cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ULUL ALBAB

"ከምትሰማዉ ይልቅ አንብበህ የምታገኘው እውቀት " ይበልጣል !ኢስላማዊ ት/ት የተለያዮ ት/ት ለመቅሰምjoinያድርጉ። commment @Ibnubaz_bot አላህ በአንተ ሰበብ አንድ ሰው ማስተካከል/ማቃናት ከቀያይ ግመሎች ይበልጥልሀል።http://t.me/Abdurahaaman17 Any comment @ibnubaz10 another chanal |||||||| @ALLAH_IS_GOD

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
600
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ፕሮግራሙ  ሊጀመር ነዉ ➘➘➘➘➘➘➘➘➘ https://t.me/ibrahim_furii?livestream=945335d5bea50efb95
Mostrar todo...
||የቁርዓን ሀለቃ ቂራዓት ሴንተር||

የቻናሉ ትኩረትና ዓላማ: – √ ቁርዓንን በማየት(በነዘር)መቅራት ለማይችሉ እገዛና ድጋፍ ማድረግ። እንዲሁም በተጨማሪ በኡስታዝ ኢብራሒም የሚሰጡ:– √ የተጅዊድ √ የቁርአን ሐለቃ √ እና የተለያዩ ደርሶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው። 🏖 ለአስተያየት☞ @AbuHiba1 ወይም☞ @Ibrohalka_botይጠቀሙ!!

sticker.webp0.77 KB
sticker.webp0.36 KB
……… ስድስቱ የተውበት መስፈርቶች ……… =========================== በህይወታችን ብዙ ጊዜ ወንጀሎችን እንፈፅማለን። አላህ ያደለው በወንጀሉ አላህ ፊት እንዳይጠየቅ ተውበት ማድረግን ያስባል። ግን ስንቱ ነው ተውበቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ እንዲሆን የሚጨነቀው? እራሳችንን በሚገባ ጠይቀን እናውቃለን?! ለመሆኑ መስፈርቶቹን ምን ያህሎቻችን በሚገባ እንለያቸዋለን? ለማያውቁ ጥቆማ፣ ለሚያውቁ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ እጠቅሳለሁ። የተውበት መስፈርቶች ስድስት ናቸው። እነሱም:– ① ኢኽላስ: – አላህን ብቻ በማሰብ መፈፀም ማለት ነው። አንድ ሰው ወንጀልን የሚተወው ዱንያዊ ጥቅሞችን አስቦ ከሆነ የመጀመሪያውን የተውበት መስፈርት ዘንግቷል። ② ወንጀሉን ማቆም:– አንድ ሰው የሚፈፅመውን ወንጀል ባላቋረጠበት ሁኔታ "ቶብቻለሁ" ቢል ቀልድ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ተውበት ያሰበ ሰው ጥፋቱን በቀጠሮ ሳይሆን ቀጥታ ሊያቆም ይገባል። ③ ወደ ጥፋቱ ዳግም ላይመለሱ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ። አንድ ሰው ከወር ቡ በኋላ እንደሚመለስ እያሰበ ረመዳን ሊገባ ሲል አንድን ወንጀል ቢተው መስፈርት ስላላሟላ ተውበት አድርጓል ማለት አይቻልም። ④ በወንጀሉ መፀፀት፦ ሰውየው ሲፈፅመው በቆየው ወንጀል ላይ ደንታ ቢስ ከሆነ ተውበቱ የሐቂቃ አይደለም። ፀፀቱ "ሰው ምን ይለኛል" ወይም "ክብሬ ጎደፈ" በሚል ሳይሆን የጌታውን ህግ በመጣሱ ሊሆን ይገባል። ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ዝሙት ፈፅመው ጌታቸው ዘንድ ካለው ሂሳብ ይልቅ ዱንያ ላይ ያለው የሰው ወሬ ሲያስጨንቃቸው ይፀፀታሉ። እንዲህ አይነት ፀፀት የተውበትን መስፈርት አያሟላም። ይልቅ ከዛሬው የበዛ ህዝብ ፊት ነገ በአኺራ መዋረድ ከመምጣቱ በፊት ትክክለኛውን ፀፀት እዚሁ ልናስገኝ ይገባል። ⑤ ተውበቱ ወቅቱን የጠበቀ መሆን። ይህም ሞት አፋፍ ላይ ከመድረሱ በፊት እና ፀሀይ በመጥለቂያዋ ከመውጣቷ በፊት መሆኑ ነው። ⑥ ወንጀሉ የሰው ሐቅ መግፋት ከሆነ ሐቁን ሊመልስ ወይም ይቅርታውን ሊያገኝ ይገባል። ያን ማድረግ ካልቻለ ዱዓእ ሊያደርግለት እንዲሁም ኢስቲግፋርና ኸይር ስራ ሊያበዛ ይገባል። © ኢብኑ ሙነወር
Mostrar todo...
#ፉዶይል_ኢብኑ_ዒያድ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - "ምርጡን ዱቄት እያወጣ እንክርዳዱን እንደሚያስቀረው ወንፊት አትሁኑ ፣ ከአፎቻችሁ ጥበብን (ጥሩ ንግግርን) ታወጣላችሁ ፣ ውስጣችሁ ደግሞ ቂምና ጥላቻ ይቀራል።" 📚 ۞【صفة الصفوة【٤٥٧/١】۞
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
አደራ! ቁርኣን እንቅራ ~ በርግጠኝነት እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ ከሚርመሰመሱ ወገኖቻችን ውስጥ ቁርኣን ያልቀሩ ብዙ ወገኖች ይኖራሉ። ወላሂ ሊቆጨን ይገባል። በዚህ አማራጮች በበዙበት ዘመን እንዴት ድንቁርናን አሚን ብለን ተቀብለን በጨለማ ውስጥ እንኖራለን? የትም ብንሆን ካለንበት ቦታ ሆነን መማር እንደሚቻል የሚታወቅ ነው። አላህ ባገራልን መንገድ እንማር። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን የተማረና ያስተማረው ነው" ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 5027] ስለዚህ ያልተማርን ጊዜ ሰጥተን እንማር። የተማርን መልክቱን እንማር፣ ባወቅነው እንስራ። በየቀኑ ከጊዜያችን ውስጥ ለቁርኣን ድርሻ ይኑረን። በምንችላት መጠን ለመሐፈዝ እንሞክር። የእድሜ መግፋት ቁርኣን ከመማር አያግድም። በርካታ ሶሐቦች በጎልማሳነት ዘመናቸው ነው ቁርኣን የቀሩት። ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አል0ባድ "አንድ ሰው ከሃምሳ አመቱ በኋላ ቁርኣን ሊሐፍዝ ይችላል ወይ?" ተብለው ተጠይቀው ነበር። ምላሻቸው እንዲህ የሚል ነበር፦ "አዎ! እኔ ራሱ ከሃምሳ በኋላ ቁርኣን ከሐፈዙት ውስጥ ነኝ። ሶሐቦች - ረዲየላሁ ዐንሁ - ትልልቅ ሰዎች ሆነው ነው ኢስላም ያገኛቸው። ከመሆኑም ጋር ቁርኣንን ሐፍዘዋል።" ስለዚህ በየትኛውም ምክንያት በልጅነቱ ቁርኣን ያልቀራ ሁሉ እራሱን አያዳክም። "በአላህ ፈቃድ እችላለሁ" ብሎ ይነሳ። ኢንሻአላህ ይችላል። አለማወቅን ታቅፈን ፈፅሞ ምቾት ሊሰማን አይገባም። ሰው እንዴት ቁርኣን ሳይቀራ እድሜውን ይፈጃል?! = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Mostrar todo...
Repost from N/a
ጌታህ ላንተ የመረጠልህን ምንም ነገር ቢሆን አትጥላ ሁሉም ነገር ለኸይር ነው። «በሚደርስብህ ፈተና ከታገስክ ትመነዳለህ፤ «በበሽታህ ከታገስክ ትመነዳለህ፣ « ባጣኸውም ነገር ሁሉ ከታገስክ ትመነዳለህ፣ «በመታገስህም ትመነዳለህ፣ የጌታህ ምርጫ ዟሒሩ ሸር ቢመስልህም ከጀርባው በኸይር እንጂ በሌላ አይመጣም። 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
Mostrar todo...
Repost from N/a
00:13
Video unavailableShow in Telegram
8.29 KB
sticker.webp0.44 KB
Photo unavailableShow in Telegram
🔴 የአረፋ ቀን ፆም! ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦ ‎﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾ “ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162 📌 ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል። 📌 ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል።ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው። 📌 ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም። 📌 በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣ 1/ ቀኑን መጾም 2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር 3/ ዱዓእ ማብዛት 📌 ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም። ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል። 📌 ማስታወሻ፦ የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ አርብ ሐምሌ 1 ነው።ለወዳጅና ዘመድም እናስታውስ። ለራሳችን፣ለቤተሰባችንና ለሀገራችን ዱዓ እናድርግ።
Mostrar todo...