ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Ir al canal en Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Mostrar más608
Suscriptores
-124 horas
-47 días
-1230 días
Archivo de publicaciones
🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹
🌹 #ጥቅምት ፲፬ (14) ቀን።
🌹 እንኳን #ከዘጠኙ_ቅዱሳን_አንዱ ለሆኑት #ለአባ_ዘሚካኤል በሚሰሩት ስራቸው አረጋዊ ለተባሉት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አረጋዊ ከዚህ ዓለም ከሞት ለተሰወሩበት ቀን ለመታሰቢያ በዓል፣ ለቊስጥንጥንያ ንጉሥ ለቴዎዶስዮስ ልጅ ለሙሽራወ #ለቅዱስ_ለገብረ_ክርስቶስና ከሮሜ ሀገር ለሆነ ለእግዚአብሔር ሰው #ለቅዱስ_ሙሴ_ለዕረፍታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከመራክዋና ከእርሱ ጋር ካሉ ሰማዕታት፣ #ከድማቴዎስና_ከምራይስ #ከአራት_መቶ_ሠላሳ_አንድ_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
🌹 #አባ_ዘሚካኤል_አቡነ አረጋዊ፦ እኚህ አባት ከ9 ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉሥ ነበሩ፡፡ እናታቸው ንግሥት እደና ይባሉ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳ ሲማሩ አድገው ወደ እስክንድርያ ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ አባ ጳኵሚስ በፈቃደ እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውን አውቀው መዓረገ ምንኵስና ሰጥተዋቸዋል፡፡
🌹 የንጉሣዊ የቅንጦት ኑሮ ንቀው ትተው ገዳም ገብተው በምንኵስና ተወስነዋል፡፡ አባታችን በተጋድሏቸውም ከአባ እንጦንስ፣ ከአባ ጳውሊ እና ከአባ መቃርስ ቀጥሎ በአራተኛ ማዕረግ አበ መነኰሳት ሆነው ተመርጠዋል።
🌹 በገዳመ ዳውናስ 7 ዓመት ከቆዩ በኋላ ወደ ሮም ተመልሰው ሲያስተምሩ የሀገራችን ኢትዮጵያን ዜና ሰምተው ለመምጣት በ480 ዓ.ም ከአባ ፍሬምናጦስ በኋላ መንገድ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በክንፉ ተሸክሞ አክሱም አድርሷቸዋል፡፡ ተመልሰውም ሄደው ስለ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መስክረዋል፡፡ "ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች" ብለው ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበው መነኰሳት ነገሯቸው፡፡ ስምንቱም ጓዛቸውን ጠቅልለው በሮም ነግሦ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉሥ አልአሜዳ በነገሠ በአምስተኛ ዓመት ማለትም በ480 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ዘጠኝ ሆነው መጥተዋል፡፡
🌹 አባ አረጋዊ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀ መዝሙራቸውን ማትያስን አስከትለው እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደረሰዋል፡፡ ከእግረ ደብር ሆነው አሁን "ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ" እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝ 90፥11-16 ላይ "በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ"። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡
🌹 ወዲያው ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡ በሰንበተ ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላቸው ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላም ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል፡፡
🌹 ስለ አባታች አቡነ አረጋዊ መሰወር፦ የእርግና ዘመኑ ደረሰ ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሆነው። በነጋም ጊዜ ቆሞ ሲለምንና ጸሎትም ሲያደርግ ተመለከተው በምን ጊዜ ወይም ሰዓት ከነሱ እንደሚሠወር ደቀ መዝሙሩ አባ ማትያስ ይጠባበቅ ወይም በልቡ ያስቡ ነበርና።
🌹 ጸሎት ያደርግ ዘንድ ቀድሞ ወደነበረበት ተመልሶ ገባ ወይም ሄደ። ዳግመኛም ሦስት ሰዓት በሆነ ጊዜ ተመልሶ መጣ ነገር ግን ከበዓቱ በደረሰ ጊዜ አላገኘውም እሱ ተሠውሯልና። በዚያም ከመቋሚያና ከመስቀል በስተቀር ምንም ያገኘው ነገር የለም ይህንኑም ለወንድምቹ ነገራቸው። እነርሱም ጮሁ ዋይ ዋይም አሉ እሱንም ያገኙ እየመሰላቸው መስቀሉንና መቋሚያውን ተሸክመው በመሳም መሪር ዕንባን አለቀሱ።
🌹 ኀዘናቸውንና ልቅሶአቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለክቡር አባታችን አቡነ አረጋዊ የተሰጠውን ቃል ኪዳን ደቀ መዝሙሩ አባ ማትያስ "ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁ" ብሎ ቃልኪዳን እንደሰጠው፡፡ "በስምህ የተማጸነውን እስከ ዐሥራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ" ብሎ ተስፋ እደነገራቸው፡፡ ነገራቸው ወንድሞቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ተደሰቱ ኀዘናቸውም ወደ ደስታ ተለወጠ ስለዚህም እግዚአብሔር አመሰገኑት።
🌹 በዚያን ጊዜ ቀለምና ብራና አዘጋጅተው ማትያስና ዮሴፍ እየነገሯቸው ለልጅ ልጅ መታሰቢ ሆኖ ይኖር ዘንድ የገድሉንና የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ጻፈ።
🌹 ከዚህም በኋላ በመነኰሳት ሥርዓት ማኅበር ሥርዓት ማኅበር ይኖሩ ዘንድ የሠራላቸውን ሥርዓት አሰቡ በሥርዓት ይመራቸው ዘንድ አባታቸው አረጋዊ ለሰጣቸው ለመንፈሳዊ አባታቸው ለአባ ማትያስም ራሳቸውን ዝቅ አደረጉ ሃሳባቸውንም የአባታቸው የአረጋዊዊን መታሰቢያ ወደማድረግ ተመለሱ።
🌹 ክብር አባታችን አቡነ አሰጋዊ የተሠወረበት ቀን በኢትዮጵያ ወር አቆጣጠር በጥቅምት ዐሥራ ዐራት ቀን በዕብራውያን ደግሞ በታስሪን ዐሥራ አንድ ቀን በኢትዮጵያዊው ንጉሥ በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት ነው። ከአባታች ከአቡነ አረጋዊ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ አረጋዊ።
✝ ✝ ✝
🌹 #የቊስጥንጥንያ_ንጉሥ_የቴዎዶስዮስ ልጅ መሽራው #ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ፦ ይህም ቴዎዶስዮስ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነው ሚስቱም በጎ የምትሠራ እግዚአብሔርንም የምትፈራ ናት ስሟም መርኬዛ ነው። እነርሱም ልጅ ስለሌላቸው ያዝኑ ነበር ወደ ኢየሩሳሌምም ሒደው ስእለትን ተሳሉ ቸር መሐሪ ወደሆነ እግዚአብሔርም ለመኑ እርሱም ልመናቸውን ተቀበሎ ይህን ያማረ ልጅ ሰጣቸው ስሙንም "አብደልመሲህ" ብለው ሰየሙት ትርጓሜውም "ገብረ ክርስቶስ" ማለት ነው ። የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ የሥጋዊንም ትምህርት አስተማሩት ።
🌹 አድጎ በጕለመሰም ጊዜ የሮሜውን ንጉሥ ልጅ አጭተው እንደ ሥርዓቱ አጋቡት ከሌሊቱ እኩሌታም በሆነ ጊዜ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ተነሥቶ ወደሙሽራዪቱ ገባ እጅዋንም ይዞ ከእርስዋ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። ከዚያም የሃይማኖት ጸሎት በአንድ አምላክ እናምናለን የሚለውን እስከ መጨረሻ ጸለየ የተሞሸረበትንም ልብስ ከላዩ አውልቆ የግምጃ ልብስን ለበሰ ወደ ሙሽሪቷም ሒዶ ራስዋን ሳማት እንዲህም እያለ ተሰናበታት "እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኑር ከሰይጣን ሥራ ሁሉ ያድንሽ"። እርሷም አልቅሳ "ጌታዬ ወዴት ትሔዳለህ ለማንስ ትተወኛለህ" አለችው እርሱም "በእግዚአብሔር ዘንድ እተውሻለሁ እኔም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሔዳለሁ የአባቴ መንግሥት አላፊ ነውና አንቺም መሐላሽን አስቢ" አላት ያን ጊዜ መሐላዋን አስባ ዝም አለች።
💥በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
⚡️⚡️⚡️ ስደተኞች ክፍል ፭ ⚡️⚡️
አቅራቢ :- አቤል ለታ
አብርሃም ሙላቱ
ሳሙኤል ገዛኸኝ
አዘጋጅ :-ኪነ-ጥበብ ክፍል
ጥቅምት 12
በዚች ቀን
የከበረ የመልአክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበአሉ መታሰቢያ ነው።
በዚች ቀን ወደ ነቢይ ሳሙኤል እግዚአብሔር ልኮታልና የዳዊት አባት ወደ ሆነ በቤተልሔም ወደሚኖር ወደ እሴይ ቤት ይሔድ ዘንድ በቂስ ልጅ በሳኦልም ፈንታ ለእስራኤል ልጆች እንዲነግስ ልጁ ዳዊትን ይቀባው ዘንድ አዘዘው።
ሳሙኤልም ወደ እሴይ ቤት ሒዶ ልጆችሕን ሁሉንም አቅርብልኝ አለው እሴይም ከዳዊት በቀር ሁሉን አቀረባቸው እርሱ በእርሻ ውስጥ በግ ይጠብቅ ነበርና።
ሳሙኤልም የምንግስት ቅባት ያለበትን ብልቃጥ በራሳቸው ከፍ ከፍ ባደረገ ጊዜ እግዚአብሔር አልመረጣቸውም ።
ሳሙኤልም እሴይን ልጆችህ እነዚህ ብቻ ናቸው አለው እሴይም በጎችን የሚጠብቅ አንድ ትንሽ ልጅ አለ አለው።
ሳሙኤልም ደግሞ እሴይን እሱ ሳይመጣ ምሳ አልበላምና ልከህ አስመጣው አለው።
እሱም ልኮ አስመጣው መልኩም ቀይ አይኖቹም የተዋቡ አርአያውም ያማረ ነው።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ይሕ ይበልጣቸዋልና ተነስተሕ ቀባው አለው።
በዚያም ጊዜ ሳሙኤል የመንግስት ቅባት ያለበትን ቀንድ አምጥቶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው ከዚያችም ቀን ጀምሮ ለሁል ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት ላይ አደረበት በእስራኤል ልጆችም ላይ ነገሠ።
ደግሞ ሁለተኛ በዚች ቀን እግዚአብሔር የመልአክት አለቃ ሚካኤልን ወደ ዳዊት ላከው ረዓይታይ ጎልያድን እስኪገደለውና የእስራኤል ልጆችን እስከሚያድናቸው ረድቶ ኃይልን ሰጠው ።
ስለዚህ የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በአሥራ ሁለት ቀን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርሥቲያን መምህራን አዘዙ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን ።
ስንክሳር ዘወርኃ ጥቅምት
ጥቅምት ፲ /10/በዚህች ቀን የቅዱስ ባኮስና ቅዱስ ሰርጊስ መታሰቢያ ነው። ባኮስ እና ሰርጊስ ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች ናቸው። ጾምን ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ ይከተሉ ነበር። ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ። እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ ጭፍሮች ሆኑ። ከቆይታ በሁዋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ። በአዋጅም ክርስቲያኖችን ያሰቃይ ይገድልም ያዘ። በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው አለቃቸው ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት። "እሺ" ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቀያና የክብር ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች ነንና ከዚህ በሁዋላ ላንተ ለጣዖት አምላኪው አንታዘዝም" አሉት። መኮንኑም በጽኑ አሰቃያቸው። እነርሱ ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም። ጥቅምት 4 ቀን በሆነ ጊዜ ግን 2ቱን ለያዩዋቸው። ቅዱስ ባኮስን ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት። ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር አስወጣችው። በአካባባቢውም ባባ እና ማማ የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት አዘዛቸው። ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ ሲጠብቁት አግኝተው በታላቅ ዝማሬ ገንዘው በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት። ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ በዚህች ቀን እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል። አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ በረከትን አግኝታለች። የመከራ ዘመን ካለፈ በሁዋላም ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል። በረከታቸው ይደርብን!አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
✞ ስንክሳር ጥቅምት 8 ✞
🌿🌿🌿
እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "አባ አጋቶን ወአባ መጥራ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
✍" አባ አጋቶን ባሕታዊ "✍
ይህንን ቅዱስ የማያውቅ የቤተ ክርስቲያን ሰው ይኖራል ብየ አልገምትም:: እርሱ ታላቅ ጻድቅ: ገዳማዊና የእግዚአብሔር ሰው ሲሆን አንደበቱን ከክፋት ይከለክል ዘንድ ለ30 ዓመታት ድንጋይ ጐርሶ ኖሯል::
ይህንን ቅዱስ ሊቃውንት ሲገልጹት:
"ክምረ ክምር ጽድቁ እስከ አስተርአየ" ይሉታል:: ትእግስቱ: ደግነቱ: አርምሞው: ትሩፋቱ ከመነገር በላይ ነው:: በነበረበት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም እንደ ኮከብ ያበራ ታላቅ አባት ነው::
ታላቁ ገዳማዊ ሰው አባ አጋቶን የታላቁ መቃርዮስ ቅዱስ ልጅ ነው:: ገዳመ አስቄጥስ እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን ስታፈራ ይህ አባት ቅድሚያውን ይይዛል:: ምንም በብዛት የሚታወቀው በአርምሞው (በዝምታው) ቢሆንም ባለ ብዙ ትሩፋት አባት ነው::
የሚገርመው የቀደሙ አባቶቻችን የፈለገውን ያህል መናኝ ቢሆኑም የሰው ጥገኛ መሆንን አይፈልጉም:: "ሊሠራ የማይወድ አይብላ" የሚለውን መለኮታዊ ትዕዛዝ መሠረት አድርገው ከተጋድሎ በተረፈቻቸው ሰዓት ሥራ ይሠራሉ::
አንዳንዶቹ እንደሚመስላቸው ምናኔ ሥራ መፍታት አይደለምና ሰሌን: ዕንቅብ: ሠፌድ የመሳሰለውን ይሠፋሉ:: ታላቁ አባ አጋቶንም በአንደበቱ ድንጋይ ጐርሶ: በእግሮቹ ቀጥ ብሎ ቆሞ እንቅቦችን ይሠፋ ነበር::
ለነገሩስ ዛሬ ዛሬ እንኩዋን ወንዶቹ ሴቶችም ብንሆን ይህንን ሙያ እየረሳነው ነው:: ቅዱሱ ግን ይሰፋና ወደ ገበያ ይወጣል:: በጠየቁት ዋጋ ሽጦት አንዲት ቂጣ (ዻኩሲማ) ይገዛል:: የተረፈውን ገንዘብ ግን እዚያው ለነዳያን አካፍሎት ይመጣል እንጂ ወደ ገዳሙ አይመልሰውም::
ታዲያ አንድ ቀን እንደልማዱ የሠፋቸውን 5 እንቅቦች ተሸክሞ ወደ ገበያ ሲሔድ መንገድ ላይ አንድ ነዳይ (የኔ ቢጤ) ወድቆ ያገኛል:: እንደ ደረሰም ስመ እግዚአብሔር ጠርቶ ይለምነዋል:: አባ አጋቶን ከእንቅቦቹ ውጪ ምንም ነገር አልነበረውምና "እንቅቡን እንካ" አለው::
ነዳዩ ግን ወይ የሚበላ: ካልሆነም ገንዘብ እንደሚፈልግ ይነግረዋል:: ወዲያው ደግሞ "የምትሠጠኝ ነገር ከሌለህ ለምን ወደ ገበያ ተሸክመህ አትወስደኝም?" አለው:: የነዳዩ አካል እጅግ የቆሳሰለ በመሆኑ እንኩዋን ሊሸከሙት ሊያዩትም የሚከብድ ነበር::
ጻድቁ ግን ደስ እያለው: ያለማመንታት አንስቶ ተሸከመው:: ከረጅም መንገድ በሁዋላም ከገበያ በመድረሳቸው አውርዶ ከጐኑ አስቀመጠው:: ያ ነዳይ አላፊ አግዳሚውን ሁሉ ቢለምንም የሚዘከረው አጣ:: አባ አጋቶን አንዷን እንቅብ ሲሸጥ "ስጠኝ?" ይለዋል:: ጻድቁም ይሠጠዋል::
እንዲህ "ስጠኝ" እያለ የ5ቱንም እንቅቦች ዋጋ ያ ነዳይ ወሰደበት:: አባ አጋቶን ግን ምንም ቂጣ ባይገዛ: በሆነው ነገር አልተከፋምና ሊሔድ ሲነሳ ነዳዩ "ወደ ቦታየ ተሸክመህ መልሰኝ" አለው:: አባቶቻችን ትእግስታቸው ጥግ (ዳር) የለውምና ጐንበስ ብሎ በፍቅር አንስቶት አዘለውና ሔደ::
ካነሳበት ቦታ ላይ ሲደርሱ ይወርድለት ዘንድ ጻድቁ ቆመ:: ነዳዩ ግን አልወርድም አለ:: መቼም እኛ ብንሆን ብለን እናስበውና . . . ምን እንደምናደርግ ይታወቃል:: ጻድቁ ግን ዝም ብሎ ቆመለት::
ትንሽ ቆይቶ ግን ስለ ለቀቀው ሊያየው ዞር ቢል መሬት ላይ የለም:: ቀና ሲል ግን ያየውን ነገር ማመን አልቻለም:: ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ:: ነዳይ መስሎ እንዲያ ሲፈትነው የነበረው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነበር::
ክንፎቹን ዘርግቶ: በብርሃን ተከቦ: በግርማ ታየው:: ከወደቀበትም አነሳው:: "ወዳጄ አጋቶን! ፍሬህ: ትእግስትህ: ደግነትህ ግሩም ነውና ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎት ተሰወረው:: ጻድቁም በደስታ ወደ በዓቱ ሔደ:: አባ አጋቶን ተረፈ ዘመኑን በአርምሞ ኑሮ ዐርፏል::
🌿" ቅዱስ መጥራ አረጋዊ "🌿
ቅዱሱ የ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያን ሲሆን በትውልድ ግብጻዊ ነው:: ከልጅነት እስከ እውቀት: ከእውቀት እስከ ሽበት ክርስቶስን ሲያመልክ ኑሯል:: ዘመኑ ክርስቲያኖች ስለ ሃይማኖታቸው ከባዱን ዋጋ (ሕይወታቸውን) የሚከፍሉበት ነበር::
በወቅቱ ብርቱ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ቢበዙም ብርቱ መንፈሳዊያን ተዋጊ ክርስቲያኖች ነበሩና ውጊያው ተመጣጣኝ ነበር:: ዛሬ ደግሞ ሁሉም በዛለበት ዘመን ላይ ተገኝተናል::
ቅዱስ መጥራ ካረጀ በሁዋላ ነገሥታቱ "ክርስቶስን ካዱ" እያሉ መጡ:: ቅዱሱ ወሬውን ሲሰማ እጅግ ተገረመ:: ምክንያቱም መድኃኔ ዓለምን መካድ ፈጽሞ የሚታሰብ ነገር አይደለምና:: ቅዱሱ አረጋዊ ስለ 2 ነገር ሰማዕትነትን ፈለገ::
አንደኛ በክርስቶስ ስም መሞት የክብር ክብርን ያስገኛልና ከዚሁ ለመሳተፍ ነው:: ሁለተኛው ግን ለወጣቶች አብነት (ምሳሌ) ለመሆን ነበር:: መልካም መሪ ባለበት ዘንድ ብዙ ፍሬዎች አይጠፉምና:: ቅዱስ መጥራ እንዳሰበው ወደ መኮንኑ ሒዶ በአሕዛብ ፊት ክርስቶስን ሰበከ:: ስለዚህ ፈንታም ብዙ አሰቃይተው በዚህች ቀን ከተከታዮቹ ጋር ገድለውታል::
አምላከ ቅዱሳን ትእግስታቸውን ያሳድርብን:: ከአባቶቻችንም በረከትን ይክፈለን::
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን !
ከግ/ደ/ዓ/ቅ/አ/ቤ/ክ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
የጽ/ቤት መልዕክት
ውድ የፍኖተ ብርሃን ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ ሰ/ት/ቤታችን በ2017 ዓ.ም አባላት ሊሄዱባቸው የሚገቡ አካሄዶችን ግዴታዎችን ለማሳወቅ ይወዳል
1. ግንኙነት ክፍሉ በሚመድበው የአገልግሎት ክፍላት ገብቶ ማገልገል
2. በሰ/ት/ቤቱ የሚሰጡ ኮርሶችን መማር
3. ልማት ክፍሉ የሚሰጣቸውን ማንኛውም አገልግሎቶች ማገልገል
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማያሟላ የመዝሙር አገልግሎት ላይ ማይሳተፍ መሆኑን እናሳውቃለን።
ጥቅምት ፮ /6/በዚች ዕለት ቅዱስ አባት አባ ጰንጠሌዎን የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው። ታላቁ ጻድቅ፣ ሰባኬ ወንጌልና ገዳማዊ አባ ጰንጠሌዎን የተስዓቱ (ዘጠኙ) ቅዱሳን መሪ ናቸው። ጻድቁ ሃገረ ትውልዳቸው ሮም ቢሆንም ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮጵያ ነው። በገዳም ትምህርቱን ካጠነቀቁ በኋላ በዚያው ጠፍተው ወደ ግብጽ ወረዱ፤ በዚያም መነኮሱ። እድሜአቸው እየገፋ ሲሔድ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስምንቱን ቅዱሳን ሰብስበው በአቡነ አረጋዊ መሪነት ወደ ሃገራችን መጡ። በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ የነበረው ንጉሥ አልዓሜዳም በክብር ተቀብሎ አክሱም ውስጥ ''ቤተ ቀጢን” የሚባል ቦታን ሰጣቸው። አባ ጰንጠሌዎን 'ጾማዕት' ወደ ሚባል ረዥም ተራራ ወጡ። በዚያም አስቀድመው ለወንጌል አገልግሎት እየተጉ ድውያንን ፈወሱ፣ ሙታንን አስነሱ፣ አጋንንትን አሳደዱ። ብዙ ተአምራትንም አደረጉ። እንዲያውም አንድ ቀን ወይራውን በጧት ተክለው በሠርክ ትልቅ ዛፍ ሆነላቸው። ከዚያ ዘንጥፈው እሳቱን በቀሚሳቸው ላይ አፍመው ማዕጠንት አሳርገዋል። የሚገርመው ያ ዛፍ ዛሬም ድረስ ለምስክርነት ቁሟል። በመጨረሻ ዘመናቸው ግን ጻድቁ አምስት ክንድ ርዝመት ባላት ጾማዕት (በዓት) ውስጥ ገብተው ቆሙ። ለአርባ አምስት ዓመታት ሳይቀመጡና ሳይተኙ በእንባ ቢጸልዩ ቅንድባቸው ተላጠ። አካላቸውም በአጥንቱ ብቻ ቀረ። በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት መድኃኔዓለም መጥቶ ''ወዳጄ! ስምህን የጠራ መታሰቢያህን በእምነት ያደረገውንም ሁሉ እምርልሃለሁ።'' አላቸው። ያን ጊዜ አጥንቶቻቸው ተወዛወዙና ነፍሳቸው በክብር ዐረገች። የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
#ጥቅምት_5
#ጻድቁ_አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ። አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ: የቅዱሳን የበላይ: ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው። አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ 1, እህል ያልቀመሱ (ምግባቸው ምስጋና ነውና) 2, ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና)። 3, ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት። 4, ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል። ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል። ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል። ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው። ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና። የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮዽያ ልዩ ፍቅር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው። ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት። በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል። የጻድቁ በዓል ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ መጋቢት 5 ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ (ቅያሪ) ሆኖ ነው።
+6
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
የካልዕ ወይም የሁለተኛ ሳምንት ማህሌተ ፅጌ በደማቅ ሁኔታ አልፎ የሳምንት ሰው ይበለን እያልን እንዲሁም በአንድነት መርሐግብር ደግሞ መንፈሳዊ ጓደኝነት በሚል ርዕሰ ቀሲስ ታምራት መልካም መልዕክት የአባትነት ምክር እንዲሁም ከአባላት ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ በመስጠት እውቀት መግበውናል ለመምህራችን ቃለ ህይወት እና ረጅም እድሜ እንመኛለን ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
03/01/2017 ዓ.ም
አባ ጊዮርጊስ ከግዞት የወጣው ዐፄ ቴዎድሮስ ሲሞት ነበር፡፡
🌹 የአባ ጊዮርጊስ ሌላው ተማሪ የነበረው ዐፄ ይስሐቅ በ1399 ዓ.ም መንግሥቱን ሲይዝ አባ ጊዮርጊስን ከግዞት አውጥቶ ወደ ጋሥጫ መለሰው፡፡ በዚያ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ እድሜው 42 ዓመት ሲሆን በስደትና በጤንነት መታወክ የተነሣ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜውን በጾም፣ በጸሎትና በድርሰት ያውለው ነበር፡፡ አንድ ቀን ቴዎድሮስ የተባለ መስፍን፣ ዳግመኛም የጦሩ አዛዥ የሚሆን፣ አባ ጊዮርጊስን ስለ ርትዕት ሃይማኖት በጠየቀው ጊዜ አባ ጊዮርጊስም "ፍካሬ ሃይማኖት" የተባለውን መጽሐፍ ደርሶ ሰጠው፡፡ ንጉሡና የምሥጢር ሊቃውንት የሆኑ ካህናት ይህንን በተመለከቱና ባነበቡ ጊዜ "በእውነት ዮሐንስ አፈወርቅና አፈ በረከት የሆነው ቄርሎስ በዘመናችን ተነሥተዋል፡፡ ኢትዮጵያም ቍስጥንጥንያን መስላለች፣ ከእስክንድርያም በላይ ከፍ ከፍ ብላለች" ብለው አደነቁ፡፡
🌹 ይህም ፍካሬ ሃይማኖት የተሰኘው ድንቅ ድርሰቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውንና የምታወግዘውን በግልጽና በዝርዝር የጻፈበት መጽሐፍ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ በፍካሬ ሃይማኖት ድርሰቱ ላይ የዘረዘራቸው የመናፍቃን ስሞችንና ክህደታቸውን ስንምለከት በዘመኑ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ስለ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያላቸውን ዕውቀት በግልጽ ያሳየናል፡፡ አባ ጊዮርጊስ መከራ ያልተለየው አባት በመሆኑ አሁንም በቤተ መንግሥት የነበሩ ሰዎች የእርሱን መከበርና መወደድ አይፈልጉትም ነበር፡፡ በተለይም "ፍካሬ ሃይማኖት" የተሰኘውን መጽሐፍ በመጻፉ በዚህም ዝናው የበለጠ ስለተነገረ እነርሱ በሁሉም ዘንድ መከበሩን አልወደዱትም ነበር፡፡ ስለዚህም ነገር ሠርተው ከዐፄ ይስሐቅ ጋር አሁንም አጣሉት፡፡
🌹 ዐፄ ይስሐቅ አባ ጊዮርጊስን አሳስሮ ውኃ ወደማይገኝበት ዓለታማ ቦታ አጋዘው፡፡ በዚያም በመከራ ለብዙ ጊዜ ኖረ፡፡ በዚያ እያለ ዘወትር በጸሎት አብዝቶ ይተጋ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ዐፄ ይስሐቅ ወደ ልቡናው እንዲመለስ አደረገ፡፡ ንጉሡ በአባ ጊዮርጊስ ላይ የፈጸመው ነገር ሁሉ ስለፀፀተው አገልጋዮቹን ጠርቶ አባ ጊዮርጊስን እንዲያመጡት አዘዘ፡፡ ነገር ግን እነዚያ ተንኮል ሠሪዎች የአባ ጊዮርጊስ መምጣት ተንኮላቸውን ስለሚያጋልጠው "አባ ጊዮርጊስ ሞቷል" ብለው አስወሩ፡፡ ይህንን ሲሰማ ዐፄ ይስሐቅ ፈጽሞ አዘነ፡፡
🌹 አባ ጊዮርጊስም ሞቷል እየተባለ መወራቱን ከደቀ መዝሙሩ ስለ ሰማ በሕይወት የመኖሩን ዜና ጽፎ ለዐፄ ይስሐቅ እንዲያደርስለት መልእክቱን በአውሎ ንፋስ አሳስሮ ላከለት፡፡ አውሎ ንፋሱ ለአባ ጊዮርጊስ በመታዘዝ ደብዳቤውን ተሸክሞ በመሄድ ዐፄ ይስሐቅ በድንኳን ተቀምጦ በነበረ ጊዜ ጉልበቱ ላይ አስቀመጠው፡፡ ንጉሡ ምትሐት የተሠራበት ስለመሰለው ደነገጠና መኳንንቱንና ሕዝቡን ሰብስቦ ጉዳዩን ገለጠ፡፡ ወዲያውም ነፋሱ ያመጣለትን መልእክት እሳት አስነድዶ ከዚያ ውስጥ ቢጥለው ሊቃጠል አልቻለም፡፡ ወደ ውኃም ቢጨምረው አልጠፋም፡፡ በዚህ ተደንቆ ወረቀቱን ከፍቶ አነበበው፡፡ ደብዳቤው ከአባ ጊዮርጊስ የተላከ መሆኑን ሲያውቅ ዐፄ ይስሐቅ ደነገጠ፡፡ እነዚያን መልእክተኞች ይዞ ወደ ወኅኒ ከጨመራቸው በኋላ አባ ጊዮርጊስን ከግዞት ያወጡት ዘንድ ላከ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሲመጣ ንጉሡ በደስታ ተቀብሎ ማረኝ ብሎ ለመነው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ይቅር አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ደብዳቤውን በማን እጅ እንደ ላከው ጠየቀው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ደብዳቤውን በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ በነፋስ እንደ ላከው አስረዳው፡፡
🌹 አባ ጊዮርጊስ ከግዞት ከተመለሰ በኋላ እመቤታችን ተገልጣለት መከራው ሁሉ እንደ ሐዋርያት መሆኑን ገለጠችለት፡፡ አእምሮውን ብሩህ፣ ልቡናውን ትጉኅ የሚያደርግ እጅግ ብዙ ምሥጢርም ነገረችው፡፡ ተሰናብታው ከሄደች በኋላ "እጅግ ብዙ መብራት አቅርቡ አምስት ፈጣን ጸሐፊዎችንም አምጡ" ብሎ አዘዘ፡፡ ከዚህም በኋላ እርሱ እየነገራቸው እነርሱ እየጻፉ እረፍት ሳያደርጉ ሦስት ቀን ሙሉ አጽፎ "መጽሐፈ ምሥጢር" የተሰኘውን መጽሐፍ ፈጸመ፡፡ አምስቱ ጸሐፍትም የየድርሻቸውን አጠናቅቀው በአንድ አደረጉት፡፡ አባ ጊዮርጊስም ይህን ተመልክቶ በእጅጉ አደነቀ፡፡ "እኔ የዚህን መጽሐፍ ቃል አልተናገርኩም፤ መንፈስ ቅዱስ በእኔ አፍ ተናገረ እንጂ" ሲል በወቅቱ መስክሯል፡፡ የመጽሐፉንም ስም "መጽሐፈ ምሥጢር" ብሎ የሰየመው ራሱ ነው፡፡ የጻፈው በ1409 ዓ.ም እድሜው 52 በደረሰ ጊዜ ሲሆን በወቅቱም የዚህ መጽሐፍ ቅጅ በነጋድያን እጅ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ሄዶ ነበር፡፡
🌹 ዐፄ ይስሐቅ ለአባ ጊዮርጊስ "ምድረ ሰዎን" የተባለውን የጳጳሳት መቀመጫ የነበረውን ሀገር በርስትነት ሰጥቶት ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ በምድረ ሰዎን ንጉሥ ይስሐቅ ክረምቱን ያሳልፍበት በነበረው ቦታ ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠራ፡፡ በዚያም በማስተማርና በጾም በጸሎት ይተጋ ነበር፡፡ በጋሥጫ እያለ ዐፄ ይስሐቅ አስጠራው፡፡ በዚያ ጊዜ ንጉሡ የመናገሻ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ ስለነበር እንዲባርክለት ፈልጎ ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ምንም እንኳን በዚያ ጊዜ ታሞ የተኛም ቢሆን ወደ ንጉሡ ተጓዘ፡፡ እዚያ ሲደርስ በጣም ተዳክሞ ነበር፡፡ ሥርዓቱን ለመፈጸምም አቅም አልነበረውም፡፡ ስለዚህም ንጉሥ ይስሐቅ በአልጋ ተሸክመውት እንዲዞሩና ቤተ ክርስቲያኗን እንዲባርካት አድርጓል፡፡ ቡራኬውን ከፈጸመ በኋላ ደቀ መዝሙሮቹን ሰብስቦ "ከሞትኩ አባቴ በጸሎተ ሚካኤል መከራ ወደ ተቀበለባትና እኔም ቤተ ክርስቲያን ወዳነፅኩባት ቦታ ወስዳችሁ ቅበሩኝ" ሲል አዘዛቸው፡፡ ለደቀ መዛሙርቱ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ የመጨረሻ የስንብት ትምህርቱን አስተማራቸው፡፡ እነርሱም በአልጋ ተሸክመውት ወደ ጋሥጫ እያመሩ ሳለ በመንገድ ላይ ሐምሌ 7 ቀን 1417 ዓ.ም በ60 ዓመቱ ዐረፈ፡፡ ከአባታችን ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቱ ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።
ወደፊት ራሱን የቻለ በቂና ብዙ ጥናት ማድረግ ሳያስፈልገን እንደማይቀር አመላካች ነው፡፡
🌹 የመጀመርያውን ድርሰቱን አርጋኖንን እመቤታችን አብዝታ ስለወደደችለት ዚማት በሚባለው ሀገር በነበረ ጊዜ "ከድርሰቶችህ ሁሉ እንደ አርጋኖን የምወደው የለም" ብላዋለች፡፡ ከዚህ በኋላ የደረሰው ድርሰት ውዳሴ መስቀል ይባላል፡፡ ቀጥሎም መጽሐፈ ስብሐት ዘመዓልት ወዘሌሊት የተባለውን ወይም እርሱ ራሱ መጽሐፈ ብርሃን ብሎ የሰየመውን መጽሐፍ አዘጋጅቷል፡፡ መጽሐፉም የእግዚአብሔርን የምስጋናውን መንገድ ያበራል፣ አብርቶ ያመለክታልና፣ ልዑላነ ብርሃን የሆኑትን የማኅበረ ቅዱሳንንና የትጉኃንን የምስጋናቸውን መንገድ ያመለክታልና፣ የእመቤታችንንም የምስጋናዋን ጣዕም ይገልጣልና መጽሐፉ "መጽሐፈ ብርሃን" ተባለ፡፡ በዘመኑ በነበረው ልማድ ካህናቱ ቍርባን በሚያቀብሉ ጊዜ ሕዝቡ ወደ ካህናቱ መጥተው ሲቀበሉ ንግሥቲቱ ግን ካለችበት ድረስ ካህናቱ ሄደው ነበር የሚያቆርቧት፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን "ይህ ቁርባን ንጉሠ ነገሥት ነውና ንግሥቲቱ ወደዚህ መጥታ ልትቀበል ይገባታል እንጂ እኛ መሄድ የለብንም" ሲል ተቃወመ፡፡ ይህ ነገር ንግሥቲቱንና አባ ጊዮርጊስን ስላጋጫቸው ዐፄ ዳዊት ችግሩን ለመፍታት አባ ጊዮርጊስን ወደ ሀገረ ዳሞት ንቡረ እድነት ሾሞ ላከው፡፡
🌹 ከዚህ በኋላ አባ ጊዮርጊስ ዋናው ትኩረቱ በድርሰቱ ላይ በማድረግ ወደ ጳጳሱ ወደ አቡነ በርተሎሜዎስ ዘንድ በመሄድ የቅዳሴ ድርሰት ለመድረስ እንዲፈቀድለት ጠይቆ ሲፈቀድለት የቅዳሴ ድርሰት ማዘጋጀት ጀመረ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ነገረ ሃይማኖትን ጠንቅቆ የተረዳና የሚያስረዳ ስለነበር በዘመኑ የተነሡ የሃይማኖት ክርክሮች ሁሉ እርሱ ከሌለ አይሳኩም ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ በሸዋ በይፋት ራሳቸውን ቤተ እስራኤል እያሉ የሚጠሩ አይሁድ ነበሩ፡፡ ከአቡነ ዜና ማርቆስ ጀምሮ ብዙ መምህራን ወደነዚህ ሕዝቦች እየተሠማሩ ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ክርስትና ለተመለሱት ቤተ እስራኤላውያን በእመቤታችን፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በአባ ኖብና በሰማዕቱ በጊጋር ስም አራት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተው ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ቤተ እስራኤላውያኑ ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስትና አልተመለሱም ነበር፡፡
🌹 ከእነዚህ አይሁድ መካከል አንዱ ከክርስቲያኖች ጋር በነገረ ሃይማኖት ለመከራከር ጥሪ አቀረበ፡፡ "ክርስቲያኖች ከረቱኝ ወደነርሱ ሃይማኖት እገባለሁ እኔ ከረታኋቸውም ወደኔ ሃይማኖት ይገባሉ" ሲል ነገሩን ጥብቅ አደረገው፡፡ ዐፄ ዳዊት ይህን ጉዳይ ሲሰማ በጣም ስለ ተናደደ ሊቃነ ካህናቱን፣ ንቡራነ እዱንና የመጻሕፍት ዐዋቂዎችን ሁሉ ከየሀገሩ እንዲሰባሰቡ አዘዘ፡፡ ነገር ግን በዚህ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ ታሞ አልጋ ላይ ነበር፡፡ አይሁዳዊው በአንድ ወገን መምህራኑ በአንድ ወገን ሆነው ክርክሩን ጀመሩ፡፡ የመጀመርያው እድል የተሰጠው ለአይሁዳዊው በመሆኑ ቀጥሎ ያለውን ጥያቄ አቀረበ፡- "እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የምትሉት ይሄ ክርስቶስ እውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ ወደ ቢታንያ በመጣ ጊዜ አልዓዛር የተቀበረበትን ቦታ ሳያውቅ ቀርቶ "አልዓዛርን የት ቀበራችሁት?" ብሎ እንደ ጠየቀ በወንጌላችሁ ተጽፏል፡፡ ለዚህ መልስ ስጡኝ፣ እኔንም ከመጽሐፈ ኦሪቴ ጠቅሳችሁ ጠይቁኝ?" ሲል የመከራከርያ ነጥቡን አቀረበ፡፡
🌹 ሊቃውንቱም በዚህ ጊዜ ታሞ አልጋ ላይ የነበረውን አባ ጊዮርጊስን እንዲመጣላቸው ፈልገው "እንዲህ ያለው ነገር ያለ እርሱ አይሆንምና አባ ጊዮርጊስ ይምጣ" ሲሉ ለዐፄ ዳዊት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በአልጋ ላይ እያለ እንዲመጣ ተደርጎ በአልጋ ላይ ሆኖ በጉባኤው ላይ ተገኘ፡፡ ጉባኤተኞቹ የቀረበውን ጥያቄ በነገሩት ጊዜ አባ ጊዮርጊስ የሰጠውን መልስ እንዲህ የሚል ነው፡- "እኔ ግን በወንጌል ሳይሆን በኦሪት እከራከርሃለሁ፡፡ የምኩራብ መጻሕፍት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን የታወቁ ናቸውና፡፡ ምኩራብ ዘራች ቤተ ክርስቲያንም አጨደችው፤ ምኩራብ ፈተለችው ቤተ ክርስቲያን ለበሰችው፤ አዳምን በገነት ሳለ አዳም ሆይ ወዴት ነህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? አብርሃምንስ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? ብሎ የጠየቀው ማነው? እስቲ መልስልኝ? ሰይጣንንስ ከወዴት መጣህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? እግዚአብሔር አብ አይደለምን?" እያሉ የጥያቄ ዓይነት ባሽጎደጎዱለት ጊዜ አይሁዳዊው መልስ አጥቶ ዝም አለ፡፡ መልስ በማጣቱም አፈረ፡፡ ንጉሡ፣ ሊቃውንቱና መኳንንቱም እጅግ ተደሰቱ፡፡
🌹 አባ ጊዮርጊስ ሌላው ያጋጠመው ክርክር ቢቱ ከተባለው ሰው ጋር ያደረገው ክርክር ነበር፡፡ ቢቱ "በምጽዓት ጊዜ የሚመጣው ወልድ ብቻውን እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይመጡም" የሚል ኑፋቄ ማስተማር ጀምሮ ነበር፡፡ ቢቱ ከዚህ ኑፋቄው በተጨማሪ የጥንቆላ ሥራም ይሠራ ነበር፡፡ ቢቱ በጥንቆላ ሥራው የተነሣ በቤተ መንግሥቱ ተቀባይነት የነበረው ሰው ነበረ፡፡ ይህን መሰሉን ተግባር አጥብቆ የተዋጋው ዘርዐ ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ ነገሥታቱ ምንም ክርስቲያኖች ቢሆኑ በዚህ መሰሉ ስንኩል ሕፀፅ ይዋጡ ነበር፡፡ ቢቱና አባ ጊዮርጊስ ወደ ንጉሥ ዳዊት ቀርበው በጉዳዩ ላይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ገለጡ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ጳጳሱና ሊቃውንቱ ባሉበት እንዲነጋገሩ ስለወሰነ ጳጳሱ እንዲመጡ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ተንኮለኛው ቢቱ ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ከተከራከረ እንደሚሸነፍ ስላወቀ "ንጉሡ የአባቶቻችንን ሃይማኖት ክዷልና አትምጣ" የሚል ደብዳቤ በአባ ጊዮርጊስ ስም ጽፎ ጳጳሱን ሊጠሩ በሄዱት መልእክተኞች እጅ ላከ፡፡ ወድያውም ለዐፄ ዳዊት ይህንን ነገር አሳበቀ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ፈጣን መልእክተኞች ልኮ የፊተኞቹ መልእክተኞች እንዲመለሱ አደረገና ደብዳቤው ተነበበ፡፡ የቢቱ ተንኮል ያልገባው ንጉሥ ዳዊት ይህን ደብዳቤ ሲመለከት አባ ጊዮርጊስን በደም እስኪነከር ድረስ እንዲደበደብ አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባው፡፡
🌹 ዐፄ ዳዊት እስኪሞትና ልጁ ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ድረስም በዚያ ቆየ፡፡ ቢቱ ግን በመልአክ ተቀስፎ ሞተ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በወኅኒ ቤት እያለ የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ እየመጡ ያጽናኑት ነበር፡፡ "ውዳሴ ሐዋርያት" የተሰኘውንና ከሐምሌ 5 ጀምሮ በ12ቱም ወራት የሚመሰገኑበት የሐዋርያትን ምስጋና የያዘውን መጽሐፍ ያዘጋጀው በወኅኒ ቤት ሆኖ ጴጥሮስና ጳውሎስ ከጎበኙት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
🌹 አንድ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ በእስር ላይ ሳሉ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት መሞታቸው ተሰማ፡፡ ሰዎችም ወደ አባታችን መጥተው "ያሳሰረህ ንጉሥ ሞቷል" በማለት ነገሩት፡፡ ይህንንም ተቻኩለው የነገሩት ያሰረው ንጉሥ መሞቱን ሲሰማ ይደሰታል ብለው ነበር፡፡ ነገር ግን አባ ጊዮርጊስ በታላቅ ሀዘን ውስጥ ሆኖ የሰጣቸው መልስ "አይ ንጉሡ ባይሞት እኔም እንደታሰርኩ ብቀር ይሻል ነበር፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትኮ እኔን ባይወደኝ የአምላክን እናት እመቤታችንን ይወዳት ነበር" አላቸው፡፡
🌹 ዐፄ ቴዎድሮስ አባ ጊዮርጊስን ከወኅኒ ቤት አውጥቶት በጥንቱ ቦታ አስቀመጠው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን የቤተ መንግሥትን ነገር ለመሸሽ ስለ ፈለገ በጋሥጫ ከመቀመጥ ይልቅ ርቆ ጥንት ወደ ነበረበት ወደ ዳሞት በመሄድ ማስተማር ጀመረ፡፡ ወደ ዳሞት ሲሄድ እግረ መንገዱን ወደ ደብረ ሊባኖስ ገብቶ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን መቃብር ተሳልሟል፡፡ በዚያ ጊዜ የደብረ ሊባኖሱ አበ ምኔት እጨጌ ዮሐንስ ከማ ነበሩ፡፡ እርሳቸውም ሰባተኛው የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ነበሩ፡፡ አባ ጊዮርጊስን በዕውቀቱ የሚቀኑበት፣ በችሎታው የሚመቀኙት ሰዎች ነገር ሠርተው ከንጉሥ ቴዎድሮስ ጋር ስላጣሉት እልም ካለ በረሃ እንዲጋዝ ተደረገ፡፡
የእነዚህን ምስጢር በልቡ ጠበቃቸው፡፡ አምስቱንም ቃላት በልቡ መዝገብነት ሰወራቸው፤ ሊገልጣቸው እግዚአብሔር አልፈቀደላትምና በተረዳ ነገር ግን መዝሙረ ዳዊት ነው፡፡ የገነትን ፍሬዎች ሁሉ የሰበሰበ መዝሙረ ዳዊት የገነት አምሳል ነውና አጋንንትን ያሳድዳል መላእክትንም ያቀርባል፡፡ እመቤታችንም ከእርሱ ተለይታ ካረገች በኋላ ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ የልቡ ዓይን ተከፈተለት፡፡ ኅሊናውም በመንፈስ ቅዱስ ክንፎች ተመሰጠ፡፡ ወደ አብም ደረሰ፤ በዚያም ኢየሱስን በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ጰራቅሊጦስንም በአንድ አኗኗር አገኘው፡፡
🌹 ከዚህ በኋላ በሐይቅ እስጢፋኖስ የዜማ የቅኔና የመጻሕፍትን ትርጓሜ ትምህርቱን በሚገባ ተምሮ አጠናቀቀ፡፡ በዕውቀቱም ቀድሞ የሚያውቁት ሁሉ ይደነቁበት ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ የያሬድን ዜማ ከአቡነ ሳሙኤል ተማረ፡፡ በዚያ ዘመን በዐፄ ዳዊት አማካይነት በሰሜን ኢትዮጵያ የያሬድ ድጓ ዋና ማዕከል በሆነው በደብረ ነጎድጓድ ተሾሞ ያስተምር ነበር፡፡ የማስተማር ሥራውን የጀመረው በዚያው በሐይቅ እስጢፋኖስ ነበር፡፡
🌹 ከሐይቅ በኋላ በዚያ ዘመን ሸግላ በመባል ትጠራ ወደ ነበረችው ወደ ትውልድ ሀገሩ ወደ ጋሥጫ ተጓዘ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ወደ ሸግላ ሲመጣ አባቱ በጣም አርጅቶና መንኲሶ ነበር፡፡ ስለዚህም በአባቱ እግር ተተክቶ በቤተ መንግሥቱ ያለችውን ሥዕል ቤት እንዲያገለግል ወደዚያው አስገቡት፡፡ በቤተ መንግሥቱም የንጉሡን ልጆች ከማስተማሩም በላይ በቤተ መንግሥቱ ዙርያ ከነበሩት ሊቃውንት መካከል አባ ጊዮርጊስ አንዱ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ግብፃዊው ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስ "ሥላሴን አንድ ገጽ" ብለው ያምናሉ ተብለው በተከሰሱ ጊዜ ነገሩን እንዲያጣሩ ከተመረጡት ከቄስ ዐፄ ተከሥተ ብርሃንና ከሐይቁ መምህር ከዐቃቤ ሰዓት ዮሴፍ ጋር አብሮ ተልኮ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስት አበው ጳጳሱን ካነጋገሩ በኋላ ክሱ ውሸት መሆኑን በማረጋገጥ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የሚገልጠውን የጳጳሱን እምነት በጽሑፍ ይዘው መጡ፡፡
🌹 በቤተ መንግሥቱ በነበረ ጊዜ የንጉሡን ልጆች ይስሐቅን፣ ቴዎድሮስን፣ እንድርያስን፣ ሀብተ ኢየሱስን፣ ሕዝቅያስን፣ ኢዮስያስን፣ ዘርዐ ያዕቆብንና ሴት ልጁን እሌኒን በምግባርና በሃይማኖት ቀርጿቸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ዘርዐ ያዕቆብ በድርሰቱ ሲመስለው ቴዎድሮስ ደግሞ በሕይወት መስሎታል፡፡ ዐፄ ዳዊት የአባ ጊዮርጊስን ሊቅነትና መልካም ሥነ ምግባር በሚገባ ስላወቀ በጋብቻ ሊዛመደው ወዶ ስለነበር ልጁን እንዲያገባ ዘወትር ይጠይቀው ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በድንግልና ጸንቶ ለመኖር እንደሚፈልግ ከመግለጽ አልተቆጠበም፡፡ የዐፄ ዳዊት ጥያቄ ስለበዛበት ወደ አቡነ በርተሎሜዎስ ሄዶ ቅስናን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው መነኰሰ፡፡
🌹 ከመነኰሰ በኋላ ወደ ሸግላ በመምጣት ለነገሥታትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ካህናት እንዲሁም በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ታላላቆች፣ ለንቡራነ እድና ለመኳንንት፣ ለመሳፍንትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ባለሟሎች ሁሉ መምህር ሆነ፡፡
🌹 አባ ጊዮርጊስ በሸግላ በነበረ ጊዜ በወባ በሽታ ታምሞ ሊሞት ደርሶ ነበር፡፡ ታምሞ በነበረ ጊዜ አንድ ሌሊት የከበሩ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ተገልጠውለት "ከእኛ ጋር ትኖር ዘንድ ልንወስድህ መጣን" አሉት፡፡ እርሱም "የድርሰት ሥራዬን ሳልሠራና እግዚአብሔርንም አብዝቼ ሳላመሰግነው አሁን አትውሰዱኝ" ሲል ለመናቸው፡፡ እነርሱም ልመናውን ተቀብለውት ከሕመሙ ፈውሰውት ሄዱ፡፡ ለዚህም ነው ከበሽታው እንደ ተፈወሰ ወድያው የድርሰት ሥራውን የጀመረው፡፡ የመጀመርያ መጽሐፉን ጽፎ እንደ ጨረሰ ጠፍቶበት ነበር፡፡ በማግሥቱ በዚያው ላይ ሊጨምር በወደደ ጊዜ የተጻፈበት ጥራዝ ቀለሙ ጠፍቶ ነጭ ሆኖ አገኘው፡፡ ስለዚህም የተሰረቀ መስሎት ልቡ አዘነ፡፡ የተስተካከሉ ጥራዞችንም በቈጠረ ጊዜ ደኅና ሁነው አገኛቸው ሁለተኛም በድጋሚ ጻፈ፡፡ በማግሥቱም እንደ መጀመሪያው ነጭ ሁኖ አገኘው እስከ ሦስትና ዐራት ቀንም እየተደጋገመ እንዲሁ ሆነ፡፡
🌹 ከዚህ በኋላ አባታችን ወደ እመቤታችን ይጸልይ ጀመረ፡፡ "ይህ የሆነ በኃጢአቴ ነውን? ወይስ አይደለም? ግለጭልኝ" አላት፡፡ አንድ ቀንም በሌሊት እኩሌታ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለጸሎት ሲሄድ እመቤታችን በድንገት በማይነገር ክብር ለጊዮርጊስ ተገለጠችለት፡፡ ከእርሷም ጋር የቅዱሳን ማኅበር ሁሉ ነበሩ፡፡ በእጇም ከፀሐይና ጨረቃ የበለጠ የሚያበራ መጽሐፍን ይዛ ነበር፡፡ ጊዮርጊስም ባየ ጊዜ ወደ መሬት ወደቀ፡፡ እንደ በድንም ሆነ፡፡ እመቤታችንም አነሣችውና "ሳትጠይቀኝ መጽሐፌን ትጽፍ ዘንድ ለምን ደፈርህ?" አለችው፡፡ "እኔ ወድጄህ ከእናትህስ ማኅፀን መርጬህ ለጴጥሮስ፣ ለጳውሎስና ለዮሐንስ አደራ ሰጥቼህ የለምን?" አለችው፡፡ አባ ጊዮርጊስም "እመቤቴ ሆይ ይቅር በይኝ፣ ደስ የሚያሰኝሽ መስሎኝ ይህን ባለማወቅ ሠርቼዋለሁና" አላት፡፡ እመቤታችንም "ወዳጄ ሆይ ይቅር ብየሃለሁ" አለችው፡፡ "ልትጽፈው የወደድኸው መጽሐፍም እነሆ በእጄ አለ፣ ከአሁን በኋላ የተወደደ ልጄ በአንደበትህ ሊገልጸው ወዷል፡፡ ነገር ግን ከአርያም ከሰማይ ኀይልን እስክትለብስ ድረስ አትቸኩል"፡፡ ይህንም ብላው ከእርሱ ተሰወረች፡፡ ያን ጊዜም ልቡ እንደ ፀሐይ በራ፣ የመለኮትም ባሕር በኅሊናው አበራ፡፡ በመንፈስ ቅዱስም መስተዋትነት የተሰወረውን ሁሉ አየ፡፡
🌹 የመጀመርያው ድርሰቱ አርጋኖን የተሰኘውና በቅኔ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚያመሰግነው መጽሐፉ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በሚወድ በንጉሥ ዳዊት ዘመንም አርጋኖን መጽሐፍን ይደርስና ይጽፍ ጀመረ፡፡ በሦስትም ስሞች ጠራው እነዚህም አርጋኖና ውዳሴ፣ መሰንቆ መዝሙር፣ ዕንዚራ ስብሐት ናቸው፡፡ ስለ መጽሐፉም ጣፋጭነት ንጉሡ ዐፄ ዳዊት ድርሰቱን በጣም ከመውደዱ የተነሣ በወርቅ ቀለም አጻፈው፡፡ ወርቁን የሚያንጸባርቅበት ድንጋይ (ዕንቊ) ባጣ ጊዜ እመቤታችን ማርያም በሌሊት ራእይ ዘማት በሚባል አገር እንዳለ ለጊዮርጊስ ነገረችው ኅብሩንም አሳየችው፡፡ አባታችን ጊዮርጊስም ከደረስኳቸውና ከተናገርኋቸው ድርሳናት ሁሉ አርጋኖን ውዳሴ ይጣፍጣል ይበልጣል አለ፡፡
🌹 እንደዚሁም በፈጣሪው ቸርነት በእመቤታችን ረድኤት ብዙ ድርሳናትንና የጸሎት መጻሕፍትን ደረሰ፡፡ የእሊህም ድርሳናት ስማቸውና ቁጥራቸው በሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ እሊህም ውዳሴ መስቀል፣ መጽሐፈ ብርሃን፣ መጽሐፈ ሰዓታት የመዓልትና የሌሊት፣ መጻሕፍተ ቅዳሴያት ናቸው፡፡ ጸሎተ ፈትቶ (የፍታቴ ጸሎት) የሐዋርያት ማኅሌት፣ መልክአ ቊርባን፣ እንዚራ ስብሐት፣ አርጋኖን ውዳሴ፣ ፍካሬ ሃይማኖት፣ ውዳሴ ሐዋርያት፣ ኖኅተ ብርሃን ይኸውም ከመጽሐፈ አርጋኖን ጋር አብሮ የታተመው ነው፡፡ ፍካሬ ሃይማኖት፣ መጽሐፈ ምስጢር፣ ሕይወታ ለማርያም፣ ተአምኆ ቅዱሳን፣ ጸሎት ዘቤት ውስተቤት፣ ውዳሴ ስብሐት፣ ሰላምታ፣ ጸሎተ ማዕድ፣ ቅዳሴ እግዚእ ካልእ፣ መዝሙረ ድንግልና የመሳሰለው ነው፡፡ ቅዱስ ገድሉ እንደሚናገረው የአባ ጊዮርጊስ "ድርሳናት ስማቸውና ቁጥራቸው በሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ነው" ብሎ ከጀመረ በኋላ በቁጥር የተወሰኑትን ድርሰቶቹን ብቻ ጠቅሶ መጨረሻ ላይ "… እና የመሳሰለው ነው" ብሎ ይደመድመዋል፡፡ ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ ደግሞ የአባ ጊዮርጊስ ድርሰቶች ከ12 ሺህ በላይ ቢሆኑም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እየሰጡ ያሉት በጣም ጥቂቶቹ ብቻ መሆናቸውን በቅዱሳን ታሪክ መጽሐፋቸው ላይ ጠቅሰውታል፡፡ ሌሎች ሊቃውንት አባቶቻችንም የአባ ጊዮርጊስን ድርሰቶች ከግምት ባለፈ ሁኔታ በቁጥር ወስኖ ለማስቀመጥ አስቸጋሪ መሆኑን ይገልጣሉ፡፡ ይኸውም
