ችግር ወይም ከበሽታ እንዲፈውሱት መለመን ይቻላል ? 🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ 🔗 ድምጽ ፋይሉን ከቴሌግራም ሊንክ ማንግኘት ይችላሉ https://t.me/ustazilyas/1112 ____ 🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አህመድ የትምህርት መድረክ https://www.facebook.com/ustathilyas @ustazilyas
Mostrar todo...
"እኔ" ገደል እንዳይከተን ~ "እኔ እኔ" ሲበዛ ለሰሚው ያቅለሸልሻል። ድንበርም ያስታል። ለራስ የተጋነነ ግምት ማሳደር ጎንበስ ብሎ ለመማር እንቅፋት ይሆናል። በ "እኔ" የተለከፈ ማንነት ከኢኽላስ ጋር የመጣላቱ እድል ሰፊ ነው። እዚህ ላይ አንድ የሚደንቅ የሶሐቦች ስብእና አለ። ከሚያስተላልፏቸው ገድሎች ውስጥ የራሳቸው ሲሆን ጊዜ "አንድ ሰው እንዲህ አድርጎ" በማለት እንደዋዛ የአንድ ማንነቱ የማይታወቅ ሰው ጉዳይ በሚመስል መልኩ የሚያቀርቡበት ሁኔታ አለ። ታሪኩ በሌላ አቅጣጫ ሲፈተሽ ግን የራሳቸው ገድል ሆኖ ይገኛል። ሱብሓነላህ! ኢኽላስን ለማረጋገጥ፣ ስግብግብ ነፍስያን ለማሸነፍ፣ በራስ ፍቅር ክንፍ ከማለት ለመዳን "እኔ፣ እኔ" በሚል ክፉ ስሜት ላይ ጦርነት ማወጅ ያስፈልጋል። ነፍሲያን ጉሮሮዋን አንቆ መያዝ። የኢኽላስ ነገር ለነፍሲያ ፈተና ነው። የአንድ ሸይኽ ደርስ ላይ የሚገርም ገጠመኝ ሰማሁኝ። የሆነ ሰው ሌሊት እየተነሳ ሶላት መስገዱ ማንም ዘንድ አለመታወቁ ይከነክነዋል። እና በብልሃት ሰጋጅነቱን ማሳወቅ ፈለገ። ፋርማሲ ገባና * "በሌሊት ሶላት ምክንያት ለሚሰማ ድካም የሚሆን መድሃኒት አለህ ወይ?" ብሎ ይጠይቃል። - "የለኝም" አለው። * "እሺ ሷሊሖችን ትውዳለህ'ንዴ?" ብሎ ይጠይቀዋል። - ፋርማሲስቱ ነገሩ ቢገርመው አሳለፈው። * "ለማንኛውም ሷሊሖችን ውድድ አላህ ይወድሃል" ብሎት ወጣ። ✅ "እኔ" ይሉኝታ ያሳጣል። ✅ "የኔ" ስግብግብ ያደርጋል። ✅ "እኔ ዘንድ" ትእቢት ያወርሳል። እነዚህ ስሜቶች ልባችንን እንዳይቆጣጠሩ መጠንቀቅ ይገባል። ጠቢቡ ኢብኑል ቀዪም - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ " 'እኔ'፣ 'የኔ' እና 'እኔ ዘንድ' ማለት ድንበር እንዳያልፍብህ መጠንቀቅ ይገባል። እነኚህ ሶስት ቃላት ኢብሊስ፣ ፊርዐውን እና ቃሩን ተፈትነውባቸዋል። 👉🏾 'እኔ ከሱ በላጭ ነኝ' የሚለው የኢብሊስ ነው። 👉🏾 'የግብፅ ግዛት የኔ ነው' የሚለው የፊርዐውን ነው። 👉🏾 '(ሀብቱን) የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ብቻ ነው' የሚለው የቃሩን ነው። ➡️ 'እኔ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ 'እኔ ባሪያ ነኝ'፣ 'እኔ አጥፊ ነኝ'፣ 'እኔ ምህረትን ለማኝ ነኝ'፣ 'እኔ ወንጀለኛነቴን የማምን ነኝ'፣ ... በሚለው የባሪያ ንግግር ውስጥ ነው። ➡️ 'የኔ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ 'የኔ ወንጀል'፣ 'የኔ ውርደት'፣ 'የኔ ድህነት' በሚለው ውስጥ ነው። ➡️ 'እኔ ዘንድ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ ደግሞ 'ምሬንም ሆነ ቀልዴን፣ ስህተቴንም ሆነ አውቄ የፈፀምኩኑን ምህረት አድርግልኝ። ይሄ ሁሉ እኔ ዘንድ አለና' በሚለው ውስጥ ነው።" 📖 [ዛዱል መዓድ] = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Mostrar todo...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

የገጠር ሰው ነው። የህይወት ትርጉሙን ከግብርናና ከከብቶች ጋር ያደረገ ዘላን የሆነ ሰው። ኢብኑ ዐባስ ጋር መጣና ጠየቀ «በእለተ ትንሳኤው ማን ነው የሚተሳሰበን?» «አላህ» አሉት ኢብኑ ዐባስ «ወረቢል ካዕባ ድነናል።» አለ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ለበሽታህ ህክምና በማድረግ ሰበብ አድረስ! ረሱል () እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لِكُلِّ داءٍ دَواءٌ، فإذا أُصِيبَ دَواءُ الدّاءِ بَرَأَ بإذْنِ اللهِ عزَّ وجلَّ.﴾ “ለሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው። የበሽታ አደጋ ከገጠማችሁ ታከሙ። በላቀው አላህ ፈቃድ ነፃ ትሆናላችሁ።” ‌ 📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2204
Mostrar todo...