cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኤልናታ

ኤልናታ ( እግዚአብሔር ስጣታ)መንፈሳዊ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶች አዳዲስ መዝሙሮች መንፈሳዊ ግጥሞች ምስሎች ያገኛሉ Join and share adrgu https://t.me/Alentan_alentan_n

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
191
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ♥️
Mostrar todo...
ከተራ እና ጥምቀት ከተራ ከተራ ማለት "ከበበ" ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ውሃን መከተር ወይም ውሃ መገደብ (መዝጋት፥ ማቆም፥ ማገድ፥ ማጠር፥ ዙሪያውን መያዝ፥ መክበብ፥ መከልከል) ማለት ነው፡፡ በጥምቀት በዓል ዋዜማ በጥር ፲ ቀን ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ወይም ጉድጓድ ተቆፍሮ፤ ድንኳን ይተክላል፥ ዳስ ሲጣል ይውላል (ምክንያቱም ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብና የበረዶ ወራት ስለሆነ ቅዝቃዜውም በወንዞች አጠገብ ስለሚያይል በባሕረ ዮርዳኖስ፥ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ድንኳን ተክለው፥ ዳስ ጥለው ያድሩ ስለነበረ ነው)፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት የምንጮች ውሃ ደካማ በመሆኑ ውሃው እንዲጠራቀም ወንዶች ጉድጓድ እየቆፈሩ፥ ሴቶች ውኃ በእንስራ እየቀዱ ከወንዞችና ከምንጮች ውኃውን ይከትራሉ፥ ይገደባሉ (አሁን በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ ይገደባል)፡፡ የምዕመናኑ አብዛኛው ስራ ውሃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ አንድም በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ባሕር ሲሻገሩ ታቦቱን ያከበሩ (የያዙ) ካህናት ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ከወንዙ መሃል ቆመው ነበር ውኃውም እንደ ባሕረ ኤርትራ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበርና ይህንንም ለማስታወስ ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡አንድም ጌታችን በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የላይኛው ሸሽቶ እንደ ክምር ተቆልሏል (ከአዳም ጀምሮ እስከ መድኅን ዓለም መወለድ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ተቋርጦ ለመቅረቱ፥ ከአበው ወደ ውሉድ ላለመተላለፉ ምሳሌ)፤ የታችኛውም ወደ ታች ሸሽቶ በመድረቁ (የአዳም ኀጢአት ከሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ሆና ለመውደቋ ምሳሌ) ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡ውኃ የሚከተርበት ቦታ " ባሕረ ጥምቀት (ጥምቀተ ባሕር)" (የታቦት ማደሪያ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ውኃው የሚከተረውም በማግስቱ ጥር ፲፩ ቀን ለሚከበረው የጥምቀት በዓል መጠመቂያና የጥምቀትን በዓል ለማክበር እንዲሆን ነው፡፡ ሌሊት ማኅሌት ተቁሞ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ፥ ጠዋት ጸሎት ተደርሶ የሚጠመቅ ሕፃን ካለ እዚያው ውስጥ ይጠመቃል፡፡ ጐበዛዝትም ለቡራኬ ይዋኙበታል ምዕመናንም እንዲሁ ለቡራኬ ይረጩታል፡፡ ያ ስፍራ በዘልማድ ጥምቀተ ባሕር ተብሎ ይጠራል፡፡ ሥርዐተ ከተራ ታቦተ ሕግ ይዞ መጓዝና ወደ ወንዝ መውረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ቀድሞ በሙሴ ኋላ በኢያሱ መሪነትም ታቦተ ሕጉን ይዘው የዮርዳኖስን ባሕር መሻገራቸውንም ልብ ይሏል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁት ጊዜ ከስፍራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት፡፡ /ኢያ.፫፥፫/ እንዲል፡፡የከተራ ዕለት ድንኳኑ ተተክሎ፥ ዳሱ ተጥሎና ውሃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የደወል ድምፅ እንደተሰማ ከልጅ እስከ አዋቂ በነቂስ ተወጥቶ በዐፀደ ቤተ ክርስቲያንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ይሰበሰባሉ፤ የየአድባራቱና የገዳማቱ ታቦት በካህናት አማካይነት በወርቅና በብር በተንቈጠቆጠ መጐናጸፊያ እየተሸፈኑ በታቦት ጉዞ (በዝግታ) ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ይጓዛሉ፡፡ በዚህም ጊዜ፤ ባለ መስቀል መፆር ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ የያዘው ግን ከሁሉም ፊት ፊት እያለ ቀድሞ ይሄዳል፡፡ የወርቅ (ወርቀዘቦ) ካባና ላንቃ የለበሱና ጥላ የያዙት ቀሳውስትና መነኰሳት ከታቦቱ ጎን፤ መስቀልና ጽንሐሕ የያዙት ከታቦቱ በፊት ማዕጠንት እያጠኑ ይሄዳሉ፡፡ እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብሰ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ ድባብ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ በፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡ ወደ ባሕረ ጥምቀቱም ሲወረድ ካባ ላንቃ፥ ጥንግ ድርብ በለበሱ፥ የብር፣ የነሐስ፣ የወርቅ መቋሚያና ጽናጽል በያዙ በማኅሌታውያን መዘምራን ደባትር ሃሌታ፣ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ዝማሬና ሽብሸባ፣ በወጣት መዘምራን ደስታ፣ በወንዶች ሆታ፣ በሴቶች እልልታ ዲያቆናቱን ቀድመው እያጀቡ ይሄዳሉ፡፡ የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ ሕዝቡም "ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ" እንዲሉ እንደየችሎታው ያለውን ልብስ (ጃኖ፣ ለምድ፣ በርኖስና የመሳሰለውን) ለብሶና አጊጦ፥ ሽማግሌዎችና የጐበዝ አለቃዎችን በማስቀደም ታቦቱን በመከተል በስተኋላ ይሄዳሉ፡፡ ነገር ግን ሴቶችና ልጆች እንደፈለጋቸው ከፊትም ከኋላም ሆነው ይሄዳሉ፡፡ ባሕረ ጥምቀትም እንደደረሱ ታቦቱ በድንኳን አጠገብ ቆሞ የዓመቱ ተረኛ ደብር (የምራት ባለተረኛ) “ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥምቃት፤ በፍሥሓ ወበሰላም" (እግዚአብሔር ወልድ በሰላምና በደስታ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከሰማያት ወደ መጠመቂያው ወረደ) የሚለው ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተደርጎ ሲያልቅ ታቦቱ ወደ ድንኳኑ ይገባል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ ግሱን ለመቃኘትና ለማሸብሸብ፣ ማኅሌት ለመቆም፣ ቅዳሴ ለመቀደስና ሌላውንም ሥርዐት ለመፈጸም ኃላፊነት ያለባቸው ተረኛ ደብር (የምራት ባለተረኞች) ሲሆኑ ለቀጣዩ (ለከርሞ) ዓመት ተረኞች የሚሆኑና በአሁኑ ዓመት የምራት ባለተረኞችን የሚረዱት ገዳማትና አድባራት ደግሞ ‹‹አንሺዎች›› ይባላሉ፡፡ የከተራ ዕለት የየአጥቢያው ሕዝብ በየዓመቱ ተራ እየገባ ራት ከየአካባቢው ስለሚያመጣ ያ ሲበላና ሲጠጣ ከቆየ በኋላ ወዲያው የሌሊቱ ጸሎት (ስብሐተ ማኅሌቱ) በተረኛው ደብር ካህናት ተጀምሮ አገልግሎቱ መላ ሌሊቱን ሲካሄድ ያድራል (እንደ ቀጨኔ ባሉ ታላላቅና የሊቃውንት መፍለቂያ አድባራት ተረኛ ቢሆኑም /በጥምቀተ ባሕሩና በቤተ ክርስቲያናቸው ጭምር/ ባይሆኑም በቤተ ክርስቲያናቸው ማኅሌቱን ቆመውና ቅዳሴውን ቀድሰው ያድራሉ) ፡፡ ቅዳሴው የሚቀደሰው ከሌሊቱ ፯-፱ ሰዓት ነው፡፡ በከተራ ዕለት የሚከናወኑ ድርጊቶች ምሳሌነት አላቸው እነዚሁም፤ #ታቦቱ የጌታችን ምሳሌ #ታቦቱን አክብሮ ይዞ የሚሄደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ምሳሌ #ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ ምሳሌ #ታቦታቱን አጅበው የሚሄዱት ምዕመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩ ሰዎች ምሳሌ #ታቦታቱ በከተራ ዕለት ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸው መድኀኔዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተራውን ሲጠብቅ አድሮ መጠመቁን ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡››ማቴ፡ ፫፥፲፫ #ጥምቀቱ የሞቱ፤ አርአያ፤ የመቃብሩ አምሳል ነው፡፡
Mostrar todo...
ጥምቀት ጥምቀት በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒያ በግዕዝ አስተርዮ በአማርኛ መገለጥ ይባላል። ቃሉ በቀጥታ ሲተረጎም በውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መጥለቅ ማለት ነው። <<ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ሃጢአት፤ ሃጢያትን በሚያስተሰርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን>>/ጸሎተ ሃይማኖት/ጌታችን ሠላሳ ዓመት ሊሆነው ስድስት ወር ሲቀረው የሊቀ ካህናቱ የዘካርያስ ልጅ ዮሐንስ ከምድረ በዳ ወጥቶ ማስተማር ጀመረ። ይህንንም ትምህርት የጀመረው ከፈጣሪው በገኘው መልዕክት ነው። ሉቃ ፫፥፩ ዮሐንስም ከቆሮንጦስ ምድረ በዳ ወጥቶ በዮርዳኖስ ዙሪያ <<መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ>> እያለ በማስተማር የንስሐን ጥምቀት ማስተማር ጀመረ። ሉቃ ፫፥፫ ሕዝቡም ትምህርቱን በመቀበል ሃጢያታቸውን እየተናዘዙ በንስሐ ጥምቀት ይጠመቁ ነበር። ማቴ ፫፥፫ የትምህርቱን እውነተኛነት ባወቁ ጊዜ ዮሐንስን ክርስቶስ ነው ብለው ጠረጠሩ። ሉቃ ፫፥15 ዮሐንስም እንዲህ ሲል እውነቱን ነገራቸው <<እርሱም፦ነቢዩ ኢሳያስ እንዳለ የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ። የተላኩትም ከፈሪሳውያን ነበሩና። እንኪያስ አንተ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካይደለህ ስለምን ታጠምቃለህ ብለው ጠየቁት። ዮሐንስ መልሶ፦እኔ በውኃ አጠምቃለሁ፤ ዳሩ ግን እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሟል፤ እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ፥ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይልቅ የሚከብር ይህ ነው>> አላቸው። ይህ ነገር ዮሐንስ ያጠምቅበት በነበረው በዮርዳኖስ ማዶ በቢታኒያ በቤተ ራባ ሆነ። በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ሃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፤ አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ ከእኔም በፊት ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኗል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው። ዮሐ 1፥20 ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን!አሜን!
Mostrar todo...
የ2014 ዓ.ም የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥ ፩. ዘመን፡ ዘመነ ማርቆስ ፪. አዲስ ዓመት፣ ርዕሰ ዓውደ ዓመት፡ ቅዳሜ መስከረም 1 ፫. በዓለ መስቀል፡ ሰኞ መስከረም 17 ፬. ጾመ ጽጌ፡ ረቡዕ መስከረም 26 ፭. ጾመ ነቢያት (ጾመ ልደት)፡ ረቡዕ ኅዳር 15 ፮. በዓለ ልደት፡ ዓርብ ታህሳስ 29 ፯. ጾመ ገሃድ (ጋድ፣ ጾመ ድራር ጥምቀት)፡ ማግሰኞ ጥር 10 ፰. በዓለ ጥምቀት፡ ረቡዕ ጥር 11 ፱. ጾመ ነነዌ፡ ሰኞ የካቲት 7 ፲. ዐቢይ ጾም፡ ሰኞ የካቲት 21 ፲፩. በዓለ ደብረ ዘይት፡ እሁድ መጋቢት 18 ፲፪. በዓለ ሆሳዕና፡ እሁድ ሚያዝያ 9 ፲፫. በዓለ ስቅለት፡ ዓርብ ሚያዝያ 14 ፲፬. በዓለ ትንሳኤ፡ እሁድ ሚያዝያ 16 ፲፭. ርክበ ካህናት፡ ረቡዕ ግንቦት 10 ፲፮. በዓለ ዕርገት፡ ሐሙስ ግንቦት 25 ፲፯. በዓለ ጰራቅሊጦስ፡ እሁድ ሰኔ 5 ፲፰. ጾመ ሐዋርያት፡ ሰኞ ሰኔ 6 ፲፱. ጾመ ድኅነት፡ ረቡዕ ሰኔ 8 ፳. ጾመ ፍልሰታ፡ እሁድ ነሐሴ 1 ፳፩. በዓለ ደብረ ታቦር፡ ዓርብ ነሐሴ 13 ✥ የዘመን ባለቤት አምላካችን ዘመኑን የንስሓ ፍሬ የምናፈራበት የምናበረከትበት ያድርግልን✥ መስከረም / ፳፻፲፬ ከማኅበረ መድኃኔዓለም ሕዝብ ግንኙነት
Mostrar todo...
➱ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን-----2 ⤵️ አቅራቢ ፦ 💠 @EOTC_library 💠 @EOTC_library_bot
Mostrar todo...
ስርዓተ ቤተክርስቲያን .pdf1.77 MB
➱ የቤተክርስቲያን አስተዳድራዊ መዋቅር ⤵️ አቅራቢ ፦ 💠 @EOTC_library 💠 @EOTC_library_bot
Mostrar todo...
የቤተክርስቲያን_አስተዳደራዊ_መዋቅር_.pdf37.56 MB
➱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ታሪክ ⤵️ አቅራቢ ፦ 💠 @EOTC_library 💠 @EOTC_library_bot
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ቤተክርስቲያን_ታሪክና.pdf4.55 KB
➱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሥርዓተ ትምህርት ⤵️ አቅራቢ ፦ 💠 @EOTC_library 💠 @EOTC_library_bot
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ቤተክርስትያን_ሥርአተ_ትምህርት.pdf1.70 KB
➱ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን-----1 ⤵️ አቅራቢ ፦ 💠 @EOTC_library 💠 @EOTC_library_bot
Mostrar todo...
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን .pdf13.31 MB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.