cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የግጥም አለም

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
220
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

።።።።።።።። ሙግት።።።።።።። በተቃርኖ ሚዛን በስህተት ሜዳ በልክነኝ ዳገት እንዴት ያል ፍርጃ ነዉ የልብን ቋጠሮ ህሊና ሲሞግት እንደ ስስ መስታወት ኪዳን ሲሰባበር ሲሰነጠቅ ውስጡ በይሉኝታ ግዞት ለወላፈን ሲቆርብ የቃል ረመጡ በባዶ ሚለፈፍ ትርጉም የተነሳ ሰሚ ያጣ ጩኸት በጅቦች ጥብቅና በግ እንደመክሰስ ነዉ ለመዥገር ዳኝነት!! እንደው ነገሩ እንጂ በዘመን የሾረ ጊዜ ያጠለለው የውስጥ ጥሞና ስጋን የሚሞግት ልብን የሚፈትን ወዴት ነዉ ህሊና??? ✍ሳሮናዊት እንድሪስ
Mostrar todo...
ፍቅርና ደዌ ነጥሎ ያወጣኝ ከሰው ዘር ጉባኤ መንፈስ ያቆረበኝ ለገላህ ሱባኤ በዳዴ እሚያስኬደኝ እያወላገደ ከእልፍ ፍጥረቱ ላንተ እያረገደ ምንድን ነዉ ሰበቡ ምንድን ነዉ ምክንያቱ? ነፍስና ስጋዬ ባንተ እየተፋቱ ለሽምግልና እንኳን አንድ ቄስ መጥፋቱ!!!!!!!! ወቸው ጉድ ሆነልህ ሰርክ ያፌ ላይ ዜማ የአንደበቴ ልሳን በመደነቅ ብዛት እፍቅህ ይመስል ከልቤ ላይ ድርሳን ቃልን አይከሽንም ጉልድፍ ነዉ ምላሴ አቡጊዳዋ ነህ ፍቅርን ስትጀምር ለዚች ምስኪን ነፍሴ : የትኛው ጠንቆይ ነዉ አንተን የመተተኝ? የትኛውስ ቄስ ነው ባንተ የገዘተኝ? ከራሴ እያጣላ ካንተ ሚያፋቅረኝ አለሜ እባክህን ይህን መልስልኝ ፋቅር ነዉ ደዌ ነዉ እንዲህ የሚያደርገኝ?? ምዕራብና ምስራቅ እኩል እንደመድረስ የፈሰሰ ውሃን መልሶ እንደማፈስ በእጅ እንደመጠገን ሰባራን ብርጭቆ በጥፊ እንደመክተት አጥንትን አውልቆ እንዲህ እንዲህ አይነት ብዙ ያደርገኛል ቃል እየነፈገ ግራ ያጋባኛል!!! በስሜት እቃቃ ባሳብ ጢባጢቤ በሠፊው አለምህ አለሜን አጥብቤ ደጃፌን ዘግቼ ያልታዘዘ አጽዋም በስምህ ይዣለሁ ክተቴን አፍርሼ ቤተስኪያን ከሄድኩኝ በመቅደሱ እጣን መልክህን አያለሁ። .ምድርን ስትረሳ ነፍሴ ስትሻገር በካህናት ዜማ ካለም ስትሰወር በዝብርቅርቅ ምናብ ጥቂት ይታየኛል ርግጥ ነው ባልልም ገነት ይመስለኛል ተረኛ እየጠበክ ከአረንጓዴው በራፍ እልፍ ፍሬዎችን ስለኔ ስትቀጥፍ እጆችህን ስትዘረጋ ልቀበልህ ስመዘዝ አደናቅፎ አነቃኝ የአስቀዳሹ ምርኩዝ። ወቸው ጉድ ነጥሎ ያወጣኝ ከሰው ዘር ጉባኤ መንፈስ ያቆረበኝ ለገላህ ሱባኤ በዳዴ እሚያስኬደኝ እያወላገደ ከእልፍ ፍጥረቱ ላንተ እያረገደ ምንድነው ሰበቡ ምንድነው ምክንያቱ ነፍስና ስጋዬ ባንተ እየተፋቱ ለሽምግልና እንኳን አንድ ቄስ መጥፋቱ!!!!! ✍ሳሮናዊት እንድሪስ @uniqe_poem
Mostrar todo...
ይህ ዋርካ የተሰኘው እና ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለበጎ አላማ እናውል በሚል መሪ ቃል ወደ እናንተ የመጣ አዲስ ቻናል ነው። በቅርቡ በተለያዩ የድጋፍ ስራዎች ስራ እንጀምራለን እባካችሁ share በማድረግ እንበዛ ዘንድ ተባበሩን ።
Mostrar todo...
#ትነበብ_አትጎዳም 🙂 እስኪ አስተውሉት ፈጣሪ አያድርገውና ከቤተሰባችሁ ከጓደናችሁ ወይንም ለናንተ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች አንዳቸው በዚህ አስከፊ የኩላሊት በሽታ ቢያዙ ፈጣሪ ከዚህ ይጠብቀን እንጂ ውጤቱ አስከፊ ነው በትንሽ ጥረት ትልቁን የሰው ልጅ ህይወት መታደግ እየተቻለ በቸልተኝነት ስናልፍ ሁሌም እነዚህን ነገሮች እናስብ:- 1.የታማሚውን ስቃይ ጣር 2.የቤተሰቦቹን ስጋት ፣ሀዘን፣ጭንቀት 3.የገንዘብ እጦታቸውን ፣መጠማትና መራባቸውን በእኛው ላይ አድርገን እናስብ ቢያንስ ከቸልተኝነት ይመልሰን ይሆናል። ነገ ይሄ ህመም ወደኛ አሐመምጣቱን በምንም ማረጋገጥ አንችልምና እባካችሁ እንተባበር ። ⚠️ ዛሬ ያልደረስንለት ወገን ነገ አይደርስልንም!!!
Mostrar todo...
፨፨፨፨፨፨፨፨ባለዛር፨፨፨፨፨፨ የልቤን ድሪቶ የሽሽቴን ገዳም የአእምሮዬን ሐሳብ አይኔ ላይ ሲገለጥ ግንባሬ ላይ ሲጻፍ አፌ ሲንተባተብ ቋንቋዬን አድምጠው አንብበው ድርሳኔን ልብህ ይሄን ይገንዘብ ሌት የሚያቃትተኝ ዘረሰብ ተኝቶ የሚያንዘፈዝፈኝ የሚያርበተብተኝ ስሌቴን አዛብቶ እያንገጫገጨ ለጉድ እያስፏጨ ጥርሴን ከጥርሴ ጋር ግብር እንዳጠጡት ልክ እንደ መተት ዛር ያስጓራኛል ድንገት በቅጽበታት እድሜ ሳልፈልግ ጠርተኸኝ ከጥንቆላህ ድግስ በግድ ታድሜ። አንድ እውነት ልንገርህ ከልቤ ትርታ ከአእምሮዬ እልፍኝ የቆረበች ነፍሴን ከኪዳን አፋተህ ዶግማዬን ነጥቀኸኝ ስጋዬን ቀርጥፈህ ጽዋዬን ያጣጣምክ ቡዳ ነህ መሰለኝ ከእኔነቴ ክታብ በሀቅ ድርሳኔ እውነቱን ስናገር ሰደብሽኝ አትበል ስላንተ ሲለፍፍ የመተትክብኝ ዛር ሰው ከመሆን መቅደስ ከህይወት ላይ ቅኔ ሰሙ ሲብጠለጠል ህብረ ቃል የሌለው ባዶ ሽሙጥ ነዉ ለግብዛን ስዕል የመተትክብኝ ዛር ድንገት ሲያወራጨኝ ሲወስደኝ ከማዶ እሳት ያሳየኛል ለያውም ተንቀልቃይ በአጥንት ማገዶ ግፍ ያስቆጥረኛል እንደ ጽድቅ ክምር ልክ እንደ ጤፍ ነዶ በነገስታት መንበር ተጠምጥሞ አያለሁ አፈቅቤ ዘንዶ። ከሻገተ ውሀ ከለዘበ እሳት ከበከተ አፈር ከቆሻሻ ንፍስ ጭቃው ሲበጠበጥ ሰው መሆን ሲወጠር ዛሬን ነው የሚሆን እያለ የሌለ የመከነ ትውልድ በጥቂት ርምጃው ሺህ ጊዜ ሚጠልፈው የትላንት ገመድ እናልህ አለሜ ወስዶ ሲመልሰኝ የመተትክብኝ ዛር አጓርቶ ሲለቀኝ የተበተብክብኝ የጥንቆላህ ክምር አይኔ ተጎልጉሎ አመዴ ቡን ይላል ንጉሠ ነገሥቱን ተሳድቤ ይሆን? ውስጤ ይታመሳል በበሽተኛ ልብ የለፈለፈውን ጤነኛ አእምሮዬ ሊከልስ ይደክማል ዳሩ ምን ያደርጋል?? የሸፈተ ንግር ከአፍ ያፈተለከ የአንደበት ወለምታ በጲላጦስ እጥበት በደንባሮች አመጽ በሄሮድስ ፈገግታ እንደምን ሊመለስ ከጥንስሱ ማጀት ከምናብ ቋጠሮ የእድሜ ዘመን ልጓም የምጸት ቀኖና በሀቅ ተሰብሮ። ብቻ ግን አለሜ ወስዶ ሚመልሰኝ ከእንባ ማዕበል ከሙሾ ቅዳሴ ሰርክ የሚጋልበኝ ጨሌ የታጠቀው ቀንዳሙ ፈረሴ ህቅታ ሊያሰማኝ ሲቃ ሊያመረግድ አርቆ ወስዶኛል በቀንዱ ወጋግቶ በዶቃ አሽሞንሙኖ ገሎ ይመልሰኛል። በዚህ ሁሉ መሀል እኔን የደነቀኝ የጫንክብኝ ልክፍት ህማሙ ጣፍጦኛል እንኳንስ ለሰሚው ለባለ ታሪኳም ትንግርት ሆኖብኛል። ያስጓራኛል ድንገት በቅጽበታት እድሜ ሳልፈልግ ጠርተኸኝ ከጥንቆላህ ድግስ በግድ ታድሜ!! ✍ሳሮናዊት እንድሪስ @uniqe_poem @uniqe_poem
Mostrar todo...