cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የግጥም ጥግ💓💟🙌

ለሁሉም ይድረስልኝ

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
147
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ቁመቱ ስለረዘመ ነገን ማየት የሚችል እየመሰለው የሚንጠራራ ብዙ ቀውላላ አለ አሉኝ ?? እውነት ነው እንዴ !?? ደግሞ ይህን ጽሑፍ የፃፈው ሰው ቁመቱ አጭር ነው በሉኝ። አይደለሁም መካከለኛ ነኝ ። ረጃጅሞችን ወደ ላይ አንጋጥጨ ለማየት አጫጭሮችን ደግሞ ጎንበስ ብየ ለማየት መሃል ላይ የተፈጠርኩ😂😂😂😂😂 እና ምን ለማለት ፈልጌ ነገን ማየት የሚችል የፈጠረህ ብቻ ነው ። አያለሁ ብለህ ከተንጠራራህ ግን እየተበትክ ነው ማለት ነው 😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂 መልካም ጊዜ ። ፊደል አስር ነኝ በጉዞ ላይ ሆኜ
Mostrar todo...
" ብልጡ ፍቅርሽ ሲያጃጅለኝ የጫርኩት" (መልአኩ ስብሐት ባይህ) ****************************** የውበት ዳርቻ የአድማሷን መባቻ። አንቺን የእኔን ጠሀይ የተድላዬን ሰማይ። ልስልሽ ፈለጌ ምስልሽን አጣሁት ከምስሌ አድርጌ። ከስብዕናሽ ጠለል ከሀሳብሽ ከፍታ አየሁኝ በሳቅሽ ጨረቃ ተከፍታ። ጨረቃ ጨረቃ ጨረቃ ጨረቃ ያቺ ድንቡል ቦቃ አንቺ ስትፈዢ ይሆን ምትነቃ? አንቺ እንደሁ አትፈዢ ከቶ አደበዝዢ በመውደድሽ ሸጠሽ ታደርጊያለሽ ገዢ። ያውም በሠላሳ ያውም በሠላሳ ክደሸ ስታበቂኝ ምንም እማልመስልሽ በገደልሽኝ ቁጥር ሳትሞች ምሞትልሽ በገፋሽኝ ቁጥር ሳትወድቂ ማነሳሽ በሸጥሽኝ መጠን ልክ ለመክሰር ምገዛሽ ይሁዳ ነሽ አንቺ እኔ ደግሞ ጌታሽ። @poem_with_mela @poem_with_mela
Mostrar todo...
#ደፋሮች 👉👉👉👉👉👉👉👉👉 ዕልፍ አስመሳዮች አዉቅልሀለዉ ባዮች መሳይ ነገረኛ ነገር ቢስ ሰነፎች በቀዬ መንደሩ ሞሉብን በርካቶች ~~~~¡~~~~~~~~~~~~ እኔ እያለሁ! ብሎ ለብቻ መደንፋት ምንም ሳይከዉኑ ህልማቸዉን ማዉራት 💨💨💨💨💨💨💨💨💨💨💨💨💨 አለሁልህ ያሉት አሉልኝ እያለ ስንቱ በህልመኛ እምነቱ ቀለለ * ይመስሉ የነበሩ ሩህሩህና አዛኝ ወሬ ብቻ ሆነዉ ብክንክን አላዛኝ በቀቢሰ ተስፋ አንዳችም ላይገኝ ሆኑ ቃለ በላ ብልጣብልጥ ሞኛሞኝ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 እዚህ ዉሀ ይዙዉ እዛ'ሳት ሲጭሩ እዚህ ደም ሲጠርጉ እዛ ሲቧጭሩ እዚህ ረሀብ የለም ሁሉ ጠግቧል ሲሉ በማስመሰል ብቻ በጣሙን ሲጥሩ ምነዉ ይህን ያህል ድፍረትን ደፈሩ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 አሚር ከማል "SHARE" @YegtmMaebel
Mostrar todo...
ያፍቃሪ ሰው ትንፋሽ *** የስልኬን የጥሪ ድምፅ አናጥቤ ወደ ጆሮዬ ለጠፍኩት፡፡ ጎረቤቴ ብሌን ነች የደወለችው፡፡ ‹‹ሄሎ ብሌንሻ›› … መልሷ ራቀኝ! ‹‹ሄሎ አይሰማሽም?›› … ፀጥ ያለ ነገር! ‹‹ኸረ ሄሎሎሎሎ ሴትዮ!›› … ዝም! ጭጭ! … የሆነ ለመረበሽ የተሰነቀረ የሚመስል የንፋስ ሹክሹክታ የሰማሁ መሰለኝ፡፡ ዘጋሁት!! : : ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የቤቴን በር ከፍታ ብሌን ብቅ አለች፡፡ ‹‹ምን ሁነህ ነው ስልኬን የዘጋኸው?›› አለች እንደ አራስ ነብር በቁጣ ጥርስ ቦጫጭቃ ልትጥለኝ እና ተወርውራ ልታንቀኝ እየቋመጠች፡፡ የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ!! አሉ የተንጣጣባቸው ‹‹ያምሻል እንዴ! ሄሎ ብል ሄሎ ብል ሄሎ ብል መች መልስ ትሰጫለሽ?›› ተንጣጣሁ!! . . አሁንም መልሱን ትታ… ከጭኖቼ ላይ ተቀምጣ በጆሮዬ በኩል ተጠግታ ትንፋሿን ደጋግማ ለቀቀች፡፡ ‹‹ሴትዮ ጤና አጣሽ እንዴ? ምን ፈልገሽ ነው ጆሮዬ ላይ…›› እጄን በመዳፏ አፈነችውና መተንፈሷን ቀጠለች፡፡ ከአፌ የሚሾልኩትን ቃላት ከመዳፏ ለማስፈንጠር አንጣጣሁ፡፡ ልክ እንደ ፈንዲሻ!! ግን ታፍነው ቀሩ፡፡ : : መዳፏን ከአፌ አንስታ ‹‹እ! ትንፋሼን እንዴት አየኸው?›› አለችኝ ፈገግ ብላ ‹‹አላየሁትም!! ትንፋሽ ደግሞ ምኑ ይታያል?›› ምንድን ነው እንዲህ ያበሳጨኝ? እኔ ላይ መተንፈሷ ወይስ የእኔን ትንፋሽ ማፈኗ? ‹‹እሽ እንዴት ሰማኸው?›› ‹‹እንደተነፈሽው›› ‹‹ሂድ እሽ ማስጠያ!›› ያን አስመሳይ ኩርፊያዋን ፊቷ ላይ ለበደች፡፡ . . ‹‹እሽ ስትሰማው የአፍቃሪ ሰው ትንፋሽ ይመስልኃል?›› ‹‹እርፍ! ብለሽ ብለሽ ትንፋሽን የአፍቃሪ፣ ያለ አፍቃሪ እያልሽ መከፋፈል አሰኘሽ!! ሆኦኦኦኦ!!›› ‹‹እኔኮ #ሰለሞን_ሰሀለ #ያፍቃሪ_ሰው_ትንፋሽ የሚል መፅሀፍ በቅርቡ አሳትሞ ሊያስመርቅ መሆኑን ስለሰማሁና ሰሞኑን ፍቅር ቢጤ እየተሰማኝ ስለሆነ በትንፋሼ እንድታረጋግጥልኝ ብዬ ነው፡፡›› ‹‹እ!›› : : በድንጋጤ ትንፋሼን ውጬ ወጣሁ፡፡ ከቤቴ!! . . . መቼም ያፍቃሪ ሰው ትንፋሽ የሚተነፈሰው ለተፈቃሪ ሰው ነው፡፡ (መጠርጠር አይከፋም!!) : አቤቱ ከዚህ ጉድ ሰውረኝ!! : : : ሶልዬ እንኳን ለዚህ አበቃህ!! ትንፋሽህን ለተፈቃሪ ወረቀቶችህ ተንፍሰህ ለማስነበብ!! … .. . #ቴቄልን እየገዛን፣ እያነበብን ኦገን!!!!!!!! . Daniel kebede "SHARE" @YegtmMaebel
Mostrar todo...
#ለቆርቆሮእኛዎች ቆርቆሮ ነን መሰል በንፋስ በጠጠር በዝናብ የምንጮህ ጫጫታ የምንወድ ኮሽ ባለ ቁጥር <><><><><><><> ቆርቆሮ ነን መሰል በሙቀት የምንግል በብርድ የምንሰልል <><><><><><><> ቆርቆሮ ነን መሰል መንጫጫት የምንወድ ሳንወነጅል 'ምንፈርድ ምንበጥስ የፍቅር ገመድ <><><><><><><><><> ቆርቆሮ ነን መሰል ያዉም ብስ የበዛዉ ጥቂቷን ጠብታ እልፍ የምናፈሰዉ ቆርቆሮ ነን መሰል ኳ ባለብን ቁጥር ብዙ የምንጫጫዉ <><><><><><><><><<><><> አዎ ቆርቆሮ ነን ጠጠር ሲወድቅብን ማጋነን የምንወድ አለት ነዉ እያልን ~~~~~~~~~~~~ አዎ ነን ቆርቆሮ መጮህ የምንችል 'ማናደምጥ ደንቆሮ ቆርቆሮ ነን መሰል የሆንን ጫጫታ ደመና የምንመኝ ፀሀይ ስትወጣ ዝናብ 'ሚያበሳጨን ሀሳበ መላጣ <><><><><><><><><><><><> በቃ ቆርቆሮ ነን አመለ ወልጋዳ ፈር ለሌለዉ ነገር ብዙ የምንዳዳ አንድ ብቻ አጥፍቶ የምንጮህ መደዳ 😥😥😥😥😥😥😥😥😥😥😥 በቃ ቆርቆሮ ነን እንመን ግድ የለም ኮሽ ባለ ቁጥር ስንጮህ የምንከርም 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 አሚር ከማል @amewegitm 'SHARE' @YegtmMaebel
Mostrar todo...
(ተይ አትሚ' ኝ) ገበሬ ነኝ እያልሽ ፆምሽን አያለው ጎተራሽም ሲታይ በሃሜት ሙሉ ነው ግና ሰብል ነው እያልሽ ስትዘሪ ከርመሽው ተይ ያለሽን ሁሉ መሬቱን ነጥቀሽው ሀሜት እሕል ላይሆን ፍሬውን አጣሽው ሀሜት እሕል ቢሆን ተዘርቶ ቢበቅል ተፈጭቶ ተቦክቶ ተጋግሮ ቢበስል በረሀብ ባልታረዝሽ ሆድሽም ባልፆመ ጎተራሽ በሞላ ጆንያሽ በቆመ ግና አይደለማ እውነታው ሌላ ነው አፍሽ እየዘራ ሆድ እየሞተ ነው የታረሰው መሬት ሀሜት የዘራሽበት ፍሬውን ሳይሰጥሽ ምላስሽ ደክሞበት ሌላ ይፈልጋል አንቺን ሊዘራበት ይኼም ይከተላል አጭዶ ላይበላበት እንዲህ ነው እውነታው ያንቺ ገበሬነት ለሆድ እየኖሩ በአፍ ሚዘራበት ሌተቀን ተለፍቶ አዝመራ የሌለበት ይሄ ነው እውነታው እውነታውን ኑሪ ገበሬ ነኝ እያልሽ ፆም አትደሪ እሕል ለመፈለግ ሀሜትን አትዝሪ!! (አዩብ ኻዛሊ) "SHARE" @YegtmMaebel
Mostrar todo...
(ተይ አትሚ' ኝ) ገበሬ ነኝ እያልሽ ፆምሽን አያለው ጎተራሽም ሲታይ በሃሜት ሙሉ ነው ግና ሰብል ነው እያልሽ ስትዘሪ ከርመሽው ተይ ያለሽን ሁሉ መሬቱን ነጥቀሽው ሀሜት እሕል ላይሆን ፍሬውን አጣሽው ሀሜት እሕል ቢሆን ተዘርቶ ቢበቅል ተፈጭቶ ተቦክቶ ተጋግሮ ቢበስል በረሀብ ባልታረዝሽ ሆድሽም ባልፆመ ጎተራሽ በሞላ ጆንያሽ በቆመ ግና አይደለማ እውነታው ሌላ ነው አፍሽ እየዘራ ሆድ እየሞተ ነው የታረሰው መሬት ሀሜት የዘራሽበት ፍሬውን ሳይሰጥሽ ምላስሽ ደክሞበት ሌላ ይፈልጋል አንቺን ሊዘራበት ይኼም ይከተላል አጭዶ ላይበላበት እንዲህ ነው እውነታው ያንቺ ገበሬነት ለሆድ እየኖሩ በአፍ ሚዘራበት ሌተቀን ተለፍቶ አዝመራ የሌለበት ይሄ ነው እውነታው እውነታውን ኑሪ ገበሬ ነኝ እያልሽ ፆም አትደሪ እሕል ለመፈለግ ሀሜትን አትዝሪ!! (አዩብ ኻዛሊ) "SHARE" @YegtmMaebel
Mostrar todo...
............. ስንቅና ማህሌት ............. _ © ሲራክ ወንድሙ _ . እኩለ ሌሊት ላይ - መርዶ እንዳባተተው ፥ እኩይ ዜና ሰምቶ - ቀልቡ እንዳቃተተው ፥ በሀሳብ ናውዤ...... በምናብ ተጉዤ..... ሽሚያ እንደበዛበት የሰንበቴ መና ፥ በናፍቆትሽ ሳሳው ፥ በትዝታሽ ጠናው ዘንድሮም እንዳ'ምና። # እንደኮከብ ድምቀት - እንደጥቢ ፍካት ፥ እንደብርሃን ዥረት - እንደሞገድ ንጣት ፥ የሚያበራ አይንሽን - የተራበ አይኔ ፥ ከስጋው ተኳርፎ - ገብቶ ከምናኔ ፥ አለም እንደናቀው - አለም እንደናቃት ፥ እንቅልፍም በኔ ላይ - መሪር ኩርፊያ አላት። . ኦኦኦኦኦ!.. . ሰማኒያ አሀዱ ፥ የቅዱሳን መፅሀፍ - አንዱ ሆኖ በአንዱ ፥ ከመስኮቱ ምዕራብ - ከማዕዘኑ ቀዬ ፥ ይታየኛል ድርድር - ከወደ ግርጌዬ ። . አሁን.... ዘራሰብ በልማድ ከትንሽ ሞቱ ጋር ግብግብ ገጥሟል። እኔ... ትንሽ ህመም አማኝ ፥ ትንሽ ሞት ረስታኝ ፥ ፍቅርሽን እያልኩኝ - እምከነከናለሁ፥ በዚህ ድኩም ሌሊት - አንቺን አስባለሁ። . ኤዲያ! . የትዝታን ክቡድ - ቀንበር ፣ የናፍቆትን ግዙፍ - ሞፈር ፣ አጥምጄ በላዬ - በምኞት ቤት ድግር፣ በኑረት ክንዴ ላይ - እየወዘወዝኩት ፣ የእምባዬን ስል ጅራፍ - እያወናጨፍኩት፣ የነብሴን ውብ ጋራ - ብራብሽ አረስኩት ። . እህ.... . እኔ ቀድሶ አዳሪ - የደብር ሲምቢሮ ፣ አንች የባላባት ጭራ - የከበርቴ ሮሮ፣ እንደ የኔታ ጋቢ - ውብ ገፅሽ ሳያድፍ፣ በሳቅሽ ቅላፄ ቅኔ ሳይዘረፍ፣ ምንጯ ስር ብቅ በይ - እኔም ከዛው አለው፣ ለሀሴትሽ ጉቦም - ዋሽንቴን ይዣለሁ። . እምም... ኩርማን ለማደሪያ - ሰው አጥር ታክኬ ፣ እንደ ፀሎት ምልጃ - አይኔን ወዲያ ልኬ፣ የህዝቡን መማረር - ይሁን ብዬ ድኬ፣ እንደ በላኝ ቅማል - በደል ሲያሳክከኝ፣ ቀስሳለሁ ብሎ ደብር መቀላወጥ እንደ ውርደት ታየኝ። . ኦኦኦኦ!.. . ያቺ ከሲታዋ - ውብ አኩፋዳዬ... ግብር እንደጠሩት - እንደ ሆዳም እረኛ፣ ፍርፋሪ ሞልቷት - ጠጋግባ በማኛ፣ ጀምበር ስታቅላላ - ከደብር ብትደርስም፣ ለሚያያት ነው እንጂ - እንደእኔ ለኖራት .. በጭራሽ አትደንቅም። . ለምን?? . እንደጭን ስር ቅማል ፣ ሀሜት ያሳክካል ። አሽሙር ያሳምማል። . አምና በዚህ ጊዜ - ከዚያ ከአረን-ጓዴ፣ ግራሩ ስር ቆሜ - በአርባ ጦም ሁዳዴ፣ እህል ውሃ ሳልል - አይቼሽ ለመግደፍ፣ ከእግዜር ጋር ቅያሜ - ለመያዝ ስጣደፍ፣ ለውብ አይንሽ ብዬ - በሀፂያት ታምሜ ፣ ከእርኩስ ሀሳብ ዳራ - ምልዋጤን ደግሜ፣ እባብ ሆኜ መጣው .... አባትሽ ገደሉኝ - አፈር ልሼ ነቃው። . ደግሞም በነጋታው.... . ሰው መሆን ውበቴን - ፍቅርሽ ሲያስመንነው ዳግም እርግብ ሆኜ አጥርሽ ላይ ብቆም የእረኞች ወንጭፍ - ቃታው የከረረ ፣ ጠጠር ተወርውሮ - አክናፌን ሰበረ። . ኦኦኦኦ.....! . ሰማኒያ አሀዱ ፣ የቅዱሳን መፅሀፍ - አንዱ ሆኖ በአንዱ ፣ ከመስኮቱ ምዕራብ - ከማዕዘኑ ቀዬ፣ ይታየኛል ድርድር - ከወደ ግርጌዬ። . አሁን..... . ወዲያ ወዲያ ወዲያ ወዲያ ከአምባው ላይ፣ ወዲያ ከደብሩ ላይ፣ ወረብ አሰካክሮት - ደወል አስደንግጦት ፣ ከቤተ መቅደሱ - ደርሶ የሚሸፍት፣ ይሰማኛል ለእኔ - የሌ'ቱ ማህሌት፣ የዲያቆናት ዜማ - የካህናት ፀሎት። ዜማው ምጥን ያለ እንደድምፅሽ ቃና ፣ እንደወፍ ዝማሬ - እንደመላዕክት ዳና። ጥፍጥ ፣ እርግት ያለ - እንደ እንደአይንሽ ብርሃን ፣ ኑረትን የሚያሞቅ - የነብስ ሀሴት ኩርማን ። . እናልሽ.. . አሁን በዚህ ሰዓት.... አሁን በዚህ ቅፅበት... የምኩራቡ እጣን - በሰመመን ሸቶኝ፣ እጅብ ያለ ጉሙ - ሲንገዋለል ታይቶኝ፣ የወረቡ ስምረት - በቁሜ አስክሮኝ፣ የቅዳሴው ዜማ - በመዳፉ ዳሶኝ ፣ ከድኩም አልጋዬ - ፈገግታሽ አብርሮኝ ፣ ካልጠራሁት አለም ከኖርኩበት ቀዬ - አድማስ አሻገረኝ። . እና . ደብሬን ክጃለሁ - ደብር ነሽ ለነብሴ ፣ ቅዳሴም ትቻለሁ - አንቺው ነሽ ምላሴ። . እናም ..... . እንደየኔታ ጋቢ ውብ ገፅሽ ሳያድፍ ፣ የእድሜሽ ጀምበር ጠልቆ ውበትሽ ሳይረግፍ ፣ በሳቅሽ ቅላፄ ቅኔ ሳይዘረፍ ፣ ምንጯ ስር ብቅ በይ እኔም ከዛው አለው ፣ ለሀሴትሽ ጉቦም ዋሽንቴን ይዣለው። ////////////___ ስንቅና ማህሌት ////////// _ _ © ሲራክ ወንድሙ ____ ታህሳስ ፳፻፲፫ ዓ.ም @yegtmMaebel @yegtmMaebel
Mostrar todo...
"ይድረስ ለኔይቱ እንስት" (መልአኩ ስብሐት ባይህ) ******************** እቴዋ መቀነቴ ድምቅ ዓለሜ በግብርሽ ክሳሜ እምዘልቅ ቆሜ ወና ነው ሌማቴ ከንቱ ነው ባዶነት እኔን እምትወክል ሰርጻ እማትገባበት በአፍላ ጅማሮ የአፍታ እድሜዬን ፈትለሽው ላትቋጪው አልቦ ክዳን ሕልሜን እቴዋ መቀነቴ አንቺ የሕዋሴ ባህር ኃዳፍ የሥጋ ነፍሴ መዳፍ በሸክላ ሰሪው የአፈር ክምር ባንቺነትሽ ግብዓት እኔነቴ ሲጣመር ምነው ግና? ምነው ግና? ስንፍ ሆነብኝ ሳልጀምረው ያ ውዳዴሽ አበቃብኝ። ምነው ግና? ምነው ግና? በፍቅራችን ቀነ ውልደት ሕልፈታቱ የታወጀ በቅምጥናው አሉታነት ለዘመናት የደረጀ ምነው? ምነው? ቅ.....ር.....ባ.....ታ.....ች.....ን ባጀ ። @poem_with_mela @poem_with_mela
Mostrar todo...