cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የፍቅር ወላፈን

የፍቅር ወላፈን ግጥሞች በሊንካችን ተቀላቀሉን ሁሌም ደስተኛ ትሆናላችሁ በቻናላችን: 🏇🏼ግጥሞች 🏇🏼ተከታታይ የፍቅር ታሪኮች 🏇🏼አጫጭር ቪዲዮወች 🏇🏼ትረካወች Love👉 can be introduced a lot ❤ ❤ ❤ ❤ ❤ ሁሌም ስለፍቅር ይቀነቀንበታል @የፍቅር ወላፈን

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
373
Suscriptores
Sin datos24 horas
-57 días
-1930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
ካንቺ ጋ ነው ማርጀት የምፈልገው !! የፊትሽን ከለር ፣ ሳቅሽን ፣አይንሽን ፣ሃዘኔታሽን ኩርፊያሽን ፣ እንዳለየሽ ሆነሽ የምታልፊኝን  ሁሉ አፈቅረዋለሁ ፦ ስትሞኚልኝ፣ ስትናፍቂኝ፣ ስታዝኝልኝ ፣ ስታስቢልኝ ስትቆረቆሪልኝ መባረኬ ይዳሰሰኛል ፦ እንቅስቃሴሽ ይመለከተኛል ስል፣  እንደሚመለከተኝ ስታረጋግጪልኝ ፣ስታስፈቅጂኝ ፣ስቆጣሽ መለሳለስሽ መቅለስለስሽን አፈቅረዋለሁ ፦ መውደዴን ስለሚገባሽ ፣ ናፍቆቴን ችላ ስለማትይው ፣ ስለምታከብሪኝ ፣ ስለምትሰሚኝ ፣ ህልሜ ላይ ሳተኩር በቀስታ ፍላጎቴን ስለምታቀብይኝ ፣ ከማንም ጋ ስለማታወዳድሪኝ ፣ ሳጣ እና ሳገኝ የምቶኝልኝ ስለማይለያይ  አፈቅርሻለሁ፦ ኤጭ 😍 ማፍቀርን የሚያክል በረከት የትኛው ነው ❤ @Yefiker_Gojo💌@Liduu_29
Mostrar todo...
00:12
Video unavailableShow in Telegram
13.81 MB
01:32
Video unavailableShow in Telegram
14.04 MB
Mostrar todo...
ደምስ ጠቅላላ የሴራሚክ ስራ

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች 1. ሴራሚክ 2. ማርብል እና ግራናይት 3. ደረጃ 4.ኘላስቲክ ታይልስ በጥራተትና በፍጥነት ሰርተን እናስረክባለን

E- bidre (ኢ ብድር) አባል በመሆን ወደ ከፍታ ማማ በጋራ.... @tesfa273
Mostrar todo...
4_5989957520683175858.mp310.99 MB
ድንግል ነሽ ልብ ይሰብራል😭😓 (ኑዕማን ኢድሪስ) (ተራኪዋ ሂክማ ናት) ከረፋዱ 4:25 እንደወትሮዬ ፌስቡክ ስገባ አራት መልዕክቶችን አገኘሁ። ሁለቱ የቅርብ ጓደኞቼ ሲሆኑ አንዱ በፌስቡክ የማዉቀዉ ኡስታዝ የጠየቅኩትን የፈታዋ ጥያቄ የሰጠኝ ምላሽ ነበር። ሌላኛዉ ደግሞ አልፎ አልፎ 'ሰላም' ይለኛል ነገር ግን እምብዛም ትኩረት ሳልሰጠዉ ለጻፈዉ ነገር ምላሽ እሰጠዋለሁ። እንደተለመደዉ ለሰላምታዉ ምላሽ ሰጥቼ ልወጣ ስል 'የሆነ ጥያቄ ልጠይቅሽ' አለኝ። ብዙ የሚያቆየኝ ስላልመሰለኝ እንዲጠይቀኝ ፈቃደኛ ሆኜ ከፌስቡክ መዉጣቴን ተዉኩት። 'ድንግል ነሽ?' ብሎ ጠየቀኝ። በእርግጥም የማይመለከተዉን ጥያቄ ጠይቆኛል ምን ብዬ ልመልስለት። ብዙ ነገር በሃሳቤ ዉስጥ ተመላለሰ። ለጠየቀኝ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ ልስጠዉ ወይስ በስድብ ላቃለዉ። ትክክለኛዉ የቱ እንደሆነ ባላዉቅም እሱ ጋር ክርክር ከምገጥም ብዬ ትክክለኛዉን መልስ ነገሬዉ ንግግራችንን ለመቋጨት ወሰንኩ። 'አዎ ነኝ' ብዬ መልሼለት ከፌስቡክ መዉጣት ተሳነኝ። ቀጣይ የሚጽፈዉን ለማንበብ ስል ኦንላይን ቆየሁ። እንዲህ ይላል ... 'በጣም ደስ ይላል። በዚህ ዘመን ከአንድ ሺህ ሴቶች አንዷ ላይ ብቻ የሚገኝ ነገር ነዉ ያለሽ። እናም በጥብቅነትሽ ልትኮሪ ይገባሻል። ... አንድ በጣም ምትፈልጊዉን ልሰጥሽ እፈልጋለሁ። ይሄ ላንቺ ያለኝን ክብር ማሳያ ይሆንልኛል።' የሚል መልዕክት ላከልኝ። ስልኬን በእጄ እንደያዝኩ በሃሳብ ሰጠምኩ። 'ማን ነዉ?፤ የት ያዉቀኛል፤ የሚያስፈልገኝን ነገር በምን ሊያዉቅ ይችላል...።' እኔን ከማድነቁ በላይ የሚያስፈልገኝ ነገር ምን እንደሆነ ለኔም ስለጠፋብኝ ምን እንደሆነ ከሱ ለማወቅ ፈለግኩ። 'ምንድን ነዉ የሚያስፈልገኝ?' በማለት ጠየቅኩት። ጽሁፉን ቀድሞ ያዘጋጀዉ በሚመስል ሁኔታ የኔ መልዕክት እሱ ጋር ከመግባቱ ቅጽበት ነበር የመለሰለኝ። 'ከዚህ በፊት በፌስቡክ ገጽሽ The joy luck club የሚል መጽሀፍ በጣም እንደምትፈልጊ ጠይቀሽ ነበር?' 'አዎ በትክክል። መጽሀፉ አለህ?' በጉጉት ነበር የጠየቅኩት። መጽሀፉን ከዚህ በፊት ማንበብ ጀምሬ ታክሲ ዉስጥ ረስቼዉ ወርጄ ጠፋብኝ። ከዚያ በኃላ መጽሀፉን ማንም ጋር ላገኘዉ አልቻልኩም። በጣም ደስ አለኝ። '... በአላህ አዉሰኝ አንብቤ በቶሎ እመልስላሀለዉ' ብዬ በመማጸን መልኩ ጠየቅኩት። 'ላዉስሽ ሳይሆን ለጥብቅነትሽ ሽልማት ልሰጥሽ እፈልጋለሁ። አሁን መስቀል ፍላወር አከባቢ ነዉ ያለሁት መምጣት ከቻልሽ ሽልማትሽን አሁኑኑ መዉሰድ ትችያለሽ' አለኝ። በደስታ ልቤ ልትወጣ ደረሰች። የጀመርኩትን ታሪክ መጨረስ ስለምፈልግ ጊዜ መፍጀት አልፈለግኩም። 'ስምንት ሰአት ይመቻሃል?' ፈቃዱን ጠየቅኩ። 'ይመቸኛል። ስትመጪ በዚህ ቁጥር ደዉይልኝ 09...' ስልክ ቁጥሩን አስቀመጠልኝ። ከቀኑ 8:00 ሰአት ከአለም ባንክ ተነስቼ መስቀል ፍላወር ደርሻለሁ። በሰጠኝ ስልክ ቁጥር ደወልኩለት። 'ሄሎ' 'አሰላሙዓለይኩም ሂክማ ነኝ' 'ወዓለይኩም ሰላም .. እንዴት ነሽ ሂክማ' 'ደህና አልሐምዱሊላህ መስቀል ፍላወር ደርሻለሁ የቱ ጋር ነህ?' 'ሂጅራ ባንክ ዋናዉ ቅርንፍ ተሻግረሽ የቆመ ያሪስ መኪና አለ ወደዛ ነይ' አለኝ። ወደነገረኝ ቦታ ስሄድ እንዳለዉ አንዲት ያሪስ መኪና ቁማለች። ዉስጡ አንድ ሰዉ ተቀምጧል። መስታወቱን ዝቅ አድርጎት ስለነበር 'ያሲን አልኩት' ሞቅ ባለፈገግታ ስሜን ጠርቶ ተቀበለኝ። ወደ መኪናዉ እንድገባ ጋበዘኝ። 'ይቅርታ ያሲን በጣም እቸኩላለሁ' አልኩት። 'እንደሰረቀ ሰዉ ላጥ አድርገሽ ልትሄጂ ባልሆነ.. በይ ግቢና ሻይ ቡና ብለን መጽሀፍሽን ትወስጃለሽ' አለኝ። ቅር እያለኝም ቢሆን ወደ መኪናዉ ገባሁ። መኪናዉን ቀስ እያለ መንዳት ጀመረ። 'መጽሃፉን ለማግኘት ቸኩለሻል መሰል?' 'አዎ.. እዚህ ድረስ የመጣሁት ለሱ አይል' ፈገግታ ፊቱን ሞልቶታል። አነጋገሩ ደስ ይላል። 'በቃ ግብዣዉ ከሽልማቱ በኃላ ቢሆንስ...' ብሎ መጽሀፉን ዘረጋልኝ ከእጁ ላይ በመቅጽበት ላፍ አደረግኩት። በሽፋኑ ማመን ስላልፈለጉ መጽሀፉን ገልጬ ተመለከትኩት። አዎ እራሱ ነዉ። በጣም ደስ አለኝ። የምር የማገኘዉ አልመሰለኝም ነበር። ስለመጽሀፉ አንዳንድ ነገር እያወራኝ ሳለ የትና በምን ሁኔታ ዉስጥ እንዳለሁ መርሳት ጀመርኩ። የሚታየኝ ነገር ሁሉ ፍዝዝ፤ ድብዝዝ ይልብኛል። ምን ሆንኩ። በግድ አንገቴን ነቅንቄ ነቃ ለማለት ብሞክርም አልቻልኩም። በተቀመጥኩበት ተልፈስፍሼ እንቅልፍ ጣለብኝ። ወደቅኩ። ከሰአት 10:30 ከባድ ራስ ምታት ተጫጭኖኝ ከእንቅልፌ ነቃሁ። አይኔን ከፈት አድርጌ ስመለከት ያለሁት ፔንስዮን ዉስጥ ይመስለኛል። ደንግጬ ከተኛሁበት ብድግ ስል ሰዉነቴ ላይ ጣል ከተደረገዉ አንሶላ ዉጭ ራቁቴን ነኝ። ሂጃቤ፤ ቀሚሴ፤ ጡት ማስያዥዬ... ምንም ነገር ሰዉነቴ ላይ የለም። ጭኔ አከባቢ 'ርጥበት ተሰምቶኝ ተጣድፌ አንሶላዉን ወዲያ ጣልኩት አልጋዉ በደም ተነክሯል። አዕምሮዬ ዉስጥ የመጣዉ 'ድንግል ነሽ?' የሚለዉ ጥያቄዉ ነበር። ክፍሉን በጩኸት ሞላሁት 'ኡኡኡ....' አይኖቼ በእንባ ተሞሉ፤ የተንጨባረረዉን ጸጉሬን ይበልጥ አንጨባረርኩት። ድምጼን የሰሙ የሆቴሉ ጽዳት ሰራተኞች በሩን ከፍተዉ በሩጫና በድንጋጤ ወደ'ኔ መጡ። 'የት ነዉ ያለሁት?' አልኳቸዉ። ጥያቄዬ በልቅሶ ዉስጥ ስለነበር እርስ በእርሳቸዉ ተያዩ። 'ሶስት ወንዶች ናቸዉ። እህታችን ታማ ከክፍለ ሃገር መጥተን ነዉ ብለዉ አቅፈዉ ያስገቡሽ። እነሱ ቀጣዩ ክፍል ይዘዋል' አሉኝ። 'ሶስት ወንዶች?' ሁለቱንም እያፈራረቅኩ ከተመለከትኩ በኃላ እንደገና ጩኸቴንና ለቅሶዬን ለቀቅኩት። እብድ ሆንኩ። ራሴን ተመለከትኩ ራቁቴን ነኝ፤ ሰዉነቴን ጠላሁት ... ፊቴን እቧጭረዉ ጀመር። ሰዎች ተሰበሰቡ... ከ 4 ወር በኃላ አልሐምዱሊላህ በህይወት አለሁ። ያዉ አላህ በየትኛዉ ወንጀሌ እንደቀጣኝ አላዉቅም። ግን ደግሞ ሁሉም ነገር ቀድሞ የተጻፈ ነዉ። የHIV መድሃኒቴን እየወሰድኩ በህይወት አለሁ። ህይወት ይቀጥላል.... @yefikrwelafen @yefikrwelafen
Mostrar todo...
😭
😓
🙏
Photo unavailableShow in Telegram
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Mostrar todo...
​​​​​​ #ብቻዬን_ላፍቅርሽ ባልኖረ ሌላ አዳም ከምድር በጠፋ፣ የኔ ብቻ እንድትሆኝ ቢደላም ቢከፋ፣ ♠ በሰፊው አለም ላይ ለጥ ባለው ምድር፣ ምናለ አምላክ ፈቅዶ ብቻችንን ብንቀር፣ ሌላ አዳሞች ቀርተው ብቻዬን ባፈቅር፣ መሬት ባዶ ትሁን ማንም አይኑርባት ከኔና አንቺ በቀር፣ 💎 ሆንሽና ስስቴ የነፍሴ ጥም አርኪ፣ ቀኔን ምታበሪ ዘወትር ስትስቂ፣ 💌 እንዳትሆኝ የሌላ ልቤ ስለፈራ፣ አዳሞችን ጠላው ስላንቺ ስራራ፣ 💍 ብቻዬን ላፍቅርሽ ማንም ሳይጋራኝ፣ ከሄዋኔ በቀር አዳም አያሳየኝ፣ 🍬 አደለም በውን ተኝቼ በህልሜ፣ ከሌላ አዳም ባይሽ ይብሳል ህመሜ፣ አልድነውም እንኳ በቅጡ ታክሜ፣ 🌼 አዳሞች ራቁ ሽሹ ከኔ ሄዋን፣ ደርሶ የነካትን አልምረውም ነፍሱን፣ 🌹 ድርድር አላውቅም እኔ በሷ ጉዳይ፣ ጦሬን እመዛለው ባልሆንም ሺ ገዳይ፣ 🍊 የኔ ብቻ እንድትሆን አምላክ ባክህ እርዳኝ፣ ከኔ ሌላ አዳም በምድር አይገኝ፣ ልሁን ከሷ ጋራ ተጋፊ ሳይኖረኝ፣ ተው አትንካት ብሎ የሚከለክለኝ፣ 🌺 የውበትሽ ማማር እጅግ ስለ በዛ፣ ሁሉም ይመኙሻል አይተውሽ በዋዛ፣ 💞 ሲረባረቡብሽ እጅግ አፈራለው፣ አዳም ከኔ ሌላ ባላይ እመርጣለው፣ ♥ ከሰዋራው ልቤ ውዴ ልደብቅሽ፣ ማንም ሳይነካብኝ ብቻዬን ላፍቅርሽ!!!    💜 @yefikrwelafen 💛 ሼር
Mostrar todo...
#ርዕስ_አልባ_ግጥም_2 . . በጠብ መንጃ አፈሙዝ የተገዛ ወንበር፣ በትውልድ ደም ላቦት የተገኘ መንበር። . . አንከባሎ ያመጣው እስኪያጠፋው ድረስ፣ ሺ ቅልጥም ቢሰበር የሺ ሰው ደም ቢፈስ። . . ለፌዝ እዘኑ እንጂ ከቶ አትሸበሩ፤ ወገን ገደል ይግባ!! ዝም ብላችሁ ምሩ፣ "ሀገር እግር ትብላ!!" እስኪያቅረን ድረስ ቅዠቱን ደስኩሩ። . . መቼም.... ቀን ያጣመመውን የትውልድ ደባ፣ ሲጎርፈው የኖረ የሻገተ እንባ። በኪነጥበቡ እስኪያለሰልሰው፣ በ"ቢቸግር" ቅኝት ስቀን እናልቅሰው። . . መኖር ሲያባዝተው ቀን ሲያንቀው አክራሞት፣ ምንም ሆኖ ያልፋል የሰው ልጆች መሞት።!! "........እንላቀስ ጎበዝ........"    ✍ ዓቢይ ( @abiye12 ) ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏 Join us 👇👇👇 @yefikrwelafen
Mostrar todo...
❤️ፍቅር ማለት ውዴ ❤️ ፍቅር ማለት ውዴ ፨ የህልሙ ዘራችን የዕውን ፍሬ አፍርቶ ፤ ቆንጅየ ልጅ ወልደን... እሱም ፍቅር ሊማር አንደበት አውጥቶ ፤ ፍቅር ማለት.... እማ? ብሎ ቢጠይቅሽ ፤ ይህንን ንገሪው ሳትፈሪ ሳይጨንቅሽ ፤ ........"ፍቅር ማለት ልጀ........ የተራ ሆሄያት ባዶ ጥርቃሚ ፤ የሶስት ፊደል ጥምረት የቀል ልቅምቃሚ ፤ የደቂቃ ስሜት....... ወይ ጊዜያዊ ጥቅም አይደለም ምስጢሩ ፤ መስጠት+መስጠት +መሰጠት .....በቃ ሁሌም መስጠት እናም ልጀ ይህ ነው የፍቅር ቀመሩ ፤...." ብለሽ ንገሪልኝ እንዲገባው አርገሽ ፤ ፍቅርን ሠጥቶ ..... ምላሽ እንዳይጠብቅ በደንብ  አስጠንቅቀሽ ፤ ...........ደግሞም እንዲህ በይው......... ......ፍቅር ማለት ልጀ... በአንዲት ውብ ማሳ ውስጥ.. ከአረም ከቁጥቋጦ ፈፅሞ በራቀች ፤ ከአንድ ገበሬ እጅ.. በፅናት ተዘርታ በዕምነት የበቀለች ፤ ........... .............ፍቅር ቡቃያ ነች ፤ የአለምን ሃይሎች አጣምሮ ያደላት ፤ የተንኮል ገሞራ ..... የሃሜት አውሎ ንፋስ ገፍትሮ ማይጥላት ፤ ገንዘብ ጎርፍ ሆኖ..... ስሯን ቢያጥለቀልቅ ፈፅሞ ማይነቅላት ፤ ፍቅር ቡቃያ ናት..........." ......ብለሽ ንገሪልኝ.... ግን ይህን ሁሉ ቃል ከአንደበትሽ ሰምቶ ፤ ....ፍቅር ማለት እማ ???? ብሎ ከጠየቀሽ ሳይረዳው ቀርቶ ፤ ....ይህንን ንገሪው "ገበሬው አምላክ ነው ማሳዋ ልባችን ፤ ዘሩ የፍቅር ቃል ቡቃያው ልጃችን ፤" እንዲያውም እንዲያውም.... ከተራ ቃላት ጋር ምን አፈታተነን ፤ ፍቅር ማለት ውዴ!!!! በቃ እኔና አንች ነን ። ❤️ ፍቅር በፍቅር የሆነ ግጥም ነው አይደል እስኪ እንደኔ ፎንቃ የገባለት ለምትወዷት share እ ጀለሶች። @yefikrwelafen   ||   📩birsh
Mostrar todo...