ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Ir al canal en Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Mostrar más602
Suscriptores
Sin datos24 horas
-87 días
-1630 días
Archivo de publicaciones
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርከ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
•ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት
ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ
ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና
ጸሐፊ እና በሰሜን አሜሪካ የኒዮርክ እና
አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ
አባላት፤
ሁሉንም ጠብቆ የሚያስጠብቅ እግዚአብሔር አምላካችን ከተሠማራንበት የጥበቃ ስፍራችን አሰባስቦ በደሙ ስለዋጃት ቅድስት ቤተክርስቲያን እንድንመክር ስለፈቀደልን ምስጋና ለእሱ እናቀርባለን፣ እናንተም እንኳን ደኅና መጣችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
“ወዘእንበለዝ ብዙኅ ባዕድ ዘረከበኒ ኲሎ አሚረ እንዘ እኄሊ ቤተ ክርስቲያናት፡- የቀረውንም ነገር ሳልቈጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሐሳብ ነው” (2ኛ ቆሮ 11፦28)
ከዚህ ጥቅስ እንደምናስተውለው ከስራ ሁሉ የሚያስጨንቅ ተግባር የቤተ ክርስቲያን ነገር እንደሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሚገባ አስቀምጦአል፡፡ እርግጥ ነው ሌሎች የሚያስጨንቁ ችግሮች በዓለም አሉ@ ግን ሌሎቹ ለጊዜውም ቢሆን ባላቸው ማቴሪያላዊ ኃይል ማስታገሥ ይችላሉ፡፡ ቤተክርስቲያን ግን ከመንፈስ ቅዱስ ከተሰጠ ረቂቅ ኃይለ መዊዕ በቀር ሌላ ማቴሪያላዊ ኃይል የላትም አይፈቀድላትምም፡፡
ይሁን እንጂ ከኃይል ሁሉ የበለጠ ኃይል እንዳለን ጌታችን ነግሮናል እኛም እናውቀዋለን፡፡ ነገር ግን የኛ ድክመት ኃይሉ እንደሚፈለገው እንዳይሰራ ያደርገዋል ይህም እውነት ነው የተሰጠን ኃይል በእኛ ድክመት የተቀዛቀዘ ቢመስልም የማይሸነፍ ነውና ኃይላችንን አውቀን ካልተጠቀምንበት እኛንም ጭምር ቀጥቶ የበላይ አሸናፊነቱን ያረጋግጣል ይህም የታየ እውነት ነው፡፡
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
ጥቅምት ፲፪ (12) ቀን።
እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት ለአንዱ ለሆነው #ለወንጌላዊ_ለቅዱስ_ማቴዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
እንኳን #ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል #ቅዱስ_ዳዊትን በሳኦል ፈንታ እንዲሾመው ለሳሙኤል ለነገረበትና #ዳዊት_ጎልያድን_በሚገድልበትን ልዩ ኃይል እዲሰጠው ለረዳበት ለወራዊ መታሰቢያ በዓል፣ #ለእስክንድርያ_ዐሥራ_ሁለተኛ ለሆነ ሊቀ ጳጳሳት ለንጹሕ ለድንግል ከሚስቱ በአንድነት ሲኖር ለ48 ዓመታት የጠባይን ፍላጎት ድል ለነሳ፤ ባሕረ ሀሳብ ለቀመረ (ላዘጋጀ) ለታላቁ አባት #ለአባ_ድሜጥሮስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከጻድቃን_ከጴጥሮስና ከተወራራሽ #ጳውሎስ_ከዲዮናስዮስ_ከያዕቆብ_ከአቡጥፋ፣ #ከቴዎድሮስና_ከሚናስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
#በዚች_ዕለት_የመላእክት_አለቃ የከበረ መልአክ #የቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም እየተካሄደ ነው
የጥቅምት 2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመካሄድ ላይ ይገኛል።
©EOTCTV
#EOTC_ETHIOPIA
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
ለሁሉም አህጉረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጥ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ መመሪያ ስለማስተላለፍ በሚል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የተጻፈ ደብዳቤ ለሁሉም አህጉረ ስብከቶች የተጻፈ ሲሆን ሁሉም በሥራቸው ለሚገኙ ገዳማትና አድባራት መመሪያውን እንዲያሰራጩና በእቅድ ውስጥ አድርገው እንዲከታተሉ በማሳሰብ የሚከተሉትን
ዋና ዋና ሐሳቦች ተግባራዊ እንዲያደርጉ መመሪያው ተላልፏል።
ይኸውም፦
፩_ በሁሉም ገዳማት እና አድባራት ለሰ/ት/ቤቶች የመምህራን ስልጠና እንዲሰጥና የመምህራን ቅጥርና ምደባ እንዲመደብ ፤
፪_ ለሰ/ት/ቤቶች ከመማሪያ ቦታ ማመቻቸትና በቂ ቦታ በማዘጋጀት የመማሪያ ክፍሎች እንዲገነቡ እንዲደረግ ፤
፫_ ለሥርዓተ ትምህርቱ ትግበራ በጀት በመመደብ መጻሕፍት ግዢ መፈጸም ፤
፬_ ለትግበራው አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት እና ምዕመናን ልጆቻቸውን ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲልኩ በየዐውደ ምህረቱ በመቀስቀስና ሥርዓተ ትምህርቱን የማስታወቅ ሥራ በመሥራት ለተግባራዊነቱ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያቱ ዕቅድ ውስጥ በማስገባት እንዲሠሩ መመሪያው ተላልፏል።
ሁሉም ሰንበት ት/ቤት በቀጣይ በሀገረ ስብከቶች ወደአጥቢያ የሚወርደውን መመርያ ደብዳቤውን ተከትሎ አፈጻጸሙን ከአንድነት መዋቅሩ ጋር በመናበብ ተፈጻሚነቱን በየአጥቢያው እንዲተገበር ክትትል እና ሪፖርት እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ያሳስባል።
የደብረ ዕንቊ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በመግባት ከደብርዋ ይዞታ 10,300 ካሬ ተወሰደ።
ጥቅምት 7 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኘው በደብረ ዕንቊ ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በመግባት በብረት እና በሽቦ ኮንክሪት አድርጎ በማጠር የደብርዋ ይዞታ መወሰዱ ነው የተገለጸው።
የፍርድ ቤቱን እግድ በመጣስ የደብረ ዕንቊ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ የታጠረው እና ከደብርዋ ይዞታ የተወሰደው 10,300 ካሬ መሆኑም ነው ተ.ሚ.ማ ያገኘው መረጃ የሚያመላክተው።
የደብረ ዕንቊ ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤም ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት መመሪያ መሰረት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በደረሰን መረጃ መሠረትም የደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የሆኑት ወጣት ታምራት ተስፋዬ እና ወጣት ንዋይ ጌታነህ ከቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ውስጥ በፓሊስ አባላት ተወስደው በላምበረት ጣቢያ ታስረዋል።
በትላንትናው ዕለት የፍርድ ቤት ውሎ የደብሯን ልጆች ለማስፈታት በተደረገው ጥረት ፍርድ ቤቱ እያንዳንዳቸው በ2000 ብር ዋስ ይፈቱ ቢልም በተጠየቀው መሰረት ተገቢው ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ ዛሬ አንፈታቸውም በማለት ሳይፈቷቸው በመቅረታቸው ዛሬ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተገልጿል።
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፲፩ (11) ቀን።
እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_የዓባይ_ውሃ ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ #በጸሎታቸው_አቁመውት ለነበሩ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ኤልያስ_ዘውቅሮ ለመታሰቢያቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
እንኳን #ለገድለኛዋ_ለቅድስት_ጲላግያ ለዕረፍት በዓል፣ #ለአንጾኪያ_ሊቀ_ጳጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_ያዕቆብ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕት_አርማሚ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሺ፥ ተመለሺ››
(መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን ፯፥፩)
ጽጌ ማለት አበባ ማለት ነው፡፡ አበባ የተባለችም ድንግል ማርያም ናት፡፡ የነገረ ማርያም ሊቃውንት እመቤታችን በአበባ፣ ልጇን በፍሬ፣ እርሷን በዕፅ፣ ልጇን በአበባ እየመሰሉ ማስተማር ልማዳቸው ነው፡፡ ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን የዜማ አባት ቅዱስ ያሬድም ‹‹በማዕከለ አስዋክ ዘጸገየት ጽጌ ሃይማኖት ዘበአማን፤ በእሾህ መካከል ያበበች በእውነት የሃይማኖት አበባ ናት›› በማለት ይገልጻታል፡፡ (ነገረ ማርያም) እሾህ በተባለ ጥንተ አብሶ አዳማዊና ሔዋናዊ ኃጢአት መካከል ያበበች የፍሬ ሕይወት ክርስቶስ መገኛ አማናዊት የሃይማኖት አበባ እመቤታችን በዚህ በአበባው ወቅት (በጽጌ ወራት) መራራው የጣፈጠበት፥ ፍሬ ሕይወት ልጇን እንዳይገሉባት መራራውን የስደት ሕይወት የተጋፈጠችበት መታሰቢያ ወቅት ነው፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨🌹✨
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ልዑክ ከስልጤ ቅበት ከተማ በሃይማኖታቸው ምክንያት ተፈናቅለው ሀብት ንብረታቸውን ጥለው ቡታጅራ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የሚገኙ ምእመናንን በቦታው ድረስ በመገኘት ጎብኝተው ከአልባሳት ውጪ #ከ600_000 (ከስድስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ድጋፍ አደረገ።
ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም ( አበባ)
በዕለቱ በደብሩ አስተዳዳሪ በክቡር መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ገብረኢየሱስ መሪነት ተፈናቃይ አባቶች ፥ እናቶች ፥ ሕጻናት እና ከአዲስ አበባ የመጡ መምህራነ ወንጌል እንዲሁም የአንድነቱ ልዑክ በተገኙበት መርሐግብሩ በጸሎት የተጀመረ ሲሆን ከጸሎቱ በማስከተል የአንድነቱ ልዑክ በሆኑት በቀሲስ አለማየሁ የቅዱስ ቂርቆስን ተጋድሎ በማንሳት ሕጻናቱን የሚያጽናና ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል። ከሳቸው በማስቀጠልም ተፈናቃይ ሕጻናቱ "ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ እና ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማነው" የሚሉ ሁለት ዝማሬዎችን አቅርበዋል። ከዝማሬው በማስከተል ከተፈናቃዮቹ አንዱ በሆኑት በቀሲስ ዳንኤል ገለጻ የተደረገ ሲሆን ተፈናቃዮቹ በእምነታችን ከተፈናቀልን 45 ቀን የሆናቸው መሆኑን ገልጸው በደረሰባቸው ጥቃት ምክንያት የተሰደዱት ኦርቶዶክሳውያን #ከ1500 በላይ መሆናቸውን እና ከተሰደዱት ኦርቶዶክሳዊያን መካከልም አብዛኞቹ ህጻናት ሲሆኑ አዛውንት ፣ ወጣቶች ፣ ጎልማሶች እና አራስ እናቶች እንደሚገኙ ፤ በስልጤ ዞን ቅበት ወረዳ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያለው ስጋት አሁንም አለመቆሙን እና ከተማዋን ከክርስቲያን የጸዳ ለማድረግ እየተሰራ ያለ ሲሆን ነገሩ በሽምግልና ይፈታል ተብሎ እስከዛሬ ብንጠብቅም እስካሁን ምንም ነገር ከሚመለከተው የመንግሥት አካልም ይሁን ከቤተክህነቱ እየተደረገላቸው እንደማይገኝ ገልጸዋል። በዚህም የሚመለከተው ሁሉ የሚጠበቅበትን ሠርቶ ወደቅያቸው እንዲመልሷቸው ተማጽነዋል።
የአንድነቱ ልዑክ በሆኑት መጋቤ ሐዲስ ሐረገወይን ገነት ስለ እመቤታችን እና ጌታችን ስደት በማንሳት "የእመቤታችንን ስደት ነው የተሰደዳችሁት እና ደስ ይበላቹ" ፤ ወደየትም አልተሰደዳችሁም ወደ እናት ቤተክርስቲያናችሁ ነው የተሰደዳችሁት ደስ ይበላችሁ በሚል የማጽናኛ ትምህርት ተሰጥተቷል።
ከአንድነቱ ልዑክ ጋር የንስሐ ልጆቻቸውን አስተባብረው ይዘው በሄዱት እና ድጋፍ ባደረጉት በመጋቤ ሐዲስ ምስጢረ ሥላሴ ማናዬ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን በትምህርታቸውም "የእናንተ ጽናት ለኛ ትምህርት ነው ከእናንተ ልንማር ነው የመጣነው እንጂ ልናስተምር አይደለም ፤ እናንተ ቤት ንብረታችሁን ለሃይማኖታቼሁ ብላችሁ ጥላችሁ ወጥታችሁ የሰማዕትነት ሕይወት እየኖራችሁ ነው ያላችሁት ፤ ስደት ክርስትናን ከሀገር ሀገር እንዲያዳርስ የሚያደርግ ነው እና እናንተም ክርስትናን ነው ያስፋፋችሁት ፤ ወንድሞች ሆይ በእምነታችሁ ምክንያት ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት (ያዕ.1፥2) ፤ ያሳደዷችሁን ውደዷቸው እንዳታቄሙባቸው ምክንያቱም ሰማዕት አርገዋችኋልና ፤ እግዚአብሔር ስደትን ብቻ ሳይሆን ማረፊያንም ያዘጋጃል እና በቤተክርስቲያን መጠለላችሁ የሚያስደስት ነው.....። ብለው እጅግ የሚያበረታ እና የሚያጸና ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።
የአንድነቱን ልዑክ መርታ በሄደችው እና የአንድነቱ ልማት እና በጎ አድራጎት ክፍል ሰብሳቢ በሆነችው ወጣት ፍርቱና በኩል ስለሂደቱ ገለጻ ያደረገች ሲሆን የአንድነቱ ልማት እና በጎ አድራጎት ክፍል የስልጤ ክርስቲያኖች መሰደዳቸው ከተሰማ ቀን ጀምሮ ከየሰንበት ት/ቤቱ እና ከአባላቱ እንዲሁም ከምዕመናን እርዳታ በማሰባሰብ የመጀመሪያ ዙር የምግብ አይነቶችን እና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለት የተደረገው ድጋፍም ለሁለተኛ ዙር የተደረገ መሆኑን በዚህም ዙር ከአልባሳት ውጪ #ከ600_000 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ የተደረገ መሆኑን በአይነትም
ሳሙና ፥ ዳይፐር ፥ ሞዴስ ፥ ፖስታ ፥ መኮረኒ ፥ ምስር ፥ባቄላ ፥ አተር ክክ ፥ የጤፍ ዱቄት፥ የስንዴ ዱቄት ፥በርበሬ ፥ሽሮ የመሳሰሉት
ቁሳቁሶች እና የምግብ እህሎች እገዛ መደረጉን ገልጻ በዚህም ድጋፍ የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ቡራኬ በመስጠት በመሸኘት እና የተባበሩትን ሰንበት ት/ቤቶች እና አባላት እንዲሁም ምዕመናን/ት በአንድነቱ ስም አመስግናለች።
በዕለቱ ልዑኩ ይዞ የመጣውን እገዛ ለደብሩ አስተዳዳሪ እና ለተፈናቃይ ወገኖቻችን ካስረከበ በኃላ ከተፈናቃዮቹ በዕድሜ ከፍ ያሉ አረጋዊ እናት እና አባቶች ምርቃት እና ምስጋና አቅርበዋል በዚህም በንግግራቸው "እዛ እያለን መቃብር ውስጥ ነበረ የነበርነው እናንተ እና ቤተክርስትያኗ ዓለም አሳይታችሁናል እናመሰግናለን ፤ ከቤታችን እና ከደብራችን ታቦተ ሕጉን ይዘን ስንወጣ ራቁታችንን ነበረ የወጣነው እናንተ ግን እያለበሳችሁን እየመገባችሁን ነው ያለነው ፤ ቅዬአችሁን ለቃችሁ ሂዱ ተብለን ብንሰደድም የብዙዎች መጠጊያ ቤተክርስቲያን እንዳለችን አሳይታችሁናል ፤ ካመጣችሁት እገዛ በላይ በትምህርቱ በመዝሙሩ እጅግ አጽናንታችሁናል አጠንክራችሁናል እናመሰግናችኋለን እግዚአብሔር ይስጥልን ፤ እንዲሁ ደግሞ ለመንግሥት አካልም ለቤተክህነቱም ችግራችንን አሳስባችሁልን ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጠን አሳስቡልን ...ብለው የአባትነት ምርቃት ምስጋና አቅርበዋል።
በመርሐግብሩ ማጠናቀቂያ ላይም በደብሩ አስተዳዳሪ በክቡር መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ገብረኢየሱስ አንድነቱ በሁለት ዙር ላደረገው እገዛ ምስጋና አቅርበው ይህ እገዛ ወደፊትም እንዳይለያቸው አሳስበዋል። ተፈናቃዮቹ ተስፋ እንዳይቆርጡም አባታዊ ማጽነኛ ቃለበረከት ካስተላለፉ በኃላ መርሐግብሩ በጸሎት ተዘግቶ በሚሰደዱበት ወቅት በመንገድ እና እዚሁ ቤተክርስቲያን በመጠለያም የወለዱትንና በአክራሪ ኃይሎች አካላዊ ጥቃት የደረሰባቸውን እና ያረፉበትን ማረፊያ የአንድነቱ ልዑክ ጎብኝተው ወደመጡበት አዲስ አበባ ተመልሰዋል።
©አዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
ለሰ/ት/ቤቶች መማሪያነት የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ።
ጥቅምት 10 / 2016 ዓ.ም ( አበባ )
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በኩል ተዘጋጅቶ ወደ እንቅሰቃሴ እየገባ በሚገኘው የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ ለ አጠቃላይ ዓለም አቀፍ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች ማብራሪያ ቀርቧል።
ማብራሪያውን የሰጡት የአገር አቀፍ ሰ/ት/ቤት አንድነት ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው እንደተናገሩት የሰ/ት/ቤች ሥርዓተ ትምህርትን ለመቅረጽ እጅግ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል።
አሁን ተቀርጾ ወደ ተግባር እንዲገባ የሚጠበቀው ሥርዓተ ትምህርት 6 ዋና ርእሶች እና አንድ ደጋፊ ርእስ ያለው ሲሆን ለዘንድሮው ዓመት ትግበራ እንዲሆን 42 መጽሐፍት ታትመው እና በሊቃውንት ጉባኤ ተገምግሞ ዝግጁ ሆኗል።
አቅራቢው በተጨማሪ እንደገለጹት ሥርዓተ ትምህርቱ አሁን ያለው ትውልድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተረድቶ መንፈሳዊ ወጣት እንዲሆን የሚያስችል ዕውቀትን የያዘ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለተግባራዊነቱ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቃ ጳጳስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዳሉት አሁን ያለውን ትውልድ ለማዳን ሰ/ት/ቤትን ማጠናከር የግድ ይለናል ብለዋል።
በተጨማሪም ሁሉም አኅጉረ ስብከቶች ሥርዓተ ትምህርቱ ተግባራዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልእክት አስተላልፈዋል።
የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የተለያዩ የአቋም መግለጫ ነጥቦችን በማውጣት ተጠናቋል።
ጥቅምት 10/ 2016 ዓ.ም ( አበባ)
ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም የጀመረው የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለተከታታይ 5 ቀናት ያደረገውን ውይይት በዛሬው ዕለት አጠናቋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት ሲከናወን የቆየው አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ከመጠናቀቁ በፊት ቃለ ጉባኤውን በማዳመጥ አጽድቋል።
በቃለ ጉባኤው ላይ እንደተጠቀሰው ጉባኤው በቆየባቸው ቀናት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚጠቅሙ ሐሳቦች በመነሳታቸው ለተግባራዊነቱ ሁሉም የራሱን ድርሻ መወጣት አለበት ተብሏል።በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ጉባኤውን የመሩበት ጥበብ አድናቆት ተችሮታል።
ጉባኤው ቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁዕ ሥራ አስኪያጁ በጉባኤው መክፈቻ ያቀረቡትን ንግግር ሙሉ ለሙሉ እንደተቀበለው በመግለጽ የተለያዩ ነጥቦችን የያዘ አቋም መግለጫ አጽድቋል።
በመጨረሻም ጉባኤው በዘንድሮው የአኅጉረ ስብከቶች ሪፖርት ላይ በአገልግሎት አፈጻጸም እና በበጀት ፈሰስ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ አኅጉረ ስብከቶችን በመሸለም ተጠናቋል።
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
ጥቅምት ፲ (10) ቀን።
እንኳን ከከሀዲ ንጉሥ መክስምያኖስ ሠራዊት ውስጥ #ለቅዱስ_ባኮስ_ባልንጀራ ለሆነ #ለቅዱስ_ሰርጊስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍት በዓል፣ ለእስክድርያ አገር ሰባተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለሆነ #ለአቡነ_አውማንዮስ ለዕረፍትና ለመስተጋድል ከተጋድሎው ብዛት የተነሣ ራሱን በሚላጭ ጊዜ በውኃ ሳያርስ ይላጭ ለነበረ #ከቀሲስ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
"#ሰላም_ለሰርጊስ_እንተ_ላዕሌሁ_ኀለፋ። መዋግደ ሥቃይ ኵሎን በምድረ ፎራት ወሩጻፋ። ሐራዊ በመጥባሕት አመ ለክሣዱ ሰየፋ። ከመ ተመነየ ወከመ ተሰፈወ ተስፋ። ለአክሊለ ሕይወት ወስምዕ ይእዜ ተወክፋ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጥቅምት_10።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
"ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ።" መዝ 117 ÷26
🎓🎓 የተማሪዎች ምርቃት 🎓🎓
በሰንበት ት/ቤቱ ሲሰጥ የቆየውን ተከታታይ ትምህርት በቀዳማይ እና በካልዓይ ክፍል ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ ተማሪዎችን የምረቃ መርሐ ግብር።
🎓🗞እሁድ ጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም
🎓🗞ከ 8:00 ሰዓት ጀምሮ
🎓🗞 በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
ሌላውና በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ዘመነ ሢመት ሥር ነቀል ማስተካከያ የተደረገበት ከዚህ በፊት ተጀምሮ መቀጠል የተሳነው ብዙዎች በየዓመቱ በሚካሔደው ጉባኤ ሲተቹት የሚሰማው ውይይት ለምን አይደረግም? የገንዘብ ሪፖርት ብቻ ነው የሚሰማው፣ ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን የመለሰና በቡድን የተደረገ ውይይትን በጋራ ማብራሪያ የሚሰጥበት አሠራር ተጠናክሮ እንደገና የተጀመረው በብፁዕ አቡነ አብርሃም የአመራር ዘመን እንደሆነ እርግጥ ነው።
በዘንድሮ ዓለም አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይም ልዩ ልዩ ወቅታዊ ጥያቄዎችን በማንሣት ውይይት ቢቀር ጥሩ ነው የሚል ዐሳብ ያነሡ የነበሩ ብዙዎች ቢሆኑም ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ግን ውይይት ሊፈራ አይገባውም። መለመድ አለበት። ችግሮች መፍትሔ የሚያገኙት በውይይት ነው።ስለዚህ ውይይት መካሔድ አለበት የሚል ጽኑዕ አቋም በማራመዳቸው የጋራም የቡድንም ውይይት በ፵፪ ኛው ዓለም አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እንዲካሔድ በአስተዳደር ጉባኤ ተወስኖ በመርሐ ግብሩ ተካቶ እነሆ ተፈጻሚ የሚሆንበት ጊዜ ሰሌዳ ላይ ደርሰናል።
በሚደረገው የቡድንም ሆነ የጋራ ውይይት ችግሮቻችንን የምንመለከትበት፣ለችግሮቻችን መፍትሔ የምንሰጥበት ሁኔታ እንደሚፈጠርም በዛሬው ዕለት በተጀመረው የውይይት መርሐ ግብር ላይ የተነሡት ዐሳቦችና ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተሰጡት ማብራሪያዎች በቂ ማሳያዎች ናቸው። በቀሪው ጊዜም ይህን መሰል ገንቢና አስተማሪ ዐሳቦችን በሚገባ በማንሸራሸር በተቋም ደረጃ መፍትሔ የሚፈለግበትን መንገድ በመጠቆም በጉባኤው ላይ የተነሡ ዐሳቦችን መሠረት በማድረግ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ የሚያርፍበትን ሁኔ ታ በማመቻቸት ቢያንስ በዚህ ዓመት ችግሮቻችንን በውል ተገንዝበን ከችግሮችን መውጣት በመጀመር ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን መታደግ እንድንጀምራለን የሚል ተስፋ አለን።
በአጠቃላይ በዘንድሮ ጉባኤያችን ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ጉባኤው መገባደጃ ቀን ድረስ የተመዘገቡ ውጤታማ ተግባራትን እውቅና መስጠት ተገቢ ስለሆነ ጉባኤው ያማረና የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ፣በልዩ ልዩ ኮሚቴዎች በመታቀፍ ውጤታማ ሥራ ላከናወናችሁ የኮሚቴ አባላት፣ለጉባኤው ሞገስ በመሆን ለሰነበታችሁ ለመላው ጉባኤ አባለት ምስጋና ሊቸራችሁ ይገባል።
ከሁሉ በላይ ዘመኑን የሚመጥን አባታዊ መልዕክት በማስተላለፍ፣ በጸሎት በመክፈትና በመዝጋት ፣አባታዊ ምክርና ትምህርት በመስጠት በትዕግሥት ጉባኤውን ሲመሩ የሰነበቱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቅድስት ጸሎትዎና ቡራኬዎ ለጉባኤያችን ሞገስ ሆኖታልና ዘወትር ቡራኬዎ እንዳይለየን እንጸልያለን።
"ልዑል እግዚአብሔር ጉባኤያችንን በሰላም ያስጨርሰን! "
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ጥቅምት ፱ ቀን ፳፻ ፲ወ ፮ዓ.ም
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ

፵፪ ኛው ዓለምአቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
****
ለ፵፪ ኛ ጊዜ የሚካሔደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓለም አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የተዋጣለት፣የተሳካና ውጤታማ በሆነ መልኩ መከናወን ይችል ዘንድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹ በሚገባ ታቅደው፣ ለእያንዳንዱ ተግባር አስፈጻሚና ፈጻሚ አካል ተቀምጦለት የተከወነ ከመሆኑም በላይ የእያንዳንዱ ኮሚቴ የሥራ አፈጻጸምና አጠቃላይ የቅድመ ዝግጅት ሥራው አፈጻጸም በብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሚመሩት አስተዳደር ጉባኤ ተገምግሞ ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ከተስተካከሉና ከታረሙ በኋላ ወደ ተግባር እንዲለወጡ ተደርጓል፤ ይህም በመደረጉ እያንዳንዱ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ያማረና የተዋበ እንዲሆን ማድረግከመቻሉም በላይ በአፈጻጸም ደረጃም ውጤት የተመዘገበበት መሆን ችሏል።
ጉባኤው ውጤታማ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር እንዲረዳን በየዕለቱ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጸሎትና ቡራኬ ተከፍቶ በቅዱስነታቸው ሊቀ መንበርነትና መመሪያ መሠረት እየተካሄድ ይገኛል ፡፡
በተለይም ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጉባኤውን ፍትሐዊ በሆነ መልኩ በመምራታቸው የሰዓት መዛነፍና የተንዛዛ ሪፖርት እንዳይቀርብ ማድረግ ያስቻለ ሲሆን ከመርሐ ግብር ውጪ የሆኑና መስመራቸውን የሳቱ እንዲሁም ከእውነተኝነት የራቁ ሪፖርቶችን በማረቅ ሐቁ በግልጽ እንዲቀመጥ ያደረጉበት ጥረትም የብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን የጉባኤ አመራር ጥበብና ብቃት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ተግባር ሆኖ ተመዝግበዋል። ጉባኤውም በተደጋጋሚ ጊዜ ይህን ሐቅ በጭብጨባ ሲገልጽ ተስተውሏል።
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
ጥቅምት ፱ (9) ቀን።
እንኳን #ኢትዮጵያዊው_ጻድቁ ለታላቁ አባት #አቡነ_መዝገበ_ሥላሴ_ለዕረፍታቸው በዓል፣ #ለኢትዮጵያዊው_ንጉሥ_ግሸን_ደብረ_ከርቤ ያለው ቅዱስ መስቀሉን በመጀመሪያ ወደ አገራችን ላስገቡት እመቤታችን ቅድስት ድንግል መማርያሜን በጣም ይወዷት ለነበሩት #የአፄ_ዳዊት_ለዕረፍት መታሰቢያ ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን።
እንኳን #ሐዋርያው_ቅዱስ_ቶማስ_በሕንድ_አገር ተአምር ላደረገበት መታሰቢያ በዓል፣ ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት #ለአቡነ_ሊዋርዮስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል፣ ለከበረ ለትሑቱ ለአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት #ለአቡነ_አትናስዮስ ለዕረፍት በዓል፣ በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን #በአንጾኪያ_አገር_የሰማዕታት መጀመሪያ ሁኖ ለሌላው #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ከኤጲስቆጶስ #ከቅዱስ_ስምዖን ከዕረፍቱ መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
በተጨማሪም ሁሉም አኅጉረ ስብከቶች ሥርዓተ ትምህርቱ ተግባራዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልእክት አስተላልፈዋል።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
ለሰ/ት/ቤቶች መማሪያነት የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በኩል ተዘጋጅቶ ወደ እንቅሰቃሴ እየገባ በሚገኘው የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ ለ አጠቃላይ ዓለም አቀፍ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች ማብራሪያ ቀርቧል።
ማብራሪያውን የሰጡት የአገር አቀፍ ሰ/ት/ቤት አንድነት ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው እንደተናገሩት የሰ/ት/ቤች ሥርዓተ ትምህርትን ለመቅረጽ እጅግ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል።
አሁን ተቀርጾ ወደ ተግባር እንዲገባ የሚጠበቀው ሥርዓተ ትምህርት 6 ዋና ርእሶች እና አንድ ደጋፊ ርእስ ያለው ሲሆን ለዘንድሮው ዓመት ትግበራ እንዲሆን 42 መጽሐፍት ታትመው እና በሊቃውንት ጉባኤ ተገምግሞ ዝግጁ ሆኗል።
አቅራቢው በተጨማሪ እንደገለጹት ሥርዓተ ትምህርቱ አሁን ያለው ትውልድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተረድቶ መንፈሳዊ ወጣት እንዲሆን የሚያስችል ዕውቀትን የያዘ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለተግባራዊነቱ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቃ ጳጳስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዳሉት አሁን ያለውን ትውልድ ለማዳን ሰ/ት/ቤትን ማጠናከር የግድ ይለናል ብለዋል።
የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የአኅጉረ ስብከቶች ሪፖርት ተጠናቀቀ
ከጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ያለው የአጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የአኅጉረ ስብከቶችን የ2015 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሲያዳምጥ ቆይቷል።
በዛሬው ዕለትም ቀሪ የውጭ አገራት አኅጉረ ስብከቶችን ሪፖርት አዳምጦ የሪፖርት መርሐ ግብሩን አጠናቋል።
የሪፖርት ማቅረብ መርሐ ግብሩ መጠናቀቅን ተከትሎ የሰ/ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ ከሰ/ት/ቤት አንድነት ጋር በጋራ በመሆን ለሰ/ት/ቤቶች መማሪያ በተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ መወያየት ጀምሯል።