#ይህንን_ያውቁ_ኖሯል! 🌟
👉ወንድ ሴትን መጨበጥ ሴትም ወንድን መጨበጥ #በእስልምናች_እንዴት_ይታያል❓
መልእክተኛው ﷺ ኢማም ዳረ ቁጥንይ በዘገቡት ሀዲስ ላይ እንደተናገሩት
((لأن يطعن أحدكم بحديدة قي رأسه خير له من أن يمس امرآة لا تحل له))
«ከናንተመካከል አንድኛችሁ
የማትፈቀድለትን ሴት ከሚጨብጥ
በብረት ጭንቅላቱን ቢወጋ ይሻለዋል»
አሁንም በሌላ ዘገባ እንደመጣልን ነብያችን ﷺ
(( ﻷﻥ ﻳﻄﻌﻦ ﻓﻲ ﺭﺃﺱ ﺃﺣﺪﻛﻢ ﺑﻤﺨﻴﻂ ﻣﻦ حديد
خير ﻟﻪ ﻣﻦ ﺃﻥ ﻳﻤﺲ ﺍﻣﺮﺃﺓ ﻻ ﺗﺤﻞ ﻟﻪ) )
«የማትፈቀድለትን ሴት ከሚነካ የአንደኛችሁ ጭንቅላት በብረት መርፌ ቢወጋ ይሻለዋል» #ጦበራኒ_ዘግበውታል
ነገር ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ቡዙ መስሊም ወንዶችና
ሴቶች የማይፈቀድላቸውን ሰዎች በመጨበጥ እራሳቸውን እየጎዱ ይገኛሉ።
ወንጀል መሆኑን ስነገራቸው ከመራቅ ይልቅ ያልሆነ ምክኒያት መደርደርን ይመርጣሉ
ምክኒያት አድርገው ከሚያቀርቧቸው ነገሮች መካከል ለአብነት ብንመለከት
*①"ልባችን ንፁህ ናት" ይላሉ!*
👉 የነዚህ ሰዎች ልብ ከነብዩﷺ ልብ የበለጠ ንፁህ ናትን?
👉ለመሆኑ በዚህ ዓለም ላይ ከነቢዩ ሶለ ሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የበለጠ ልቡ ንፁህ የሆነ ሰው አለን?
👉ከርሳቸው በላይ ልቡ መልካም ነገር የሚያስብ ሰው አለን?
ይህ ከመሆኑ ጋር *እኔ ሴቶችን(ያልተፈቀደላቸውን) አልነካም ነበር* ያሉት።
②↠"ይህንን መተው ለኛ ሀገር ይከብዳል"*
እስልምና የመጣው ነብያችንም ﷺ
የተላኩት ለዓለም እንጂ ለሳውዲ፣ ለኢትዮጲያ፣ ለዓረብ፣ ለፈረንጅ፣ ለጥቁር ለሀብታም፣ ለድሀ ብለው በመለየት አይደለም አላህ እንዲህ ይላል:-
*ﻭﻣﺎ ﺃﺭﺳﻠﻨﺎﻙ ﺇﻻ ﺭﺣﻤﺔ ﻟﻠﻌﺎﻟﻤﻴﻦ*
«ለዓለማት እዝነት ቢሆን እንጂ አላክንህም»
☆ስለዚህ ሸሪዓችን ማንንም ሳይለይ ሁሉንም ይመለከታል!
እስቲ ሁላችንም አንዴ ቆም ብለን እናስተውል በሚስማር ጭንቅላታችን ተወግቶ በአንድ ጎን ገብቶ በሌላ ጎን ቀዶ መውጣቱ የማትፈቀድን ሴት ከመጨበጥ ይሻላል መባሉ
አያሰደነግጥምን?
አላህ እርሱን የሚፈራ ልብ ይስጠን!!!
በመጀመርያ ደረጃ መጨበጥ የተፈቀዱ ዘመዶች እንመልከት
#ውድ_ወንድሜ
አክስትህ፣የአባትህ አክስት፣ ሴት አያትህ በእናትም በአባትም ፣እናትህ፣ እህትህ፣ የወንድምህ ልጅ፣ የእህትህ ልጅ፣ ሚስትህ፣ ልጅህ፣ አክስትህ፣ የሚስትህ እናት ለአንተ ያለ ስሜት እንድትጨብጥ የተፈቀዱ ሲሆን።
#ለውዷ_እህቴ
አባትሽ፣ የእናትሽን አጎት፣የአባትሽን አጎት ፣አያትሽን በናትም ባባትም፣ ወንድምሽ፣ አጎትሽ፣ ባልሽ፣ ልጅሽ፣ የወንድምሽ ልጅ፣ የእህትሽ ልጅ፣ የባልሽ አባት እነዚህን ያለ ስሜት መጨበጥ የተፈቀዱልሽ የቤተሰብ አባላት ናቸው።
#ውድ_ወንድሜ ሆይ! እንድትጨበጥ የተከለከሉ ዘመዶችህ እወቃቸው👇
❌የአጎትህ ልጅ ሶቶቹን(በእናትም በአባትም)
❌የአክስትህ ልጅ ሴቶቹን (በእናትም በአባትም)
❌የወንድምህ ሚስት
❌የሚስትህ እህት
👆እነዚህ ሴቶችና ሌሎችንም(ባእድ የሆኑትን) ልትጨብጣቸው አልተፈቀደልህም!
#እህቴ_ሆይ! መጨበጥ የተከለከሉ ዘመዶችሽ እወቂያቸው👇
❌የአጎትሽ ልጅ (በእናትም በአባትም)
❌የአክስትሽ ልጅ (በእናትም በአባትም)
❌የባልሽ ወንድም
❌የእህትሽ ባል
👆እነዚህና ሌሎችም ወንዶች ልትጨብጫቸው አልተፈቀደልሽም!
#ወንድምና_እህቶቼ ሆይ! ይህ በወንጀል ላይ ችክ ማለታችን እስከመቼ ነው? ቀብር እስክንገባ? የሰዎችን ወሬ እየፈራን የአሏህን ህግጋቶች እንጥሳለን እንዴ?!
አንተን፣ እኔን ፣እሷን ፣ሁላችንንም የፈጠረንን ለዓለማቱ ጌታ ያለን ፍራቻ የታል?
☞ሰዎች እያፈርን
☞የሰዎችን ጌታ አናፍርምን
አላህ እርሱንና መልክተኛውን ﷺከሚታዘዙት መልካም ባሮቹ ያድርገን !አሚን 🤲🤲