es
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Ir al canal en Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Mostrar más
603
Suscriptores
Sin datos24 horas
-87 días
-1630 días
Archivo de publicaciones
የኅዳር  ጽዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል  በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

የኅዳር  ጽዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል  በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የኅዳር ጽዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ! ኅዳር
+3
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የኅዳር ጽዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ! ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም

የእመቤታችን ጽዮን ማርያም በዓለ ንግስ በወላይታ በኦቶና ደብረ ጽዮን በድምቀት ተከበረ።
+4
የእመቤታችን ጽዮን ማርያም በዓለ ንግስ በወላይታ በኦቶና ደብረ ጽዮን በድምቀት ተከበረ።

የጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ቃጅማ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅድስት ማርያም አብያተ ክርስቲያናት በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡
+3
የጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ቃጅማ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅድስት ማርያም አብያተ ክርስቲያናት በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡

የእመቤታችን ጽዮን ማርያም በዓለ ንግስ በአክሱም ጽዮን ማርያም በድምቀት ተከበረ።
+2
የእመቤታችን ጽዮን ማርያም በዓለ ንግስ በአክሱም ጽዮን ማርያም በድምቀት ተከበረ።

ዓመታዊው የኅዳር ጽዮን ክብረ በዓል በአዳማ ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ካቴድራል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
+3
ዓመታዊው የኅዳር ጽዮን ክብረ በዓል በአዳማ ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ካቴድራል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

🌹እንኳን ለጽዮን ማርያም ማሕደረ አምላክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🌹ጽዮን ማለት ጸወን፣ አምባ ፣ መጠጊያ ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም
🌹እንኳን ለጽዮን ማርያም ማሕደረ አምላክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🌹ጽዮን ማለት ጸወን፣ አምባ ፣ መጠጊያ ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል። 🌹አምላከ ቅዱሳን የአማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያምን ጣዕሟን ፍቅሯን ጸጋ በረከቷን ያሳድርብን አሜን √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፳፩ (21) ቀን። እንኳን#ለእናታች_ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_ታቦተ_ጽዮን የፊልስጥኤማውያን ጣዖት ዳጎንን ለሰ
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝       ✝ #ኅዳር ፳፩ (21) ቀን። እንኳን#ለእናታች_ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_ታቦተ_ጽዮን የፊልስጥኤማውያን ጣዖት ዳጎንን ለሰባበረችበት (ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ # 1ኛሳሙ 5)፣ #ወደ_ኢትዮጵያ_ገብታ_አክሱም ለመጀመርያ ጊዜ ለከበረችበትና ታቦተ ጽዮን ከነበረችበት ድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት #በተአምራት_አብርሃና_አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በመንፈስ ቅዱስ ገብታ ለተገኘች ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና ለኢትዮጽያዊው ጻድቅ #ለአቡነ_ተወልደ_መድኅን ለበዓላቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሮሜ አገር ከሆነ ተአምራት ከሚያደርግ (ከገባሬ መንክራት) #ከቅዱስ_ጎርጎርዮስ ዕረፍት፣ ከእስክድርያ ሃምሳ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_ቆዝሞስ ዕረፍት ከእስሙናይ አገር ሰማዕታት #ከእልፍዮስ_ከዘኬዎስ_ከሮማኖስ፣_ከዮሐንስ፣ #ከፊቅጦርና_ይስሐቅ ከመታሰቢያቸው፣ ከብርሌና ከብርጭቆ ሠሪዎች ልጅ ከሆነ ከአስዩጥ ሀገር #ከቅዱስ_አባት_ከአባ_ዮሐንስ_ዕረፍትና፣ ጫብሬ ከምትባል ከአገር ድልበት #ከቅድስት_ዲቦራ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ

 🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊   ጾም - ፩ " በጾም አፋችሁ ብቻ ሳይሆን ዐይኖቻችሁ ፣ እግሮቻችሁ ፣ እጆቻችሁና የሰውነታችሁ ሕዋሳቶች በሙሉ ይጹሙ እግሮቻችሁ የኃጢአት ሥራን ለመፈጸም ከመፋጠን ይጹሙ ዐይኖቻችሁ ውጪያዊ በኾነ ውበት ምክንያት ከመቅበዝበዝ ይጹሙ ጥሉላት [የፍስክ ምግብ] እየበላችሁ አይደለም አይደል? እንኪያስ በዓይኖቻችሁ ክፉ ነገር አትብሉ  የሚታዩ ነገሮች ለዐይን ምግቦች ናቸውና ጆሮዎቻችሁም ይጹሙ የጆሮ ጾም ሐሰተኛ ወሬንና ሐሜትን አለመስማት የመሳሰለ ነው አንደበታችሁም ከከንቱ ንግግር ይጹም፡፡ ዓሣንና ሌሎች ጥሉላትን ከመብላት ተከልክለን ሳለ  ነገር ግን ወንድሞቻችንን በሐሜት የምናመነዥካቸውና የምንበላቸው ከኾነ ምን ጥቅም አለው? ወንድሙን የሚያማና የሚነቅፍ ሰው እርሱ የወንድሙን አካል ያቆስላል  ሥጋውንም ይበላል ለዚህም ነው ሐዋርያው ይህን አስመልክቶ እጅግ የሚያስደነግጥ ንግግርን የተናገረው እንዲህ ሲል ፦ "እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" [ገላ.፭:፲፭] ስታሙ በጥርሳችሁ የወንድማችሁን ሥጋ አትነክሱም ነፍሱን ግን ታቆስሏታላችሁ እንዲህ በማድረጋችሁ ራሳችሁን  ወንድማችሁንና ሌሎች ብዙ ሰዎችን ትጎዳላችሁ፡፡ አንደበታችሁ ክፉ ነገርን ከመናገር ካልጾመ ጉዳቱ በዚህ ብቻ አያበቃም በሐሜታችሁ እናንተን የሚሰማ ወንድማችሁን የሐሜት ተባባሪ ይኾናል በዚህ ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርጉታላችሁ የራሱን ኃጢአት እንዳይመለከት ስላደረጋችሁት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል በዚህ ሰዓት የሌሎች ወንድሞቹን ድካም እየተመለከተ እርሱ ግን በመጾሙ ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል "    📌📌    ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ📌📌 💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፳ (20) ቀን። ✝ እንኳን #በወንጌላዊ_ቅዱስ__ማርቆስ እጅ ጵጵስና ለተሾመው ለእስክንድርያ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለቅዱስ_
✝ በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝            ✝ #ኅዳር ፳ (20) ቀን። ✝ እንኳን #በወንጌላዊ_ቅዱስ__ማርቆስ እጅ ጵጵስና ለተሾመው ለእስክንድርያ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_አንያኖስ_ለዕረፍት በዓልና ለሠራዊት አለቃ ለከበረ #ለሰማዕት_ቅዱስ_ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት በዓል በሰላም አደረሰን።                                                           ✝ ✝ ✝ ✝ #ሊቀ_ጳጳስ_ቅዱስ_አንያኖስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አረማውያን ናቸዉ እርሱም ጫማ ሰፊ ነበር ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስ ወደ እስክንድርያ አገር መጀመርያ በገባ ጊዜ እግሩን ተደናቅፎ ጫማው ተቆረጠ እንዲሰፋለትም ወደ ጫማ ሰፊ አንያኖስ ዘንድ ሔደና ጫማውን ሰጠው መስፋትም በጀመረ ጊዜ መስፊያው ጣቱን ወጋው በዮናኒም ቋንቋ "አቴኦስ" አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም የእግዚአብሔርን ስም ሲጠራ በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰገነው። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በሕገ ወጥ ታጣቂ ኃይሎች ባለፉት 3 ቀናት ብቻ በደረሰ ጥቃት ከ36 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተገለጸ፡፡ ኅዳር 19/2016 ዓ.ም ለደህንነታቸው ሲባ
+1
በምሥራቅ አርሲ  ሀገረ  ስብከት  ሽርካ ወረዳ በሕገ  ወጥ  ታጣቂ  ኃይሎች  ባለፉት 3 ቀናት ብቻ  በደረሰ ጥቃት  ከ36 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተገለጸ፡፡ ኅዳር 19/2016 ዓ.ም ለደህንነታቸው  ሲባል  ስማቸውን  መግለፅ ያልፈለጉት ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን  መረጃ ያደረሱን ተጎጂዎች  እንደገለጹት  ከሆነ  በሶሌ መድኃኔ ዓለም  እና  ሴሮ  ቅዱስ  ሚካኤል  ቤተክርስቲያን  ኅዳር  13  ቀን   በተፈጸመው  አሰቃቂ  ግድያ  28  ኦርቶዶክሳዊን  መገደላቸው  በመጠቆም   ኅዳር  17 ቀን  2016  ዓ.ም ደግሞ  8  ምእመናን  በድምሩ  36  ምእመናን  መገደላቸው ጠቅሰዋል፡፡  በርካቶችም   ከባድና  ቀላል  የአካል  ጉዳት እንደደረሰባቸው  ተጠቁሟል፡፡  በሽርካ ወረዳ  በተደጋጋሚ  ግዜ  በደረሰው  ጥቃት  ነፍሰጡር  ሴትን  ጨምሮ  ጨቅላ  ሕጻናት  የተገደሉ  ሲሆን  የሟቾች  ቁጥር  አሁንም  ሊጨምር  እንደሚችል ገልፀዋል። በአካባቢው  ምእመናን  ላይ  እንዲህ  አይነት  መሰል  ጥቃት  ሲፈጸም በአንድ  ሳምንት  ውስጥ  ለሶስተኛ  በ2016  ዓ.ም  ደግሞ  ለአራተኛ  ጊዜ  መሆኑንም   ተናግረዋል ። ጥቃቱ  የደረሰባቸው  ምእመናን  በአሁኑ  ወቅት  በከፍተኛ  ስጋት  ውስጥ  የሚገኙ ሲሆን በአካባቢው  እየደረሰ  ያለውን  አሰቃቂ  ግድያ   አስመልክቶ  ለሚመለከታቸው  የመንግስት  የጸጥታ  አካላት  ሀገረ ስብከቱ  የማሳወቅ ስራ  እንደሚሰራ  ተገልጿል ። መረጃው የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን  ነው::

💥💥💥💥💥💥💥💥💥💫💫💫💫💫💫💫💫💥💥💥💥💥💥💥💫💫💫💫💫💫💫💥💥💥💥 #ለ20ኛ ጊዜ"አንድነታችን ለቤተክርስቲያናችን" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቀቀ!!! 16/03/2016 ዓ.ም 💥💥💥💥💥💫💫💫💫💫💥💥💥💥💥💫💫💫💫💫💫💥💥💥💥💥💫💫💫💫💫 ከሕዳር 15-16/2016 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጠናቀቀ። በጉባኤውም ላይ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ እና የአሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ፣ መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሳኤ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ኃላፊ ፣ መልአከ ብርሃናት ቀሲስ ተክለርትዕ ገብረ ወልድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ ፣ መምህር ደምስ በየነ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ክፍል ዋና ኃላፊ ፣ የሀገር አቀፍ እና የአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሥራ አመራር አባላት ፥ የአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የሥራ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በሁለተኛው ቀን የጉባኤው የጠዋት ውሎው በ5 የትኩረት አቅጣጫ ላይ ትኩረቱን ያደረገውን የ2016 ዓ.ም የመጪው የ6 ወር ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከተሳታፊዎች ብዙ ግብአቶች ተገኝቷል። ለተነሱትም ጥያቄዎች ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ እና መምህር አንተነህ አወቀ የአንድነቱ ዋና ጸሐፊ መልስ ሰጥተውባቸዋል። ከምሳ መርሐግብር በኃላ በቀጠለው በከሰዓቱም መርሐ ግብር የሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላትና ምዕመናን በቃለ አዋዲ በተሰጣቸው የመወሰን ድርሻ እንዲሁም የአንድነቱን አወቃቀር ሥልጣንና ኃላፊነት የሚዳስስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። በመቀጠልም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መመምሪያ እና በአንድነቱ የተዘጋጀውን የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም ቤተክርስቲያን አሁን ካለችበት ፈተና (ከወቅታዊ ) አንጻር ቤተክርስቲያናችንን ልንጠብቅ ንቁ የሆነ ተሳትፎ ሊኖረን ይገባል ሲሉ መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሳኤ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ኃላፊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ባስተላለፉት አባታዊ ምክር "መልካም አገልጋይ በንጉሡ ይወደዳል።" በሚል መነሻ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ትውልድን በመቅረጽ የሚያገለግሉት አገልግሎት በንጉሥ እግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ሊሆን እንደሚገባው ፤ አንድነትን በማጠናከር በሰፊው መሥራት እንደሚገባ መክረዋል። በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይም ላለፉት 3 ዓመታት የአንድነቱ የሥራ አመራር በመሆን የኃላፊነት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የሥራ አመራሮች በጸሎተ ማርያም ሸኝቶ ከ7ቱም ክፍላተ ከተማ አንድነት የተወከሉትን እና የተመረጡትን የአዲስ አበባው አንድነት አዲሱን ሥራ አመራር በማጽደቅ እንዲሁም በዚሁ የሥራ አመራር ላይ ከተመረጡት ውስጥ የአንድነቱ ጽ/ቤት ተቋቁሟል። በዚህም፦ ፩.ላዕከ ኄራን መንክር ግርማን በድጋሚ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ በማድረግ ፤ ፪.ዲ/ን በላይ ገ/ሕይወት የአንድነቱ ምክትል ሰብሳቢ ፤ ፫.ወጣት ኤደን ሀብቱ የአንድነቱ ዋና ጸሐፊ አድርጎ በመምረጥ ሰይሟል። ለእዚሁ አገልግሎታቸው የተቃና እንዲሆን በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ጸሎተ ማርያም ተደግሞላቸው የሥራ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። በመጨረሻም ላይም የጠቅላላ ጉባዔው በሁለቱ ቀናት ሲወያይበት በቆየው ዙሪያ የአቋም መግለጫ በማውጣት ጉባኤው በጸሎት ተጠናቅቋል። #የአዲስ_አበባ_ሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት 💥💥💥💥💫💫💫💫💥💥💥💥💫💫💫💫💫💥💥💥💥💫💫💫💫💥💥💥💥💫💫💫💫💥💥💥

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፲፱ (19) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ለዓለም_ብርሃን ለሆኑት እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው #ከሃያ_አራቱ_ካ
✝ በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝           ✝ #ኅዳር ፲፱ (19) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ለዓለም_ብርሃን ለሆኑት እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው #ከሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ_ጋር_የሥላሴን_መንበር ላጠኑት #ለአቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት_ለልደታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።                              ✝ ✝ ✝ ✝ #አባ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት፦ አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊት እናታቸው ዳግም ሞገሳ ይባላሉ፡፡ ትውልድ ሀገራቸው ወሎ መቄት እንጂፋ ነው፡፡ አባታችን አባ ዮሴፍ ኅዳር 19 ቀን ሲወለዱ በርካታ ሙታን ተነሥተዋል፡፡ ይህም ቅዱስ ያዩትና የሰሙት እስቲያደንቁት ድረስ በአባቱ ቤት ሳለ የዚህን ዓለም ጥበብ ሁሉ ተማረ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ተረጐመ ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾሙት። ✝ የነፍሱንም ድኅነት እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ብርሃናዊ መልአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ላከለትና "ዮሴፍ ሆይ ይህን ኃላፊውን ዓለም ትወድዋለህን አስጸያፊ አይደለምን በውስጡም ያለ ሁሉ" አለው። ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ እርሱ የመረጠውን መንገድ ይመራው ዘንድ እግዚአብሔር እየለመነ ጾምና ጸሎትን ጀመረ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

የጠቅላይ ቤተክህነትና የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባዔ አባላት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ የጋራ ጉባዔ በማድረግ ላይ ናቸው። ኅዳር 18 /2016  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳደር ጉባኤ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ጋር በሁለትዮሽ የአሰራር ሒደት፣በመልካም አስተዳደር፣በሕግ ፣ደንቦችና መመሪያዎች አከባበር በአጠቃላይ ሥራዎችን በተቋማዊ አሰራር ሒደት በማከናወን ዙሪያ የጋራ መድረክ ተዘጋጅቶ ውይይት እንዲደረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ዛሬ ኅዳር ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ የጋራ ጉባኤ በማካሔድ ላይ ናቸው። በጉባኤው መክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ የተገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት፣ቃለ በረከትና ቡራኬ በቤተክርስቲያናችን ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር ሁላችንም እናውቀዋለን።ማስተካከልም እንችላለን ብለዋል። እኛ በቤተክርስቲያናችን የሚስተዋለውን ችግር ለማስተካከል የምንቸገረው ልባችን ስላልተስተካከለ ነው።ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ራሳችንን ሳናስተካክል ሌላውን ማስተካከል ስለማንችል ቅድሚያ ራሳችንን ለማስተካከል ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል ብለዋል። አያይዘውም  ሁላችንም የቆምነው ለቤተክርስቲያናችን እንጂ ለሌላ ዓላማ አይደለም።ያሉት ቅዱስነታቸው  ችግሮቻችንን ለመፍታት መወያየት ተገቢ ነው።"ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም" እንደሚባለው ሁሉ ችግሮቻችንን ለመፍታት ከልብ ከተነሳን የሚያስቸግር ነገር ይኖራል ብለን አናምንም ካሉ በኋላ ከተጠያቂነትና ከተወቃሽነት ለመዳን፣ቤታችንን ለማቅናትና ለማስተካከል የሚጎለን ምንድነው ?ያሉት ቅዱስነታቸው ይህን ለማድረግና ቤተክርስቲያናችንን ለመጠበቅ ሙሉ ሥልጣንና ኃላፊነት እያለን መቸገራችን ያስገርማል ብለዋል። ዘወትር ሁላችንም ራሳችንን መመርመር አለብን የት ነው ያለነው፣ምንድነው የምንሰራው፣ወዴት ነው የምንሔደው ብለን ራሳችንን  በመጠየቅ ያለፈውን ጊዜ ችግሮች ማሰብና በተሰጠን መንፈሳዊ ኃላፊነት ልክ በመስራት ቤተክርስቲያንን መጠበቅና ምዕመናንን የሚያረካ ተግባር መፈጸም ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው ሁላችንም ራሳችንን በአግባቡ በመመርመር ራሳችንን እናስተካክል ካሉ በኃላ በአንድነትና በጽናት ለቤተክርስቲያናችን እንቁም።በመመካከር አንድ ሆነን በመቆም ለቤተክርስቲያን ህልውና በጋራ እንስራ እኛ ተመካሪዎች አይደለንም መካሪዎች እንጂ ስለዚህ መመካከር ችግሮችን ለመቅረፍ የሚጠቅም ስለሆነ ተመካክረን እንስራ  ችግሮችንም በግልጽ በማውጣት ለችግሮቻችን መፍትሔ በማበጀት  ለውጤት ልናበቃው ይገባል በማለት አባታዊ መልእክታቸውን በማጠናቀቅ ጉባኤውን በይፋ ከፍተዋል። ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት፦ መልካም አስተዳደርን ለማምጣትና ችግሮችን ለመፍታት ውይይት ወሳኝ ነው።ቅዱስነትዎም  በቤተክርስቲያናችን መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን  የዘወትር  ምኞትዎና ጸሎትዎ እንደሆነ ይታወቃል። በዚህ ጊዜ የሚታየውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በጋራ ተወያይተን መፍታትና የቁጥጥር ሥርዓታችንን በማጥበቅ ችግሮችን በአግባቡ መፍታት አለብን ብለዋል አያይዘውም  ህገወጥ ቅጥርና ዝውውርን በተመለከተ እየተከናወነ የሚገኘውን ህገ ወጥ ቅጥርና ዝውውር በማረም በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በቀረበው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት መስራት ይኖርበታል ብለዋል። ሀገረ ስብከቱና ጠቅላይ ቤተክህነቱ ተናበውና ተግባብተው መስራት በሚገባቸው ጉዳዩች ላይም ሕግንና ሕግን መሰረት አድርገን መስራት ስለሚገባቸው ይህን መድረክ ለማዘጋጀት ተገደናል ያሉት ብፁዕነታቸው የዚህ መድረክ ዓላማ ለመወነጃጀል ለመነቃቀፍና ለመተቻቸት ሳይሆን በመወያየትና በመግባባት በሀገረ ስብከቱ የሚታዩትን ችግሮች ለመፍታት ነው  በማለት የመክፈቻ ንግግራቸውን አጠቃለዋል። ጉባኤው በዛሬው እለት  በሚያካሒደው ጥልቅ ውይይት ሕግ፣መመሪያ፣ደንቦችና ተቋማዊ አሰራሮችን በጠበቀ መልኩ ሥራዎችን በማከናወን  ማዕከላዊነትን ባለማክበር ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ተቋማዊና ሕጋዊ አሰራሮችን በመተግበር በሀገረ ስብከቱና በጠቅላይ ቤተክህነት መካከል  መዋቅራዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር የሚያስችሉ ልዩልዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።