cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ethio- Education

Addis Ababa Ethiopia ትክክለኛና አስተማማኝ ት/ት ነክ መረጃዎችንና ነፃ የት/ት እድሎች በፍጥነት የምታገኙበት ሀገራዊ የቴሌግራም ገፅ #ለ ኢትዮጵያውያን https://t.me/Studentresult_bot #ለባህር ማዶ https://t.me/resultG12_bot

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
1 697
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በትግራይ ክልል በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያስተምሩ የነበሩ ሕንዳዊያን የታገደ የባንክ ሒሳባቸው እንዲከፈትላቸው በአዲስ አበባ የሚገኘው የሕንድ ኤምባሲ ለመንግሥት ጥያቄ አቅርቧል። ኤምባሲው ጥያቄውን ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና ለውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በደብዳቤ ማቅረቡ ታውቋል። ለመምህራኑ ያልተከፈላቸው የሰኔ እና የሐምሌ ወር ደሞዛቸውም እንዲከፈላቸው ኤምባሲው ጠይቋል። ወደ አዲስ አበባ የተመለሱ ከ50 በላይ ሕንዳዊያን መምህራን ከኤምባሲው ውጭ ሆቴል ተቀምጠው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ። #ዋዜማራዲዮ @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከጀርመኑ ቢውዝ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። በበይነ መረብ አማካኝነት የተፈፀመው ስምምነቱ፤ በተለይ በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል። ስምምነቱ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ የሰው ኃይል ለማሠልጠን መልካም ተሞክሮዎቻቸውን ለመለዋወጥ ያስችላቸዋል። #ሀዋሳዩኒቨርሲቲ @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 640 ሺህ ብር የሚገመት የአልባሳት፣ የፍራሽ እና ዊልቼር ድጋፍ ለደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል አድርጓል። ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ድጋፉን ለጠቅላላ ሆስፒታሉ ያደረገው ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በቀረበለት ጥያቄ መሠረት መሆኑ ተገልጿል። የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች የቦንጋ ዩኒቨርሲቲን በመወከል ድጋፉን የደባርቅ ሆስፒታል እና የሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት አስረክበዋል፡፡ 6 ዩኒቨርሲቲዎች መሰል ድጋፍ በቀጣይ ቀናት እንደሚያደርጉም ተገልጿል፡፡ #ደባርቅዩኒቨርሲቲ @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተቋሙ ተሽከርካሪ ከቡሌ ሆራ ከተማ በቅርብ ርቀት የቃጠሎ አደጋ እንደደረሰበት አሳውቋል። ዩኒቨርሲቲው ከተሽከርካሪው ቃጠሎ ጋር ተያይዞ ከዞኑ የፀጥታ እና ደህንነት እንዲሁም ከፍትህ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል። ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መግለጫ፤ "ለፖለቲካ ትርፍ የሚታትሩ አካላት የተቋሙን የልህቀት ጉዞ ለማደናቀፍ እና ከ3 ዓመት በፊት ወደ ነበረበት የሁከት ማዕከልነት ለመመለስ ሌት ተቀን እየሰሩ ይገኛሉ" ብሏል። "እነዚህ አካላት" የተቋሙ ተሽከርካሪ ተጋባዥ መምህራንን ይዞ በመጓዝ ላይ እያለ የቃጠሎ አደጋ እንዲደርስበት ማድረጋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ድርጊቱ በተቋሙ ላይ የተቃጣ የጥፋት ተግባር እንደሆነም ነው የጠቆመው። የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራን እና ሠራተኞች ከአባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአካባቢው ወጣቶች ጋር በመሆን ከዞኑ የመንግስት አመራሮች እና የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት ማድረጉን ገልጿል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ጥቃቱ "የፀረ-ለውጥ አካላት ተግባር እና የግል ጥቅም ፈላጊዎች ሴራ ነው" በማለት አውግዘውታል። ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ በተከናወነው የትምህርት፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና ኢንዱስትሪ ትስስር ሀገር ዐቀፍ ኮንቬንሽን ላይ ተሸላሚ እንደነበር አይዘነጋም። ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ የ2013 ዓ.ም አዲስ ገቢ፣ የክረምት እና የቅዳሜ እና እሁድ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል። #ቡሌሆራዩኒቨርሲቲ @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የምርምር ጆርናሎችን ማውጣት እንደሚጀምር አሳውቋል። የተቋሙ ጆርናል (JOLIS) ከ1996 እስከ 2006 ይታተም እንደነበር የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርሀነመስቀል ጠና (ዶ/ር) አስታውሰዋል። ተቋሙ በአፕላይድ ዩኒቨርሲቲነት መለየቱን ተከትሎ የምርምር ጆርናሎችን ማስጀመር እንዳስፈለገው ነው የተገለፀው። በቅርቡም አራት ጆርናሎችን ማውጣት እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚታተሙ 16 ጆርናሎች ለ3 ዓመታት የሚቆይ እውቅና ባለፈው ወር መስጠቱ ይታወሳል። @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር "የከፍተኛ ትምህርት እና ሥልጠና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አማካሪ ምክር ቤት" ሊያቋቁም ነው። የምክር ቤቱ አባል መሆን የሚፈልጉ የዘርፉ ሙያተኞች እስከ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም ማመልከት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አሳውቋል። ከፍተኛ ክህሎትና ልምድ ያላቸው በተግባር የተፈተኑ የቴክኖሎጂ ሙያተኞችን ብቻ በተቀመጡ መስፈርቶች አማካኝነት ለምክር ቤቱ አባልነት እንደሚቀበል ሚኒስቴሩ ገልጿል። አመልካቾች በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ተቀጥረው የሚሠሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል ተብሏል። አማካሪ ምክር ቤቱ የICT መሠረተ ልማት ማጎልበት፣ የከፍተኛ ትምህርት ዲጂታላይዜሽን፣ የሶፍትዌር ማበልፀግና መሰል ኃላፊነቶች ይኖሩታል። #MoSHE https://forms.gle/DcZ6QWCVzAKs9A2N7 @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አያኖ በራሶ (ዶ/ር) እና የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አሰፈጻሚ ፍሰሐ እሸቱ (ዶ/ር) ስምምነቱን ተፈራርመዋል። በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ተቋማት በጋራ ተጠቃሚ በሚያረጓቸው በርካታ ፕሮጀክቶች ላይ ይተባበራሉ። ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ኢኒሼቲቭ የአካባቢው የማስተባበሪያ ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን ደቡብ ክልል እና ሲዳማ ሞዴል ፐርፐዝ ብላክ ክልሎች ይሆናሉ። ሁለቱ ተቋማት በአካባቢው የሚተገበሩ ፕሮግራሞችን የሚደግፍ አሰተባባሪ ግብረ ኃይልም ያቋቋማሉ። ስልጠናዎችን መስጠት፣ የሥራ እድል መፍጠር እና ለምርምሮች የገንዘብ ድጋፍ ማፈላለግ ላይ ተቋማቱ እንደሚተባበሩ ተገልጿል። #ሀዋሳዩኒቨርሲቲ @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
በራያ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች በዚህ ሳምንት እንደሚወጡ ይጠበቃል። በዩኒቨርሲቲው 1 ሺህ የሚጠጉ የሌሎች ክልሎች ተወላጅ ተማሪዎች እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ። በትምህርት ላይ የቆዩት የራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፤ ረቡዕ ነሐሴ 05/2013 ዓ.ም የሴሚስተር ፈተናቸውን በማጠናቀቅ እንደሚወጡ የቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ምንጮች ተናግረዋል። አክሱም ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ባሳለፍነው ሳምንት በሁለት ዙር መውጣታቸው ይታወቃል። በተመሳሳይ በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የነበሩ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች ሐምሌ 30/2013 ዓ.ም እንደወጡ መዘገባችን ይታወሳል። በትግራይ ክልል የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሙሉ ለሙሉ ለማስወጣት በትኩረት እየሠራ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል። ከትግራይ ክልል የተመለሱ ተማሪዎች ቀጣይ እጣ ፈንታን በተመለከተ ሚኒስቴሩ ከተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማት ጋር እየሠራ መሆኑን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ መግለፁ አይዘነጋም። @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሀገር ዐቀፍ የሕግ መውጫ ፈተና ለ146 ተማሪዎች ሰጥቷል። በዩኒቨርሲቲው የሕግ ትምህርት ቤት ለሚማሩ 59 የሕግ ተመራቂ ተማሪዎች እና በሌሎች የሕግ ትምህርት ቤቶች የመውጫ ፈተናውን ወስደው ላላለፉ 87 ተማሪዎች ፈተናው መሠጠቱ ተገልጿል። የመውጫ ፈተናው ተመራቂ ተማሪዎች መሰረታዊ የሕግ ክህሎትና ዕውቀት ምን ያህል እንደቀሰሙ የሚመዘኑበት መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የሕግ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ጎድሴንድ ኮኖፋ ገልፀዋል። ተማሪዎች ለመመረቅ የመውጫ ፈተናውን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል። አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የሕግ መውጫ ፈተና መሰጠት ጀምሯል። #አምዩ @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...
መሀመድ ኡስማን (ዶ/ር) የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል። ዩኒቨርሲቲው አዲስ ፕሬዝዳንት ለመቅጠር አራት ዕጩዎችን ሲያወዳድር ቆይቷል። የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቀረቡትን ዕጩዎች የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድ፣ የስትራቴጂክ ዕቅድ ገምግሞ ቃለመጠይቅ በማድረግ መሀመድ ኡስማን (ዶ/ር) ከ92 በመቶ በላይ በማምጣት በሰፊ ልዩነት እየመሩ መሆናቸውን መግለፁን መዘገባችን ይታወሳል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) በፃፉት ደብዳቤም፤ መሀመድ ኡስማን ከነሐሴ 04/2013 ዓ.ም ጀምሮ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን አሳውቀዋል። አዲሱ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፤ ሦሥተኛ ዲግሪያቸውን ከህንዱ አንድህራ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት አጊኝተዋል። @tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Mostrar todo...